Thursday, February 27, 2014

መልአከ መንክራት ግርማ ወንድሙ በመላው ዓለም እየተዘዋወሩ እንዲያገለግሉ ፍቃድ ተሰጣቸው

ከዚህ በፊት መምህር ግርማ ወንድሙ ከ እስጢፋኖስ ቤ/ክ አገልግሎት መታገድ በተያያዘ የቀድሞው የቅዱስ እስጢፋኖስ ቤ/ክ አስተዳዳሪ መላከ ሰላም ዘላለም እሰይ ስለ መምህር ግርማ ምን ይላሉ? በሚል አገልግሎታቸው የተቋረጠበትን መልካም ያልሆነ ድርጊት እና የመምህር ግርማ ወንድሙን እውነተኛ ማንነት የሚያስረዳ ቃለምልልስ አስደምጠን ነበር:: ከታች በተያያዘው ደብዳቤ ላይ መላከ መንክራት ግርማ ወንድሙ በመላው ዓለም እየተዘዋወሩ እንዲያገለግሉ ፍቃድ የተሰጣቸው መሆኑን ያሳያል::
ደብዳቤው እንደሚከተለው ይነበባል
ቀን 26/12/2005
መልአከ መንክራት ግርማ ወንድሙ በኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተክርስቲያን መንበረ ፓትርያርክ ልዩ ጽ/ቤት በመላው ዓለም እየተዘዋወሩ የወንጌል አገልግሎትና እንዲሁም የሕሙማን ሐብተ ፈውስ እንዲሰጡ ከብጹዕ ወቅዱስ አባ ማትያስ ቀዳማዊ ፓትርያርክ ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት ዘኢትዮጵያ ሊቀ ጳጳስ ዘአክሱም ወዕጨጌ ዘመንበረ ተክለሃይማኖት መልካም ፍቃድ የተፈቀደልዎት ሲሆን ይህን አውቀው በፍቅር በሰላም እንዲያገለግሉ እናስታውቃለን::
በክርስቶስ ሰላም
ተጨማሪ መረጃ
http://www.zehabesha.com/amharic/archives/13144
መልአከ መንክራት ግርማ ወንድሙ ማናቸው?

VDC part 26 ወጥቷል::

የቀድሞው የእገዳ ደብዳቤ

በሮም ለሚገኙ አብያተ ክርስቲያናት የተላከ ደብዳቤ 25/09/2006



Friday, February 21, 2014

ተዓምረኛው ንቡ ሚካኤል ቤተክርስቲያን


በስመ አብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ አሐዱ አምላክ አሜን

“የእግዚአብሔርን ሥራ በምድር ያደረገውን ታምራት እንድታዩ ኑ” መዝ. 45፡8
በንብ መንጋ የተከበበው የበሻሌ (ንቡ) ቅ/ሚካኤል፣ ቅ/እስጢፋኖስ እና ወአባ ሰላማ ከሳቴ ብርሃን ቤተክርስቲያን አመሰራረትና ገቢረ ተዓምራት አጭር መግለጫ

ቤተክርስቲያኑ ከመመስረቱ በፊት በቦታው ላይ ሲከናወኑ የነበሩ ልዩ ልዩ ታምራት፡-
1. ለብዙ ዓመታት ከተለያየ ቦታ ተጣልተው የነበሩ ምዕመናን ቦታው ላይ እየመጡ እርቀ ሰላም ሲፈጽሙበት ኖረዋል፤
2. ቤተክርስቲያኑ ከተተከለበት ቦታ ትልቅ የጽድ ዛፍ ላይ የሚወጣው ሙጫ እንደ እጣን ጢስ ሽታ ለብዙ ዓመታት አካባቢውን መዓዛው (ሽታው) ያውድ ነበር፡፡



3. በዚሁ ቦታ ላይ ሌሊት ሌሊት የመላዕክት ዝማሬ (ጣዕመ ዜማ) የከበሮ ድምጽ ይሰማ እንደነበረ በዕድሜ የገፉ የአካባቢው አዛውንቶች ተናግረዋል፡፡
4. በአካባቢው ከሚኖሩ ምዕመናን መካከል በመልካም ስራቸው የታወቁና ከ90 ዓመት በላይ ዕድሜ የነበራቸው እናት የቅዱስ ሚካኤል ታቦት (ጽላት) እንደሚተከል በተደጋጋሚ ለሕዝበ ክርስቲያኑ ይናገሩ ነበር፡፡
5. ቀደም ሲል በእነ አብርሃ ወአጽብሃ ዘመነ መንግሥት አካባቢ ጀምሮ ከተለያየ አካባቢ የሞቱ አባቶች አስከሬናቸው እየመጣ ሥርዓተ ቀብር ሲፈጸምበት የቆየ እና በተለያየ ጊዜ የቀስተ ደመና ብርሃን በመቃብሩ ላይ ይታይ እንደነበር በአካባቢው የሚኖሩ በዕድሜ የገፉ አዛውንቶች በግልጽ መስክረዋል፡፡ ዛሬም መቃብሩ በግልጽ ይታያል፡፡ ይህ ሁሉ ታሪክ ሲከናወን ከቆየ በኋላ እግዚአብሔር የፈቀደው ጊዜ ሲደርስ በአካባቢው ከሚኖሩ በዕድሜ ከገፉ አዛውንቶች መካከል በአንድ አርሶ አደር ምዕመን አማካኝነት በእግዚአብሔር ፈቃድ በተደጋጋሚ ራዕይ ተገልጾላቸው ያርሱበት የነበረውን ይዞታቸውን መሬት ለዚህ ታቦት መትከያ ቤተክርስቲያን እንዲሰራ መሬት በመስጠት አሁን በሚገኘው መቃኞ ቤተክርስቲያን ግንቦት 12 ቀን 2001 ዓ.ም ታቦቱ ሊገባ ችሏል፡፡
በቤተመቅደሱ ስለሚገኘው የንብ መንጋ አገባብ (አመጣጥ)