Tuesday, August 19, 2014

ከእጇ ዘይት የሚፈልቅ የቅድስት ኤልሳቤጥ አስገራሚ ታሪክ

ወንድሞቼ እና እህቶቼ ይህንን ድንቅ ተአምር ስናገር እግዚአብሔር ምን ያህል ታላቅ እንደሆነ እመቤታችንም ምን ያህል ክብርት እንደሆነች እያደነቅሁ ነዉ፡፡ ነገሩ እንዲህ ነዉ ይህች የምትመለከቷት ቅድስት የድሮ ስሟ ሳሚያ ዮሴፍ ባሲሊዮስ ትባላለች፡፡ የቅርብ ጊዜ ቅድስት ናት ያረፈችውም 6 ወር በፊት ነዉ፡፡ ከእጇ ዘይት የሚፈልቅበት ምክንያቱ እንዲህ ነዉ፡፡ይህች ሴት በኃጥያት ትኖር ነበር(በሕይወቷ ቤተ ክርስትያን የሔደችዉ ልጇን ክርስትና ልታስነሳ ነበር) ሴት ልጇ ደግሞ ወደ ቤተክርስትያን ትሄዳለች ልጅቷ ስለእናቷ ወደ ቤተክርስትያን እንድትሔድላት ትጸልይ ነበር እናትየዋ በቀን 60 ሲጋራ ከማጨሷም በላይ ልጅቷን ልትመታት ትደርስ ነበር በቤቱ የአቡነ ሺኖዳ ስብከት ከተከፈተ ንዴቱ ይብስባት ነበር ዘፈን ከሆነ ግን ደስታውን አትችለውም፡፡ልጅቷ ግን መፀለይዋን አላቋረጠችም እንደውም ንስሐ አባቷን እያመጣች ልታስመክራት ስትሞክር ፈቃደኛ አልነበርችም፡፡ነገር ግን ንስሐ ተስፋ አልቆረጡም እንደውም በቅዳሴ ጊዜ ስሟን ጠርተዉ ስለፀለዩላት በሌላ ቀን ሲመጡ ተቀበለቻቸዉ ከመግባታቸዉ በፊት በሩ ላይ የመስቀል ምልክት አድርገዉ ነበር፡፡ከዚያ ለምን ወደ ቤተከርስትያን አትመጪም ሲሏት ቤተክርስትያን ያሉት ሰዎች ጥሩ አይደሉም ምክንያቱም ቅዱስ ቁርባን ተቀብለናል ብለዉ ግን ደግሞ ይተማማሉ አንዱ ላንዱ ጥሩ ጥሩ አይመኙም ብላ ለካህኑ ነገረቻቸዉ እርሳቸውም ልጄ ኃጥያተኛም እንዳለ ሁሉ ጻድቃንም አሉ ስለዚህ ጻድቃኖችንም ማየት ይኖርብናል ብለዉ ነገሯት ከዚያም ልጇ ከትምህርት ቤት ስትመጣ የእናቷን እና የካህኑን ውይይት ስታይ ደነገጠች ተደሰተችም ከዚያም ዓርብ ቤተክርስትያን እንድትሔድ ቃል አስገባቻት(ዓርብ ያለችበት ምክንያት ግብፅ ውስጥ ዓርብ በሙስሊሞቹ ምክንያት ሰለሚዘጋ እሁድ ደግሞ በክርስያኖቹ ምክንያት ስራ ዝግ ነዉ፡፡ቅዳሜ የስራ ቀን ነዉ፡፡

ከዚያም ዓርብ ደርሶ ቤተክርስትያ ሄዱ ቅዳሴዉ ሲጀመር እናትየዋ ማልቀስ ጀመረች ሙሉ ቅዳሴውን እስኪያልቅ ታለቅስ ነበር፡፡ካህኑ ቅዳሴውን በዓረብኛ ነበር የቀደሰዉ በኮፕት ቋንቋ ከቀደሰ ግን ቋንቋ ከቀደሰዉ ገና ከጅምሩ ላይገባት ስለሚችል ብሎ
ነዉ፡፡(ኢትዮጵያ ሁለት ቋንቋ እንዳለት ማለትም ግዕዝና አማርኛ እዲሁም ግብፅ ዓረብኛ እና ኮፕት ቋንቋ አላት ግዕዝን ሁላችንም እንደ ማንረዳዉ ሁሉ ኮፕትንም ማንም ስለማይረዳዉ ነዉ በዓረብኛ የቀደሰዉ፡፡ ነገር ግን የግብፅ ሙስሊሞች ኮፕት ቋንቋን አይጠቀሙበትም፡፡አያውቁትም፡፡)ከዚያም ወንጌል ሲነበብ ስለንስሐ ነበር የሚነበበዉ ከዚያም ቅዳሴዉ ስነ ስርዓት ከተፈፀመ በኋላ ካህኑ እንዴት አየሽዉ ሲላት እርሷም መልሳ ደስ ብሎኛል ካሁን በኋላ አልቀርም ብላ ደስ ብሎአት ትናገር ነበር፡፡በይ እንዳትቀሪ ብሎ ከካህኑ ካላት በኋላ ተሰነባብተዉ ተለያዩ ከዚያም እየመጣች ቤተክርስትያን መከታተል ጀመረች የሚገርመዉ ነገር በትምህርተ መስቅል ማማተብ አትችልም ነበር፡፡ካህኑም ሁሉንም ነገር ማለትም ከአባታችን ሆይ ጀምሮ አስተማራት ከተማረችም በኋላ ስለ ንስሐ ተማረች ከተማረችም በኋላ ንስሐ ገብታ የጌታችንን ቅዱስ ስጋውንና ክቡር ደሙን ተቀበለች ንስሐ በምትገባበትም ወቅት ሆነ ቅዱስ ስጋውን ክቡር ደሙን በምትቀበልበት ሰዓት ታለቅስ ነበር፡፡ዕንባዋም ፅዋዉ ጫፍ ላይ ጠብ አለ፡፡ካህኑም ጠንቀጠቀጠ እንደዚህ አይነት ሰዉ አጋጥሞት ስለማያውቅ ነበር፡፡
 

ከዚያም ቤተክርስትያንን ከመውደዷም በላይ በየቀኑ ትሄድ ነበር፡፡መዝሙራቱንም ሁሉ በቃሏ አጠናች ከዚያም የበጎ ነገር ጠላት የሆነዉ ሰይጣን በድሮ ወዳጆቿ እያደር ይፈትናት ነበር ነገር ግን እርሷ ታሸንፈዉ ነበር፡፡ሲከፋትም ካህኑ ጋር ትሄድና ስትነግረዉ ፈተናዉ ለበረከት ነውና አይዞሽ ይላታል፡፡ከዚያም የተረገመ ዲያቢሎስ ባልታወቀ ምክንያት በእባጭ በካንሰር እንድትመታ አደርጋት ያበጠውም ደረቷ ሳንባዋ ጭምር ነበር ከዚያም ዶክተሮች 5 ደቂቃ የሚያስታግስላት ጨርቅ አሰሩላት፡፡በመቀጠልም ካይሮ ሄዳ ቀዶ ጥገና እንድታደርግ ወይም ደረቷ እንዲቆረጥ (በግብፅ ባሕል በተለይ ለካህናት ለጳጳሳት ለዲያቆናት ሴቶች ደረት ላይ ያለዉ ነገር አይጠራም ለዚያ ነዉ ደረት ያልኩት፡፡)ይወሰናል ከዚያም ወደ ጌታ እግዚአብሔር ትጸልይ ነበር በህልሟም አንዲት አሮጊት ሴትዮ መጥታ ሣሚያ አይዞሽ አትፍሪ ትላት ነበር፡፡በጠዋት ለካህኑ ስትነግረዉ አይዞሽ ለበረከት ነዉ ይላት ነበር ነገር ግን በነጋታዉ ተመሳሳይ ህልም አየች ካህኑም ማናት ብሎ የቅዱሳን ሴቶች ስዕል ሲያሳያት ከዚህ ውስጥ አይደለችም ብላ ነገረችዉ፡፡በመቀጠልም እስኪ ንገሪኝ ምን አይነት ሴት ናት ብሎ ሲጠይቃት መጠነኛ ሰውነት ያላት ነጭ ልብስ የለበሰች እንደዚሁም የቆዳ መስቀል ጠለቀች ነች አለችዉ፡፡ እርሱም ለበረከት ነዉ አላት ከዚያ የደርት መቆረጡ ነገር አልዋጥልሽ ስላላት ለመሄድ ፈቃደኛ አልነበረችም ነገር ግን ግን የምትኖርበት ክፍለ አገር ፖርት ሰዒድ ይባላል የዚያ አገረ ስብከት ሊቀ ጳጳስ አንባ ታድሮስ(አቡነ ታድሮስ) /ቤቱ ጠርቷት አነጋገራት ለምንድነዉ የፈራሽዉ አላት እርሷም ቀዶጥገናውን ፈራሁት አለችዉ እርሱም ለስጋሽ እንድታስቢ አልፈልግም ነገር ግን ደረትሽን አስወግጂዉ ቢሉሽ አስወግጂዉ ለስጋሽ እንታስቢ አልፈልግም እና አላት፡፡እርሷም እሺ አሁን ስለተረጋጋሁ ስጦታ ስጡኝ ብላ ጠየቀችዉ እርሱም ቅድስት ድንግል እንደ ምትወጃት አውቃለሁ የእርሷን የአንገት ሐብል እሰጥሻለሁ ብሎ አጠለቀላት(ባንድ ጎኑ እመቤታችን ልጇን አቅፋ ባንድ በኩል ደግሞ የመገለጧ ስዕል ያለበት እኛ ኢትጵያውያን የኪዳነ ምህረት ስዕል የምንለዉ)፡፡እርሷም በጣም ደስ ብሎአት ከጽ/ቤቱ ወጣች፡፡


ከዚያም ያስተማራት ካህን ባለቤት ለምን እኛ ጋር አትድሪም ምክንያቱም ለመናኽሪያውም ቅርብ ስለሆነ አለቻት፡፡በነገሩ ተስማታ እንደምትመጣ ቃል ገብታ ቤቷ ተመለሰች ከዚያም 4 ሠዓት ሩብ ጉዳይ ሲል ካህኑ ቤት መጣች ባለቤቱም ተቀበለቻት ስትገባም ዕጣን ዕጣን የሚል ሽታ ሸተታት እርስዋም ደስየሚል የቤተክርስትያን ሽታ ይሸተኛል አለቻት የካህኑም ባለቤት እኔ አይሸተኝም ብላ መለሰችላት(ጉንፋን ይዞአት ነበር) ካህኑም መጥተዉ ሳሚያን ሲያይዋት ደስ አላቸዉ፡፡ሁሉም ፀሎት አድርገዉ ራት በልተዉ ልጆቹን ካክስታችሁ(ካክስታችሁ ያሉበት ምክንያት በግብፅ ባሕል ታላላቅ ሰዎችን ዘመድም ሌላም ሰውም ቢሆን እንኳን ቢሆን አጎት አክስት በመባል ነዉ የሚጠራዉ ፡፡) ሳሚያ ጋር ተኙ ሲሎቸዉ፡፡አንተኛም አሉ ከልጆቹም አንዱ ካህኑ ቤት ሲገቡ ባባ ባባ የቤተክርስትያን ሽታ የሚመስል ሽታ ይሸተኛል በሎአቸዉ ነበር፡፡ ከተኙም በኋላም ከለሊቱ 7 ሠዓት ሳሚያ መጮህ ጀመርች እርሷም እህ እህ አመመኝ ትል ነበረ፡፡ካህኑም ሲነሱም ጥጮህ ነበር ወደ ክፍሏ ሲገቡ ደም በደም ሆናለች የማስታገሻውም ጨርቅ ተነስቶ መስቀል ተስሎበታል እጢዎችወጥተዉ ደረቷ ላይ ተቀምጠዋል ደንግጠውም ሲጠሯት ሳሚያ ድንግል ማርያም ትል ነበር ከዚያ ማደንዘዣ ሸተተኝ ብላ ተመልሳ ተኛች፡፡ጠዋት ካህኑ 12ሰዓት ተነስቶ ለባለቤቱ አኔ ቤተክርስትያን መሔዴ ነዉ(ኪዳን ሊያደርስ)እባክሽ አደራ ጠብቂያት ብሎአት ሔደ፡፡ሲመለስም ባለቤቱ በደስታ ብዛት ድንግል ማርያም ለሳሚያ ተዓምር ሰራችላት እያለች ትናገር ነበር ከዚያም ምን ሆንሽ ብለዉ ሲጠይቋት ሌሊት እንደተኛን እመቤታችን ቅድስት ድንግል ማርያም ተገለጠችልኝ በመቀጠልም ሳሚያ ቀዶ ጥገና ላከናውንልሽ ነዉ የመጣሁት አለችኝ አኔም እንዴ ጡቴን ልትቆርጭንኝ ነዉ እንዴ አልኳት እርሷም የማክምሽ እኔ ስለሆንኩ አትፍሪ አለቺኝ ከእርሷ ጋር ሁሌ በሕልሜ የማያት አሮጊቷ ሴትዮ እናት መልዓክ የሚመስል ትንሽ ልጅ ነበረ፡፡ከዚያ ወደ ሰማይ ይዛኝ ሄደች በመቀጠልም አንድ ሽማግሌ ሰውዬ ቆዬኝ እኔንም ጠብቁኝ አለ ማነዉ እርሱ ብዬ እመቤታችንን ስጠይቃት የቅዱስ አባ ቢሾይ ቤተክርስትያን የበላይ ጠባቂ ነዉ፡፡(ጻድቁ አባ ቢሾይ) ነዉ አለቺኝ የምንራመደውም የዕጣን ጢስ በመሰለ ደመና ነበረ፡፡ ከዚያም ወደ ትልቅ የሚያምር ቤት ደረስን እመቤታችን በመጀመሪያ ስትባ የበሩ መከፈት አላስፈለጋትም ነበር እም እንደዚሁ ገባን፡፡በመቀጠልም በቃላት ሊነገር የማይቻል ውበት ነበረዉ በሚያምሩ ነጫጭ መጋረጃዎች ተሸፍኗል፡፡በቤቱ በነበረዉ መልካም መኝታ ላይ ተኛሁ፡፡አሮጊቷ ሴትዮ እና ጻድቁ አቡነ ቢሾይ አጄን ያዙኝ ከዚያም ለእመቤታችን ፈራሁ አልኳት እርሷም አትፍሪ አለቺን ልክ ስትነካኝ የማሳከክ ሰሜት ተሰማኝ እና አመመኝ ብዬ አጄን ከቅዱሳኑ አስለቅቄ የሚየመኝ ቦታ ላይ አስቀመጥኩት(ካህኑና ባለቤቱ ይሰሙት የነበረዉ ድምፅ ነዉ፡፡እመቤታችንም ቅዱሳኑኑ በቁጣ አይን ስትመለከታቸዉ ደግመዉ ጥብቅ አድርገዉ ያዙኝ ጻድቁ አቡነ ቢሾይ በማማበል መልክ እጄን መታ መታ ያደርጉኝ ነበር ከዚያም ሁለት ክንፍ ያለዉ ልጅ ለእመቤታችን የሆነ ነገር ይሰጣታል ግን አየታየኝም ከዚያም ከደረቴ ጀምሮ እስከ እላይ ድረስ ከፈተችዉ እጢውን ሁሉ አወጣችዉ፡፡ ከልቤ ያለዉ ነገር ሁሉ ተነሳልኝ፡፡በደሙ እያጠቀሰች በተጠመጠመልኝ ሻሽ ላይ በደሜ መስቀል ሰራችበት(በደም እያጠቀሱ እንዲያውም በጣት እያጠቀሱ ግሩም የሆነ መስቀል መስራት አይቻልም፡፡በማስመሪያ ተለክቶ የተሳለ ነበር የሚመስለዉ፡፡) እና የከፈተችውን መልሳ ዘጋችዉ(ስፌት ግን አልበረውም እንደውም አዲስ ቆዳ ተፈጠረልኝ ነበር የሚመስለዉ፡፡ከዚያም ሁሉም ተሰወሩ እርሷ እና ቅዱሳን መላዕክት ቀርተዉ ነበር፡፡በመቀጠልም ይህንን ዕጢ ዘይቱን የዘሽዉ ነይ አለችኝ አኔም ዘየቱን የት ነዉ አልኳት ከዚያም ተሰወረችብኝ፡፡ታሪኩን ካበቃች በኋላ ዘይቱን የሚባለዉ የት ነዉ ብላ ጠየቀች ካህኑም ዘይቱን በሚባል ሰፈር የእመቤታችን ቤተክርስትያን አለ፡፡እዚያ ቤተክርስትያን ላይ እመቤታችን የተገለፀችበት ነዉ ብሎ ነገራት፡፡ከዚያም ለሌሎች ካህናት ለሊቀ ጳጳሱ ተደውሎ ተነገራቸዉ እርሳቸውም መጥተዉ አይተዉ ጌታ እግዚአብሔርን አመሰገኑ የከተማዉ ሰዉ ሙስሊምም ክርስትያንም ሰማ እንዳንድ የሙስሊም ጋዜጦች ተዓምሩን አጠራጣሪ ለማድረግ ሞክረዉ ነበር ብፁዕ ወቅዱስ አቡነ ሽኖዳ ሳልሳዊ ይህንን ሰምተዉ ተዓምር የተፈፀመላትን ሴት አነጋግረዉ መረጃ አይተዉ እውነት ነዉ ብለዉ ለህዝቡ ይፋ አድርገዋል፡፡


ከዚያም እመቤታችን ከአስር ቀናት በኋላ ለሳሚያ ተገለጸችላት ሳሚያም እመቤታችን ውብ ሆና በነገስታት ወንበር ላይ ተቀምጣ ግርማዋ የሚያስፈራ ሆና አየቻት በመቀጠልም እመቤታችንም ሳሚያ ሰዎች ስላላመኑ በጣም አዝኛለሁ በመሆኑም ማንም የማይቀማሽን ነገር እሰጥሻለሁ ስለዚህ ራስሽን ለእግዚአብሔር ለዩ ይህንን ዓለም ተዬና ፈጣሪሽን አገልግዬ አለቻት ከእመቤታችንም አጠገብ በብዚ የሚቆጠሩ መላዕክት ነበሩ፡፡ ሳሚየም ወደ እመቤታችን ዞር ብላ ይህች አሮጊት ሴትዮ ማነች ብላ ጠየቀቻት እመቤታችንም እርሷን አሮጊት ብሎ መጥራት አይገባም ደግሞም ስሟን ራስሽ ጠይቂያት ብላ መለሰችላት ሳሚያም ስትጠይቃት ኤልሳቤጥ እባላለሁ የመጥምቁ ዮሐንስ እናት ነኝ አለቻት ሳሚያም መልሳ ታዲያ ስዕልሽ በእኛ ዘንድ አይገኝም አለቻት ቅድስት ኤልሳቤጥም መልሳ የልጄ የመጥምቀ መለኮት ቅዱስ ዮሐንስ ስዕል አላችሁ ስለዚህ እኔ በዚያ አለሁ አለቻት፡፡የትንሹ ልጅ ስም ደግሞ ሕፃኑ ሰማዕት ቅዱስ አባኖብ ነበረ(አባኖብ ካህን ሳይሆን አባትነህ ብለን እደምንለዉ በኮፕት ቋንቋ የወርቅ አባት የሚል ትርጉም አለዉ)፡፡ስለሆነም ሁሉንም ቅዱሳን ስም አወቀች፡፡


ከዚህ ሁሉ በኋላ አንድ ቀን ቅዳሴ እየስቀደሰች እያለች ፊቷ በዘይትና በሽቶ ባለዉ እምነት ተሞላ በመቀጠልም ከእጇ ዘይት መንጠባጠብ ጀመረ ቀጥሎም ስጋ ወደሙ ስትቀበል ይባስ ባሰበት ከዚያም ስለነገሩ ለብፁዕ ወቅዱስ አቡነ ሽኑዳ ተነገራቸዉ እርሳቸውም ነገሩን አረጋግጠዉ እውነት እንደሆነ ይፋ አደረጉ ቀጥሎም የእመቤታችን የመገለጧ ስዕል(ኪዳነምህረት የምንለዉ ስዕሏ ግብፆች የመገለጣ ስዕል ይሉታል እመቤታችን በዘይቱን ስትገለጥ በዚህ መልክ ነበር የታየችዉ፡፡)በመቀጠልም የአገረ ስብከቱ ጳጳስ የታሶኒ ልብስ አለበሳት(ታሶኒ ማለት ኑሮዋ በግል ቤቷ ሲሆን ነገር ግን ቤተክርስትያንን የምትከባከብ ሕፃናትን የምትከባከብ ነች፡፡ወይም የሴት ዲያቆን ማለት ነዉ፡፡ ማለትም መንበር ገብታ አትቀድስም ግን ከላይ የጠቀስኩትን ነገሮች የምታሟላ ነች፡፡ እመቤታችንም ራስሽን ለእግዚአብሔር ለዩ እንዲሁም ማንም የማይቀማሽን ነገር እሰጥሻለሁ ስላለቻት ነዉ የታሶኒነት ማዕረግ የተሰጣት፡፡)ስሟም ተቀይሮ ኤልሳቤጥ ተብሎአል፡፡ይህ ዘይት ከእመቤታችን ስዕል ላይ እየወረደ ከስሩ ባለዉ ፕላስቲክ ላይ ይጠራቀማል ቀለሙም ነጭ(ውሃ መሳይ)ነዉ በተለይም ሽታዉ ደግሞ በጣም ልዪ ልዩ ደስ የሚል ነዉ(በቃላት ሊገለጥ አይቻልም፡፡)ይህ ተዓምር ከተፈፀመ 20 አመቱ ነዉ፡፡የእመቤታችን ስዕል ዘይት እያፈሰሰ እስካ አሁን ድረስ አለ፡፡የታሶኒዋ ደግሞ ቀላ ያለ ዘይት ነዉ አንዳንዴም እምነት ይወጣት ነበር፡፡ብዚ ሰዎች ሙስሊም ክርስትያን ጴንጤ ካቶሊክ የተባለ አይቱን እየወሰደ እየተቀባ ይገኛል፡፡እየተፈወሰም ነዉ፡፡ሙስሊሞች ምን አሉ መሰላችሁ ወርቅ በዘይት መልክ ፈሰሰ ብለዉ ተናግረዋል፡፡የልዑል እግዚአብሔር ቸርነት የእመቤታችን አማላጅነት የቅድስት ኤልሳቤጥ፣የጻድቁ የአቡነ ቢሾይ፣የሕፃኑ ሰማዕት የቅዱስ አባኖብ ተራዳኢነት ከሁላችን ጋር ይሁን አሜን፡፡