Sunday, March 26, 2017

ዘብር ቅዱስ ገብርኤል


በሰሜን ሸዋ በመንዝ በላሎ ወረዳ ውስጥ የሚገኝ የመላዕኩ የቅዱስ ገብርኤል ቤተክርስቲያን አለ ይህ ቤተክርስቲያን ዘብር ቅዱስ ገብርኤል ሲባል መስቀልና መቋሚያ ተቆሞ የሚፀለይበት አስደናቂ የፈውስ ቦታ ነው። በዚህ ቤተክርስቲያን ከ50 ዓመት በላይ ደብሩን ያስተዳደሩ የበቁ አባት የ103 ዓመት የዕድሜ ባለፀጋ ኤኔታ አክሊሉ ይገኛሉ ። በዘመናችን እግዚአብሔር ካስቀመጠልን የፀሎት አባት የብቃት ደረጃ ላይ ከደረሱ አባቶች መካከል አንዱ ናቸው ። ኤኔታ አክሊሉ ኮርያ ከወንድማቸው ጋር ዘመተዋል በዚያም በጦር ሜዳ ከወንድማቸው ጋር ስዕለት ተሳሉ፤ስለቱም በሰላም ለሀገራችን ቃበቃህን ዕድሜ ልካችንን በድንግልና በክህነት እናገለግላለን ብለው ለዘብር ገብርኤል ተሳሉ እግዚአብሔርም ሰለታቸውን ሰምቶ እንቅፋት ሳይመታቸው እሾክ ሳይወጋቸው በሰላም ወደ ሀገረ እግዚአብሔር ኢትዮጰያ ተመለሱ ። ኤኔታ አክሊሉም በስዕለታቸው መሰረት በክህነት ዘብር ማገልገል ጀመሩ ወንድማቸው ግን ስዕለቱን ወደ ጎን በመተው ሚስት አገባ ኤኔታም ወንድሜ ነው ዘር ይተካ ሳይሉ ወንድማቸውን ጠርተው ይህ በአንተ ዘንድ አይደረግ ስዕለትንም አትርሳ ብለው ወቀሱት ንስሀ ገብቶ አብሮ በክህነት እንዲያገለግል መከሩት እርሱ ግን አሻፈረኝ ብሎ እምቢ አላቸው ወድያውም ሚስቱ ሞተች ፤ እርሱም የጥፋት ሰው ነውና ድጋሚ ሌላ ሚስት አገባ ኤኔታም እጅግ አዝነው ተቆጡት ምክራቸውንም አልሰማ ሲል በመጨረሻ ወንድማቸው ራሱ ሞተ አባታችንም አልቅሰው ቀበሩት። ኤኔታ አክሊሉ በዘብር አገልግሎታቸውን ቀጠሉ በእጃቸው የተማሩ ከ55ሺ በላይ ሊቃውንት አፈሩ ፣ኤኔታ የማያውቃቸው የቤተክርስቲያን ሊቅ የለም በመላው ኢትዮጰያ ያስተማሯቸው ሊቃውት እንደ ሰማይ ከዋክብት እንደምድር አሸዋ የበዙ ናቸው ፣አሁን ከ400 በላይ የቆሎ ተማሪ በስራቸው ይገኛል በዚህ ተጋድሎቸው የተመለከተው ጠቅላይ ቤተክህነት የጵጵስና ማዕረግ ሊሰጣቸው ጥሪ አቀረበላቸው እርሳቸው ግን በኮሪያ የገቡትን ቃል አስበው አልፈልግም ዕድሜ ልኬን ዘብር ገብርኤልን ላገለግል ስዕለት አለብኝ ብለው የክህነት ሹመቱን መለሱት፤ እውነተኛ አገልጋይ የቤተክርስቲያን ባለውለታ ድንቅ አባት ናቸውና ።

አንዴ እንዲ ሆነ ኤኔታ አክሊሉ ተማሪ በሚያስተምሩበት ጊዜ ተማሪያቸው እየሞተ ተቸገሩ ሀገሩ ላይ ታላቅ መቅፀፍት ሆነ በዚህም የተነሳ አባታችን ወደ ደብረ ሊባኖስ ሄደው የፃድቁ አባታችንን የአቡነ አብተማርያምን ታቦት ተሸክመው ወደ ዘብር ገብርኤል ይዘው መጡ ኤኔታ አክሊሉ የአብተ ማርያም ቃል ኪዳን መቅሰፍት አራቂነት ጠንቅቀው ያቃሉና ታቦቱን ከመንበሩ ቢያስቀምጡት መቅሰፍት ከአገሩ እርቆላቸዋል አንድም ተማሪ ከዚያ በኃላ ሞቶባቸው አያውቅም። ኤኔታ የሚሞቱበትን ቀን የሚያቁ ሲሆን ወደእርሳቸው የሚመጣውን ሰው ማንነት የማወቅ ፀጋ አላቸው ማህራችን ላይ ዘብር ተብሎ የሚጠራ ሲሆን ከአዲስ አበባ እንደሚመጣና ቤተክርስቲያኑን በዓለም ደረጃ የሚያስተዋውቅ መሆኑን የተናገሩ ሲሆን ትንቢታቸውም ተፈፅሞ በክብር ተቀብለሁን እኛም የማንጠቅም ባሪያ ስንሆን ገዳሙን በዓለም ደረጃ አስተዋውቀናል ኤኔታ አክሊሉ የፀሎት አባት ሲሆኑ ምግባቸውም አጥቢት እና አጃ ብቻ ነው እርሷን ለቁመተ ስጋ ነው የሚመገቡት፣ አንድ ጊዜ እርሳቸው ቤት ገብቼ አልጋቸው ላይ እንድቀመጥ አደረጉኝ ስለቤተክርስቲያኑ አንዳንድ ነገር ለመነጋገር በዚያ ጊዜ ብዙ ክርስቲያኖች በእጃቸው መስቀል ለመሳለም ቤታቸውን አጨናንቆት ነበር ቤቱ ጠባብ ከመሆኑ የተነሳ ከአራት ሰው በላይ ማስተናገድ አይችልም ሰው ውስጥ ተጨናንቆ ገብቶ ቀሪው ውጪ ጋር ተራ እየጠበቀ ሰልፍ ይዟል በመሀል የወረዳው ፀሐፊ መርጌታ ጥላውን የሕዝቡን መጨናነቅ የቤቱን ጥበት ተመልክተው ከበር ሊመለሱ ሲሉ ኤኔታ አክሊሉ ሰው ሳይጋርዳቸው ግድግዳ ሳይሸፍናቸው ድምፃቸውን ከፍ አድርገው ና አንተ የወረዳው አትመለስ ግባ ብለው መጥራታቸውን የወረዳው ፀሐፊ ደንግጠው የገቡበትን ቀን አረሳውም አርባራ መዳኒዓለም ቤተክርስቲያን ከሽቦ አጥር በኃላ ምንም ነገር አይነሳም አንዲት እህታች የሾላ ፍሬ አንስታ ቦርሳዋ ውስጥ ብትከት መኪናችን ሶስት ጊዜ ጎማ ፈነዳብን በዚህ የተነሳ በጣም ተጨንቀን ሳለ እህታችን የሾላ ፍሬ ከቦርሳዋ አውጥታ እኔ ከተከለከለ ቦታ አንስቼ ነው ብላሰጠችን እኛም ፀሎት አድርገን ምሕረቱን እንዲያደርግልን ተማፅነን ጎማችንን አስተካክለን ተነስተን ዘብር ገባን እኔም ወደ እኚ የበቁ አባት ጋር ለመባረክ አቀናው ወደያው ሲያዩኝ እየሳቁ አጠገባቸው እንድቀመጥ አድርገው የሆነውን ነገር ቦታው ላይ እንደተገኙ አድርገው የደረሰብንን መከራ ራሳቸው መናገር ጀመሩ እኔ እጅግ ደነገጥኩኝ እሳቸው አይዞ መላዕኩ ከእናንተ ጋር ነው ብለው አረጋጉኝ ይህንን ቀን መቼም ቢሆን አረሳውም በእውነት በእሳቸው እጅ መባረክ መታደል ነው ክብራቸው ቢረቅብን ከግሪክ ሀገር የክህነት ልብስ አስመጥተን ብሰጣቸው ለእናንተ ስል ለአንድ ቀን እለብሰዋለው ብለው አንድ ቀን ስለፍቅር ለብሰው በነጋታው የኬሻ ቆባቸውን አደረጉ። የዚህችን ዓለም ጣዕም ንቀዋልና አይናቸው ከፀሎትና ከእንባ ብዛት የተነሳ ደክሟል የፃድቅ ክብሩ የሚገለጠው ሲሞት ነውና ያልተነገረ ብዙ አለና ወደ ሀገራቸው ከመሄዳቸው በፊት በረከታቸውን እናግኝ መልክቴ ነው በቀጣይም ስለ በረሃው አባት አባ ላዕቀ ስለ ኢትዮጰያ የተናገሩትን እና ያጫወቱኝ ታሪክ ይዤላችሁ እቀርባለው አስከዛው ሰላመ እግዚአብሔር ከእናንተ ጋር ይሁን አሜን