Wednesday, February 8, 2017


ዛሬ የአባታችን የአቡነ ገብረ መንፈስ ቅዱስ ታላቅ የድህነትን ስጦታ ስለተቋደሰች እህታችን ላይ የተፈፀመውን ድንቅ ታምር ላውጋችሁ፣ ከስር ፎቶው ላይ የምትመለከቷት እህታችን በጡት( thoracic cancer) ካንሰር ደዌ ተይዛ ለዘመናት በመፍቴህ አልባ እንቅስቃሴ የአለም ሆስፒታሎችን በር በማንኳኳት ስትዳክር ቆይታለች ።ከሃገር ውስጥም ሆነ ከሃገር ውጪ ባሉ ስመጥር የህክምና ዶክቶሮች ዘንድ በመቅረብ ለችግሯ መፍቴህ የሚሆናትን መንገድ ስታፈላልግ ብትደክምም አንዳቸውም ከስቃይዋ ሊያሳርፏት አልቻሉም ። ባላት ሙሉ አቅም መነካት እና መደረስ አለበት የተባሉትን ሁሉ ብትነካም የበሽታው ህመም እና ስቃይን እንዳያድግ ከማድረግ አላገዳቸውም ።ኑሮዋ በስቃይ ላይ ስቃይ በህመም ላይ ህመም የሆነላት ይህች እህታችን ግን በአንድ ወቅት ከአንድ ወዳጇ ታምራዊ ፀበል ከወደ አርባምንጭ እንደፈለቀ እና ብዙዎች በመጠመቅ እንደተፈወሱ በመንገር አይኗን ገልጣ ሞትን ከመጠባበቅ እድሏን እንድትሞክር ይነግሯታል።እሷም ይህን ጥሪ ችላ ለማላት ባትፈልገውም ልሞክረው በሚል ሃሳብ ወደ ስፍራው (ዝጊቲ አርባምንጭ) ትመጣላች ።በተፀበለችው ቀናት ሁሉ በሽታው ከሚያደርስባት ስቃይ እና ህመም ማገገም እና ማረፍ ጀመረች ።ከጥቂት ሱባኤ በሃላ የልዑል እግዚአብሄር የማዳን ፍቃድ በአባታችን አቡዬ ገብረ መንፈስ ቅዱስ ፀበል ላይ በመስፈፍ እህታችንን ሙሉ በሙሉ ከበሽታዋ እንድትድን እና እንድትፈወስ አደረጋት። ይህንንም በአለም የህክምና ምርመራ በማረጋገጥ የአቡዬን ድንቅ ስራን ለአለም በመስበክ ምስክርነቷን በተለያዩ ጉባኤዎች ላይ ሰጥታለች ።ይህን የአባታችንን ውለታ የማይረሳ ልብ ያላት እህታችን ከሞት ፅልመት በፈውሳቸው ጎትተው ላወጧት አባታችን ውለታ በማሰብ የደብሩን ህንፃ ቤተክርስትያኑን ብቻዋን በአዲስ መልክ ለመስራት በማቀድ እና በማሰብ የ20 ሚሊዬን ብር የቤተክርስትያን ዲዛን በማሰራት እና ግንባታውን በመጀመር በስራ ላይ ትገኛለች ።
 

No comments:

Post a Comment