አርብ ገበያ ነን፡፡ አርብ ገበያ የታች ጋይንት ወረዳ ዋና ከተማ ናት፤ አዲስ አበባ ከአርብ ገበያ 775 ኪሎ
ሜትር ትርቃለች፡፡ የታች ጋይንት ብዙው የአየር ንብረት ወይና ደጋማ ነው፡፡ እንደ ቤተ ልሔም ያሉ ጥንታዊ መንፈሳዊ
ስፍራዎች የሚገኙባት ወረዳ ከልዳ ጊዮርጊስ እስከ ደቃ ቂርቆስ አስደናቂ የሆኑ መንፈሳዊ መዳረሻዎች ቢኖሩባትም
ብዙም አትታወቅም፡፡ ከራሷ ተሻግሮ የሀገር ልጅ ሊኮራበት የሚገባውን ቀደምት ቅርስ ፍለጋ መጥተናል፡፡
ሰጎዳ ማርያም ከአርብ ገበያ 11 ኪሎ ሜትሮች ያክል ትርቃለች፡፡ የደብሯ የጽሑፍ ሰነዶችና የሀገሬው ቃል
ጥንታዊነቷን ይገልጻል፡፡ የተተከለችው በአብርሐ አጽበሐ ሲሆን የሰነዶቹ ምስክርነት በ330 ዓ.ም. እንደተሰራች
ያትታል፡፡ አቡነ ሙሴ የተባሉ ከግብጽ የመጡ ቅዱስ አባት የተከሏት እንደሆነች ታሪኳ የሚያስረዳው ሰጎዳ ማርያም
አስገራሚ በሚባል አሰራር የታነጸችና ከመሬት ተገናኝታ በልዩ ሁኔታ የተፈጠረች ደብር ናት፡፡
ዘመኗን
ወደ ኋላ ቆጥሮ ከ 1600 ዓመታት በፊት ይህንን ትሰራ የነበረች ሀገር ለሰራቸው የምትሰጠው ቦታ ምን እንደሆነ
ከሚያሳብቁ የሀገራችን መስህቦች አንዷ ናት፡፡ የተነጠፈ ዐለት ድንቅ ቤተ ክርስቲያን የሆነባት ሰጎዳ ማርያም ውስጧ
በማህሌትና በመቅደስ የተከፋፈለ ነው፡፡
ምድር ውስጥ ብትሆንም ቀደምት ጥበበኞች የኪነ ህንጻ ጥበበኛነታቸውን ዘመን አሻግረው ማሳየት የቻሉበት አሰራርን ተላብሷል፡፡ ከአናትና በጎን በኩልና በላይኛው ክፍል ለብርሃን ማስገቢያ የተተው መስኮቶች አሉ፡፡ የእነኚህ መስኮቶች አቀማመጥና አቅጣጫ ትክክል መሆኑን በውስጠኛው ክፍል ያለውን በቂ ብርሃን በመመልከት ይደመሙበታል፡፡
የውስጥ ስዕሎቿ ከዐለቱ ህንጻ እኩል ዘመን ባይኖራቸውም እድሜ ያስቆጠሩ ናቸው፡፡ በርካታ ጥንታዊ ቅርሶች የሚገኙባት ሰጎዳ ማርያም የሚበልጠው መገለጫዋ ምንፍስና በመሆኑ ከነገስታት ስጦታዎች ይልቅ የቀደሙት የበቁ አባቶቿ መገልገያ ቁሳቁሶች በክብር ተይዘው የሚጠበቁባት ታሪካዊና መንፈሳዊ ስፍራ ናት፡፡