Wednesday, February 1, 2017

"የጎጆዋ አርሴማ" - ድንቅ ነገር


☞ እንሆ በአዲስ አበባ በቦሌ ቡኒ ቅዱስ እግዚአብሔር አብ እና ቅድስት አርሴማ ቤተክርስቲያን የተከናወነ ድንቅ ነገር !!!!!! እንዲህ ሆነ በ ጥር 10 2009 ዓ ም የጥምቀት በዓለ ክብር ከተራውን ፈጽመን እንሆ በ 13 የቅዱስ እግዚአብሄር አብ , ቅድስት ኪዳነምህረት ,ተክልዬ, አና አርሴምዬን አጅበን ወደ መንበረ ክብሩ ደረስን ስርአተ ቤተክርስቲያኑን አከናውነን በእግዚአብሔር ፈቃድ እና በአባቶች ራዕይ ጽላቷ የመጣችው ቅድስት አርሴማ በድጋሚ ከገዳማውያን አባቶች የተነገሩትን መልእክት በአውደ ምህረት ተናገሩ እንዲህ አሉ "ሰማዕቷ ቅድስት አርሴማ ጥንታዊ ለዛ ያለው ጎጆ ቤተክርስቲያን ሰርታችሁ በዛ አስገቡኝ " ብላለች ብለው ራዕዩን ተናገሩ ፡፡

ከዚህ በኀላ ማሳረጊያ ጸሎት ተደርጎ ታቦታቱ ወደመንበረ ክብራቸው ሲገቡ የቅድስት አርሴማን ያከበሩት አባት ተፍገመሙ ምን አልባት እረጅም መንገድ ስለተጓዙ ይሆናል በሚል ሌላ ካህን ተቀየሩ እንዲሁ እኒህ አባት ተንቀጠቀጡ በዚህ ጊዜ ምዕመናን በለቅሶ በዋይታ ተንበርክከው ማልቀስ ጀመሩ በዚህ ጊዜ ካህኑ ወደ ኀላ መልሳቸው እኛም ታቦቱን በማጀብ በእግዞታ ተከተልን በቅጽረ ቤተክርስቲያኑ ውስጥ በስተ ምስራቅ በኩል በጣም ቆንጆና ደልዳላ ቦታ ላይ ስትደርስ ካህኑን አቆመቻቸው በዚያች ቦታ ጸሎት ተደርጎ መሰረት ተጣለ ፡፡ ከዚህ በኀላ በነባሩ ቤተክርስቲያን በረንዳ ላይ ድንኳን ተጥሎ ታቦቷ በዛ አደረች እስካሁን በዛው ትገኛለች ፡ በአለቱ በተገኘው ገቢ እና በበጎ አድራጊዎች ታግዞ ጎጆ ቤትዋ በመሰራት ላይ ትገኛለች እንግዲህ በሰማዕቷ መልካም ፈቃድ በቀን 28/05/09 ዓም ጸሎተ ምህላ አድርሰን ቅዳሴ ቤቷን ለማክበር በዝግጅት ላይ እንገኛለን የሰማዕቷ ወዳጅ የሆነ ሁሉ በቤቷ እንድትገኙ ጥሪዋን ታስተላልፋለች ፡፡ታዋቂው እና ፈዋሹ የሰማዕቷ የማር ጸበል እንዳያመልጣችሁ ይህም ከመቅደሳ የተገኘ ነው ፡፡እንዲሁም ሀብተ ፈውስ ባላቸው አባት በመምህር አብርሃም የጸበል አገልግሎት ይሰጣል ፡፡ አድራሻ ከጎሮ ወደ ቱሉዲምቱ በሚወስደው መንገድ ላይ ሁለተኛውንና ትልቁን ድልድይ ሳይሻገሩ አስፋልቱ ዳር ላይ ይገኛል እግዚአብሔር አብ እና ቅድስት አርሴማ ቤተክርስቲያን ፡፡ለበለጠ መረጃ 0913511802 ወይም 0936451511ይደውሉ፡፡ በተጨማሪ ☞መንፈሳዊ ጉዞ የምታዘጋጁ መንፈሳዊ ማህበራት አና የቤተክርስቲያን ልጆች ወር በገባ በ 6 ወደዚህች የበረከት ደብር በሆነች ምዕመናንን እንድታስጎበኙልን እና ምዕመናንን የበረከቱ ተካፋይ ታደርጓቸው ዘንድ ቤተክርስቲያን ጥሪዋን ታስተላልፋለች ቤተክርስቲያናም ማንኛውንም መንፈሳዊ ተግባራት ታከናውናለች ፡፡የሰማዕቷ ቅድስት አርሴማ በረከት ይደርብን አሜን፡፡
ጸሐፊ ዲ/ን ኤርምያስ ግርማ


የቅድስት አርሴማ አዲስ ፀበል


No comments:

Post a Comment