Friday, April 25, 2014

ከአፄ ዋሻ ማርያም ገዳም የተሰረቀው ታቦት ከጅቡቲ በተዓምራት ተመለሰ



የእስራኤልን አምላክ ታቦት ስደዱአት፤ እኛንና ሕዝባችንን እንዳትገድል በስፍራዋ  ትቀመጥ፡፡ /1ኛ ሳሙ. 5፤ 12/
በሰሜን ሸዋ ሀገረ ስብከት በደብረ ብርሃን አካባቢ ከአፄ ዋሻ ማርያም ገዳም የተሰረቀው የመድኀኔዓለም ታቦት ከጅቡቲ በተዓምራት ተመለሰ፡፡

ከአፄ ዋሻ ማርያም ገዳም የተሰረቀው የመድኀኔዓለም ታቦት ጅቡቲ ውስጥ ለ17 ዓመታት በአንድ ግለሰብ ቤት ተደብቆ ከቆየበት ተዓምራቱን በመግለጡ በተደናገጠው ቤተሰብ ጠቋሚነት፤ ጅቡቲ ለሚገኘው ለምሥራቀ ጸሐይ ቅዱስ ገብርኤል ቤተ ክርስቲያን  በማስረከብ ሚያዚያ 17 ቀን 2006 ዓ.ም. ወደ ኢትዮጵያ ተመልሷል፡፡

“በ1938 ዓ.ም. የተቀረጸውና በአፄ ዋሻ ማርያም ገዳም የነበረው የመድኀኔዓለም ታቦት ሐምሌ 28 ቀን 1989 ዓ.ም. የቤተ ክርስቲያኑን በርና መስኮት ተሰብሮ  መሰረቁን ለወረዳው ቤተ ክህነትና ለፖሊስ በወቅቱ አሳውቀን ነበር፡፡ ለማፈላለግ ያደረግነው ጥረት ሁሉ መና ሆኖብን ቆይቷል፡፡ እግዚአብሔር በወደደ ጊዜ ወደ ቤቱ ይመለስ ዘንድ ፈቀደ፡፡” ይላሉ የገዳሙ አስተዳዳሪ ቄስ ኃይለ ጊዮርጊስ መኮንን፡፡

ጅቡቲ እንዴት እንደተወሰደ እስካሁን በግልጽ የታወቀ ነገር እንደሌለ የሚገልጹት የጅቡቲ ምሥራቀ ጸሐይ ቅዱስ ገብርኤል ቤተ ክርስስቲያን አስተዳዳሪ ቆሞስ አባ ዮናስ መልከ ጼዲቅ “ታቦቱ በግለሰቡ ቤት ታላቅ ተዓምራትን ነው ያደረገው፡፡ በቤቱ ውስጥ ደብቆ ያስቀመጠው ግለስብ ሚስት ስታብድ ልጁ ሞቶበታል፡፡ በዚህ የተደናገጠው ሌላው የሰውየው ልጅ በቤታቸው ውስጥ ታቦት እንዳለና ወደ ቤተ ክርስቲያን እንዲወሰድ ባቀረበው ጥያቄ መሠረት ጉዳዩን በመከታተል ከጠቅላይ ቤተ ክህነት፤ ከውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር፤ በጅቡቲ የኢትዮጵያ ኤምባሲና ከሌሎችም ጋር መረጃ በመለዋወጥ ወደ ኢትዮጵያ ለማምጣት ችለናል” ብለዋል፡፡

ምንጭ

4 comments:

  1. Please change either the back ground color or the font color . It is impossible to read. Thank you

    ReplyDelete
    Replies
    1. Thanks for the comment. Actually, the main page is white and the background is black. I wrote with black fonts on a white background. Therefore, it should be very easy to read. I suppose it could be your browser.

      Delete
    2. Thankyou. I tried viwing the page from my phone. I will try it from a PC.

      Delete
  2. Please change either thefont color or the background color. Sinxe both coors are black (dark colors ) its impossible to read. Thank you

    ReplyDelete