የእመቤታችንን ተአምር ልንገራችሁ ማለትም ለእኔ ያደረገችልኝ ስሜ ዲያቆን ሳሙኤል ሀ'/ማርያም ይባላል የተወለድኩት
በምስራቁ የሀገራችን ክፍል ሲሆን በዛ አካባቢ ኢ አማንያን ይበዛሉ ተወልጄ አንድ ዓመት ሲሞላኝ በፀና መታመሜን እና
እናቴ ለድንግል ማርያም ተስላ እንደተረፍኩኝ ትነግረኛለች ከዛም
5 ዓመት እንደሞላኝ እናቴ ስዕለቷ ለቤተክርስቲያን ብፅዓት አድርጋ መስጠት ስለነበረ ወደ ታላቁ ገዳም አሰቦት
ደብረ ወገግ ገዳም ወስዳ ለአበ ምኔቱ አስረከበችኝ ልብ በሉ ይህ ገዳም ወንዶች ብቻ የሚኖሩበት ገዳም ነው እኔም
ገና ብላቴና ሳለሁ ከአባቶች ጋር ተቀላቀልኩኝ በመቀጠልም ካለ ወጥ የሚበላውን የቃል ኪዳን ዳቤ እየበላሁ የቆሎ
ትምህርቴን ጀመርኩኝ ህፃን ስለነበርኩኝ አዕምሮዬ ያስተማሩኝል ሁሉ ይቀበል ነበር በእንደዚህ ያለ ህይወት እየኖርኩኝ
የግብረ ዲቁና ትምህርቴን አጠናቀቁኝ ከዛም ማዕረገ ዲቁና ተቀበልኩኝ አሁን ላይ ልብ በሉ ገዳሙ የዓንድነት ገዳም
ስለሆነ የቀንድ ከብቶች እና የጋማ ከብቶች አሉት ስለዚህም ባህታውያን መናኞች እንዚህን ከብቶች በየተራ ወደ ጫካ
በማሰማራት ይጠብቃሉ በተጨማሪም ለተላላኪነት ሁለት ሁለት ህፃን ይመደብላቸዋል በእንደዚህ ዓይነት ሁኔታ እኔም በ1991 ዓ.ም ምደባው ደረሰኝ ግንቦት 21 የመቤታችን ዕለት ማለትም 20 ለ21 አጥቢያ ህልም አየሁ አስደንጋጭ ህልም
በወቅቱ ያሳድጉኝ የነበሩ አባት ባህታዊ ኀይለ ሚካኤል ስነግራቸው ገባድ ነገር ይገጥማሀል ግን ምን አትሆንም አሉኝ
እሺ አባቴ ፀልዩልኝ ብዬ አብረን ከተመደብነው ልጅ ጋር ወደ ጫካ ሄድን የሄድንበት ጫካ በአካባቢው ስም ሶራ
ይባላል ብዙ ኢ አማንያን ዘላኖች ያሉበት ቦታ ነው ከዛም ልክ ከኑ 6 ሰዓት ግንቦት 21 1991 ዓ.ም አስደንጋጭ
ነገር ተከሰተ ሽፍቶች ማለትም በአጋባቢው አጠራር ኢሳዎች ያዙን እጃችንን የፍጥኝ አሰሩን ልብ በሉ እኛ ገና
ያልጠነከርን ጨቅላዎች ነበርን ኡኡኡ ብለን ጮህን ከተራራው ድምፅ በስተቀር የደረሰልን የለም ሊያርዱን ቢላዋ
ከሰገባቸው መዘዙ ጭንቀት ተፈጠረ አስተውሉ የሞት አፋፍ ላይ ነው ይህ በእንዲህ እዳለ በደመነፍስ እየታገልኩኝ ወደ
ሰማይ ቀና አልኩኝ አንድ ነገር በአፌ ወጣ በታፈነ ድምፅ የአምላኬ እናት የጭንቅ አማላጇ ማርያም ሆይ እባክሽ
ከልጅሽ ጋር ድረሽልኝ ከዚህ ጭንቅ ካወጣሽኝ በእራሴ እጅ የተሰራ ሰሌን (ማለትም የዘንባባ ሥሪት ምንጣፍ)
ለቤተክርስቲያንሽ አስገባለሁ ብዬ ድምፄን ከፍ አድርጌ ጮኩኝ እመቤቴ በፍጥነት ደረሰችልኝ ሊያርደኝ የሚታገለኝ ሰው
ከመቅፅበት ለቀቀኝ እኔም እሮጨ ነጭሎ የሚባል ዛፍ ስር ተደበኩኝ እመቤቴ በውስጤ ገባች አንዱ ጓደኛዬም እንዲሁ
ተሳለ ደረሰችለት እነኛ አራጆች የእኛን ፊት ማየት አቅቷቸው ከብቶቹን በመያዝ ወደ ገላግሌ የሚባል አካባቢ ሮጡ
እኔም በእመቤቴ ምልጃ ከሞት ተርፌ ወደ ገዳሙ እሮጥኩኝ የአደጋ ደወልም ደወልኩኝ ሁሉም መናንያን ምንድነው ብለው
ተሰበሰቡ የሆነውን ነገርኳቸው ሁሉም በህብረት እንባቸውን አውጥተው አለቀሱ ከሞት የአተረፈኝን የድንግል ማርያምን
ልጅ አመሰገኑ ከዛ ከብቶችን የዘረፉት ሰዎች ሲካፈሉ እርስ በእርስ ተገዳደሉ የአካባቢው ሽፍቶችም ወተቱን ሲጠጡ
በተቅማጥ መሞት ጀመሩ የሚያደርጉት ሲጠፋቸው ገዳሙ ይቅርታ ያድርግልን ብለው ከብቶቹን መለሱ እናም ዛሬ ላይ ዓለም
የእመቤታችንን ምልጃ ይሰማ ዘንድ ውስጤ አስገደደኝ ይህ ታሪክ ህያው እግዚአብሔር ያውቃል እሙን ነው ሼር በማድረግ
ለዓለም እናድርስ የገዳሙ ታሪክ በዘሁ አምድ ይቀጥላል ለእኔ የደረሰች ድንግል ማርያም የአምላክ እናት ለእናንተም
ትድረስላችሁ
አሜን
አሜን
አሜን
ያነበበው ሁሉ ሼር እንዲያደርግ በድንግል ማርያም ስም እጠይቃለሁ
ለበለጠ መረጃ 0911072282 ዲያቆን ሳሙኤል
አሜን
አሜን
አሜን
ያነበበው ሁሉ ሼር እንዲያደርግ በድንግል ማርያም ስም እጠይቃለሁ
ለበለጠ መረጃ 0911072282 ዲያቆን ሳሙኤል