Tuesday, December 31, 2013

ተአምር በ አቡነ ገብረ መንፈስ ቅዱስ ቤተ ከርስቲያን /ሽሬ/

በሰሜን ትግራይ ክልል ከሽሬ ከተማ ወጣ ብሎ ማይ ወይኒ አቡነ ገብረ መንፈስ ቅዱስ ቤተ ከርስቲያን ለረጅም አመታት በዓታቸውን አጽንተው የኖሩ እድሜ ጠገብና ፍጹም ጸሎተኛ የሆኑ ታላቅ አባት ነበሩ:: ባለፈው ዓመት ማለትም ኅዳር 2005 ሊቀ ትጉኃን ደረጀ ነጋሽ (ዘ ወይንዬ) በሚያዘጋጀው መንፈሳዊ ጉዞ አክሱም ጽዮን ደርሰን ስንመለስ፡ ወደዚህ ታላቅ ገዳም ለመሳለምና የእኚህን ቅዱስ አባት በረከት ለመቀበል የጉዞ ማኅበሩ በየዓመቱ እንደሚያደርገው ገብተን ነበር:: ገመና ሸፋኙ ይቅር ባይ ጌታ እኔን ደካማውን ልጁን ሳይገባኝ የዚህ በረከት ተካፋይ አደረገኝ:: ይህንን ፎቶ አሁን የለቀኩበት ዛሬ እኚህ ቅዱስ አባት በዚህ ዓመት በማረፋቸው ምክንያት ነው::
 
 
 
 
 
 
 
መምሕር ጻውሎስ መልከ ስላሴ ከተጠቀሱት አባት ጋር
ዘንድሮ የሄደው የአክሱም ተጓዥ ሁሉ እንደተለመደው ወደ ቦታው ቢሄድም እኚህን አባት በአካለ ሥጋ አላገኛቸውም ሕይወታቸውን ሙሉ ታምነውለት የኖሩለት እግዚአብሔር ዘንድ : በይባቤ መላእከት እና ዝማሬ ካህናት ታጅበው ሄደዋል:: የኖሩበት ዘመን ከሁለት መቶ ዓመታት በላይ እነደሆነ ይነገራል:: ዘንድሮ ኅዳር አቦ ለቁስቋም ዋዜማ ካህናቱ በአገልግሎት ላይ ሳሉ ያልተለመደ እንግዳ ድምጽ ሰሙ: ይኸውም ከካህናቱ ድምጽ በላይ የነምር (ነብር) ድምጽ ቤተ ክርስቲያኑ ውስጥ ይሰማ ነበር ይላሉ ካህናቱ:: ውዲያውም ድንገት እንግዳ የሆኑ አባቶች መነኮሳት በኚህ ታላቅ አባት በአት (ቤት) ተገኙ:: እነርሱም በመንፈስ ቅዱስ ራእይ እኚህን ታላቅ አባት በክብር ገንዘው እናዲያሳርፉ ከዋልድባ የተላኩ አባቶች ነበሩ:: እነሆ ሳይገባን እኛም ልናገለግልባት የቆምንባት ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ማለት ይህቺ ናት የማትመክን ዛሬም ቅዱሳንን የምትወልድ ሁሌም ተአምር የምትሰራ እነዚህን የመሳሰሉ አባቶችን ያፈራችና ወደፊትም የምታፈራ: በተቀደሱ ጸበሎችዋ የምትፈውስ፡ ተፈትና የምታሸንፍ ሁሌም በድንቅ ነገሮች የተመላችና በዙ ምስክሮች ያሏት ናት:: ተዋሕዶን ይጠብቅልን የአባታችን በረከታቸው ይደርብን በቦታው ተገኝተን ምስክርነቱን አድምጠን ለመባረክም ያብቃን:: "እንግዲህ እነዚህን የሚያህሉ ምስክሮች እንደ ደመና በዙሪያችን ካሉልን፥ እኛ ደግሞ ሸክምን ሁሉ ቶሎም የሚከበንን ኃጢአት አስወግደን፥ የእምነታችንንም ራስና ፈጻሚውን ኢየሱስን ተመልክተን፥ በፊታችን ያለውን ሩጫ በትዕግሥት እንሩጥ፤ እርሱ ነውርን ንቆ በፊቱም ስላለው ደስታ በመስቀል ታግሦ በእግዚአብሔር ዙፋን ቀኝ ተቀምጦአልና። "( ዕብ ፲፪፥፩ )
 ምንጭ
 የመምሕር ጻውሎስ መልከ ስላሴ ምስለ ገጽ (ፌስ ቡክ) የተወሰደ

ተአምራት በባሕታዊ ሳሙኤል ሶሙናዊ 

Miracles of Legedadi Saint Mary Church