Wednesday, July 30, 2014

ድንቅ ተዓምር በሸንኮራ ቅዱስ ዩሐንስ ጸበል


የተወደዳችሁ የእግዚያብሔር ቤተሰቦች ዛሬ የምንመሰክራላችሁ ተዓምር ለወንድም አንተነሕ ኃይሌ የተደረገለት ሲሆን: ይህ ወንድም በ2005 ዓ.ም ታሞ ወደ ሕክምና ጣቢያ በመሔድ ምርመራ ያደርጋል:: ነገር ግን ውጤቱ አስደንጋጭ ብሎም ያልተጠበቀ ነበር:: የሕክምና ዶክተሩ የአንጀት ካንሰር እንዳለበት ይነግሩታል:: ይህ ብቻ አደለም ሌላ በጣም ተስፋ አስቆራጭ ነገርም ነገሩት እርሱም በዚች አለም በህይወት ሊቆይ የሚችለው ቢበዛ ለ 3ወር ብቻ እንደሆነም ጭምር ያስረዱታል:: በዚህም አስደንጋጭ ዜና ተስፋ መቁረጥ ቢደርስበትም የተለያዩ ሆስፒታሎች ጋር በመሔድ የሕክምና እርዳታን ይሞክር ጀመር:: ለምሳሌ ኮርያ ሆስፒታል: ተክለሐይማኖት ሆስፒታል: ብሩክ ክሊኒክ ላንድ ማርክ እና ጥቁር አንበሳ ሆስፒታል ከሔደባቸው የተወሱኑ የሕክምና ጣቢያዎች ሲሆኑ የተሻላ ነገርን ግን ማግኘት አልቻለም:: በስተመጨረሻ ላይ ግን ወደ እግዚያብሄር መፍትሔዎች አዳኝነት በመመለስ በሸንኮራ ዩሐንስ ጸበል በመጠጣት የእግዚያብሔር አዳኝነትን መጠባባቅ ያዘ:: በዚህ አመት ባደረገው ምርመራ በአሁኑ ግዜ በጥሩ የጤና ሁኔታ ላይ ሲሆን "የካንሰር ስፔሻሊስት" እና የቅዱስ ዩሐንስ ሸንኮራ ጸበል ረድተውኛል" ሲል ቃል በቃል ተናግሯል:: ከዚህ በታች በምታዩት ፎቶ ላይ ዶክመንቶቹን እያሳየ እንዳለ እናያለን::

"እግዚያብሄር በጻድቁ እንደተገለጠ እወቁ..":: መዝ 4:3