Monday, June 13, 2016

ተነግሮ የማያልቀው የሸንኮራ ዮሐንስ ድንቅ ተአምር

ስለ ሸንኮራ ቅዱስ ዮሐንስ ጸበል ምን ያህል ያዉቃሉ? የሸንኮራ ዮሐንስ ፀበል በአማራ ክልል በሰሜን ሸዋ ዞን በምንጃር ሸንኮራ ወረዳ ንዑስ ከተማ በሆነችዉ በባልጪ ከተማ አጠገብ በርካታ ተገልጋዮች ከተለያዩ ቦታዎች በመምጣት ፈውስ የሚያገኙበት ፀበል ነው፡፡ ፀበሉ በፈዋሽነቱ በይፋ መታወቅ የጀመረዉ:- አባ ካሳ የሚባሉ መናኝ ባህታዊ በሸንኮራ ቅ/ዮሐንስ ቤ/ክ መቃብር ቤት ዉስጥ ዘግተዉ ይኖሩ ነበር፡፡ ከእለታት አንድ ቀን በህልማቸዉ ከቤተ ክርስቲያኑ በስተምስራቅ ከወንዙ ዉስጥ ጸበል ፈልቋልና ወርደህ አይተህ ለህዝቡ ንገር እዉራን የሚያበራ፣ ለምፅ የሚያነፃ፣ ጎባጣ የሚያቀና ጸበል ፈልቋል በልና ንገር ብሎ በህልማቸዉ ነገራቸዉ፡፡

ሲነጋ ጠዋት በተነገራቸዉ መሰረት ወደ ወንዝ ወርደዉ ጸበሉን ሲፈልጉ አላገኝ አሉት፡፡ አባ ካሳ የዕድሜ ባለፀጋ ሲሆኑ ሲፈልጉ ዉለዉ በድካም ወደ ቤታቸዉ ተመለሱ፡፡ እንደገና ሌሊት በህልማቸዉ "ጠዋት ተነሣና ወደ ጸበሉ ዉረድ ጸበሉ ከጫካ ዉስጥ ፈልቆ ታገኘዋለህ ከፊ ከፊትህ የምትመራህ ርግብ ታሳይሃለች"አላቸዉ፡፡ በታዘዙት መሰረት ከጠዋት ተነስተዉ ወደ ወንዝ ሲሄዱ ርግብ ከፊት ከፊት እየመራቻቸዉ ከወንዙ ዉስጥ ሲደርሱ ጸበሉ ከፈለቀበት ገደል ላይ ክንፏን ዘርግታ አረፈች፡፡ከዚያም አባ ካሣም እግዚአብሔርን አመስግነዉ የፈለቀዉን ጸበል ጠጥተዉ እግራቸዉን ክፉኛ በሽታ ያማቸዉ ስለነበር ጸበሉን ሲያስነኩት ከያዛቸዉ በሽታ ወዲያዉኑ ተፈዉሰዋል፡፡ ከዚህ በኋላ አባ ካሳ የፈለቀዉን ጸበል ለህዝቡ ነግረዉ ሚያዝያ 30 ቀን ታቦተ ህጉ ወደ ጸበሉ ወርዶ በደማቅ ሁኔታ ተክብሯል፡፡ ይህንን ራዕይ ያዩት ሚያዝያ 15ቀን 1654 ዓ.ም ገደማ ሲሆን 354 ዓመት ያስቆተረ ጸበል ነዉ ተብለዉ ይገመታል፡፡ የቅዱስ ዮሐንስ በረከት ከሁላቸን ጋር ይሁን አሜን ።


ቤቱ ከአፋፍ ላይ ጸበሉ ከጅረት የድውያን ዳባሽ መጥምቀ መለኮት የስሙ ትርጉዋሜ ፍስሐ ወሐሴት በልደቱ የፈታ የአባቱን አንደበት እማሆይ ሂሩተ ገብርኤል ይባላሉ ተወልደው ያደጉት እዚሁ አዲስ አበባ ነው ትምህርታቸውን ጨርሰው ዮንቨርስቲም የሁለተኛ አመት ተማሪ ሳሉ በደረሳቸው መለኮታዊ ጥሪ በምናኔ ወደ ገዳም በመግባት ለ5 አመታት አገልግለው ደጅ ጠንተው በገዳሙ ማህበር ፈቃድ ምንኩስናቸውን ተቀብለው አገልግሎታቸውን በሰፊው በመስጠት ላይ ሳሉ ድንገት ባላሰቡት ሁኔታ በጡት ካንሰር በሽታ ይለከፋሉ አዲስ አበባ ለህክምና በመምጣት በጥቁር አንበሳ ሆስፒታልና በሌሎችም የግል ህክምና መስጫ ምርመራ ቢያደርጉም የታመመው አካል በአስቸኩዋይ ካልተቆረጠ ካንሰሩ ይሰራጫል ይባላሉ ህመሙ ከባድና ጽኑ ነበር በተለይ የጨረር ህክምና ተብለው የባሰ ተሰቃዮ እማሆይ ምርር ብለው ያለቅሳሉ ገና በማለዳ ነፍሴን ለገነት ስጋዬን ለአራዊት ብዬ መንኜ እንዴት ገላዬ ተገልጦ ክብሬ ይቃለላል ይህስ እንዲሆን አምላኬ ለምን ፈቀድክ ብለው ያዝናሉ የታመመ አካላቸውን ለማስቆረጥ ቀጠሮ ይይዛሉ እማሆይ እንደተናገሩት ፒያሳ አካባቢ ነዳይ መስለው ተሰውረው የሚኖሩ ባህታዊ ከጊዮርጊስ ቤተክርስቲያን ስወጣ "ሸንኮራ ዮሐንስ ሂጂ አንቺ ፈላሲ "ይሉኛል የምን እብድ ነው ብዬ አለፍኩት ክንክን አደረገኝና ተመልሼ ባይ ጠፉብኝ ልቤ ተነሳሳ ስቃዮ ደግሞ ረፍት ነሳኝ ደምና መግል ከታመመው አካሌ ይወርዳል እንደምንም ሸንኮራ መሪ ሰው ይዜ ገባው እምነቱን ጸበሉን ስቀባው ከረምኩኝ ይፈስ የነበረው የደም ጎርፍ ጠፋ ህመሜም ቀነሰ እንቅልፍም በደንብ እተኛ ጀመር ሰላሜ ተመለሰ የቀጠሮውም ቀን አለፈ ፍጹም ጤነኛ ሆንኩኝ የአይነ ከርሙ ባህታዊ ነብየ ልኡል ሰማእቱ መጥምቁ የጌታዬ የአምላኬ ወዳጅ በአድያመ ዮርዳኖስ በሸንኮራ ምድር በስሙ በፈለቀው ጸበል ጡቴን ከመቆረጥ አዳነኝ ዳግም ተመርምሬ ፍጹም ጤነኛ ነሽ ተብያለው ወደምወደው ገዳሜ በደስታ ተመልሻለው ብለዋል እናታችንይህን ያደረገ የዮሐንስ አምላክ ክብር ይግባው ይግባው ከኛም የማይበጀንን ነገር ቆርጦ ይጣልልን አሜን