Showing posts with label ተአምራት በሸንኮራ ዮሐንስ. Show all posts
Showing posts with label ተአምራት በሸንኮራ ዮሐንስ. Show all posts

Tuesday, September 19, 2017

ሙስሊሟዋ ድንቅ ተዓምር በሸንኮራ ዮሐንስ ተደረገላት

" ደስታና ተድላም ይሆንልሃል፥ በመወለዱም ብዙዎች ደስ ይላቸዋል። በጌታ ፊት ታላቅ ይሆናልና፥ የወይን ጠጅና የሚያሰክር መጠጥ አይጠጣም፤ ገናም በእናቱ ማኅፀን ሳለ መንፈስ ቅዱስ ይሞላበታል።ከእስራኤልም ልጆች ብዙዎችን ወደ ጌታ ወደ አምላካቸው ይመልሳል " ሉቃ.1፡14
ሸንኮራው ቅዱስ ዮሐንስ ድንቅ ተአምር
ሃይማኖቴ "ወልድ ፍጡር፣ ቤተክርስቲያን ድንጋይ ናት" ሎቱ ስበሐት ። ከሚሉ አሕዛብ ወገን ነበርኩ የምትለዋ እህታችን መኖሪያዋ በመዲናችን አዲስ አበባ ነው ። ክርስቲያን የሚባል አልወድም፣ ፍጹም ጥላቻንም የተሞላው ነበርኩ። አምላኬን ያስደሰትኩ መስሎኝ አንድ አብሮ አደግ ክርስቲያን ጓደኛ አለችኝ። ብሰድባት ብተፋባትም ጉዳይዋ አይደለም ኣትቀየመኝም። ቅዱስ ዮሐንስን በጣም ትወደዋለች።
እኔ በስኳር በሽታ ምክንያት አንድ እግሬ በጋንግሪን (የተወሰነ አካል መሞት) እንዲቆረጥ ሐኪም ወሰነ። ያች ጓደኛዬ ግን የዮሐንስ ጸበልን ቤቴ አመጥታ ሰጠችኝ። ተቀብያት ከፊቷ ይህ እኮ "ውሐ" ነው ተረት አታውሪ ብዬ ስደፋው የጸበል ዕቃውን የያዘ እጄ ሰለለ ሽባ ሆነ፤ ደነገጥኩኝ። የጥፋተኝነት ስሜት ተሰማኝ። አይዞሽ ምልክት ነው መጥምቁ ያማልድሻል አለችኝ። "ኦፕራሲዮኑን ተይው አንቺ ካልዳንሽ እኔ ሃይማኖቴን እቀይራለው" ስትል ቤተሰቤ በሃሳብ ለሁለት ተከፈለ። እግሬ በአስቸኳይ ይቆረጥ ተብሏል። እግሬም ቁስሉ ሽታ አመጣ። በዚያ ላይ በሃይማኖቴ፣ ቤተሰቤ ሁሉ በአይነ ርግብ ተሸፍኖ የሚሄድ ነው። መገላለጥ የለም፤ "እዛ ብትሔጂ እንረግምሻለን" አሉኝ። በመጨረሻ ውሳኔ የኔ ሆነና ከሶስት ቤተሰብና፣ ከዚህችው ወዳጄ ጋራ ሸንኮራ ሄድን። ወደ ጸበሉ መውረድ አልቻልኩም አምጥተው አጠመቁኝ። ቁስሉ እንደቅርፊት ወደቀ። እንደውም ጸበሉን የደፋሁበት እጄ ዳነ። የምን መቆረጥ የምን ጋንግሪን።
የሕመሜም ምክንያት የነበረው 23 አመት ያሰቃየኝ ስኳሩም ዳነ። አብራኝ የሄደች አንድዋም ቤተሰቤ በፍንጢጣ ኪንታሮት ትሰቃይ ነበር የባህል መድሐኒት ወስዳ ጽኑ ህመም ላይ ነበረች እርስምዋ ዳነች።በሰማዕትነት ለአምላኩ ምስክር የሆነው መጥምቁ ዮሐንስ ከአምላክ አማልደህ ካዳንከኝ ጥላ በሬ ላምጣ አልልም አንተ ምስክር ለሆንክለት “በክርስቲያን አምላክ በኢየሱስ ክርስቶስ አምናለው” ብዬ ነበር።
ይህም ድኜ ለስዕለቴ በቃው ከስምንት ቤተሰቤ ጋር ሃብተ ወልድና ስመ ክርስትና ተቀበልኩኝ። ትለናለች።
እህተ ዮሐንስ፤ፍቅርተ ዮሐንስ፤ወለተ ብርሐን፤ተጠምቀ መድህን፤ክፍለ ዮሐንስ፤ገብረ ዮሐንስ፤ወልደ ዮሐንስ፤አርከ ዮሐንስ ተብለን የቀራኒዮ ቤዛ ወደ አብ ወልደ ማርያም ኢየሱስ ክርስቶስ ነቢይ ሳይሆን አምላክ እንደሆነ አምነን በአብ በወልድ በመንፈስ ቅዱስ ስም ተጠምቀናል።
ቅዱስ ዮሐንስም ተአምር ግን ድሮ ነው የጀመረው ጎረቤቴ ዝክሩን ስታደርግ አትጥሪኝ እላት ነበር። ዝክሩንም አልበላም ጣኦት አምላኪ አድርጌ ነው የምቆጥራት። የክርስቲያኖች አምላክም ብዙ ነበር የሚመስለኝ። አወይ አለማወቅ በድብቅ ግን ዝክሩን በልጆች ስም አስመጥቼ እበላ ነበር።ይጣፍጠኛል ለካ በስተመጨረሻው የሕይወት እንጀራን ስጋ ወደሙ ሊያበላኝ ኖሯል እንዲያ የጣፈጠኝ፤ ትላለች እህታችን በጥምቀቱ ስነ ስርአት በዓይኔ በአካል ተገኝቼ በከተማችን በሚገኝ አንድ አጥቢያ ተከታትያለው ይለናል አንተነህ ሐይሌ።
እኛ የእምነት አቃቂር ስናወጣ ጥቅስ ስናገላብጥ የዛሬ 2000 አመት አንገቱ የተቆረጠው መጥምቁ ዮሐንስ ስንት የጠፋውን መንጋ ጥቅስ ሳይጠቅስ ቃላት ሳያዥጎደጉድ በፍቅሩ አስሮ በምልጃው ጠብቆ ለጌታው ምርኮን አስገባ። ይህን ያደረገ የመጥምቁ አምላክ ክብር ይግባው ዮሐንስ ነቢይ ሰማዕት እኛንም ያማልደን አሜን።
ከአንተነህ ኃይሌ ገጽ ተገኝቶ ጥቂት እርማት የተደረገበት የእውነት ምስክርነት። ወደፊት ግለሰቦቹ አነጋግረን የበለጠ መረጃ ለማድረስ እሞክራለሁ። “ እላችኋለሁ፥ እንዲሁ ንስሐ ከማያስፈልጋቸው ከዘጠና ዘጠኝ ጻድቃን ይልቅ ንስሐ በሚገባ በአንድ ኃጢአተኛ በሰማይ ደስታ ይሆናል።”ሉቃ 15:7

Wednesday, June 8, 2016

ተአምራት በሸንኮራ ደብረ መንክራት ቅዱስ ዮሐንስ

ሸንኮራ ዮሐንስ ከአየር ላይ ሲታይ የገደሉ መሐል ጸበሉ ያለበት ነው ያች 8የማይበልጡ የጭራሮ ጎጆ የነበረች መንደር ዛሬ የፈውስ መዲና ሆና ዘምናለች 20 ሰው የምትይዘው ቤተክርስቲያን ዛሬ ታላቅ ህንጻ ተገንብቶባታል የነፍስም የስጋም ሆስፒታል ሆናለች አጥቢያዋ



















አቶ በላይ ደምሴ የተባሉ አባት ከባሌ ክፍለሐገር
ሁለቱም ጆሮዋቸው መስማት አይችልም ነበር አባታችን የመጥምቁን የፈውስ ዝና ቢሰሙም ወደ ሸንኮራ ለመምጣት አቅም ያጣሉ አንድ በአካባቢያቸው የሚያውቁትን ወጣት ጸበል አምጣልኝ ብለው 500 ብር ለትራንስፓርት ሰጥተው ይሸኙታል ልጁ እዛው ሲያውደለድል ተደብቆ ከርሞ ከወንዝ ውሐ ቀድቶ ይሰጣቸዋል አቶ በላይም የተሰጣቸውን ውሐ በእምነት ሲጠጡት ጆሮዋው ተከፈተ ድንቅ ነው በዚያው ቅጽበት የወጣቱ ሁለቱም ጆሮ መስማት አቆመ ይህ ወጣት ጥፋቱን ያውቃልና በንስሐ አባቱ አማካኝነት ወደ ሸንኮራ መጥቶ ለነፍስም ለስጋው ንስሐ ገብቶ ቀኖና ተቀብሎ ይፍታህ በሚባልበት 14ኛ ቀኑ ላይ ጆሮው ተከፍቶ በአንደበቱ የሰራውን ጥፋትና የተደረገውን ድንቅ ተአምር መስክሮዋል ይህን ያደረገ የመጥምቁ አምላክ ክብር ይግባው አሜን

ወ/ሮ ሐዱሽ ገ/ዋህድ ይባላሉ ከገጠሪቱ ኢትዮጵያ 16 አመት የታወረ አይናቸውን ለመታከም ነው ወደ መሐል ሐገር የመጡት አዲስ አበባ ኦፕራሲዮን ቢያደርጉም ተስፋ የለውም እንዲሁ ይኑሩ ይባላሉ ቤተክርስቲያን ለመሳለም ሄደው የሸንኮራን ታሪክ ሰዎች ሲያወሩ ሰምተው አድራሻ ጠይቀው መሪ አስታማሚ ይዘው ጉዞ ወደመጥምቁ ቤት ተከራይተው ጸበሉን መጠመቅ ይጀምራሉ 8ኛ ቀን ላይ ወደ ጸበሉ መውረጃ ገደሉን መንገድ ከመሪያቸው ጋር ይጀምራሉ መሪያቸው ድንገት ወደ ጫካ ለሽንት ትገባለች እሳቸውም ከምቆም ብለው መንገድ ይጀመራሉ በምርኩዛቸው ድንገት ያላሰቡት ነገር ተከሰተ የለበሱትን ነጠላ ቆንጥር ያዘብኝ መንገዱም ቁልቁለት ላይ ነበርና የያዝኩትምርኩዜም ከእጄ አምልጦ ተንሸራቶ ርቆ ወደቀ በቆምኩበት ደነገጥኩኝ ተማረርኩኝ ሞቴን ተመኘው አዘንኩኝ ምነው ዮሐንስ ብዬ ነጣላዬን ከእሾኩ ለማላቀቅ ፊቴን ሳዞር የጠፋው አይኔ ቦግ አለ ማመን አልቻልኩም እየተመራው የወረድኩትን ገደል ህዝቡን እየመራው በእልልታ በሆታ ወጣውት ብለው መስክረዋል እኝህ እናት በወቅቱ ከደስታቸው ብዛት ግቢው ውስጥ ይንከባለሉ ነበር ይህን ያደረገ የመጥምቁ አምላክ ክብር ይግባው አሜን

ሸንኮራን የሚያውቅ ሁሉ ምንትዬ ዮሐንስ ምን እንዳደረገላት የማያውቅ የለም በስምዕ ጽድቅ ጋዜጣ በዜና ቤተክርስቲያን በደብሩ መጽሔት ታሪክዋ በሰፊው ተመዝግቦዋል ስቃየ ብዙዋ እህታችን አዲስ አበባ ጎፋ መካነ ህያዋን ቅዱስ ገብርኤል ሰንበት ተማሪ የሆነችው ምንትዬ ታሪክዋ ሰፊ ስቃይዋ ዘግናኝ ነበር አትተኛም አትቀመጥም አትራመድም የዮሐንስ ያለህ ያዮ ይመስክሩ በልብ በኩላሊት በደም ብዛት እረ የበሽታዋ አይነት ብዛቱ መለኮትን ባጠመቀበት እጁ ዮሐንስ የታሰረችበትን ደዌ ሁሉ ፈታት ከሰውነትዋ የሚወደው ደምና መግል ተወግዶ ሞትሽን ጠብቂ በሳጥር ተቁዋጥረሽ ልትጣይ ነው የተባለችው ምንትዬ ይህው ዛሬ በእግርዋ ቆማ የመጥምቁን ደጅ ጥዬ አልሄድም ብላ እንግዳ ተቀባሪ ጸበልተኛ አጉራሽ ሆናለች እስቲ ሰኔ 30 ኑና የመጥምቁን ታሪክ ጽናት ትእግስትዋን ተማሩ ህወታችሁን አለምልሙ የምስጋናን ህይወት እንድትጀምሩ የቀጠሮ ሰው ይበለን አሜን

እናታችን ከባሌ ነው የመጡት ያወኩዋቸው ጫካ ጸበል ለመጠጣት ወጥቼ ነው ወይዘሮ ደሜ ይባልሉ ከንፈራቸው ላይ በወጣ ቁስል ምክንያት መላ ፊታቸው ይቆስልና ሽታም ያመጣል በሐኪም ብዙ አቅሜን ጨረስኩኝ ጠንቁዋይም ገንዘቤን ጨረሰብኝ የሸንኮራ ዮሐንስን ድንቅ ተአምር ሰማው ተነስቼ መጣው ጠረኔ ከሰው ስለማያቀላቅልና የቆሰለው ፊቴንም ደፍሮ የሚያይ ስለሌለ ጫካ እውላለው ጸበልም ሰው ሳይኖር እወርዳለው አሉኝ በእውነት ዘግናኝ አጋጣሚ ነበር 8አመታት የተሰቃዮበት ያ የቆሰለው ፊት እንደ ሰንኮፍ ውልቅ ብሎኝ በቁስል የነፈረው ከንፈራቸው ደርቆ ጠረን መአዛቸው ተለውጦ በዛ ህመምተኛ በነበረ አንደበታቸው እልልታን ብቻ ሳይሆን ንስሐ ገብተው ስጋ ወደሙም ተቀብለው ብጽአታቸውን በእጃቸው የፈተሉትን ግምጃ ስእሉን ሲጋርዱ አይቻለው እኝህ ምስኪን እናት ሸንኮራ ለጥቂት ሳምንታት ተቀምጠው ነው ፈውስን ያገኙ ዛሬ በየአመቱ ሰኔ 30 ከደጁ አይቀሩም የኛንም ክፉ መአዛ አምላከ ዮሐንስ ያጣፍጥልን አሜን

በሸንኮራው ዮሐንስ ጸበል ከጡት ካንሰር የዳነችው
የአጥቢያችን ብስራተ ገብርኤል ነዋሪ ሳባ ሐብቶም እህቴም እናቴም የሆነችው ሳባ ወደ ሸንኮራ ከመሄድዋ በፊት በጽኑ ስቃይ በካንሰር በሽታ ትሰቃይ ነበር በወቅቱ የነበራት ስቃይ ከቃላት በላይ ነበር አቅሙም ነበራትና ያልደረስችበት ህክምና የለም በተለይ የግል ሐኪምዋ ፕሮፌሰር ታዬ እንዲሁም በጥቁር አንበሳ ብሩክ ክሊኒክ ህክምናዋን ብትከታተልም ካንሰሩ ወደ መላ አካላትዋ ተሰራጭቶ ሞትዋን ስትጠብቅ ወደ ምንጃር ሸንኮራ ጸበል በመምጣት ሸንኮራ በወቅቱ ጥቂት ጎጆዎች ብቻ የነበረባት ትንሽ መንደር ነበረች ከሞላ ቤትዋ ወጥታ የጭራሮ ጎጆ ተከራይታ ጸበልዋን ጀመረች ጽናትዋ ትእግስትዋ ይደንቅ ነበር ቅዱስ ዮሐንስ ደጅ ጥናትዋን ስቃይዋን ተመልክቶ ከአምላኩ አማልዶ በህልም በራእይ ሳይሆን በገሐድ በመገለጥ እንደዳበሳትና 4አመት በዘግናኝ ሁኔታ ያበጠው ሰውነዋ ፈንድቶ ብዙ ደምና መግል ከሰውነትዋ ወጥቶ ፈውስን ተቀዳጅታለች አዲስ አበባ መጥታ ተመርምራ ሙሉ ጤናማ መሆንዋን አረጋግጣለች ይህው 17 አመት ሆናት የቀብር ማስፈጸሚያ በርበሬ የተፈጨላት ጤፍ የተሸመተላት የንፍሮ እህል የተለቀመላት መግነዝ ጨርቅዋን ከቤት ብሞትም ብላ ይዛ የወጣችው ሳባ መጥምቁ ዳብሶ ፈውስን አግኝታ ለእንባ አድርቅ የታሰበው እህል ለዝክር ሆነንዋል ሳባቆማ ትሆዳለች በእለተ ፋሲካ በየአመቱ ቤትዋን በአወደ አመት ዘግታ የአክፋይዋን በመጥምቁ ደጅ ላሉ ካህናት ጸበልተኞች ነዳያን ይዛ ጾም ታስፈታለች መጥምቀ መለኮት ነብየ ልኡል እኛ ከማናውቀው የታሰርንበት ክፉ ነገር ይፍታን አሜን

ነቢየ ልኡል ሐዋርያው ሰማእቱ መጥምቀ መለኮት ድንግላዊው ባህታዊው ካህኑ ከሴት ከተወለደ የሚተካከለው የሌለ ቅዱስ ዮሐንስ በልደቱ የአባቱን የታሰረ አንደበት የፈታ የስሙ ትርጉዋሜ የሁሉ ደስታ የሆነ ዛሬም በደዌ የታሰረውን በጸበሉ የሚፈታ ቃልኪዳኑ ዛሬም ያልተሻረ በመጥምቁ ደጃፍ ያገናኘን በፎቶ የምናየው ወንድም በሸንኮራ ጸበል የተፈወሰ ነው
የቀጠሮ ሰው ይበለን አሜን



ፀበሉ ፈዋሽ ዘብር ቅድስ ገብርኤል


 ምንጭ