Sunday, March 30, 2014

ባሕታዊ አባ ገብረ ጊዮርጊስ

ባሕታዊ አባ ገብረ ጊዮርጊስ በቦሌ አየር ማረፊያ ደ/ፀ/ቅ ጊዮርጊስ ቤተ ክርስቲያን የተደረጉ የስብከት እና የፈውስ አገልግሎት

Holy water at Entoto Kidane Mihret Church የ እንጦጦ ኪዳነምህረት ጸበል

Thursday, March 20, 2014

ሰበር ዜና - ሕገ ወጥ ደብዳቤ

የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተክርስቲያን "መልአከ መንክራት ግርማ ወንድሙ" በሚል ስያሜ የተበተነው ደብዳቤ ሕገ ወጥ በመሆኑ የሚመለከተው ሁሉ ይህን ግንዛቤ እንዲወስድ አሳሰበች፡፡
በሚል ከዚህ ጋር ተያይዞ የወጣውን እና የተሰራጨውን ደብዳቤ አስነብበናል:: አሁን ከ ከ ቅዱስ ፓትሪያሪኩ  http://www.eotc-patriarch.org/#
 ድኅረ ገጽ በወጣው መግለጫ ደብዳቤው ጥንቃቄ እንዲደረግበት ማሳሰቢያ ተሰጥቷል:: ደብዳቤው ከታች እንደምትመለከቱት ነው::
የቀድሞውን ደብዳቤ በተመለከተ መምህር ግርማ በሬድዮ አቢሲኒያም ሆነ ተከታታይ በወጡት VCD 26 እና 27 ላይ የተናገሩት ነገር የለም:: ደብዳቤውም ወጣ የተባለበት ከአመት በላይ ያለፈው ግዜ 05/19/2005 በዚህ ጉዳይ ላይ መምህር ግርማ ያረጋገጡልን ነገር የለም:: ስለዚህ ይህን አይነት ድርጊት እየሰራ የመልአከ መንክራት ግርማ ወንድሙን ስም ለማበላሸት የሚጥሩ ስላሉ እርሳቸውን ተጠያቂ ከማድረግ እንድንቆጠብ እናሳስባለን:: ሰሞኑን የርሳቸው ቭኢዲዮ ከነድረገጹ ሁሉ በማጥፋት የ እግዚያብሔር ስራ እንዳይተላለፍ እንቅፋት የሆኑ እንዳሉ የምናውቀው ነው:: ከ ሁለት ደርዘን በላይ ምስሎች አሁን በ ንቁ ተአምረ ጽዩን ማየት የሚቻለው የተወሰኑንት ብቻ ነው::

ይህ ድረ ገጽ የተሳሳተ መረጃ በማቅረብ አላስፈላጊ መደነጋገር ውስጥ ስለከተትን ይቅርታ እንጠይቃልን::  የመምህር ግርማ አገልግሎት መስፋፋት እና የሕዝቡን መዳን ስለምንወድ አገልግሎታችንን ከበፊቱ ይልቅ የተጠናከረ እንዲሆን እንተጋለን:: 

መዝ 119: 121 "ፍርድንና ጽድቅን ሠራሁ፤ ለሚያስጨንቁኝ አሳልፈህ አትስጠኝ።"