ትውልድ ሁሉ ብፅእት የሚላት በተለይ እኛ ኢትዮጵያውያን እንደ ነብሳችን የምንሳሳላት የእናታችንና የእመቤታችን
የቅድስት ድንግል ማርያም ቅዱስ መካነ መቃብርና የተነሳችበት/ያረገችበት ቅዱስ ጣራ ከታች በፎቶ እንደምታዩት ይህን
ይመስላል። የሚገኘውም እየሩሳሌም ውስጥ በቄድሮን ሸለቆ አካባቢ ነው።የእመቤታችን ምልጃና ፀሎት በረከትና ረድኤት
ከኛ ከምንወዳት ልጆቿ ጋር ለዘላለም ይኑር! በረከቱ ለእናንተም ይድረስ።
ድንግል በእውነት ተነስታለች ምስክሩም ይኸው ያረገችበት ቅዱስ ጣራ በቄድሮን ሸለቆ (Kidron Valley) ይህን ይመስላል። ይህንን ቅዱስና ድንቅ ቦታ ለሌሎች ሼር በማድረግ እናንተም የበረከቱ ተካፋዬች ሁኑ! እኛ የድንግል ልጆች ስለምናምነው ቀጥተኛና እውነተኛ የተዋህዶ ሀይማኖት ትክክለኛ መረጃና ከልብ ስለምንወዳት ድንግል ማርያም የማንጠራጠርበት ምክንያት አለን። በዚህ ለማያምኑትና አማላጂነቷን ለሚክዱ እመቤታችን ልቦናቸውን ትመልስልን!!!