Tuesday, December 27, 2016
ዋካ ቅድስ ጊዮርጊስ ገዳም
በ15ክ/ዘመን የተመሰረተው አብነ ጵጥሮስ የቀደሱበት የባረኩት በደመና የመጣ ታቦት ቀድሞ ከ15ክ/ዘመን
በፊት/ መንዝ ዋካየአብይ ገብረመንፈስቅድስ ገዳም/ ሲሆን 15ክ/ዘመን ላይ ዋካ ቅድስ ጊዮርጊስ ገዳም ተብላል፡፡በጣም ስለት ሰሚ ነው፡ጣልያን በወረረን ግዜ ቦንብ ጥለው ቤተክርስቲያኑን ሊያቃጥሉ ቢወረወሩ
ቤተክርስቲያኑ አልቃጠል ሲላቸው ሰውን ፡ካህኑን እየገደሉ ቤተክርስቲያኑ አልቃጠል ሲላቸው የታቦቱን መጎናጸፍፊያ
ለብሰው ሲሂድ ከዋካ ከቦታ አልፈው ሂደው ጉርሙኝ ቆላውየ4ሰዓት መንገድ ልብሱን ለብሶ ለብሰው ጣሊያኖቹ
ሲሂድየአካባቢው ሰው /አቶ ተገኝ/የሚባሉ ሰው ይህ በምታዩት ጋሻ በመከት ጣሊያኖቹን በመግደልና ገደል በመክተት
የጊዮርጊስ መጎናጸፊያ አስመልሰው መጎናጸፊያው(ልብሱ ):በዋካ ጊዮርጊስ ይገኝል፡፡
አቶ ተገኝ ጀግና ተብለው
የደጃዝማች መሀረግ ሲሰጣቸው ቁረብ ሰጋወ ደሙ ተቀበሉ ሲላቸው በመንዝ አካበቢ ጀግና ሲሞት ቀረርቶ
;ይሸለላል;ይፎከራል ይህ ሳይደረግ ጀግና አይቀበርም፡፡እና አቶ ተገኝ ቁረብ ሲባሉ እኔን ጊዮርጊሰ ጀግና አርጎ
ጠላቱን ገድይ ልብሱን አስመልሻለሁ እና ቁርባኑን ሰጋ ደሙን ጊዮርጊሰ ያቀዋል፡ሳይሸለልልኝ ሳይፋከርልኝ ብለው
በ110አመታቸው ሞቱ፡፡ የሚገርሙአባት ናቸው በጀግና አሟሟትየተፋከረ፡እየተሸለለ በጀግና አቀባበር በ110አመታቸው
አርፈዋል፡፡ስለት ሰሚው ዋካ ጊዮርጊስ የዱሮው ቤተክርስቲያንሳይፈርስ ሌላ ቤተክርስቲያን በመሰራት ላይ ሲሆን መርዳት
ለእግዚአብሔር ማበደር ሲሆን ስለት ሰሚውን ዋካን በምንችለው አቅም እንርዳ የቤተክርስቲያኗ መሰረቱ በመሠራት
በመውጣት ላይ ነው፡፡በረከቱ በያለንበት ከጊዮርጊሰ ይደርብን፡፡አሜን
ቦታው-+መንዝ ዘብር ገብርኤል ከአ/አ 260ኪሜ ሲሆን ከዘብር የ4ሰዓት መንገድ ሲሆን 4wdመኪና ቦታው ድረስ ይገባል ሜዳ ቀላል መንገድ ነው፡፡
ቦታው-+መንዝ ዘብር ገብርኤል ከአ/አ 260ኪሜ ሲሆን ከዘብር የ4ሰዓት መንገድ ሲሆን 4wdመኪና ቦታው ድረስ ይገባል ሜዳ ቀላል መንገድ ነው፡፡
Sunday, November 27, 2016
በራእይ አዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ እንደሚገኝ የታየው ታቦት ተገኘ
“ቅ/ሚካኤል ሚዛንና ሰይፍ ይዞ በዩኒቨርሲቲው ፩ኛ በር በኩል እየወሰደ ያሳየኛል፡፡”
/ታቦቱ መኖሩን የጠቆሙት ባለራእዩ ባሕታዊ በለጠ ዘነበ/
/ታቦቱ መኖሩን የጠቆሙት ባለራእዩ ባሕታዊ በለጠ ዘነበ/
* * *
(አዲስ አድማስ፤ ዓለማየሁ አንበሴ፤ ቅጽ ፲፮ ቁጥር ፭፻፹፤ ቅዳሜ፣ ኅዳር ፲፯ ቀን ፳፻፱ ዓ.ም.)
በአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ 6 ኪሎ ካምፓስ ሙዝየም ውስጥ፣ ከግማሽ ክፍለ ዘመን በላይ ያስቆጠረ ታቦት የተገኘ ሲኾን፤ ታቦቱ ለኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን እንደተመለሰ ታውቋል፡፡
በዩኒቨርሲቲው ግቢ ታቦት ስለመኖሩ፣ “ራእይ ታይቶኛል” የሚሉ ባሕታዊ ለጠቅላይ ቤተ ክህነት ባስታወቁት መሠረት፣ ጥናት ተደርጎ መኖሩ በመረጋገጡ፤ ከዩኒቨርሲቲው ጋር ብዙ ድርድር ከተደረገ በኋላ፣ ኅዳር 10 ቀን 2009 ዓ.ም.፣ ታቦቱ ለጠቅላይ ቤተ ክህነት መመለሱን በጉዳዩ ተሳታፊ የነበሩት መጋቤ ምሥጢር ቡሩክ አሣመረ ለአዲስ አድማስ ተናግረዋል፡፡
“ታቦቱ በዐፄ ኃይለ ሥላሴ ጥያቄ እንደተቀረፀና የቅዱስ ሚካኤል ታቦት መኾኑን የሚገልጽ ማስታወሻ ተገኝቷል፡፡ ታቦቱ ከ68 ዓመት በላይ ዕድሜ እንዳለውም ታውቋል፤” ብለዋል – መጋቤ ምሥጢር ቡሩክ፡፡
ታቦቱ በዩኒቨርሲቲው ስለመኖሩ፣ ባሕታዊ በለጠ ዘነበ የተባሉ በራእይ ታይቶኛል በሚል በተደጋጋሚ ሲናገሩ እንደነበር የጠቆሙት መጋቤ ምሥጢር ቡሩክ፤ “ቅዱስ ሚካኤል ሚዛንና ሰይፍ ይዞ በዩኒቨርሲቲው ካምፓስ አንደኛ በር በኩል እየወሰደ ያሳየኛል፤” እያሉ ይናገሩ እንደነበርና፣ ይህንንም በ2003 ዓ.ም. አካባቢ ለፓትርያርክ አቡነ ጳውሎስ መግለጻቸውን፤ ነገር ግን ትኩረት የሚሰጣቸው ሳያገኙ መቅረታቸውን ያስታውሳሉ፡፡
ባሕታዊው፣ በ2007 ዓ.ም. ይህንኑ ራእይ ለብፁዕ ወቅዱስ
ፓትርያርክ አቡነ ማትያስ ማሳወቃቸውንና የሚመለከታቸው የጠቅላይ ቤተ ክህነቱ የሥራ ሓላፊዎች ጉዳዩ እንዲጠና
ማዘዛቸውን መጋቤ ምሥጢር ቡሩክ አውስተው፣ በጥናቱም ጽላቱ በዩኒቨርሲቲው ውስጥ መኖሩ መረጋገጡን ገልጸዋል፡፡ ይህን
ተከትሎም ታቦቱ ለቤተ ክርስቲያንዋ እንዲመለስ ከዩኒቨርስቲው ጋር በርካታ የደብዳቤ ልውወጦች ተደርገዋል፡፡
መጀመሪያ ላይ ዩኒቨርሲቲው የጥናትና ምርምር ተቋም እንደመኾኑ፣
ቅርሶችን ተከባክቦ የመያዝና ለትውልድ የማስተላለፍ ሓላፊነት እንዳለበት በመግለጽ፣ ታቦቱን ለቤተ ክርስቲያንዋ
ለመመለስ በእጅጉ ተቸግሮ ነበር፤ ይላሉ መጋቤ ምሥጢር ቡሩክ፡፡ ኾኖም ጽላት ለቱሪስቶች(ለጉብኝት) ክፍት ኾኖ መታየት የሌለበት የሥርዓተ አምልኮ መፈጸሚያና መግለጫ በመኾኑ፣ በዩኒቨርሲቲው ሙዝየም ውስጥ ቢቀመጥ ትርጉም እንደሌለው ስምምነት ላይ በመደረሱ፣ የመንበረ ልዑል ቅዱስ ማርቆስ ቤተ ክርስቲያን በአደራ ተረክቦ እንዲያስቀምጥ መደረጉን ለማወቅ ተችሏል፡፡
ታቦቱ፣ አልተረስቶን በሚል ስያሜ፣ በመዝገብ ቁጥር
1761 ተመዝግቦ የተገኘ ሲኾን፣ ሚስተር ስቴፈን ራይት በተባለ ሰው፣ እ.አ.አ ሰኔ 12 ቀን 1961 ወደ ሙዝየም
መግባቱን መጋቤ ምሥጢር ይናገራሉ፡፡ ነገሥታት ታቦት አስቀርፀው በቤተ መንግሥታቸው በሚገኙ አብያተ ጸሎታት(ሥዕል ቤቶች) የማስቀመጥ ልምድ እንደነበራቸው የጠቀሱት መጋቤ ምሥጢር ቡሩክ፤ ምናልባትም ዐፄ ኃይለ ሥላሴ ይህን የቅዱስ ሚካኤል ታቦት ሳያስቀርፁት እንዳልቀረ ግምት መኖሩን አመልክተዋል፡፡ “ታቦቱ በዩኒቨርሲቲው ሙዝየም 3ኛ ምድር ቤት ውስጥ ለብቻው በተሠራ ቤት ውስጥ ተደብቆ ነው የተገኘው፤ የሙዝየሙ ሠራተኞች እንኳን ታቦት መኖሩን አያውቁም ነበር፤” ብለዋል መጋቤ ምሥጢሩ፡፡
ከሰኔ 12 ቀን ጀምሮ፣ ከመልአኩ ቅዱስ ሚካኤል ጋር ይገናኙ
እንደነበር የገለጹት ባለራእዩ ባሕታዊ በለጠ ዘነበ፣ በተደጋጋሚ ወደ ፓትርያርኩ ጽ/ቤት እየሔዱ ቢናገሩም ትኩረት
አለማግኘታቸውን ጠቅሰው፣ በኋላ የቤተ ክርስቲያኒቱ የልማትና ክርስቲያናዊ ተራድኦ ኮሚሽንና የቤተ መዛግብትና ቅርስ ክፍል ሓላፊዎች ባደረጉት ከፍተኛ ጥረት ታቦቱን ከዩኒቨርስቲው ለመረከብ መቻሉን ለአዲስ አድማስ አስረድተዋል፡፡
በአዲስ አበባ ዩኒቨርስቲ የታሪክ ምሁር የኾኑትን ፕ/ር አሕመድ ዘካርያን ስለ ጉዳዩ ጠይቀናቸው ምላሽ ለመስጠት ፈቃደኛ ሳይኾኑ ቀርተዋል – “አኹን ብዙም የምገልጸው ነገር የለም፤” በማለት፡፡
በዩኒቨርሲቲው ሙዝየም የተገኘውን የቅዱስ ሚካኤል ታቦት አስመልክቶ፣ ለብዙኃን መገናኛ እና ለሕዝብ ይፋ ለማድረግ፣ ለጥር 8 ቀን 2009 ዓ.ም. መርሐ ግብር መያዙን መጋቤ ምሥጢር ቡሩክ አስታውቀዋል፡፡
አኹን በ6 ኪሎ የሚገኘው የአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ ዋናው ግቢ፣ የግርማዊ ቀዳማዊ ንጉሠ ነገሥት ዐፄ ኃይለ ሥላሴ ገነተ ልዑል ቤተ መንግሥት የነበረ ሲኾን፣ ታቦቱን በአደራ የተረከበው የመንበረ ልዑል ቅዱስ ማርቆስ ቤተ ክርስቲያንም፣ የንጉሠ ነገሥቱና ቤተሰቦቻቸው ሥዕል ቤት(ጸሎት ቤት)
ኾኖ ያገለገለ ነው፡፡ የ1953 ዓ.ም. መፈንቅለ መንግሥት ተከትሎ የንጉሡ ቤተ መንግሥት ወደ ኢዮቤልዩ በመዛወሩ፣
የገነተ ልዑል ቤተ መንግሥትን ለትምህርት ተቋምነት በስጦታ አበርክተዋል፤ ጸሎት ቤት የነበረው የመንበረ ልዑል
ቅዱስ ማርቆስ ቤተ ክርስቲያንም ለሕዝብ አገልግሎት የሚሰጥ ኾኗል፡፡
የቅዱስ ገብርኤል ጽላት በአንድ አባት ራእይ ተገኘ
Tuesday, November 15, 2016
የእመቤታችን የቤት እቃዎች በግብጽ
እመቤታችን በግብፅ ውስጥ በነበረችበት ወቅት ልጅዋን ኢየሱስ ክርስቶስን ሦስት አመት ከስድስት ወር ከ10 ቀን ሲሆን እመቤታችን በወቅቱ ትገለገልበት የነበረው ሙቀጫዋ ፣ድስቷ እንዲሁም: ጌታችንን ገላዉን ልብሱን ታጣጥብበት የነበረዉ
ከዲንጋይ የተሰራ መገልገያ ዕቃዎችዋ ሲሆን ይህን ቅዱስ ስፍራ ለማየት የታደሉት ምዕመናን ጭምር
ደስታቸውን በእልልታ ና በዝማሬ በድምቀት እያከበሩት ይገኛል።
Wednesday, September 21, 2016
የቅድስት አርሴማ አዲስ ፀበል
አዲስ የፈለቀ ታላቅ የፀበል ፈውስ ስፍራ ኑ እና የእግዚአብሔር ድንቅ ስራውን መስክሩ::
ቸው ቅዱሳን ስም የሰጠንን ታላቁን የፀበል ፈውስ ነው፡፡ ቅዱስ ፀበል አፍልቆ ህዝቡን እየባረከና እየፈወሰ ይገኛል፡፡ አንከሶች መርገጥ (ቆመው መሄድ) ችለዋል እጃቸው የተቆለፈ ሽባዎች እጃቸው ተፈቶላቸዋል በአልጋ የመጡ ተፈውሰው በእግራቸው ሄደዋል በውስጥ ደዌ የሚሰቃዩ ፈውስ አግኝተዋል እባብ፣ አባጨጓሬ እና ወስፋት ከሆዳቸው ፀበሉን በመጠጣት ወጥቷል፡፡ ከኤች አይ ቪ ኤድስ ከትቪ በሽታ የተፈወሱ ሰዎች አሉ ከአኪንታሮት በሽታ የተፈወሱ ሰዎች አሉ
ፀጋ እ/ር በባዛላቸው በመላው ኢትዮጲያ ባገለገሉ አባት ታግዞ በመቶ የሚቆጠሩ ሰዎች በቅድስት አርሴማ ፀበል ከቁስል ነገር ድነዋል፡፡
አድራሻ ከ ከዊንጌት አደባባይ ተሻግራቸው ወደ ሙለጌታ አባት መናፈሻ በሚወሰደወ መንገደ ከደረሱ ሰዉቸነ መጠየቅ ይቻላል ለበለጠ መረጃ
0910792943(አባ ዜና)
0913986208 ወይም
0920146348.
የሰማእቷ እናታችን ረድኤል በረከት ይደርብን አሜን::
Sunday, August 14, 2016
ተዕምረኛ ድንጋዪች በዳጋ እሥጢፋኖስ
አቡነ ኂሩተ አምላክ ሁለት ድንጋዮችን በተረአምራት እንደ ታንኳ አድርገው በመጠቀም ጣና ባሕርን በበትረ መስቀላቸው እየቀዘፉ ዳጋ ወደተባለው ደሴት ገብተዋል፡፡ ጻድቁ የጣናን ባሕር እንደ ታንኳ ተጠቅመው የተሻገሩባቸው እነዚያ ሁለት ትላልቅ ድንጋዮችም ዛሬ በገዳሙ ውስጥ የጻድቃን ማረፊያ (ምዕራፈ ጻድቃን) ተብሎ በሚጠራው ቦታ ላይ በክብር ተቀምጠው ይገኛሉ፡፡ እሳቸው ያን ጊዜ ያረፉበት ቦታ ዛሬም ድረስ ‹‹ዓቃቤ ሰዓት›› እየተባለ በመዓርግ ስማቸው ይጠራል፡፡ አቡነ ኂሩተ አምላክ በቦታው ላይ በጽኑ ተጋድሎ ኖረው ሥርዓቱን አጽንተው ተጋድሎአቸውን ጨርሰው በዛሬዋ ዕለት ነሐሴ 8 ቀን በክብር ዐርፈዋል፡፡ በረከታቸው ይደርብን፡፡
Wednesday, August 10, 2016
ጎንድ ተክለ ሐይማኖት ገዳም
ጎንድ ተክለ ሐይማኖት ገዳም ከአማራ ክልል ርእሰ መዲና ባህር ዳር ተነስተን ዘንዘሊማ ሐሙሲት ከዚያም የፎገሮቹን አገር ወረታን እያቆራረጥን አዲስ ዘመን
እንደደረስን የጎንደሩን መስመር ተከትለን የጻድቋን እናት ጣራ ገዳም ደንን እያማተርን በውብ የአእዋፍ ዜማ
ተደምመን ከተቻለ መኪናችን ቆም አድርገን ሰላም ለኪ ብለን በአጸዶቿ መአዛ ህሊናችን ሰብስበን ጉዟችን አሁንም
ወደፊት ስንቀጥል የሊቦ ከምከምና የጎንደር ዙሪያ ወረዳ መካለያ የሆነችውን በ'ራሷ ጊዜ መድመቅና ከተሜነት
የጀመረችው ሰንደባ ወንዟን አርኖን ተንተርሳ ውብ የሆነውን አየሯን እየለገሰች ትጠብቃለች ወንዟ አርኖ አመቱን ሁሉ
ደከመኝ ሰለቸኝ ሳይል ለአርሶ በሌው ውሐውን ይለግሳል አርሶ አደሩም የተለያዩ ምርቶችን እያመረተ ሲያሻው ወደአዲስ
ዘመን ያልያ ወደእንፍራዝ በትናንሽ ታክሲዎች እያጓጓዘ ለከተማው ማህበረሰብ ይቀልባል። አርኖ የባለፉት ወራሪዎቻችን
የጣሊያን ሰዎች ስያሜውን እንደሰጡት ይናገራል። ከ'ዚህች ትንሽየ የገጠር ከተማ እልፍ እንዳሉ በቅርብ ርቀት ጋርኖን
ተንተርሳ እንፍራዝን ታገኟታላችሁ፡፡ እንፍራዝ ቀደምት ከተማ ስትሆን ከ'ሷ በቅርብ ርቀት የደብሳን ግንብ የጉዛራ
ቤተ መንግስት አጼ ሰርጸ ድንግል በ15ኛው መቶ ክፍለ ዘመን የከተመበት እንደነበር ታሪክ በየድርሳኑ ይዘግባል።
ከዚህም ጋር በተገናኜ እንፍራዝ የአጼ ቴዎድሮስ እናት ርስት ቦታ ስትሆን ተወላጅነታቸውም 'ዚህች ከተማ አካባቢ
እንደነበረ የታሪክ ዘካሪዎች በየጦማራቸው ከትበውታል፡፡
እንፍራዝ ፍቅር ተዘርቶ የበቀለባት ትንሽ ቦታ ግን ማህበረሰቦቿ ተቻችለውና ተረዳድተው የሚኖርባት ከደረቅ ወደብ ተነስተው የሚመጡ ተሳቢ መኪኖች ጎንደር በር ጣዕመት ወደባህርዳር መውጫ አልሚ ምግብ ቤት እረፍት አድርገው ያሻቸውን በልተው ጠጥተው ይጓዛሉ። ትናንሽ ህጻናት ቆሏቸውን በሰፌድ ብትን አድርገው ይውሰዱ ይብሉ እያሉ በውብ ፈገግታቸው ራብን አፈ ድሜ ያበሉታል። እንዳልኩት እንፍራዝ ካረፉ በኋላ ጉዞዎን እንደቀጠሉ ቁልቋል በር ላይ የሰፈሩትን የወረኢሉ ሙስሊሞች ወሎ ያለን እስኪመስለን ድረስ "ዴ " ን አጥበቀው እየጠሩ በፈገግታ ያስዋኛሉ። መኪና ላይ አያጧቸውም ተሳፍረው አብረው ካገኟቸው እንዴት ከወረኢሉ እንደመጡ 'ዚህ አካባቢ ሰፍረው እንደቀሩና ተላምደው በፍቅር እየኖሩ እንዳሉ በሚያምረው ልሳናቸው ይተርካሉ፡፡ " በል አቦ ጃል ዴርሻለሁ ወገን" ብለው ዳገታማውን ጉዞ ይያያዙታል። ቁልቋል በርን እንደጨረሱ የጎንደር ዙሪያ ወረዳ ርእሰ መዲና ማክሰኝትን ያገኛሉ።
ከዚህን በኋላ መኪና ካልያዙ ወርደው የደጎማ ታክሲ ያልያ አውቶብስ ያገኛሉ። ጉዞዎን ከጎንደርም የመጣ ይሁን ከባህርዳር ጅማሬው ከተማዋ ላይ ነው፡፡ ከከተማዋ 3 ኪሎሜትር በላይ ከተጓዙ በኋላ የአርባያውን መገንጠያ ያገኛሉ። ይህ መነሻ ወደተነሳንበት ጎንድ ተክለ ሐይማኖት ገዳም ይወስደናል፡፡ ከጎንደርም ከባህርዳርም የመጣ ተጓዥ ከአስፓልት ወጥቶ የጠጠር ጎዳናውን ይያዙታል፡፡
ከ'ዚህ መነሻ አስፓልት ተነስተን ጎንድ ለመድረስ 24 ኪሜ አካባቢ የሚርቅ ሲሆን መንገዱን እየተንገራገጩ መጓዝ የግድ ይላል።
ደጎላን ዳስንና ድንዛዝን ከታለፈ በኋላ አስራ ዘጠኝ ሐያ ኪሎ ሜትር እንደተጓዙ የኢብን ኢብራሂም አልቃዚ ( ግራኝ እጁ ) የሞተበትን ስፍራ ያገኛሉ። ይህ ቦታ የፖርቱጋል ወታደሮችን መርቶ የመጣው ክርስቶፎር ደጋማ (የመርከበኛው የቫስኮ ደጋማ ልጅ ) ቱርኮች ቀይ ባህር ቢገሉትም ተተኪው የነበረው በርተለሚዎዝ ዲያዝ የንግስቲቱን ሰብለ ወንጌል ልጅ የአባቱን የልብነ ድንግልን መንበረ ስልጣን እንዲመልስ ከፍተኛ ጉትጎታ ታደርግ ነበርና ክርስቲያኖቹ ፖርቱጋሎች አግዘውት ከ'ዚህ ስፍራ ግራኝንና ተከታዮቻቸውን ድል አደረጉ። ግራኝ በኢትዮጵያ ታሪክ የቆየባቸው 15 አመታት የተረጋጉ አልነበሩም። መጨረሻውም በዚህ ስፍራ በሞት ተቋጭቷል። ያልተረጋጉ የጦርነት ውሎዎች በሟቹ ደጋማ ሰም ከተሰየመችው ከተማ ደጎማ በቅርብ ርቀት ሲከናወን ይህንን ስፍራ የአገሬው ሰዎች "የድል በር " ብለው ይጠሩታል፡፡ ተራራማው የድል በር ላይ ተሁኖ ፊት ለፊት ደጎማን ከበስተኋል አድርገን ስንመለከት ደንቀዝንና የበለሳን ፈፋዎችና የተራራ ሰንሰለቶች ያያሉ። በእውነት የኢትዮጵያዊነት ህብር የሚገለጽበት ስፍራ ወኔ የሚሰነቅበት ስፍራ ቢባል ማጋነን አይሆንም። ከምናብ ትውስታ በኋላ ወደፊት ሁለት ኪሎ ሜትር እንደተጓዙ ጎንዶችን ታገኛላችሁ። ይህ ስፍራ ወደ ከፍተኛ የተራራ ነጥብ መሄድዎትን ይነግርዎታል ጠንካራ ብርድ አለና ጃኬት መያዙዎትን ያረጋግጡ።
ጭራቆ ወንዝ ላይ እግረዎትን ተለቃልቀው ከፈለጉ ደጎማ አርፈው ቢወጡ ጥሩ ነው። ከአፍ የሚጣል አይጠፋምና ያልያ ግን መኪናዎን ደጎማ ትተው የጎንድ ተክለ ሐይማኖትን ገዳማ የእግር ጉዞ ይያያዙታል።
የአየሩ መአዛ ከሌሎች ገዳማት በላቀ ሁኔታ ይጠራዎታል። የቅዱሳኑ መአዛ አለማዊነትን ይደፍቃል በግምት ከተራራማው ክፍል ወደታችኛው የበለሳ ተዳፋት ይምዘገዘጋሉ። መንገዱን የገዳሙ መስራች አባት አባ ዮሐንስ ( ዘግብጽ ) ሲሆኑ እኝህ አባት ለበለሳ በረከት ናቸው። በስጋዊ የህይወት ዘመናቸው በለሳ የወተቱና የወገሚቱ የማሩና የቅቤውን ሁኔታ ስናስብ ልብን ቀስፎ ይይዛል። በጸሎታቸው ጸላኤን ረትተው ሊጥልባቸው የነበረውን የተራራ ናዳ ገስጸው አንጠልጥለውታል፡፡ ዛሬ ድረስ ናዳው ተንጠልጥሎ ይታያል። ከዚህም በላይ ደግሞ ሊያስታቸው የመጣን ጸላኤ አሰልጥነው መንገድና ዘመናዊ ሊባል የሚችል የመስኖ ካናል አሰርተውታል። መልሰው እንደገና በር ቆልፈው በአንዱ ዋሻ ዘግተውበታል።
አቡነ ዮሐንስ ዘግብጽ በረጅም ዘመናቸው በአካለ ስጋ እያሉ ለዚህ ገዳም ስርአት ሰርተው አልፈዋል። በኋላም ጻድቁ ተክለ ሐይማኖት በእንግድነት መጥተው ለጻድቁ ዮሐንስ ስርአተ ምንኩስናን ሰጥተዋል። የቆብ አባትም ጭምር ናቸው፡፡ ትውልድ በዘመን ጅረት ቢያልፍም ጎንድ ( ጉንደ ወይን) ከአስራ አንደኛው አስራ ሁለተኛው ክፍለ ዘመን ጀምሮ በቅድስና ኖሯል እኛ ደግ አባታችንም በአካለ ስጋ ለረጅም ጊዜ ቆይተዋል። ምንኩስና ሰርተው ህዝብን እየማለዱ ለትውልድ አስተላልፈዋል። ከ400 በላይ መነኮሳት በብህትውና ይኖሩበታል፡፡ እያንዳንዱ መነኩስና መነኮሳይት የተለየ ስፍራ አላቸው። ገዳሙ ሰፊ የሆነ ክልል ያለው ሲሆን መነኮሳቱ ጠንካራ የስራ ባህል ለማየት የሚፈልግ የየትኛውም ማህበረሰብ ክፍል ያለምንም እርዳታ በጾም በጸሎት በርትተው ደግሞ ለአንዲት ማእድ ሲሉ ሰርተው እንጅ ለምነው ያቆሙት ቤት የላቸውም። ነገረ ስራቸው ሁሉ ክርስትና ብቻ ነው የፊታቸው ጥንካሬ አለምን ድል ያደረጉበት ሰይፋቸው ጽናት ይሆናል። ጉንደ ወይን ባለፉት የታሪክ ዘውጋችን ስናነሳ ሲሲኒዮስ ካቶሊክን ሲቀበል " ሲሲኒዮስ ይፍለስ ፋሲለደስ ይንገስ " ያሉት የጉንደ ወይን መነኮሳት ናቸው፡፡ ያሉትም አልቀረ ከደንቀዝ ቤተ መንግስት ተነስተው እስከ ላይማው ሰሜን ድረስ ደማቸውን አፍስሰዋል። (ደንቀዝ የአጼ ሲሲኒዮስ መናገሻ ከተማ የነበረች ሲሆን ከጎንድ በቅርብ ርቀት ትገኛለች፡፡) የገዳሙ መነኮሳት ከሌሎቹ ታላላቅ ገዳማት ጋር የጠበቀ ግንኙነት አላቸው፡፡ በገዳሙ ሁለት አብይት በአላት አሉ፡፡ ነሐሴ 24 የጻድቁ ተክለ ሐይማኖት እረፍት ይዘከራል። በዚህን ወቅት ከተለያዪ ስፍራዎች ተሳላሚዎች ይመጣሉ፡፡ መነኮሳቱ ለመጣው ተሳላሚ ሁሉ ምግብ ያቀርባሉ የማረፊያ ቦታ ያዘጋጃሉ።
ፍራፍሬው በቆሎው እሸቱ እንደልብ ነው። ጉንደ ወይን የተገኘው ሁሉ ይበላል። በሚገርም ሁኔታ በሺዎች የሚቆጠሩ ተሳላሚዎች መጥተው ንፍሮ ቅቅሉን ጠግበው በልተው ለጉዞ ስንቅ ይቋጥራሉ። ጠላ ለመጀመሪያ ጊዜ የተጠመቀበት ስፍራ ነው ብንል ማጋነን አይሆንም፡፡ ይህንን ጠላ ደግሞ የሚጠምቁት ወንዶቹ መነኮሳት ናቸው፡፡ ሌላው ከላይ የስራ ባህላቸው ለመነሻ ብጠቅስም መነኮሳቱ ወንዶቹ ያረሱት፥ አያርሙም ፥ ያረሙት አያጭዱም፥ ያጨዱት አይወቁም። ምርት የሚያጓጉዙት ሌሎች ናቸው፡፡ ስርአታቸው ሁሉ ህግ ነው። የሐይማኖታዊ ስርአቶቻችንን ዶግማና ቀኖና በጥብቅ አባታዊ ፍቅር ተምሮ ለመውጣት ጉንደ ወይን መምጣት።
የሚያምረውን ተፈጥሮአዊና ሐይማኖታዊ ስፍራ ይዩ በተጨማሪም በጸበሉ ፈውስን ያገኛሉና ጉንደ ወይን ይምጡ...
ድንቃ ድንቅ ገቢረ ተዐምራት በ ወይንዬ አቡነ ተክለ ሃይማኖት ወአቡነ ህጻን ሞዓ ገዳም
Tuesday, July 26, 2016
ድንቅ ተአምር በሽንቁሩ ቅድስ ሚካኤል
ዛሬ ኪዳነ ምህረት በእለተ ቀኗ በሽንቁሩ ቅድስ ሚካኤል ፅበል ስፍራ የተደረገ ድንቅ ተአምር .
የእግዚአብሔር ድንቅ ተአምር ለዓለም ይመስክሩ..!!!
እንደምን ከረማችሁ ወዳጆቼ ባለፈው የራሴን ታምር መስክሬላችሁ ነበር አሁን ደሞ እኔ ከተከራየሁበት ቤት አጠገብ የምትጠመቅ በ አለም ስሙዋ ወይዘሮ ማሬ የተባለች የ ቅዱስ ሚካኤል ወዳጅ በ ሽንቁሩ ደብረ መድሀኒት ቅዱስ ሚካኤል ፀበል የተደረገላትን ድንቅ ታምር እንደዚ ትናገራለች ለዘመናት እግሩዋን እያስነከሰ በጣም ያሳምማት ነበር የምትሰራው የምግብ ስራ ስለነበር እሱዋ ግን እረጅም ሰአት የምትቆምበት ነበር የመሰላት ነገሩ ግን ወዲህ ነው በ ቅርብ በጓደኞችዋ የተሰራባት መተት ነበር ቆማ እንዳትሰራ እና እንደልብ እንዳትራመድ ነበር የተፈለገው ታድያ በ ቅዱስ ሚካኤል ምልጃ ፀበሉን ለ 4 ወር ስትጠመቅ ቆይታ ዛሬ በ16/11/2008 ዓ.ም ከ ቀኝ እግሩዋ ላይ አንድ ባለ ኮፍያ ሚስማር በ ስስ ላስቲክ ተጠቅልሎ ወጥቶላታል። የሚደንቀው ነገር ሚስማሩ ሲወጣ ምንም የህመም ስሜት አልነበረውም ደምም አልነበረውም እኔን የፈወሰ መላኩ ቅዱስ ሚካኤል እናንተንም ይርዳ ትላለች።
ወ/ሮ ማሬን ማግኘት እና መርዳት ለምትፈልጉ
+251920 34 3349 ደውለው ማረጋገጥ ይችላሉ።
የቅዱስ ሚካኤል አምላክ ይክብር ይመስገን።
ይህን ድንቅ ተአምር ለአለም ይመስክሩ ዘንድ በቅዱስ ሚካኤል ስም እጠይቃለው።

Source: Memher Pawlos Melkea Selasie
Thursday, July 21, 2016
ማርያም ውቕሮ
ከአለት
ተፈልፍለው ስለተሠሩ ውቅር ሕንፃዎች ሲነሳ ቀድመው የሚጠቀሱት የላሊበላ ውቅር አብያተ ክርስቲያናት ናቸው፡፡
በ12ኛውና በ13ኛው ምታመት በንጉሡ ቅዱስ ላሊበላ ዘመንና ከርሱም በኋላ የታነፁት እነዚህ ውቅር ሕንፃዎች በዩኔስኮ
በዓለም ቅርስነት የተመዘገቡ ናቸው፡፡ የእነዚህን ውቅር አብያተ ክርስቲያናት የግንባታ ውርስ ከዘመነ አክሱም
ትውፊት የቀጠለ እንደሆነ የሚመለከት ቢሆንም፣ በአንዳንዶች በኩል በውጭ ሰዎች እንደታነፁ የሚያመለክቱ አልታጡም፡፡
ሁለተኛውን አተያይ ተቀባይነት እንደሌለው ከሚጠቅሱትና ከዘመነ አክሱም የቀጠለ እንደሆነ አመላካቹ ከላሊበላዎቹ
ውቅሮች 800 ዓመታት አስቀድሞ በትግራይና በዋግ ውስጥ ውቅር አብያተ ክርስቲያናት መገንባታቸው እንደሆነ ይወሳል፡፡
ከሃምሳ ዓመት በፊት በአዲስ አበባ (በሚያዝያ ወር 1958 ዓ.ም.) በተደረገው ሦስተኛው የኢትዮጵያ ባህልና ጥበብ ዓለም አቀፍ ጉባኤ ‹‹በትግራይ ጠቅላይ ግዛት ስለሚገኙ በውቅር የታሠሩ አብያተ ክርስቲያናት›› በሚል ርእስ ጥናት ከነ ልዩ ልዩ ማስረጃዎች ጋር ያቀረቡት ዶ/ር አባ ተወልደመድኅን ዮሴፍ (1908-1959) በተለያዩ የትግራይ አውራጃዎች 120 የውቅር ሕንፃዎች እንደሚገኙ ገልጸው ነበር፡፡
በጽሑፎቻቸውም እንደሚታየው በትግራይ የሚገኙትን ኢትዮጵያን የሚያኮሯትን የታሪክ የጥበብና የሃይማኖትም ቅርሶች በመግለጻቸው ቀድሞ አስደናቂዎች በሆኑ በላሊበላ ሕንፃዎች የበለጸገውን የአገሪቱን የሥነ ጥበብና የሃይማኖት ታሪክ በበለጠ እንደሚበለጽግ አድርገዋል፡፡
ከእነዚህ 120 ውቅር ሕንፃዎች መካከል አንዷ የሆነችው ማርያም ውቅሮ ቤተ ክርስቲያን ከ50 ዓመት በፊት እንደምትታወቀውና በዶ/ር አባ ተወልደ መድኅን እንደተመዘገበው፣ በዓድዋ አውራጃ በእምባሰነይቲ ወረዳ፣ በአሁኑ አከላለል በማዕከላዊ ዞን በወርዒለኸ ወረዳ በእምባሰነይቲ ንኡስ ወረዳ የምትገኘው እንዳማርያም ውቕሮ ቤተ ክርስቲያን በአራተኛው ምታመት (357 ዓ.ም.) በወንድማማቾቹ ነገሥታት አብርሃ ወአድብሃ መመሥረቷ ይነገራል፡፡
የማርያም ውቕሮ ሕንፃ ሲገለጽ
ከማዕከላዊ ዞን መቀመጫ ከአክሱም ከተማ 112 ኪሎ ሜትር፣ ከሐውዜን 34 ኪሎ ሜትር፣ ከመቐለ 125 ኪሎ ሜትር ርቀት ላይ የምትገኘው ማርያም ውቕሮ ቤተ ክርስቲያን ከውቅሩ ሕንፃ ጀርባ ለጥ ያለ ሜዳ በመሆኑ በዚያው መስመር የሚመጣ መንገደኛ ወደ ገደል እንዳይወድቅ ከመሥጋት ባለፈ፣ ቤተ ክርስቲያን መኖሩን የሚያሳይ ነገር የለም፡፡ ከሰባት ኪሎ ሜትር ርቀት ከነበለት በሰሜን ምሥራቅ አቅጣጫ በፊት ለፊት የሚመጣም አሻግሮ ቢያይም ሕንፃ ቤተ ክርስቲያኑን እንዳይመለከት በዙሪያው ያሉ ኮረብታዎች ይሸፍኑታል፡፡ ከገደላማው ኮረብታ ቀረብ የሚል ተጓዥ ከጠባቦቹ የመግቢያ በሮች ይልቅ ጎልተው የሚታዩት በውቅሩ ከፍታ መስኮት መስሎቹ ሽንቁሮች በውስጡ ቤተ ክርስቲያን እንዳለ ያመለክቱታሉ፡፡
የውቅር ሕንፃው ጠቅላላ ስፋት 20.6 ሜትር በ10.3 ሜትር ሆኖ ከፍታው (ቁመቱ) 6.9 ሜትር ነው፡፡
እንደ አስረጂው መልአከ ሰላም ዓምደብርሃን ገብረፃድቅ አገላለጽ፣ የቤተ ክርስቲያኑ አሠራር ካንድ ቋጥኝ ኮረብታ (ተራራ አከል) ተፈልፍሎ አንድ ወጥ በሆነ ውቅር ድንጋይ የታነፀ፣ ‹‹ዓመደ ጭዳ›› የሚሉት ባለአርባ አራት ምሰሶ ሆኖ በየምሰሶው ማዕዘን ጫፍንና ጠርዝ በተለያየ መልክ የተቀረፁ ሐረጎች፣ የመስቀል የማኅተምና በብዙ ኅብረ ጥበብ የተዋቡ ቅርፆች አሉበት፡፡ በየሕንፃው ግድግዳም የሥነ ሕንፃ ጌጣጌጥና ቅርፃ ቅርፅ ያሉበት ዕፁብ ድንቅ ሕንፃ ነው፡፡ በነባር ስሙ መቅደስ፣ ቅድስትና ቅኔ ማሕሌት ያለው ሲሆን በቅኔ ማሕሌቱ ከራሱ በተያያዘ ከሕንፃው በቅርፅ ተፈልፍሎ የወጣ በአንድ አካል ልክ የተቀረጸ ልዩ መልክና ውበት ያለው ቅርፅ ይታያል፡፡ የደብሩ አለቃ ወይም የአስተዳዳሪ መቆሚያም ማረፊያም ነው፡፡
ከቅኔ ማሕሌት በስተሰሜን በኩል ‹‹ምቅዋም ንግሥት ማርያም›› የሚሉት ሕንፃ አለ፤ የሴቶች መቆሚያና መፀለያ ነው፡፡ በዚያውም ወደ ቅድስት መግቢያ በር አለው፤ መንበረ ታቦቱ ሦስት ሆኖ የቅድስት ማርያም የቅዱስ ሚካኤልና የቅዱስ ገብርኤል ሲሆን ሁሉም በቅርፅ ተፈልፍለው የወጡ ናቸው፡፡
የቅድስት ማርያም መንበር ከላይ ከመንበሩ መጠን ቀስተ ደመና የሚመስል ቅርፅ አለው፡፡ የቤተ ክርስቲያኑ መግቢያዎች ሦስት በውስጥ ሦስት በውጭ ስድስት ሲሆኑ ባለሁለት ደረጃዎች ናቸው፡፡ የእነዚህ መዝጊያዎች አበው እንደሚናገሩት ከእምባጮ ዕፅ የተሠሩና እስካሁን ድረስ በአገልግሎታቸው ጉድለት የሌለባቸው ጥንካሬያቸው እንደተጠበቀ ይታያል፡፡ መወርመሪያውና መሸጎጫውም አብሮ ካንድ እንጨት የተሠራ ነው፡፡
ከቅኔ ማሕሌቱ በላይ እንደፎቅ ሆኖ የቅዱስ ጊዮርጊስ ቤተመቅደስ (ቤተ ጊዮርጊስ) ይገኛል፡፡ በትግራይ ከሚገኙት ውቕር አብያተ ክርስቲያናት አንዱ የሚለየው ባለፎቅነቱ ነው፡፡ ወደፎቁ ለመውጣት አዳጋች በመሆኑ ‹‹ነፍስህን ለፈጣሪ ሰጥተህ ነው በመሰላል የምትወጣው›› ይላሉ፡፡ ከቅድስቱ ውስጥ በስተሰሜን የመድኃኔዓለም ቤተ መቅደስ የሚሉት የነበረ ቢሆንም በአሁኑ ጊዜ የንዋየ ቅዱሳቱ ማከማቻ ቤተ መዛግብት አድርገውት ይታያል፡፡ ቤተልሔሙም እንደ ቤተ ክርስቲያኑ ሁሉ ውቅር ሕንፃ ነው፡፡
ሌላው አስደናቂ ምስጢርና ሁልጊዜም እንደተአምር እየተቆጠረ የሚነገርለት በቅድስቱ ሕንፃ ወለል በግራ በኩል ባለመዝጊያ የሆነ ረዥም የጉድጓድ ዋሻ አለ፡፡ በውስጡ የሚገኝ የምንጭ ውኃ ጥልቅ በመሆኑ በረዥም ገመድ ወይም መጫኛ አድርገው እየቀዱ ለቅዳሴና ለጠበል ይጠቀሙበታል፡፡ ዋሻው ሰፊ ሆኖ በምንጩ ውኃ ዳር የእግር መንገድ አለው ይባላል፡፡ የዕድሜ ባለጸጎች የሆኑት የደብሩ ካህናት የባትሪ ወይም የፓውዛ መብራት ተይዞ በዋሻው ብዙ መንገድ የሚያስኬድ ርቀት እንዳለው ይናገራሉ፡፡
ቤተ ክርስቲያኗ ከሌሎች ውቅር ሕንፃዎች ሁሉ የበለጠችና ልዩ የሚያደርጋት የቤተ ክርስቲያኑ ሕንፃ የታነፀበት መሣሪያ ‹‹እብነ አድማስ›› የሚባል የሰው እጅ በማይደርስበት የቤተ ክርስቲያኑ ሕንፃ ጣሪያ ላይ በብረት ሰንሰለት ተንጠልጥሎ መገኘቱና መታየቱ ነው፡፡ በዚያ ላይም ‹‹በዕብራይስጥ›› ቋንቋ የተጻፈ ጽሑፍ በቅርጹ ላይ ይገኛል፡፡
አለቱን እያቀለጡ ሕንፃውን የገነቡበት እብነ አድማስ ላይ የተጻፈው ጽሑፍ አለመተርጎሙና አለመጠናቱ የደብሩ አገልጋይ ቄስ ዘማርያም ተክለ ሃይማኖት ያወጋሉ፡፡ ከሦስቱ እብነ አድማሶች አንዱ በፋሺስት ኢጣሊያ ወረራ ጊዜ መነቀሱም ይወሳል፡፡
ይሁንና ይህን አስደናቂ የሆነውን የእምባሰነይቲ ውቅሮ ቅድስት ማርያም ሕንፃ ቤተ ክርስቲያን አናጺው ማነው? የሚል ጥያቄ በሚነሳበት ጊዜ በአካባቢው ሲነገር የኖረ የተለያየ አፈ ታሪክ ቢኖርም በጽሑፍ የተደገፈ ታሪክ እንደሚያስረዳው ከክርስቶስ ልደት በኋላ በ4ኛው ምታመት ነገሥታቱ አብርሃና አጽብሐ እንደአነጿት ያረጋግጣል፡፡ ከአብርሃና አጽብሐ ገድል የተገኘው የተመረጡ ነገሥት አብርሃ ወአጽብሐ ለዚያ ደብር (ተራራ) ሌላ መቅደስ (ቤተ ክርስቲያን) አነጹ፤ ይህችውም ኦር ለተባለው ወንዝ አቅራቢያ ናት›› ሲል ያስረዳል፡፡ ኦር ማለት በአገሬው ሕዝብ ቋንቋ ወርዒ ማለት ሲሆን በአሁኑ ጊዜ ደግሞ ወርዒ ለኸ እየተባለ የሚጠራው ነው፡፡
ቱሪስቶችን የምትናፈቀው ማርያም ውቕሮ
ከ1600 ዓመታት በላይ ዕድሜ ያስቆጠረችው የማርየም ውቕሮ ሕንፃ ምዕመናኑ በተጨማሪ ቱሪስቶችን ይናፈቃል፡፡ እንደ አካባቢው ኅብረተሰብም ሆነ ደርሶ ተመላሹ አገላለጽም በአስደናቂ ሕንፃነቱ ለዓለም ቅርስነት ለመመዝገብ አቅም ያለው ቢሆንም በመሠረተ ልማት በተለይም በመንገድ ችግር ምክንያት ለዓለም ሕዝብ ቀርቶ ለአገር ቤትም ብዙ ሳይታወቅ ቆይቷል፡፡
እንደ መልአከ ሰላም ዓምደ ብርሃን ገብረፃድቅ መግለጫ፣ በሁለት አቅጣጫ በሐውዜንና በዓድዋ ዕዳጋ ዓርቢ በኩል እስከ ነበለት ከተማ ድረስ የነበረው የመንገድ ችግር የተቃለለ ቢሆንም፣ ከነበለት ከተማ እስከ ማርያም ውቕሮ ሕንፃ ድረስ ያለው መንገድ ግን በምስማዕ ወንዝ ድልድይ አለመሠራት ምክንያት ችግሩ አሁንም እንዳለ ነው፡፡ በጋ ሲሆን ብቻ አንዳንድ ጠንከር ያሉ ተሽከርካሪዎች በብዙ ጥንቃቄ እስከ ቤተ ክርስቲያኑ ድረስ ይደርሳሉ፡፡
ሰኔ 21 ቀን 2008 ዓ.ም. በተከበረው ሕንፀተ ቤተ ክርስቲያን በዓል የተገኙት ብፁዕ ወቅዱስ አቡነ ማትያስ ቀዳማዊ ይኸንኑ የመንገድ ችግር አንስተው በተለይ መንግሥት ትኩረት እንዲሰጥበት ጥሪ አቅርበዋል፡፡
‹‹የዚህ ታሪካዊ ቦታ ሃይማኖታዊ ቅርስን በማስጠበቅ አካባቢውን በማጽዳትና በማልማት የተጀመረው ልማት ቀጥሎ፣ የአካባቢው ተወላጆችና ምዕመናን እንዲሁም የቅርሱ ተቆርቋሪዎች በመተባበር መንገዱንና ድልድዩን አሠርታችሁ ለቱሪስቶች መስሕብነት የተመቻቸ ማድረግ ይጠበቅባችኋል፤›› ብለዋል፡፡
‹‹ፍጡነ ረድኤት››
ከሺሕ ዓመታት በላይ ዕድሜ ያስቆጠረው ውቅር ሕንፃ በዘመን እርጅና ሳቢያ አካባቢው ምቹነት አጥቶ ለምዕመናኑም ሆነ ለካህናቱ፣ ለአካባቢው ኅብረተሰብ አዳጋች ሆኖ ዘመንን ቆጠረ፡፡ ለመሳለምም ሆነ ለመጎብኘት የሚደርሰውም ቁጥር አነስተኛ ሆነ፡፡ በአጥቢያው የንግሥ በዓል ኅዳር እና ሰኔ በ21ኛው ቀን ከማይለዩ በቀር፡፡
መልአከ ሰላም ዓምደ ብርሃን በድርሳናቸው እንደገለጹት፣ የቤተ ክርስቲያኑ ቅፅረ ግቢ አፈሩ እየተሸረሸረ አልቆ፣ ወደ ቤተ ክርስቲያኑ ለመግባትና ለመውጣት በተለይ ሌሊት በጨለማ ጊዜ እያንሸራተተ እጅግ ያስቸግር ነበር፡፡ ይህንን የተገነዘቡት የአካባቢው ተወላጅና በዲቁና ያገለገሉት በጎ አድራጊው አቶ ብርሃነ ግደይ ከባለቤታቸው ወ/ሮ ዓለም አረጋዊ ጋር በመሆን ከአራት ሚሊዮን ብር በላይ በሆነ ወጪ ለደብሩ የሚጠቅሙ የልማት ሥራዎችን ሠርተዋል፡፡ ለዕርዳታ ፈጥነው ደርሰዋል፡፡ ፍጡነ ረድኤት ሆነዋል፡፡ ወደ ቤተ ክርስቲያኑ መዳረሻ የሚወስደውን ወጣ ገባ አስቸጋሪ መንገድ ለማስተካከል ሰፊ ዓውደ ምሕረት እንዲሆን በአራት ዕርከን ደልድለው ምቹ አገልግሎት እንዲሰጥ በማድረግ እንዲሁም ለእንግዶች (ጎብኚዎች) ማረፊያና መጠለያ አዳራሽና አምስት የመኝታ ክፍሎችና የንጽሕና ክፍሎች ማሠራታቸው በምረቃው ወቅት ተወስቷል፡፡
የመሠረተ ልማት ሥራዎቹን ቅዱስ ፓትርያርኩ አቡነ ማትያስ የመረቁ ሲሆን በሥነ በዓሉ ላይ እንደተናገሩትም ‹‹የቀደሙት አባቶቻችን እግዚአብሔር በገለጸላቸው ጥበብ ይህን አስደናቂ ሕንፃ ሠርተው ማስተላለፋቸውን ታሪክ ሲያስታውሳቸው እንዲኖር ሁሉ፣ እንደዚሁም በጎ አድራጊው አቶ ብርሃነ ግደይ በዚህ ታሪካዊ የቅርስና የሃይማኖት ቦታ በሠሩት በጎ ሥራ ሁሉ ታሪክ ለዘላለም እንደሚያስታውሳቸው እሙን ነው፡፡››
የ51 ዓመቱ ድምፅ!
በልዑል ራስ መንገሻ ሥዩም አሳሳቢነት፣ በውቅር ስለተሠሩት የትግራይ አብያተ ክርስቲያናት ሕንፃዎች ለመጀመሪያ ጊዜ በ1958 ዓ.ም. በይፋ በዓለም አቀፍ ጉባኤ በሰነዶች በታጀበ ማስረጃ ያስተዋወቁት፣ ነፍስ ኄር ዶ/ር አባ ተወልደመድኅን ዮሴፍ ለፈጸሙት አኩሪ ተግባር በወቅቱ ቀዳማዊ ኃይለሥላሴ ላንድሮቨርና ዘመናዊ የሥዕል ማንሻ (ካሜራ) ከወርቅ ሜዳሊያ ጋር ሸልመዋቸው ነበር፡፡ ከጉባኤው አንድ ዓመት በፊት ኅዳር 7 ቀን 1957 ዓ.ም. በአዲስ ዘመን ያሰሙት ድምፅ አሁንም ገደል ማሚቶ ሆኖ ያስተጋባል፡፡ እንዲህ ሲሉ ጽሑፋቸውን ጀመሩ፡፡
‹‹አንድ የውጭ አገር ሰው ሊቅ በቅርብ ዓመታት በአማርኛ ታትሞ በወጣ የኢትዮጵያ ታሪክ መጻፉ ውስጥ፤ ስለ ላሊበላ ሕንፃዎች ብቻ ሲናገር እንዲህ ይላል፤›› ሲሉም ቀጠሉ፡፡ ‹‹የኢትዮጵያን ታሪክ የሚመረምሩ ሁሉ፤ እስካሁን ድረስ የላሊበላ አብያተ ክርስቲያንናት የተፈለፈሉበትን የጥበብ ምሥጢር አላገኙትም፡፡ እንደዚህም ማለት በዓለም ላይ ብቻውን የሚገኘውን እንደዚህ ልዩ የሆነውን ሥራ በምን ዓይነት መሥራት እንደቻሉ አላወቁትም ማለት ነው››፡፡ አያይዘውም ሠለሱ፡፡ ‹‹በተጠቀሰው የታሪክ ጸሐፊ ሐሳብ ላይ እርሱን በመከተል ይህንንም ማሰብ እንችላለን፤ ማለት ለግብጽ የፒራሚድ ሐውልቶች ትልቅ መታሰቢያና መለዮ እንደሆኑ ለኢትዮጵያም የአክሱም ሐውልቶችና ከመቶ የሚበልጡ የላሊበላና የሰቆጣ፤ የትግራይ ሕንፃ ውቅር አብያተ ክርስቲያናት አስደናቂዎች መታሰቢያዎችና መለዮዎች እንደሆኑ አሳምረን መገንዘብ አለብን፡፡ ስለዚህም ከሁሉም የዓለም አህጉሮች ኢትዮጵያ አገራችን ብቻ ግምት የሌለው ታሪካዊ ሀብት፣ ማለት ከመቶ በላይ የሆኑ በውቅር የታነፁ አስደናቂዎች አብያተ ክርስቲያናት እንደሚገኙባት ማወቅ፤ ለኢትዮጵያን ሁላችን ወሰን የሌለው ደስታ ሊሰማን ይገባል፡፡
‹‹ተራራዎች እየፈለፈለች፤ በትልቅ ጥበብና ትጋት አለቶችን እየወቀረች የማይፈነቀል የክርስትና ትልቅ እምነቷን በጠንካራው አለትና በተራራዎች ሆድ ውስጥ የመሠረተች ታላቋ ኢትዮጵያ አገራችን፣ በሌሎች የዓለም አህጉሮች የማይገኙ፤ በብዛታቸውና በአስተናነጻቸውም የሚያስደንቁ በውቅር የታነፁ አብያተ ክርስቲያኖቿ በእውነቱ ልትኮራባቸውና ልትደሰትባቸውም የሚገባት ናት፡፡ ዳሩ ግን በዚሁ ምክንያት ለእነኚህ ለምትኮራባቸው ሐውልቶችና በውቅር ለተሠሩ አብያተ ክርስቲያኖቿ ባስፈላጊ ዘዴና ጥንቃቄ ልትይዛቸው ከማርጀትና ከመበላሸትም ልትጠብቃቸው ይገባታል፡፡ እንዲሁም ተገቢ በሆነ ዝግጅት በውቅር ስለ ተሠሩ አብያተ ክርስቲያኖቿ የታተሙ ጽሑፎችን እየዘረጋች በሞላው ዓለም እንዲታወቁ ማድረግ፣ የተባሉት ሐውልቶቿና አብያተ ክርስቲያኖቿ በደንብ ተጠብቀው ለመጪዎች ትውልዶች ማስተላለፍ ኢትዮጵያ ከፍ ያለ ኃላፊነትና የተቀደሰ ተግባር እንዳለባት ልትዘነጋው አይገባትም፡፡››

ማርያም ውቕሮ - ከዓለም የተደበቀው የ1600 ዓመቱ ቅርስ
የእመቤታችን የቅድስት ድንግል ማርያምና የአርባ ሓራ መድኃኒዓለም ተዐምር
Thursday, July 14, 2016
አባ ጊዮርጊስ ዘጋስጫ ያደረጉት ተአምር
አንድ አምላክ በሚሆን በአብ በወልድ በመንፈሰ ቅዱስ ስም አሜን
ዛሬ በዓመታዊ የዕረፍታቸው በዓል ታስበው የሚውሉት አባ ጊዮርጊስ ዘጋስጫ ያደረጉት ተአምር ይህ ነው፡- አምሃራ ሳይንት ቦረና ከአባ ጽጌ ድንግል ገዳም የ5 ሰዓት የእግር መንገድ ከተሄደ በኋላ የአባ ጊዮርጊስ ዘጋስጫ ገዳም ይገኛል፡፡ ይኽ የአቡነ ጽጌ ድንግል ገዳም ከአቡነ ጊዮርጊስ ዘጋስጫ ገዳም ጋር የሚያገናኘው ‹‹የእግዜር ድልድይ›› የተባለ አስገራሚ ታሪክ ያለው ድልድይ አለው፡፡ ሁለቱ ቅዱሳን በመንፈስ ተጠራርተው ለመገናኘት ቢያስቡም ታላቁ የወለቃ ወንዝ ሞልቶ በአካል ሳይገናኙ ቀሩ፡፡ በዚህም ሁለቱ ቅዱሳን አዝነው ከወንዙ ወዲያና ወዲህ ሆነው አፈር ተራጭተው ቢመለሱ ያ የተራጩት አፈር በተአምር ድልድይ ሆነ፡፡ ድልድዩን ሁለቱም በበዓታቸው ሆነው በመንፈስ አዩት፡፡ ጠላት ሰይጣንም ይህንን ሲያይ ድልድዩን በትልቅ ሹል ድንጋይ በስቶ ሊያፈርሰው ሲል አባ ጊዮርጊስ በመንፈስ አዩትና ከጋስጫ ተነሥተው በደመና ተጭነው በመሄድ ሰይጣኑን በግዘፈ ሥጋ ገዝተው ያንን አፈርስበታለሁ ያለውን ትልቅ ድንጋይ አሸክመውት ደብራቸው ጋስጫ ድረስ ወስደውታል፡፡ ያ ድንጋይ ዛሬ በገዳሙ ደወል ሆኖ እያገለግለ ይገኛል፡፡ ድልድዩም እስካሁን ድረስ ለአካባቢው ሙስሊም ማኅበረሰብ ብቸኛው የወለቃ ወንዝ መሻገሪያቸው ሆኖ እያገለገላቸው ይገኛል፡፡
በተአምራት የተሠራው የእግዜር ድልድይ
አባ ጊዮርጊስ የፈለፈሉት ድንቅ ቤተ መቅደስ
ሰይጣን ድልድዩን ሊያፈርስበት የነበረው ትልቁ ሹል ድንጋይ አሁን በጋስጫ ገዳም ለመነካካቱ ደወል ሆኖ ያገለግላል

ሌላው በእነዚህ ሁለታ ታላላቅ ገዳማት ያየሁት እጅግ አስገራሚ ነገር ቢኖር ሻሾ የሚባለው ነው፡፡ ይኸውም ታማኙ ውሻ ሻሾ በ2006 ዓ.ም እኔ ከአባ ጽጌ ድንግል ገዳም ወደ አባ ጊዮርጊስ ዘጋስጫ ገዳም ለመድረስ የ5 ሰዓት የእግር መንገድ መሄድ ግዴታ በሆነብኝ ሰዓት አሰልቺውን
የበረሃ ጉዞ ከአንድ ጓደኛዬ ጋር ስንጓዝ ሙሉውን የ5 ሰዓቱን መንገድ ይመራን የነበረው ታማኙ ውሻ ሻሾ ነበር፡፡
ደክሞን ስናርፍ አብሮን እያረፈ፣ መሄድ ስንጀምርም አብሮን ከፊት ከፊት እየተራመደና መንገዱን እየመራ እዛው ገዳሙ
አደረሰን፡፡ ሻሾ ዛሬ ከሰው ይበልጥ ናፈቀኝ፡፡ የጻድቁን የአባ ጊዮርጊስ ዘጋስጫን በረከት አንድም ታማኙን ሻሾን
ለማግኘት መስከረም ላይ ከግሸን መልስ ለመሄድ አስቤያለሁና አምላከ ቅዱሳን ይፍቀድልኝ፡፡
ከአባ ጽጌ ድንግል ገዳም እስከ አባ ጊዮርጊስ ገዳም ድረስ ያለውን የ5 ሰዓት የእግር መንገድ ከፊት ከፊት እየመራ በረሃውን አቋርጦ የወሰደኝ የገዳሙ ታማኝ ውሻ ሻሾ- ከገዳሙ በቅርብ ርቀት ላይ ከደረሰ በኃላ ሲያሳርፈን፡፡
የግሸን ተጓዞች ይኽን አጋጣሚ ብትጠቀሙ በረከቱ ዕጥፍ ድርብ ይሆንላችኃል፡፡ ከደሴ በግማሽ ቀን ወግዲ የምትባል ከተማ በማደር በቀጣዩ ቀን በአሕዛብ የተከበቡትንና እጅግ አስገራሚ የሆኑትን የአባ ጽጌ ድንግል ገዳምንና የአባ ጊዮርጊስ ዘጋስጫ ገዳምን መሳለም ይቻላል፡፡ እዛው አካባቢ ደግሞ ጸበላቸው ውስጥ እንጨት ሲነከርበት መቁጠሪያ አድርጎ የሚሰጠውን የአቡነ ገብረ እንድርያስን ገዳም መሳለም ይቻላል፡፡

Wednesday, July 13, 2016
ከሰማይ መና የሚወርድበት ሰረድኩላ ሚካኤል
ከሰማይ መና የሚወርድበት ሰረድኩላ ሚካኤል አስተዋሽ ያጣ
ሊታወቅ የሚገባ ብዙ ታሪክ ያለው ቤተክርስቲያኑ ፈርሶ የሚሰራው የሚረዳው የሚያስታዉሰው ያጣ ተምረኝዉ የቅዱስ ሚካኤል ገዳም ::
መንዝ እመጋ ቆላ አካባቢ ሰረድኩላ ቅድስ ሚካኤል :-
ይህን ገዳም እስራኤላዎቹ በደመና መጥተዉ ና ክንፍ ያላቸው ከመሰረቱት ከ፬4ቱ ቅዱሳን አንዱ /ናአድ/ የመሰረቱት ገዳም ነው፡፡
ይህን ገዳም እስራኤላዎቹ በደመና መጥተዉ ና ክንፍ ያላቸው ከመሰረቱት ከ፬4ቱ ቅዱሳን አንዱ /ናአድ/ የመሰረቱት ገዳም ነው፡፡
ይህ ገዳም ትልቅ ዋሻ በቤተክርስቲያኑ አካባቢ ይገኝል፡፡
ዋሻው ውስጥ ሲገቡ ያልፈረሱ ብዛትያላቸው ክንፍ ያላቸውና ክንፍ የሌላቸዉ አፅመ ቅዱሳን/ይታያሉ፡፡በዚህ ዋሻ ውስጥ ማንም ሰው ሂዶ ሊያየው የሚችል /መና/ ከሰማይ ይወርዳል፡፡በዚያ አካባቢ ታይቶ የማይታወቅ አህል ነገሮችአና መና በዋሻው ውስጥ በብዛት ተንጠልጥለው እና ዙሪያው ሁሉ፡ ሽንብራ;አተር;ባቂላ ና የተለያዩ የማይታወቁ ጥራጥሪዎች ና /የኮክ ፍሬ/ ይታያሉ፡፡

የሚገርመው እዚያ አካባቢ ኮክ አያቁም አይበቅልም፡፡አይተውትም
አያቁም፡ዋሻው ውስጥ ሲገብ በብዛት የኮክ ፍሬ ይታያል፡፡የተለያዩ ቅርሶች በዋሻው ውስጥ ይታያሉ፡፡ ይህን
ቦታ ቤተክርስቲያናችን አለማሳወቋ በጣም ያሳዝናል እግዚአብሔር ግዜ አለው ለዚህ ቦታ ወገኖቺ በቅዱስ ሚካኤል ስም
ይህን ቦታ አሳውቁ የማይታወቁ ቅርሶች ያለበት ቦታ ነው፡፡እንጠብቀው፡እንከልለዉ፡እንከባከበው አደራ እላለሁ ፡፡ ቤተክርስቲያኑ አርጅቶ በራሱ ግዜ ፈርሶ አስተዋሽ አጥቶ ፡፡በአዲስ መልክ ለመስራት የአገሩ ሰወች ኮሚቴ አቋቁመው
በመለመን ላይ ናቸው፡፡
የሚካኤል ወዳጆች ሚካኤልን የምትወዱ:የምትዘክሩ በቅዱስ ሚካኤል ስም እርዱት እናሰራው
በጣም ታዕምር ያየሁበት እና የቅዱሳን ቦታ ነው፡፡/የሰረድኩላ ቅዱስ ሚካኤል በቤታችን ይግባ;ሀሳባችን
ያሳካልን፡፡አሜን!!!
ቦታዉ፡-ከአ/አ ሰሜን ሸዋ መንዝ ሞላሌ በእመጋ ኡራኤል ኢየሱስ ገዳም አካባቢ፡መንዝ ከሞላሌ ከተማ የ፭5ሰዓት የእግር መንገድ ሰረድኩላ ሚካኤል ይባላል፡፡
ጩጊ ማርያም- ከጸበሉ ጠጥተው ስጋቸው ያልፈረሰ ፍየሎች
Friday, July 8, 2016
የሸንኮራው ዮሐንስ ተነግሮ የማያልቀው ተአምር!!!!!!!!!
ሰውነቴ በለምጽ የተመታው ነፍስ ሳላውቅ በህጻንነቴ ነው የምትለዋ የጎንደርዋ አጸደ ማርያም ነፍስ ሳውቅ ማፈር ጀመርኩኝ ትምህርቴንም አቁዋርጩ ወደ መሐል ሐገር መጣው ሰው ቤት ለመግባት ማን ይቅጠረኝ ፊቴን ሲያዮ ይደነግጣሉ ከሰው ተጠግቼ በቆሎ መሸጥ ጀመርኩኝ የዛሬ አመት ክረምቱ ሲገባ አንዲት ሴት ልትገዛኝ መጥታ ስለ ሸንኮራ ነገረችኝ አቅም የለኝም ለመሄድ ስላት ጸበልና እምነቱን ሰጠችኝ ማታ ሰውነቴን ተቀብቼው አደርኩኝ አታምኑኝም ለድህነቴ ምክንያት ሁለቱም እጆቼ ጠዋት ስነሳ ሌላ መልክ አምጥተዋል ደነገጥኩኝ ሰው ሲያየኝ ደነገጠ ምን መድሐኒት ነው አሉኝ ጨርቄን ማቄን ሳልል ሸንኮራ መጣው መጥምቁ ምን ተስኖት ሰውነቴ በሙሉ ዳነ ከሰው እኩል አቆመኝ አዲስ አበባ ስመጣ የሚያውቁኝ ጠፋውባቸው መላ አካሌ በለምጽ ተመቶ ነበርና ስድን አዲስ ሌላ ከለር ሌላ ሰው ሆንኩኝ መጥምቅዬ ከጌታው አማልዶ ምንም የማላወቀውን በሸንኮራው የሰርክ ጉባኤ ትምህርት ለንስሐ ለስጋ ወደሙ በቃው እደጁ ያወቁኝ እናት በግል ሆቴላቸው ቀጥረውኝ ጥሩ ደሞዝ አገኛለው ከዝናብና ብርድ ዳንኩኝ ትላንት በበዓሉ ግቢው በእልልታ ስታቀልጥ ነበህ እህታችን እኔን የዳበሰ የዮሐንስ አምላክ ሁላችሁን ይዳብሳችሁ ትላለች አሜን
ተአምር በ አቡነ ገብረ መንፈስ ቅዱስ ቤተ ከርስቲያን /ሽሬ/
Thursday, July 7, 2016
Wednesday, July 6, 2016
መጥምቁ ዮሐንስ ከዘመኑ እሳት አወጣኝ
አጸደ ማርያም እህታችን በአዲስ አበባ አንድ ጭፈራ ቤት ውስጥ በዘፋኝነት ትሰራ ነበር የስራ ባልደረባዋ በኤችአይቪ በሽታ ተይዛ
ወደ ሸንኮራ ጸበል ትሄዳለች አጸደ ማርያም እህትዋን ለመጠየቅ ሸንኮራ ወርዳ ሳለ የዮሐንስን ታሪክ አንገቱም በዘፈን ምክንያት እንደተቆረጠ ትሰማለች ይልቁንም ጉዋደኛዋ ያቀረበችላት የተመርመሪ ጥያቄ ያስጨንቃታል አዲስ አበባ መጥታ ስትመረመር የHiv ቫይረስ በደምዋ ይገኛል ደጋግማ ከ3ወራት ቆይታ በሁላ ስትመረመር ለውጥ የለም በመጨረሻ ወደ ሸንኮራ ዮሐንስ ጸበል በመምጣት ንስሐ ገብታ ጸበልዋን ለ1 አመት ስትከታተል ቆይታ ድጋሚ ለምርመራ ስትመጣ ደምዋ ንጹህ እንደሆነ ይነገራታል በስእለትዋ መሰረት ስጋ ወደሙ ተቀብላ ከቀደመው ህይወትዋ እራስዋን አግላለች መጥምቁ የፈወሳት በሽታዋ ብዙ ነው ከዘፋኝነት 13 አመት ሲጋራና ጫት ስትወስድም ነበር ከዝሙት መንፈስ ከጥንቁልና አምልኮ ተላቃለች ያቁዋረጠችውን ትምህርት ቀጥላ ሸንኮራ ባወቀቻት እህት እርዳታ ድግሪዋን ይዛ ትዳር መስርታ ልጅም ወልዳ አዲስ አበባ ቃሊቲ አካባቢ ትኖራለች ያችም ቀድማ የታመመች እህታችን በሽታዋ ድና ሰሜን ወሎ አንድ ገዳም ውስጥ በምናኔ ትኖራለች ክብር ለዮሐንስ
ለክርስትና ስጦታ መተት በአሻንጉሊት ተቀብሮ የተሰጣት እናት - ድንቅ ተዓምር
Friday, June 17, 2016
የሽንቁሩ ቅዱስ ሚካኤል ጠበል ድንቅ ተአምር
እባክሆን ይህን ያላመነ የሚያምንበት ያመነ የሚፅናበትን ተአምር ለወዳጅ ዘመድዋ ያድርሱል...!!!
በስመአብ በወልድ በመንፈስ ቅዱስ አሃዱ አምላክ አሜን
ደዌ ለፈተናም በ ሀጢያት ምክንያትም በብዙ ብዙ ምክንያት ይመጣል እግዚአብሄር አምላክ ፈቅዶ በቸርነቱ ይህን አደረገልኝ እንጂ እንደኔስ ሀጢያት ሌላም በተገባኝ ነበረ ለበሽታዬ ምክንያት ሀጢያት እንደሆነ ስለገባኝ እግዚአብሄርን እየተመላለስኩ በ እንባ ይቅርታ መጠየቅ ጀመርኩ።
ያልሄድኩበት ፀበል ያልያዝኩት ሱባኤ አልነበረም ነገር ግን (የ እግዚአብሔር ምህረት በጊዜዋ ነው ብሎ ነብዩ ቅዱስ ዳዊት እንደተናገረ ሁሉ በመጨረሻ የ ሽንቁሩ ቅዱስ ሚካኤልን ታምር እና ዝና ሰምቼ ወደ ሽንቁሩ መጣሁ እንደቦታው ስርአት ንስሀ ገብቼ ፀበሉን ተጠምቄ መጠጣት ስጀምር ፀበሉን ከጠጣሁ ቡሀላ ባሉ 5 ደቂቃዎች ውስጥ ከሆዴ ውስጥ በስርአት የተከተፈ ስጋ
የሚመስል ነገር ይወጣ ነበር።
በሁኔታው ስደናገጥ በቦታው የቆዩ ፀበልተኞች አይዞህ ይሄ የሚወጣው መርዙ ነው በርታ ይሉኛል ቆይቶ አረንጉዋዴ ፈሳሽ ከሆዴ ወጣ ከዛቡሀላ ከበሽታዬ ሙሉ ለሙሉ ተፈውሻለሁ እኔን የረዳ እናንተንም ይርዳ አሜን።
ይህ የምትመለከቱ ምስል ወንድማችን ባለፈው የሽንቁሩን ደብረ መድሀኒያአለም ቅዱስ ሚካኤል ቦታ ጠይቆኝ በሙሉ እምነት በመሄድ ዕፀበሉ ቦታ በመሄድ ንሰሃ ገብቶ ካንተ በቀር ማንም የለኝ ብሎ በበሽታው ሲጨነቅ ሲጠበብ ይሄው እንደምታዩት ለዘመናት ሲያሰቃየው የነበረውን በሽታ በቅዱስ ሚካኤል ሀይል ፀበሉን በመጠጣት ይሄን ከሆዱ ውስጥ አውቶለታል።
እውነት እንደ ዛሬ የተደሰትኩባት ቀን የለችኝ የሰው ልጅ ስቃይ ሲፈታ ከማየት የበለጠ ምን ደስታ አለ።እንግዲህ እኛ የምናመልከው የምናምነው ፀበል ይሄ ነው ታምሩ ኦርቶዶክስ በማንኛውም በምታደርገው ነገር አትሳሳትም።
ወንድሜ ከዚህ በላይ ታምሩን ለመናገር ያብቃ ለእርሱ የደረሰ አምላክ ስንት በየቤታችን የሚሰቃዩ ያልጋ ቁራኛ ሆነው የሚሰቃዩ እህት ወንድሞች አሉን በምህረቱ አይን ይጎብኝልን።
ታምሩን ሼር በማድረግ ይተባበሩን ሁላችንም ለደጁ አብቅቶ ታምሩን ለመስከር ያብቃን ይችን ቀን በጉጉት እጠብቃት ነበር በእውነት ለእግዚአብሄር የሚሳነው ነገር ምን አለ።

የቅድስት አርሴማ ተአምር
እግዚአብሔር ክብር ምስጋና ይድረሰው የሰማእቷ የቅድስት አርሴማ ተአምር ለኔም አርጋልኛለች ላገኘሁት ሉ ተአምራቷን መሰክራለሁ ፍሬሕይወት ለማ እባላለሁ ምኖረው ለንደን ነው ቤተሰቦቼ ይርጋለም ነው ሚኖሩት በየጊዜ እነሱን ለማየት ስሄድ ፀበሏን እየተጠመኩ ነው ምመጣው
ብዙ ነገሮችን አርጋልኛለች የአህኑ ተአምር ግን እናቴ ታመመችብን ስራ ፍቃድ ብጠይቅ አልተሰጠኝም ጠዋት ማታ በፀሎት
አምላኬን እየለመንኩ እናቱን እመቤቴን አማልጅኝ እያልኩ ሰማእቷን እየለመንኩ ልክ ፋሲካ እሁድ ሊሆ ሁለት ቀን ሲቀረው ፍቃድ ተሰጠኝ እናቴም አዲስአባ ቤቴል ሆፒታል ለሁለትሳምንት ከትቆየች በሗላ ወደይርጋለም ተመልሳ ቤት
ተኝታለች ቅኝ እጇና እግሯ እይቀሳቀስም ቤት ሆኗ ፀበሉን ህክምናውንም እየተከታተለች ነው እኔም ለ20 ቀን ፍቃድ
ተሰጥቶኝ ልክ የፋሲካ እለት ማታ ተሳፍሬ ሰኞ ጠዋት አዲሳባ እንደገባህ ቀጥታ ወደይርጋለም ሄድኩ አርሴማ ፀበል
እናቴን ይዠ የተወሰነ ቀን ተጠመቅን መሄጃዪ ደረሰና ልክ አውሮፕላን እንደተሳፈርኩ በቀኝ በኩል ጎኔ ላይ ጠዘጠዘኝ
ስነካው ብጉር ይመስላል አበጥ ብሎአል በማግስቱ በጣም አበጠ ህመሙ ህይለኛ ስለነበር ፋርማሲ ቅርቤ ስለነበረ ሄጄ
ሳሳያቸው ሆስፒታል ሂጂ አለኝ እኔም ስራ መግባት ስላለብኝ ወደቤቴ ተመልሼ ከይርጋለም አርሴማ ያመጣሁት ማር ነበረኝ
ቅብት አድርጌው ፕላስተር ለጥፌበት ስራዪ ሄድኩ ህመሙ የት ደረሰ ሳልል ጠፋ ቀኑን ሙሉ ምንም ህመም ሳይሰማኝ ዋለ
ስነካው ግን እብጠቱ እንዳለ ነው ህመሙ ስለተወኝ አርሴምዬን በልቤ እያወደስኩ ስራ ጨርሼ ማታ ቤቴ ገብቼ ፀሎቴን
አድርሼ ፕላስተሩ አነሳሁትን ያበጠውን ነካ ሳረገው ነፍስ ያለው የሚንቀሳቀስ ነጭ ትል ተፈትልኮ ወጣ
አርሴምዪ በፀበሏ ቀጥቅጣ በማሯ ፈንቅላ በሽታዬን አወጣችልኝ ለእናቴ ሄጄ እኔ ተፈውሼ መጣሁ የቅድስት እርሴምዬ ገድሏ ታምራቷ ብዙ ነው የወጣውን ትል ቪድዮና ፎቶ ለብቻው ልኬአለሁ የሰማእቷ በረከት ይደርብን
Thursday, June 16, 2016
የቅድስት አርሴማ ተአምር
የ
ሰማዕቷን የቅድስት አርሴማ ተአምር ልንገራችወ ፎቶዉ ላይ የ ሚታይዋት ታላቅ እህቴ ፋቅረ ማርያም ትባላለች በዝህ
አመት በ ቡዳ መንፈስ ስትሰቃይ ነበር ነገር ግን በ አለም ላይ የተወከለችዉ ሰማዕቷ እኛም ቤት መጣች በ ሚያዝያ
ወር በ ቀን 9ከ ምሽቱ 4 ሰዓት አከባብ እህቴ ታመመች ቤት ዉስጥ ከ ታናሽ ወንድሜ አብሮን ልያድር ከመጣዉ ከ
አጎቴ ልጂ እና ከ እኔ በቀር ሌላ ማንም አልነበረም ግራ ገባን ጎሬበት ተጠራ ሰዉ ተሰበሰበ ( ጠናዳም ግዛዋ...)
አጠኗት መንፈሷ ወድያዉ መለፋለፋ ጀመረች የመጀመርያ ቃሏ ግን "አርሴማ ምታቃጥለኝ አንሶነዉ እናንቴ
ምታቃጥሉኝ"የምል ነበር ካህን ተጠራ ተፀበለች የት እንዳየቻት በ ጥርሷ እንደገባች
እና ማንነቷን ተናገረች የን ዕለት በማግስቱ ከ ረፋዱ10 ሰዓት ላይ እለካታለዉ ብላ ተገዝታ ወጣች በዝህ ሁኔታ
እስከ ማክሴኞ ቀጠልን ዕረቡ ዕለት ልክ ከ እረፋዱ 10 ሰዓት ላይ ጀመራት ያለን አማራች ቦንጋ ሄዳ እንድትፀበል
ማድረግ ነበር ለ እናታችን ተደዉል ተነገራት እና ለመጨረሻ ጊዜ ቤት ተፀብላ እናታችን ይዛት ወደ ቦንጋ ሄዱ ከዛም
አባታችንም እዛዉ ቦንጋ ክዳነምህረት ፀበል እየተፀበለ ስለነበር ከሱጋር እዛዉ እንድትፀበል ታስቦ በማግስቱ ወደዛዉ ሄዱ ከተፀበለች በዋላ ግን ክዳነምህረት ወደ ቅድስት አርሴማ ላከቻት ምክኛቱም ሁሉም ሰማዕታት የወከሏት እሷን ስለሆነ ነዉ ከዛንቀን ጀምሮ እዛዉ ሰማዕቷ ገዳም ገብታ መፀበል ጀመረች በየቀኑ ስንደዉል የ ምንሰማዉን ነገር ማመን ከበደን ለካ በ እህቴ ላይ አድራ ቤታችንን ልታፀዳልን ነበር በቅናት መንፈስ ተነሳስተዉ እህቴ እንድታብድ በተሰቦቻችን እንዳይስማሙ በ እያንዳዳችን ላይ ታስቦ የተሰራ ተንኮል ነበር ድመት ገለዉ በ 7 ምስማር ወጥረዉ በ ቤታችን ጓሮ እንደተቀበረ እና እሷ እንደምታወጣልን ሰማዕቷ በ እህቴ ተመስላ ነገረችን በዝህ ሁኔታ መፀበሏን ቀጠለች ከ ጥርሷ1ጠጠር ወጣ ከዛም እዛዉ እያለች ሰሞነ ህማማት ደረሰ ሰማዕቷ መንፈሷን ገዝታ በቀጠሮ ማለትም እሰከ ሰኔ ስድስት እንዳትመለስ አዘዘቻት ነገር ግን "ህማማቱን እስከ ስቅለት ልጄ ከነጋር ደጄ ትስገድ " አለች ሌላም ትዛዝ " ልጄ መነፅር ትጠቀም በዛ መነፅር ላይም ሀይሌ ያርፍበታል ሰኔ 6 ምዛን ዉሰዷት ቀርዉ 6 ጠጠር እዛ ይወጣል " የምል ነበር እኛም በቃሏ መሠረት ይደረግ የተባለዉን ሁሉ አደረግን ፀሎተ ሐሙስ ከ ሰአት በዋላ ወደበት ተመለሰች በ አሉን በሰላም አሳለፍን የ ቀጠሮዉን ቀን መጠባበቅ ጀመርን በ መሀል ግን ሰማዕቷ ብዙ ታምሯን በ እኛቤት አደረገች ቁልፍ ጠፍቶብን ስንጨነቅ ለ እህቴ በ ህልሟ መታ ቁልፉ የት እንደ ወደቀ ነገረቻት ቁልፉን ከተባለዉ ቦታ አገኝነዉ ብቻ ብዙ ታምሯን እያየን ግኔቦት 8 ደረሰ አሁንም ቤት ዉስጥ ማንም አልነበረም እንደልማ ዳችን ተሰብስበን ተለቪዥን እያየን የ አጎቴ ልጂ እግሩን ተንተርሳ የ ሰማዕቷን ፎቶ እያየች ማልቀስ ጀመረች ምን እደሆነች ስንጠይቃት ፍቅርተ እንዳል ሆነች እና መንፈሷ እተገረፈች እደሆነ ገረችን ደነገጥን ካህን ልንጠራ ስናስብ " ማንንም እንዳጠሩ ፀበልም ካህንም አታምጡ ሴማዕቷ በ ዘንባባዋ እየገረፈችኝ ነዉ" አለች ተረጋጋን ልክ 3 ሰዐት ስሆን ፀሎት አደረገች በ መጨረሻም ሰማዕቷ ተመስላመታ እንዳንፈራ ና ሁሌም ከቤታችን እንደሆነች ነገረችን በሚግስቲም ቀጠለ 12 ስሆን ምካኤል ገረፋት በ 13 ሰማዕቷ በ14 አቡነ 16 ክድዬ እያለ እስከ ቀን 4 ቆየ ልክ ከ ለልቱ 9 ሰዓት ላይ ተቀብሮ የ ነበረው የጠላት ስራ በ ሰማዕቷ ትዛዝ መሠረት እንደምታዩት ከነ ምስማሩ ወጣ በቀን 5ወደ ምዛን ሄዱ ስሄዱ ፀበሉ መዘጋቱ ያዉቁ ነበር ግን በዛ ምትክ ወደ እመቤታች በቴክርስትያን እንድሄዱ ታዘዙ ከዛም ሰማዕቷ ተመስላ ስለ ፀበሏ መዘጋት አለቀሰች ምዕመኑም አብሯት አለቀሰ እንሆ ዛሬ የመጨረሻዋ ቀን 7 በማያልቀዉ ፈዉሷ የ ቀረት 6 ጠጠሮች ወተዉ እርኩስ መንፈስ ተቃጥሎ ኤህቴ ተፈወሰች ቤታችን ሰላም ገባ ክብር ለ መድአንአለም የኛን ሰላም የ መለሰችልን ሳሰለች የፈወሰችን ቅድስት አርሴማ በ ሁላችዉም ቤት ትግባ ወስበአት ለ እግዝአብሔር!!!

አንዲት እህት ከሆዷ ውስጥ ጥቁር ወፍ ወጣላት
Monday, June 13, 2016
ተነግሮ የማያልቀው የሸንኮራ ዮሐንስ ድንቅ ተአምር
ስለ ሸንኮራ ቅዱስ ዮሐንስ ጸበል ምን ያህል ያዉቃሉ?
የሸንኮራ ዮሐንስ ፀበል በአማራ ክልል በሰሜን ሸዋ ዞን በምንጃር ሸንኮራ ወረዳ ንዑስ ከተማ በሆነችዉ በባልጪ ከተማ አጠገብ በርካታ ተገልጋዮች ከተለያዩ ቦታዎች በመምጣት ፈውስ የሚያገኙበት ፀበል ነው፡፡
ፀበሉ በፈዋሽነቱ በይፋ መታወቅ የጀመረዉ:-
አባ ካሳ የሚባሉ መናኝ ባህታዊ በሸንኮራ ቅ/ዮሐንስ ቤ/ክ መቃብር ቤት ዉስጥ ዘግተዉ ይኖሩ ነበር፡፡
ከእለታት አንድ ቀን በህልማቸዉ ከቤተ ክርስቲያኑ በስተምስራቅ ከወንዙ ዉስጥ ጸበል ፈልቋልና ወርደህ አይተህ
ለህዝቡ ንገር እዉራን የሚያበራ፣ ለምፅ የሚያነፃ፣ ጎባጣ የሚያቀና ጸበል ፈልቋል በልና ንገር ብሎ በህልማቸዉ ነገራቸዉ፡፡
ሲነጋ ጠዋት በተነገራቸዉ መሰረት ወደ ወንዝ ወርደዉ ጸበሉን ሲፈልጉ አላገኝ አሉት፡፡ አባ ካሳ የዕድሜ ባለፀጋ ሲሆኑ ሲፈልጉ ዉለዉ በድካም ወደ ቤታቸዉ ተመለሱ፡፡ እንደገና ሌሊት በህልማቸዉ "ጠዋት ተነሣና ወደ ጸበሉ ዉረድ ጸበሉ ከጫካ ዉስጥ ፈልቆ ታገኘዋለህ ከፊ ከፊትህ የምትመራህ ርግብ ታሳይሃለች"አላቸዉ፡፡ በታዘዙት መሰረት ከጠዋት ተነስተዉ ወደ ወንዝ ሲሄዱ ርግብ ከፊት ከፊት እየመራቻቸዉ ከወንዙ ዉስጥ ሲደርሱ ጸበሉ ከፈለቀበት ገደል ላይ ክንፏን ዘርግታ አረፈች፡፡ከዚያም አባ ካሣም እግዚአብሔርን አመስግነዉ የፈለቀዉን ጸበል ጠጥተዉ እግራቸዉን ክፉኛ በሽታ ያማቸዉ ስለነበር ጸበሉን ሲያስነኩት ከያዛቸዉ በሽታ ወዲያዉኑ ተፈዉሰዋል፡፡ ከዚህ በኋላ አባ ካሳ የፈለቀዉን ጸበል ለህዝቡ ነግረዉ ሚያዝያ 30 ቀን ታቦተ ህጉ ወደ ጸበሉ ወርዶ በደማቅ ሁኔታ ተክብሯል፡፡ ይህንን ራዕይ ያዩት ሚያዝያ 15ቀን 1654 ዓ.ም ገደማ ሲሆን 354 ዓመት ያስቆተረ ጸበል ነዉ ተብለዉ ይገመታል፡፡ የቅዱስ ዮሐንስ በረከት ከሁላቸን ጋር ይሁን አሜን ።
ቤቱ ከአፋፍ ላይ ጸበሉ ከጅረት የድውያን ዳባሽ መጥምቀ መለኮት የስሙ ትርጉዋሜ ፍስሐ ወሐሴት በልደቱ የፈታ የአባቱን አንደበት እማሆይ ሂሩተ ገብርኤል ይባላሉ ተወልደው ያደጉት እዚሁ አዲስ አበባ ነው ትምህርታቸውን ጨርሰው ዮንቨርስቲም የሁለተኛ አመት ተማሪ ሳሉ በደረሳቸው መለኮታዊ ጥሪ በምናኔ ወደ ገዳም በመግባት ለ5 አመታት አገልግለው ደጅ ጠንተው በገዳሙ ማህበር ፈቃድ ምንኩስናቸውን ተቀብለው አገልግሎታቸውን በሰፊው በመስጠት ላይ ሳሉ ድንገት ባላሰቡት ሁኔታ በጡት ካንሰር በሽታ ይለከፋሉ አዲስ አበባ ለህክምና በመምጣት በጥቁር አንበሳ ሆስፒታልና በሌሎችም የግል ህክምና መስጫ ምርመራ ቢያደርጉም የታመመው አካል በአስቸኩዋይ ካልተቆረጠ ካንሰሩ ይሰራጫል ይባላሉ ህመሙ ከባድና ጽኑ ነበር በተለይ የጨረር ህክምና ተብለው የባሰ ተሰቃዮ እማሆይ ምርር ብለው ያለቅሳሉ ገና በማለዳ ነፍሴን ለገነት ስጋዬን ለአራዊት ብዬ መንኜ እንዴት ገላዬ ተገልጦ ክብሬ ይቃለላል ይህስ እንዲሆን አምላኬ ለምን ፈቀድክ ብለው ያዝናሉ የታመመ አካላቸውን ለማስቆረጥ ቀጠሮ ይይዛሉ እማሆይ እንደተናገሩት ፒያሳ አካባቢ ነዳይ መስለው ተሰውረው የሚኖሩ ባህታዊ ከጊዮርጊስ ቤተክርስቲያን ስወጣ "ሸንኮራ ዮሐንስ ሂጂ አንቺ ፈላሲ "ይሉኛል የምን እብድ ነው ብዬ አለፍኩት ክንክን አደረገኝና ተመልሼ ባይ ጠፉብኝ ልቤ ተነሳሳ ስቃዮ ደግሞ ረፍት ነሳኝ ደምና መግል ከታመመው አካሌ ይወርዳል እንደምንም ሸንኮራ መሪ ሰው ይዜ ገባው እምነቱን ጸበሉን ስቀባው ከረምኩኝ ይፈስ የነበረው የደም ጎርፍ ጠፋ ህመሜም ቀነሰ እንቅልፍም በደንብ እተኛ ጀመር ሰላሜ ተመለሰ የቀጠሮውም ቀን አለፈ ፍጹም ጤነኛ ሆንኩኝ የአይነ ከርሙ ባህታዊ ነብየ ልኡል ሰማእቱ መጥምቁ የጌታዬ የአምላኬ ወዳጅ በአድያመ ዮርዳኖስ በሸንኮራ ምድር በስሙ በፈለቀው ጸበል ጡቴን ከመቆረጥ አዳነኝ ዳግም ተመርምሬ ፍጹም ጤነኛ ነሽ ተብያለው ወደምወደው ገዳሜ በደስታ ተመልሻለው ብለዋል እናታችንይህን ያደረገ የዮሐንስ አምላክ ክብር ይግባው ይግባው ከኛም የማይበጀንን ነገር ቆርጦ ይጣልልን አሜን

Thursday, June 9, 2016
ተአምራት በሸንኮራ ደብረ መንክራት ቅዱስ ዮሐንስ - 2
በሸንኮራው ቅዱስ ዮሐንስ ጸበል እጹብ ድንቅ ተአምራት የተደረገላቸው ግብጻዊትዋ እናቴ
ወ/ሮ ናዲያ ሁለተኛዋ እናቴ ኢትዮጵያ አቡነ ዘበሰማያት ብለህ እራይ የምታይባት ቅድስት ምድር ናት የሚሉ ከ40 አመት በላይ የሚኖሩት እዚሁ አዲስ አበባ ነው እኔ የማውቃቸው አፍ ከፈታው ከህጻንነት እድሜዬ ጀምሮ ነው በአፍሪካ ህብረት ከወላጅ እናቴ ጋር ረጅም አመት ሰርተዋል ዛሬም በመስራት ላይ ይገኛሉ እኝህ እናት ግብጽ ደማንሁር የምትኖር አብሮ አደግ እህታቸው በማህጸንዋ ውስጥ ምን እንደሆነ ያልታወቀ ነገር ተገኝቶ ለ5አመታት ስትሰቃይ ልጅ ነው አንዳንዴምን እጢ ነው ስትባል በመጨረሻ ወደ አውስትራሊያ ሄዳ ኦፕራሲዮን ብትደረግም ምንም ማህጸንዋ ውስጥ አልተገኘም በቅድመ ምርመራ ዶክተሮቹ ምንነቱ ያልተለየ ነገር አለ መውጣት አለበት ብለው ነው የከፈትዋት በመጨረሻም ወደ ግብጽ ተስፋ ቆርጣ ተመልሳ ሳለ ወ/ሮ ናዲያ የቀድሞውን ፓትርያርክ አቡነ ጳውሎስን ከቅድስት ስላሴ ቀዳሽ እያሉ ከ60ቹ ጀምሮ ይተዋወቃሉና ቡራኬ ለመቀበል ሄደው ችግራቸውንም አውርተው ሲጨርሱ ፓትርያርኩ የዮሐንስን ጸበል ላኩላት ብለዋቸው ኖሮ እኔን ይጠይቁኛል ግዜ ስላልነበረ ከወ/ሮ ሳባ ሐብቶም ቤት ጸበሉን ተቀብዬ ሰጠዋቸው ታማሚዋ ጸበሉ ግብጽ ደርሶ በቀመሰችበት ደቂቃ ያ ያሰቃያት ለሐኪሞች ከአእምሮ በላይ የነበረው ነገር እንደ ልጅ 5አመት ይዛው የተንከራተተችው ማህጸዋ ተከፍቶ የተሰወረው 2ኪሎ እጢ ወጣ እላይዋ ያደረው እርኩስ መንፈስም ታሪኩን ለፈለፈ ዛሬ እህታችን ትዳር ይዛ የ1 ልጅ እናት ሆና ካናዳ ትኖራለች መጥምቁንና ያከበረውን አምላኩን ሸንኮራ ድረስ መጥታ ደጁን ስማ ስጦታዋን አስገብታለች ለናዲያ ያደረገውን አስደናቂ ተአምር ወደፊት እናወራዋለን የመጥምቁ አምላክ ክብር ምስጋና ይግባው አሜን

የመጥምቁ ዮሐንስን ድንቅ ተአምር በህጻን አንደበቱ የመሰከረው ህጻን ፍቅረ ዮሐንስ ናዝሬት ከተማ ተወልዶ
ያደገው ይህ ልጅ ባጋጠመው የአጥንት ካንሰር ምክንያት በህክምና መፍትሔ ሲጠፋ ወላጅ እናቱ ወደሸንኮራ ዮሐንስ ይዛው
ትመጣለች ክብር ምስጋና ለዮሐንስ አምላክ ካርድ አውጣ ኤክስሬ ተነሳ መድሐኒት ግዛ የለ የመጥምቁ ጸበል የታመመ
እግሩ ሲመታው ያሰቃየው የነበረው በነቀርሳ(ካንስር)የተበላው አጥንቱ ስጋውን ዘንጥሎ ወጥቶ ጤናውን አግኝቶዋል ቆሜ
እራመዳለው ኩዋስ እጫወታለው ትምህርቴንም ጀምሬያለው ብሎ በህጻን በሚጣፍጥ አንደበቱ የወጣለትን አጥንት ይዞ
ከወላጅ እናቱ ጋራ ምስክርነቱን በአወደ ምህረቱ ሰጥቶዋል የዮሐንስ አምላክ ክብር ይግባው
Wednesday, June 8, 2016
ተአምራት በሸንኮራ ደብረ መንክራት ቅዱስ ዮሐንስ
ሸንኮራ ዮሐንስ ከአየር ላይ ሲታይ የገደሉ መሐል ጸበሉ ያለበት ነው ያች 8የማይበልጡ የጭራሮ ጎጆ የነበረች
መንደር ዛሬ የፈውስ መዲና ሆና ዘምናለች 20 ሰው የምትይዘው ቤተክርስቲያን ዛሬ ታላቅ ህንጻ ተገንብቶባታል
የነፍስም የስጋም ሆስፒታል ሆናለች አጥቢያዋ
አቶ በላይ ደምሴ የተባሉ አባት ከባሌ ክፍለሐገር
ሁለቱም ጆሮዋቸው መስማት አይችልም ነበር አባታችን የመጥምቁን የፈውስ ዝና ቢሰሙም ወደ ሸንኮራ ለመምጣት አቅም ያጣሉ አንድ በአካባቢያቸው የሚያውቁትን ወጣት ጸበል አምጣልኝ ብለው 500 ብር ለትራንስፓርት ሰጥተው ይሸኙታል ልጁ እዛው ሲያውደለድል ተደብቆ ከርሞ ከወንዝ ውሐ ቀድቶ ይሰጣቸዋል አቶ በላይም የተሰጣቸውን ውሐ በእምነት ሲጠጡት ጆሮዋው ተከፈተ ድንቅ ነው በዚያው ቅጽበት የወጣቱ ሁለቱም ጆሮ መስማት አቆመ ይህ ወጣት ጥፋቱን ያውቃልና በንስሐ አባቱ አማካኝነት ወደ ሸንኮራ መጥቶ ለነፍስም ለስጋው ንስሐ ገብቶ ቀኖና ተቀብሎ ይፍታህ በሚባልበት 14ኛ ቀኑ ላይ ጆሮው ተከፍቶ በአንደበቱ የሰራውን ጥፋትና የተደረገውን ድንቅ ተአምር መስክሮዋል ይህን ያደረገ የመጥምቁ አምላክ ክብር ይግባው አሜን
ወ/ሮ ሐዱሽ ገ/ዋህድ ይባላሉ ከገጠሪቱ ኢትዮጵያ 16 አመት የታወረ አይናቸውን ለመታከም ነው ወደ መሐል ሐገር
የመጡት አዲስ አበባ ኦፕራሲዮን ቢያደርጉም ተስፋ የለውም እንዲሁ ይኑሩ ይባላሉ ቤተክርስቲያን ለመሳለም ሄደው
የሸንኮራን ታሪክ ሰዎች ሲያወሩ ሰምተው አድራሻ ጠይቀው መሪ አስታማሚ ይዘው ጉዞ ወደመጥምቁ ቤት ተከራይተው ጸበሉን
መጠመቅ ይጀምራሉ 8ኛ ቀን ላይ ወደ ጸበሉ መውረጃ ገደሉን መንገድ ከመሪያቸው ጋር ይጀምራሉ መሪያቸው ድንገት ወደ
ጫካ ለሽንት ትገባለች እሳቸውም ከምቆም ብለው መንገድ ይጀመራሉ በምርኩዛቸው ድንገት ያላሰቡት ነገር ተከሰተ
የለበሱትን ነጠላ ቆንጥር ያዘብኝ መንገዱም ቁልቁለት ላይ ነበርና የያዝኩትምርኩዜም ከእጄ አምልጦ ተንሸራቶ ርቆ
ወደቀ በቆምኩበት ደነገጥኩኝ ተማረርኩኝ ሞቴን ተመኘው አዘንኩኝ ምነው ዮሐንስ ብዬ ነጣላዬን ከእሾኩ ለማላቀቅ ፊቴን
ሳዞር የጠፋው አይኔ ቦግ አለ ማመን አልቻልኩም እየተመራው የወረድኩትን ገደል ህዝቡን እየመራው በእልልታ በሆታ
ወጣውት ብለው መስክረዋል እኝህ እናት በወቅቱ ከደስታቸው ብዛት ግቢው ውስጥ ይንከባለሉ ነበር ይህን ያደረገ
የመጥምቁ አምላክ ክብር ይግባው አሜን
ሸንኮራን የሚያውቅ ሁሉ ለምንትዬ ዮሐንስ ምን እንዳደረገላት የማያውቅ የለም በስምዕ ጽድቅ ጋዜጣ በዜና
ቤተክርስቲያን በደብሩ መጽሔት ታሪክዋ በሰፊው ተመዝግቦዋል ስቃየ ብዙዋ እህታችን አዲስ አበባ ጎፋ መካነ ህያዋን
ቅዱስ ገብርኤል ሰንበት ተማሪ የሆነችው ምንትዬ ታሪክዋ ሰፊ ስቃይዋ ዘግናኝ ነበር አትተኛም አትቀመጥም አትራመድም
የዮሐንስ ያለህ ያዮ ይመስክሩ በልብ በኩላሊት በደም ብዛት እረ የበሽታዋ አይነት ብዛቱ መለኮትን ባጠመቀበት እጁ
ዮሐንስ የታሰረችበትን ደዌ ሁሉ ፈታት ከሰውነትዋ የሚወደው ደምና መግል ተወግዶ ሞትሽን ጠብቂ በሳጥር ተቁዋጥረሽ
ልትጣይ ነው የተባለችው ምንትዬ ይህው ዛሬ በእግርዋ ቆማ የመጥምቁን ደጅ ጥዬ አልሄድም ብላ እንግዳ ተቀባሪ
ጸበልተኛ አጉራሽ ሆናለች እስቲ ሰኔ 30 ኑና የመጥምቁን ታሪክ ጽናት ትእግስትዋን ተማሩ ህወታችሁን አለምልሙ
የምስጋናን ህይወት እንድትጀምሩ የቀጠሮ ሰው ይበለን አሜን
እናታችን ከባሌ ነው የመጡት ያወኩዋቸው ጫካ ጸበል ለመጠጣት ወጥቼ ነው ወይዘሮ ደሜ ይባልሉ ከንፈራቸው ላይ በወጣ
ቁስል ምክንያት መላ ፊታቸው ይቆስልና ሽታም ያመጣል በሐኪም ብዙ አቅሜን ጨረስኩኝ ጠንቁዋይም ገንዘቤን ጨረሰብኝ
የሸንኮራ ዮሐንስን ድንቅ ተአምር ሰማው ተነስቼ መጣው ጠረኔ ከሰው ስለማያቀላቅልና የቆሰለው ፊቴንም ደፍሮ የሚያይ
ስለሌለ ጫካ እውላለው ጸበልም ሰው ሳይኖር እወርዳለው አሉኝ በእውነት ዘግናኝ አጋጣሚ ነበር 8አመታት የተሰቃዮበት
ያ የቆሰለው ፊት እንደ ሰንኮፍ ውልቅ ብሎኝ በቁስል የነፈረው ከንፈራቸው ደርቆ ጠረን መአዛቸው ተለውጦ በዛ
ህመምተኛ በነበረ አንደበታቸው እልልታን ብቻ ሳይሆን ንስሐ ገብተው ስጋ ወደሙም ተቀብለው ብጽአታቸውን በእጃቸው
የፈተሉትን ግምጃ ስእሉን ሲጋርዱ አይቻለው እኝህ ምስኪን እናት ሸንኮራ ለጥቂት ሳምንታት ተቀምጠው ነው ፈውስን
ያገኙ ዛሬ በየአመቱ ሰኔ 30 ከደጁ አይቀሩም የኛንም ክፉ መአዛ አምላከ ዮሐንስ ያጣፍጥልን አሜን
በሸንኮራው ዮሐንስ ጸበል ከጡት ካንሰር የዳነችው
የአጥቢያችን ብስራተ ገብርኤል ነዋሪ ሳባ ሐብቶም እህቴም እናቴም የሆነችው ሳባ ወደ ሸንኮራ ከመሄድዋ በፊት በጽኑ ስቃይ በካንሰር በሽታ ትሰቃይ ነበር በወቅቱ የነበራት ስቃይ ከቃላት በላይ ነበር አቅሙም ነበራትና ያልደረስችበት ህክምና የለም በተለይ የግል ሐኪምዋ ፕሮፌሰር ታዬ እንዲሁም በጥቁር አንበሳ ብሩክ ክሊኒክ ህክምናዋን ብትከታተልም ካንሰሩ ወደ መላ አካላትዋ ተሰራጭቶ ሞትዋን ስትጠብቅ ወደ ምንጃር ሸንኮራ ጸበል በመምጣት ሸንኮራ በወቅቱ ጥቂት ጎጆዎች ብቻ የነበረባት ትንሽ መንደር ነበረች ከሞላ ቤትዋ ወጥታ የጭራሮ ጎጆ ተከራይታ ጸበልዋን ጀመረች ጽናትዋ ትእግስትዋ ይደንቅ ነበር ቅዱስ ዮሐንስ ደጅ ጥናትዋን ስቃይዋን ተመልክቶ ከአምላኩ አማልዶ በህልም በራእይ ሳይሆን በገሐድ በመገለጥ እንደዳበሳትና 4አመት በዘግናኝ ሁኔታ ያበጠው ሰውነዋ ፈንድቶ ብዙ ደምና መግል ከሰውነትዋ ወጥቶ ፈውስን ተቀዳጅታለች አዲስ አበባ መጥታ ተመርምራ ሙሉ ጤናማ መሆንዋን አረጋግጣለች ይህው 17 አመት ሆናት የቀብር ማስፈጸሚያ በርበሬ የተፈጨላት ጤፍ የተሸመተላት የንፍሮ እህል የተለቀመላት መግነዝ ጨርቅዋን ከቤት ብሞትም ብላ ይዛ የወጣችው ሳባ መጥምቁ ዳብሶ ፈውስን አግኝታ ለእንባ አድርቅ የታሰበው እህል ለዝክር ሆነንዋል ሳባቆማ ትሆዳለች በእለተ ፋሲካ በየአመቱ ቤትዋን በአወደ አመት ዘግታ የአክፋይዋን በመጥምቁ ደጅ ላሉ ካህናት ጸበልተኞች ነዳያን ይዛ ጾም ታስፈታለች መጥምቀ መለኮት ነብየ ልኡል እኛ ከማናውቀው የታሰርንበት ክፉ ነገር ይፍታን አሜን

ነቢየ ልኡል ሐዋርያው ሰማእቱ መጥምቀ መለኮት ድንግላዊው ባህታዊው ካህኑ ከሴት ከተወለደ የሚተካከለው የሌለ ቅዱስ
ዮሐንስ በልደቱ የአባቱን የታሰረ አንደበት የፈታ የስሙ ትርጉዋሜ የሁሉ ደስታ የሆነ ዛሬም በደዌ የታሰረውን በጸበሉ
የሚፈታ ቃልኪዳኑ ዛሬም ያልተሻረ በመጥምቁ ደጃፍ ያገናኘን በፎቶ የምናየው ወንድም በሸንኮራ ጸበል የተፈወሰ ነው
የቀጠሮ ሰው ይበለን አሜን
የቀጠሮ ሰው ይበለን አሜን
ፀበሉ ፈዋሽ ዘብር ቅድስ ገብርኤል
ምንጭ
Monday, June 6, 2016
Thursday, June 2, 2016
Wednesday, June 1, 2016
መጻሕፍቶቻችን ስለ ቅ/ያሬድ ምን ይላሉ?
መጻሕፍቶቻችን ስለ ቅ/ያሬድ ምን ይላሉ?
ኢትዮጵያ ተለይታ ከምትታወቅባቸው እና ቤተ ክርስቲያናችንም ለሀገሪቱ ካበረከተቻቸው ብዙ ነገሮች አንዱ ያሬዳዊ ዜማ ነው። የዚህ ልዩ ሀብት ጀማሪ የሆነው ግንቦት ፲፩ ቀን ክብረ በዓል የሚደረግለት ቅ/ያሬድ ኢትዮጵያዊ ቅዱስ፣ ካህን፣ ሊቅ፣ መዓርዒረ ዜማ፣ ደራሲ (የዜማ እና የመጻሕፍት)፣ የመጻሕፍት መምህር
፣ ባለቅኔ (በድጓው ውስጥ ያሉ
ቅኔዎችን መዘርዘር ይቻላል)፣ ሰማዕት (ያሬድ ማኅሌተ እግዚአብሔርን ሲያደርስ ንጉሡ ገብረ መስቀል ተመስጦ እግሩን
ስለወጋው ደሙን አፍስሷልና) ወዘተ. የሚሉት ስለ ክብሩ የሚቀጸሉ መጠሪያዎቹ ናቸው። ኢትዮጵያ ተለይታ ከምትታወቅባቸው እና ቤተ ክርስቲያናችንም ለሀገሪቱ ካበረከተቻቸው ብዙ ነገሮች አንዱ ያሬዳዊ ዜማ ነው። የዚህ ልዩ ሀብት ጀማሪ የሆነው ግንቦት ፲፩ ቀን ክብረ በዓል የሚደረግለት ቅ/ያሬድ ኢትዮጵያዊ ቅዱስ፣ ካህን፣ ሊቅ፣ መዓርዒረ ዜማ፣ ደራሲ (የዜማ እና የመጻሕፍት)፣ የመጻሕፍት መምህር
ቅ/ያሬድ ሲነሳ ሁሌም ቀድሞ በአእምሯችን የሚመጣው በኢትዮጵያ ውስጥ ዜማን የጀመረ መሆኑና ግእዝ፣ ዕዝል፣ አራራይ ብሎ በሦስት መደብ መክፈሉ ነው። ዜማው ከዛሬ 1500 ዓመታት በፊት ተጀምሮ እስከ ዛሬ ድረስ የማይሰለችና ልዩ መንፈሳዊ ሐሴትን የሚያጎናጽፍ ሰለሆነ በእርሱ ዜማ የመመሠገነው ልዑል አምላክ፣ አመሥጋኞቹ ካህናትንም ምድራውያን መላእክት የሚያሰኝ ነው። ቅ/ያሬድ ከመነሳቱ በፊት በኢትዮጵያ ውስጥ እንደ ውርድ ንባብ ያለ ትሑት ቃል እንጂ ምልክት ያለው በዜማ የሚደርስ ማሕሌት አልነበረም። ስለዚህ ዜማ ሲነሳ ያሬድ መጠራቱ አይቀሬ መሆኑን ሁሉም የሚስማማበት ነው። ሌላው የቅ/ያሬድ አስተዋጽኦ እና በብዙዎች ዘንድ የማይታወቀው ሥራው በኢትዮጵያ ውስጥ የመጀመሪያው ደራሲ እሱ መሆኑ ነው። እስካሁን በተደረገው ጥናት የኢትዮጵያ ጽሑፎች እስከ ያሬድ መነሳት ድረስ ትርጉሞች (በተለይ ከግሪክ ቋንቋ) ነበሩ። ብሔራዊ ድርሰትን (ሀገር በቀል) በኢትዮጵያ የጀመረ ያሬድ ነው። ለዛሬ የማቀርበው ጽሑፍ ቅ/ያሬድ የደረሳቸውን መጻሕፍትና የኋላ ሊቃውንት ስለ እርሱ ክብር የጻፉትን በመጠኑ ይመለከታል። (ስለ ሕይወት ታሪኩ በብዙ ቦታ ስለተጻፈ ብዙም አልዳስሰውም።)
በሀገራችን ከሚገኙት መጻሕፍት ስለ ቅዱስ ያሬድ የሚናገሩ መጻሕፍት በርካታ ናቸው፤ በጥቅሉ በሦስት ዋና ዋና ክፍሎች እንመድባቸዋለን። የመጀመሪያዎቹ ራሱ ቅ/ያሬድ የጻፋቸው የዜማ መጻሕፍት ሲሆኑ፤ ሁለተኛዎቹ ስለ ቅ/ያሬድ ክብር የተደረሱ የምሥጋና ድርሰቶች፤ ሦስተኞቹ የቅ/ያሬድን ታሪክ የያዙ ሌሎች መጻሕፍት ናቸው። ዝርዝራቸውን ቀጥሎ እንመልከት።
ሀ) እርሱ የጻፋቸው፤
ከላይ በመግቢያው እንዳልነው ቅ/ያሬድ የምሥጋና እና የአምልኮ መግለጫ የሆኑ የዜማ መጻሕፍትን በግዕዝ ቋንቋ ጽፏል። እነዚህም በስፋት የሚታወቁት አምስቱ የዜማ መጻሕፍቱና በታሪክና በትውፊት የተቀበልናቸው ሌሎች መጻሕፍት ናቸው። እነርሱም፥
1) ድጓ - ከቅ/ያሬድ ድርሰቶች ውስጥ ትልቁ የዜማ መጽሐፍ ድጓ ሲሆን በሦስት ዋና ዋና ክፍሎች የተከፈለና በቤ/ክ ከዓመት እስከ ዓመት የሚደርስ ምስጋና ነው። በተለያዩ ዘመናት የተገለበጡ የድጓ ቅጂዎች በኢትዮጵያ የሚገኙ ሲሆን አንዳንድ ጠቃሚ እና ትክ የማይገኝላቸው ቅጂዎች ከባሕር ማዶ ተሻግረው ይገኛሉ (ለምሳሌ ቫቲካን [Vat. Aeth. 28]፣ በርሊን [Orient. 1000])። በሀገራችን ከሚገኙት ዕድሜ-ጠገብ ድጓዎች መካከል በላሊበላ ቤተ-ጊዮርጊስ የሚገኘው (12ኛ መ/ክ/ዘ)፣ በጣና ቂርቆስ የሚገኘው (13 መ/ክ/ዘ)፣ በደብረ ብርሃን የሚገኘው (16ኛመ/ክ/ዘ)፣ የሐይቁ ድጓ (17መ/ክ/ዘ)) ይጠቀሳሉ። “መጽሔተ፡ ጥበብ” በመባል የሚታወቀው የቅ/ቤተልሔም (ደ/ጎንደር) ድጓ ለምስክር አብነት ነው።
2) ጾመ ድጓ - በዐቢይ ጾም የሚደርስ ምሥጋና ነው። ጾመ ድጓ በዋናው ድጓ (ከአስተምህሮ ድጓ) ክፍል ተካቶ ይገኛል። ክፍሉ በዓቢይ ጾም ውስጥ ባሉት ሰንበታት ልክ ሲሆን ተራቸውም፤ ዘወረደ፣ ቅድስት፣ ምኵራብ፣ መጻጕዕ፣ ደብረ፡ ዘይት፣ ገብር፡ ሔር፣ ኒቆዲሞስ እና ሆሣዕና የሚል ነው።
3) ምዕራፍ - ይህ የዜማ መጽሐፍ ከመዝሙረ ዳዊት የተውጣጡት ምሥጋናዎችን በመስመር በመስመር እየከፈለ የሚደርስ የስብሐተ እግዚአብሔር መጽሐፍ ነው።
4) ዝማሬ - ማሕሌት ሲቆም የሚደርስ ሆኖ በጊዜ ቅዳሴ ከድርገት በኋላ የሚቀርብ ምሥጋና ነው። ዝማሬ አምስት ክፍሎች ያሉት ሲሆን እነዚህም ኅብስት፣ ጽዋ፣ መንፈስ፣ አኮቴት እና ምስጢር የሚባሉት ናቸው። የዚህ የዝማሬና የመዋሥዕት ማስመስከሪያ ቤተ ጉባኤው ቅ/ያሬድ ባስተማረበት ቦታ በዙርአባ አረጋዊ ቤ/ክ (ደቡብ ጎንደር) ነው።
5) መዋሥዕት - ካህናት በተዋሥኦ (በመቀባበል) የሚያዜሙት ሲሆን በተለይ በጸሎተ ፍትሐት ጊዜ እና በቀዳም ሥዑር ዕለት የሚደርስ ምሥጋና ነው።
6) አንቀጸ ብርሃን - ቅ/ያሬድ ይህን የእመቤታችንን ምሥጋና ያደረሰው በአክሱም ጽዮን ቤ/ክ ውስጥ ከታቦተ ጽዮን ፊት ቆሞ ሲሆን ድርሳኑ ይህንን እንዲህ ይገልጻል “ወሶቤሃ፡ ቦአ፡ ያሬድ፡ ውስተ፡ ታቦተ፡ ሕጉ፡ ለእግዚአብሔር፡ እንተ፡ ይእቲ፡ ገበዘ፡ አክሱም፡ ወአንበረ፡ ፪እደዊሁ፡ ውስተ፡ ርእሰ፡ ታቦት፡ ወከልሐ፡ በልዑል፡ ቃል፡ እንዘ፡ ይብል፡ ቅድስት፡ ወብፅዕት፡ ስብሕት፡ ወቡርክት፡ ክብርት፡ ወልዕልት፡ አንቀጸ፡ ብርሃን፡ መዓርገ፡ ሕይወት፡ እስከ፡ ተፍጻሜቱ። ..... ።” ገድሉ እና ተአምሩ (ሦስተኛው) እመቤታችንን እየለመነ አንቀጸ ብርሃንን በዕዝል ዜማ ሲያደርስ ቁመቱ አንድ ክንድ ያህል (“ተለዓለ፡ መጠነ፡ እመት፡”) ከምድር ወደ ላይ ከፍ ይል እንደነበር መዝግበውታል። ለዚህ ጸሎት ምላሽ እመቤታችንም ተገልጻ በቃል ታናግረው ነበር።
7) የሦስት ቅዱሳንን ገድል ጽፏል፤ በትውፊት እንደሚታወቀው ቅ/ያሬድ ከዘጠኙ ቅዱሳን መካከል የሦስቱን ቅዱሳን ገድል ጽፏል። እነዚህም ገድለ አረጋዊ፣ ገድለ ጽሕማ እና ገድለ ይምአታ ናቸው።
8) ቅዳሴ - የታተሙት ቅዳሴያት 14 በብዛት ይታወቃሉ፤ ነገር ግን ያልታተሙ ሌሎች ስድስት ቅዳሴያትም አሉ፤ የቅ/ያሬድ ቅዳሴም ካልታተሙት አንዱ ነው።
ለ) ስለ ቅ/ያሬድ ክብር የተጻፉ
ከኢትዮጵያ ቅዱሳን ሊቃውንት ግንባር ቀደም የሆነው ማሕሌታይ ያሬድ በዜማ ደራሲነቱ በዓለም ደረጃ የሚታወቅ ሲሆን ካበረከተው ዘመን ተሻጋሪ ሥራ አኳያ ስናየው ግን ስለ እርሱ ክብር የተጻፈው አነስተኛ ነው። ድርሳን እና ገድል ተጽፎለታል ሆኖም በጣም አጫጭር ናቸው። እስካሁን ከተገኙት ውስጥ ዕድሜ ጠገብ የሆነው በሐይቅ ገዳም (ደቡብ ወሎ) ከሚገኘው “ገድለ ቅዱሳን” ውስጥ የሚገኘው “ድርሳን ወገድል ዘቅ/ያሬድ” ሲሆን የተጻፈበት (የተቀዳበት) ዘመኑም በ16ኛው መ/ክ/ዘ ነው። በሁለተኛ ደረጃ ጥንታዊ የሚባለው የቅ/ያሬድ ድርሳን እና ገድል በ17ኛው መ/ክ/ዘ/ የተጻፈው እና በሀገረ እንግሊዝ የሚገኘው ሲሆን፤ ሦስተኛው ደግሞ በዘመዶ ማርያም (ሰሜን ወሎ) የሚገኘው ሲሆን ዘመኑም በ18ኛው መ/ክ/ዘ ነው። በ19ኛው እና በ20ኛው መ/ክ/ዘ ሌሎች በርካታ ቅጂዎች በብዙ ቦታዎች ይገኛሉ። በውጭ ሀገር ከሚገኙት ቅጂዎች ውስጥ በፓሪስ ቤ/መጻሕፍት የሚገኘውን ገድል ኮንቲ ሮሲኒ የሚባል ምሁር ከግዕዝ ወደ ላቲን ተርጉሞ እ.ኤ.አ. በ1904 አሳትሞታል። ድርሳን፣ገድል፣ ተአምር እንዲሁም መልክአ ያሬድን ይዟል። ቀጥለን በዝርዝር እንመልከታቸው፤
1) ድርሳነ ያሬድ - ለቅዱስ ያሬድ ታሪክ ዋና ምንጭ ሆኖ የሚጠቀሰውና ከገድሉ ይልቅ ስፋት ያለው ድርሳኑ ነው። ሲጀምር እንዲህ ይላል፥ “በስመ፡ አብ፡ ወወልድ፡ ወመንፈስ፡ ቅዱስ፡ ፩አምላክ። ድርሳን፡ ዘቅዱስ፡ ያሬድ፡ ካህን፡ ቀርነ፡ ቤተ፡ ክርስቲያን፡ ዘይጼውዖሙ፡ ለመሃይምናን፡ ከመ፡ ይሴብሕዎ፡ ለእግዚአብሔር፡ በክላሕ፡ ወበዓቢይ፡ ቃል፡ ከመ፡ ሱራፌል። ....”
2) ገድለ ያሬድ - የቅ/ያሬድን የሕይወት ታሪኩንና ተጋድሎውን ዜና በአጭሩ የሚዘክር ሲሆን ሲጀምር እንዲህ ይላል፥ “በስመ፡ አብ፡ ወወልድ፡ ወመንፈስ፡ ቅዱስ፡ ፩አምላክ። ገድል፡ ወስምዕ፡ ዘቅዱስ፡ ወንጹሕ፡ ወብፁዕ፡ ወኅሩይ፡ ያሬድ፡ ካህን፡ ጸሎቱ፡ ወበረከቱ፡ ወሀብተ፡ ረድኤቱ፡ የሀሉ፡ ምስሌነ፡ ....”
3) ተአምረ ያሬድ - ካህኑ ያሬድ የፈጸማቸው ገቢረ ተአምራት በርካታ ቢሆኑም በገድሉ ላይ ተመዝግበው የምናገኛው ግን ሦስት ናቸው።
4) መልክአ ያሬድ - የኋላ ሊቃውንት ስለ ቅ/ያሬድ ክብር እንዲሆን “መልክእ” ደርሰውለታል። ሲጀምር እንዲህ ይላል፥ “በስመ፡ እግዚአብሔር፡ ሥሉስ፡ ዘበሰማያት፡ አቡነ። በምግባር፡ ወግዕዝ፡ ዘወለደነ። ያሬድ፡ ወጠንኩ፡ ለመልክእከ፡ ድርሳነ። አብርህ፡ ኅሊናየ፡ ወዘልብየ፡ ዓይነ። ወበልሳንየ፡ ጸሐፍ፡ ሐዲሰ፡ ልሳነ።” ... ይህ መልክእ በብዙ ቦታ የሚገኝ ሲሆን እኔ ማስተያየት የቻልኩት ፓሪስ ከሚገኘው እና ኮንቲ ሮሲኒ (1904) ካሳተመው ነው።
5) የግንቦት ፲፩ ስንክሳር ንባብ - የግዕዙ ስንክሳር (እንዲሁም የባጅ - እንግሊዝኛ ትርጉም 1928፣ የኮሊ - የፈረንሳይኛ ትርጉም 1997፣ የትንሣኤ ማሳተሚያ ድርጅት ሕትመት - የአማርኛ ትርጉም 1993 ዓ.ም.) ስለ ቅ/ያሬድ ሕይወት ይዘረዝራል። ሲጀምር እንዲህ ይላል፤ “ወበዛቲ፡ ዕለት ካዕበ፡ አዕረፈ፡ ያሬድ፡ ማኅሌታይ፡ አምሳሊሆሙ፡ ለሱራፌል። ወዝንቱ፡ ቅዱስ፡ እምአዝማዲሁ፡ ለአባ፡ ጌዴዎን፡ ውእቱ፡ እምካህናተ፡ አክሱም፡ ....”
6) ነግሥ ዘያሬድ - ለቅ/ያሬድ ካተደረሱት የ“ነግሥ” ምሥጋናዎች መካከል አንዱ አባ ጊዮርጊስ ዘጋሥጫ የደረሰው ብሎ ይጀምራል፥ “ያሬድ፡ ቀሲስ፡ መዓርዒረ፡ ዜማ፡ ማኅሌታይ። መዓንዝር፡ ከመ፡ ወልደ፡ ዕሴይ። .....” ሁለተኛው ደግሞ አፄ ዘርአ ያዕቆብ የደረሰው ምሥጋና ሲሆን እንዲህ ይላል “ሰላም፡ እብል፡ ለያሬድ፡ ቀሲስ፡ ምሉዐ፡ መንፈስ፡ ለኢትዮጵያ፡ ነደቀ፡ በሃሌ፡ ሉያ፡ ምድራስ። አስተባልሐ፡ ደቂቃ፡ በዜማ፡ ሠላስ። መኃልይሁ፡ ውዱስ። በስብሐት፡ ሐዲስ።”
7) አርኬ - ፓሪስ የሚገኘው (ኮንቲ ሮሲኒ ያሳተመው) እና በትንሣኤ ማሳተሚያ የታተመው የስንክሳሩ አርኬ ስለ ቅ/ያሬድ ምሥጋናውን እንዲህ ብሎ ይጀምራል - “ሰላም፡ ለያሬድ፡ ስብሐተ፡ መላእክት፡ ለሕዋጼ። እንተ፡ አዕረገ፡ በልቡ፡ ሕሊና፡ መንፈስ፡ ረዋጼ።...”። በ17 መ/ክ/ዘ የተጻፈውና ለንደን (ብሪቲሽ ቤ/መ) የሚገኘው የስንክሳር አርኬ እንዲህ ይላል፤ “ሰላም፡ ለዝክረ፡ ስምከ፡ ዘተጸውዖቱ፡ መዓር።...”
ሐ) ስለ ቅ/ያሬድ የሚያስረዱ ሌሎች መጻሕፍት
1) ገድለ አረጋዊ - ከላይ እንዳየነው በትውፊት የገድለ አቡነ ጸሐፊ ቅ/ያሬድ እንደሆነ ይነገራል። የታተመው ገድለ አረጋዊ የጸሐፊነቱን ሚና ለሌላ ይሰጠዋል፤ ሁለቱን ሃሣቦች ስናገናዝባቸው ሊሆን የሚችለው መጀመሪያ ያሬድ ጽፎት በኋላ ሌሎች ገልብጠውታል ማለት ነው። ወደ ገድለ አረጋዊ ስንዘልቅ በርካታ ቦታዎች ላይ የቅዱስ ያሬድን ታሪክ መዝግቦት ይገኛል። ያሬድ በዘመነ ገብረ መስቀል ማሕሌቱን እንደጀመረ፣ ድርሰቱን ከብሉይ ከሐዲስ እንዳውጣጣው፣ ዜማውን ከመላእክት እንደሰማው፣ ወዘተ.... ይዘረዝራል። እንዲሁም ወደ ደብረ ዳሞ ወጥቶ ሕንጻ ቤ/ክ ሲመለከት “ወከልሐ፡ በቃለ፡ መዝሙር፡ ወይቤ፡ ይሔውጽዋ፡ መላእክት፡ እስመ፡ ማኅደረ፡ መለኮት፡ ይእቲ፡ ዖድክዋ፡ ዖድክዋ፡ ዖድክዋ፡ ወርኢኩ፡ ሥነ፡ ሕንጼሃ፡ ለቅድስት፡ ቤተ፡ ክርስቲያን።” ብሎ እንደዘመረ፡ ይናገራል።
2) ድርሳነ ዑራኤል - የቅ/ያሬድን ታሪክ ከያዙት የቤ/ክ መጻሕፍት መካከል አንዱ ድርሳነ ዑራኤል ሲሆን እመቤታችን ተገልጻ ቅ/ኤፍሬምንና አባ ሕርያቆስን “ዜማ እንዲደርስልኝ ውዳሴዬንና ቅዳሴዬን ለያሬድ ስጡት” ብላ እንዳዘዘቻቸውና ቅ/ያሬድም በተሰጠው ሀብተ ዜማ እንደዘመረ ይናገራል። ለቅ/ያሬድ ጽዋዓ ልቡና ያጠጣው መራሔ ብርሃናት ዑራኤል እንደሆነ ድርሳነ ዑራኤል ይገልጻል።
3) መጽሐፈ አክሱም - ይህ መጽሐፍ የአክሱም ጽዮንን ታሪክ እና የርስት ጉልቷን ሥሪት የሚናገር ሲሆን ስለ ቅ/ያሬድ ዜማ ድርሰት ይናገራል። እንዲሁም ከላይ በድርሳነ ዑራኤል የተገለጸውን ታሪክ (እመቤታችን ተገልጻ ቅ/ኤፍሬምንና አባ ሕርያቆስን “ዜማ እንዲደርስልኝ ውዳሴዬንና ቅዳሴዬን ለያሬድ ስጡት” ያለችውን) መዝግቧል።
4) ታሪከ ነገሥት - የኢትዮጵያን ታሪክ ከያዙት መጻሕፍት አንዱ የሆነው የዙርአባ (ዙራምባ) ታሪከ ነገሥት የቅ/ያሬድን ታሪክ የያዘ ሲሆን በተለይ በዑራኤል መሪነት ከአጼ ገ/መስቀልና አባ አረጋዊ ጋር ወደ ዙርአባ ተራራ እንደወጡ፣ በዙርአባ ለሦስት ዓመታት ቅ/ያሬድ ዝማሬና መዋሥዕትን እንዳስተማረ ይናገራል።
የቅዱስ ያሬድ በረከት ከሁላችን ላይ ይደርብን፤
ግንቦት ፳፻፰
Monday, May 30, 2016
ፖርት ሳይድ ማርያም ፡ ዘይት የምታፈልቀው ስእል
እህታችን ማሕሌት መኮንን በግብጽ ፖርት ሳይድ ማርያም ተገኝታ ዘይት የምታፈልቀውን የእመቤታችንን ስእል ተኣምሩን በ ምስል ወድምጽ ታቀርብልናለች፥፥ ከዚህ በፊት ስለዚህ ተኣምር በሚከተሉት ፖስቶች ኣስነብበን ስለነበር በተያይዝነት ብታነቡት ሙሉ ተኣምሩን ትረዳላችሁ::
ከእጇ ዘይት የሚፈልቅ የቅድስት ኤልሳቤጥ አስገራሚ ታሪክ
ፖርት ሳይድ ማርያም በግብጽ
Subscribe to:
Posts (Atom)