አቡነ ኂሩተ አምላክ ሁለት ድንጋዮችን በተረአምራት እንደ ታንኳ አድርገው በመጠቀም ጣና ባሕርን በበትረ መስቀላቸው እየቀዘፉ ዳጋ ወደተባለው ደሴት ገብተዋል፡፡ ጻድቁ የጣናን ባሕር እንደ ታንኳ ተጠቅመው የተሻገሩባቸው እነዚያ ሁለት ትላልቅ ድንጋዮችም ዛሬ በገዳሙ ውስጥ የጻድቃን ማረፊያ (ምዕራፈ ጻድቃን) ተብሎ በሚጠራው ቦታ ላይ በክብር ተቀምጠው ይገኛሉ፡፡ እሳቸው ያን ጊዜ ያረፉበት ቦታ ዛሬም ድረስ ‹‹ዓቃቤ ሰዓት›› እየተባለ በመዓርግ ስማቸው ይጠራል፡፡ አቡነ ኂሩተ አምላክ በቦታው ላይ በጽኑ ተጋድሎ ኖረው ሥርዓቱን አጽንተው ተጋድሎአቸውን ጨርሰው በዛሬዋ ዕለት ነሐሴ 8 ቀን በክብር ዐርፈዋል፡፡ በረከታቸው ይደርብን፡፡