በልበሌቲ ጽጌ ገነት ቅዱስ ጊዮርጊስ ቤተ ክርስቲያን ከአዲስ አበባ 418 ኪሎ ሜትር ርቀት ላይ ይገኛል።
ቦታውም ለመድረስ ከአዲስ አበባ በናዝሬት፣ አሰበ ከዛም በበዴይሳ አድርገው ወደ ገለምሶ ይጓዛሉ በመጨረሻም
ቤተክርስቲያኑ የሚገኝበት በልበሌቲ መሻገር ይኖርቦታል። መንገዱ ለማንኛውም መኪና ምቹና ቤተ ክርስቲያኑም መንገድ
ዳር በመሆኑ ምንም እንግልትና የእግር ጉዞ የለውም።
ይህ ቤተ ክርስቲያን የሚገኘው በምዕራብ ሐረርጌ ሐብሮ ወረዳ በልዩ ስሙ በልበሌቲ በመባል በሚታወቀው መንደር ሲሆን ለምዕራብ ሐረርጌ የመጀመሪያው ቤተክርስቲያን ነው። የተተከለውም በእምዬ ምንሊክ በፊታውራሪ ዘመንፈስ በ1870 ከአርሲ እያስገበሩ ሲመጡ በምዕራብ ሐረርጌ ሲያልፉ እንደተከሉት ይነገራል። ቤተ ክርስቲያኑ ሲዘዋወር አሁን ያለበት ቦታ ሰባተኛው ሲሆን እምዬ ምንሊክ ለቤተ ክርስቲያኑ የሰጡት ርስት 18 ጋሻ መሬት ቡሩሪ በሚባል ቦታ ህንጻውም ባለ ደርብ(under ground) የሆነ ነበር። በጣልያን ወረራ ጊዜ ቤተ ክርስቲያኑ በመቃጠሉ ከተሰጠው ርስት በመነሳት በሽሽት ቀርጫ የሚባል ጫቃ ውስጥ ለ 5 ዓመት ስብሐተ እግዚአብሔር ሲደርስ ቆይቷል። በዚህ ወቅት ያ 18 ጋሻ መሬት የለውም እዛ ቦታ ላይ ሌሎች ሁለት ቤተ ክርስቲያን ታንጸው እሱ የሚገኘው ሌላ አዲስ በተመራው ቦታ ላይ ነው። በዚህ ቤተ ክርስቲያን የሚነግሱ ታቦታት ሶስት ሲሆኑ እነሱም ቅዱስ ጊዮርጊስ በሚያዚያ 23ና ጥር 18፣ ኪዳነ ምህረት በየካቲት 16፣ ሩፋኤል በጷግሜ 3 ይነግሳሉ።
ደብሩን ምን ልዩ ያደርገዋል
ስለት ሰሚነቱ
በአገር ውስጥም ከአገር ውጪም ባሉ የአካባቢው ሰዎች የበልበሌቲው ጊዮርጊስ አንተው ስለቴን ፈጽምልኝ ብለው የተሳሉ ሁሉ ላመኑት ክርስቲያኖች ብቻ ሳይሆን ከክርስናው ውጪ ላሉትም ሰዎች እንኳ ሳይቀር ስለታቸው ደርሶላቸው በድብቅ (ሰው በመላክ) በግልጽም (ራሳቸው በመምጣት) ስለታቸውን ይልካሉ። በሐኪም እንደማይወልዱ የተነገራቸው፣ ትዳር ያጡ፣ በህመም የሚሰቃዩ፣ ውስብስብ ችግር የገጠማቸው፣ ብዙ ብር ጠፍቶባቸው የነበሩ ሌሎች ሌሎችም የህይወታቸው እንቆቅልሽ ተፈቶላቸው አምላከ