መንግስተ ሰማያት እውን ናት - እማሆይ ወለተ ጊዮርጊስ በኦፕራሲዮን ግዜ መንግስተ ሰማያት እና ሲኦልን እንዳዩ ይመሰክራሉ::
Heaven is for real - Emahoy Welete Giorgis- Near death experience
Heaven is for real - Emahoy Welete Giorgis- Near death experience
ቤተክርስቲያኑ ከመመስረቱ በፊት በቦታው ላይ ሲከናወኑ የነበሩ ልዩ ልዩ ታምራት፡-
ባለፈው ጥቅምት ወር የቅዱስ ገብርኤል ዋዜማ ዕለት ከምሽቱ አምስት ሰዓት ላይ ባለቤቴ ከሥራ ከሚመጣበት ከተለመደው ሰዓት አንድ ሰዓት ቀደም ብሎ በራችንን ለመክፈት የሚታገል ሰው እንዳለ ስለሰማን እኔና ልጆቼ የምናደርገው ቢቸግረን ለባለቤቴ ስልክ ደወልንለት። ስልኩንም እንደደወልን እቤታችን በር ላይ የባቤቴ ስልክ ሲያቃጭል ሰማን። በዚህም በሩን ለመክፈት የሚታገለው ባለቤቴ እንደሆነ አወቅን። ወዲያውም እኔና ልጆቼ ተሯሩጠን ሄደን በሩን ስንከፍት ባለቤቴ እንደሰከረ ሰው እየተንገዳገደ ራሱን ችሎ መቆም አቅቶት አየነው። ግራ ተጋብተን ምን እንደሆነ እንኳ ሳንጠይቀው ዝም ብለን ደግፈነው ወደ ቤት አስገባነው። ኃይለኛ ራስ ምታት እንዳለበት ሲነግረን ይሻለዋል ብለን የራስ ምታት መድኃኒት ሰጥተን አስተኛነው። በማግስቱም የቅዱስ ገብርኤል ዕለት በዋሽንግተን ኃይለኛ አውሎ ነፋስ ይነፍሳል ተብሎ ስጋት ስለነበር መ/ቤት ሁሉ
ዝግ እንደሚሆን በመገናኛ ብዙኃን ተነግሮ ነበር። እኔም አጋጣሚውን በመጠቀም ቤተሰቡ በሙሉ ቁርስ አብረን እንድንበላ ልጆቼን ቀሰቀስሁና አባታቸውን አስነስተው ወደ ገበታው እንዲቀርቡ ነገርኳቸው። ባለቤቴ ከመኝታው ተነስቶ ከተጣጠበ በኋላ ወደ ገበታው ለመቅረብ ሲመጣ መራመድ አልቻለም። ዝልፍልፍ አለ። ሁላችንም ተደናገጥን። ልጆቼም ስልክ ደውለው አምቡላንስ ጠሩ። ባለቤቴም በአስቸኳይ ለሕክምና ወደ ዋሺንግተን ሆስፒታል ማዕከል ተወሰደ። እዚያም እንደደረሰ ሐኪሞቹ በሚያውቁት መንገድ ሁሉ መርምረው ምንም ሕመም ሊያገኙ አልቻሉም። ሊነጋጋ ሲል ጧት ላይ ለሕመሙ ማስታገሻ ብለው መርፌ ሲወጉት አንቀጠቀጠውና ደካከመው። መተንፈስ አቃተው፣ አንደበቱም ተያዘ።እንደሞተ ሁሉ ሰውነቱ ቀዘቀዘ ። በዚህን ጊዜ በመሳሪያ ኃይል እንዲተነፍስና ደሙም እንዲጣራ አደረጉ። ሆዱን ከፍተው ለማየት ቢሞክሩ ሰውነቱ ከፍሎሪዳ እንደመጣ ገና ከማቀዝቀዣ እንደወጣ ሥጋ ድርቅ ብሎ ስለት የማይደፍረው ሆነ። ሐኪሞቹ የሚያደርጉት መላው ጠፋቸው። አንድ ጊዜ ሳንባው ተቃጥሏል፣ ትንሽ ቆይተው ጉበቱ ተበላሽቷል፣ ከዚያም ኩላሊቱ አይሠራም ሲሉ ጥቂት ቀናት አለፉ።