የኢንተርኔት አገልግሎት ፈጣን ባልሆነበት ቦታ 
በአማራጭነት ይህንን በጽሑፍ መልክ ያንብቡ:: ረጅም ትምሕርት ሲሆን በተቻለ መጠን በቂ መልክቱን በጽሑፍ 
አቅርበናል:: የቃላት ግድፈት ካለ እያረሙ እንዲያነቡ እንጋብዛለን::
የጸሎት ቦታ እንዴት ላዘጋጅ?
ክፉንና
 ደጉን ለመለየት አምልኮ ያስፈልጋል:: አምልኮ የሌለበት ህይወት አለም ላይ የወደቀ ነው ስለዚህም የአምልኮት ራእይ
 አንድ ክርስቲያን ሊኖረው ይገባል:: ማምለክ ማለት እግዚያብሔርን ከልብ መውደድ: ቃሉን በልቦና ማኖር: እና መጠበቅ: 
እርሱን ተስፋ ጉልበታችንን ማድረግ ነው:: በተግባር ደግሞ ኑሮን ጠባይን ለእግዚያብሔር መስጠት: ውስጣዊ ህይወታችንን 
ለክብሩ የተዘጋጀ ማድረግ :: ስለ ሐጢአታችን ንሰሐ ገብተን ሥጋውና ደሙን መውሰድ: እለት እለት ስለበደላችን 
ስለሐጢአታችን ለእግዚያብሔር መንገር:: እለት እለት እግዚያብሔርን የምናመሰግንበትን ግዜ ካገኘን የአምልኮት 
ሕይወት ገበና አለን ማለት ነው:: ሰብአ ሰገል ክርስቶስን በፍቅር ፈልገው እንደመጡ አንድ ክርስቲያንም ክርስቶስን 
ፈልጎ መምጣት አለበት:: በአምልኮት ባሕርይ ሔሮድስን ማለፍ ቅድሚያ የሚሰጠው ነገር ነው:: ሔሮድስ ማለት የዚህ 
አለም ነገሮች ናቸው እነዚህም :የአለምን ሰዎች እውቀት: ሳይንስ እግዚያብርሔን የሚከለክል : የድንግል ማርያም ልጅ ክርስቶስን
 የሚከለክል ነው:: ሔሮድስ ማለት ሐብት : ስልጣን: ማዕረግ የመሳሰሉት እነዚህ ሁሉ የሔሮድስ መንገድ ጠቋሚ 
ናቸው:: ሰዎች የጥፋት ሞት ውስጥ የሚገቡት የአምልኮት ሕይወት በማጣት ነው:: እግዚያብሔርን የሚፈልጉ ሰዎች ሔሮድስ
 ጋር መቅረት የለባቸውም:: ኮከቡን ማየት አለባቸው ኮከቡም ያለው በሰማይ ነው::
ብዙ
 ክርቲያኖች ወደ እግዚያብሔር ቤት አይሔዱም ወይም ወደ ሰማይ ቀና አይሉም:: በዚህም ወደ ልባቸው የሚሔድባቸው 
መጣባቸው:: ሰይጣን ወደ ቤታቸው ወደ ኑሮአቸው ወደ ሕይወታቸው መጣ:: በዚህ ዓለም ገለልተኛ ሆኖ መኖር አይቻልም:: በዚህ 
አለም ሁለት ነገር ነው ያለው:: ጽድቅና ኩነኔ: ጨለማና ብርሃን: ሓጢአትና ጽድቅ: ሰላምና ጦርነት::ከፈለክ ወደ 
ብርሃን ካልፈለክ ወደ ጨላማ: ከፈለክ  እውነት ካልፈለክ ሐሰት: እንዲህ በጥንድ የተያያዘ ነው:: የእግዚያብሔርን 
በቅድምያ ከሰማን የእግዚያብሔር ጽድቅ ይገለጥልናል: የሰዎችን ከሰማን ሁል ግዜ እንደተደናገግርን ተስፋችንን 
በአልሆነ አቅጣጫ እየጠበቅን እንኖራለን:: ሔሮድስ ክፉ መሆኑን የምናውቀው ስናመልክ ነው::
የጸሎት ቦታ

የጸሎት
 አቅጣጫ ምስራቅን የተመለከተ መሆን አለበት:: በመንበርከክ በግንባር ልክ የእመቤታችን የቅዱስ ሚካኤል የቅዱስ እና
 የቅዱስ ገብርኤል በግራና ቀኝ : በመቆም ልክ የስላሴ የመድኃኔአለም ስእል ይደረጋል:: ከስእሉ ራቅ የሚባለው 
ክፍተቱ 
የመጽሐፍ መግለጫ ያህል ነው:: ስእሎቹ ተጸልዮባቸው ቅባ ቅዱስ ይቀባሉ ቢቻል ቤተ ክርስቶያን ተባርካው በቅዳሴ ግዜ
 ቅባ ቅዱስ ተቀብተው መሆን አለበት:: ስእሎቹ በጥሩ ፍሬም የተሰሩ ስእሎች መሆን አለባቸው:: ከስራቸው የጸሎት 
ወሃ : እጣን: እምነት:የወይራ ዘይት: የመጽሀፍ ማስቀመጫ: የምንጠቀምባቸው እንደ ሽቶ ዎች ካሉ አጠገብ መሆን
 አለባቸው:: ሽቶ የሚወዱ ዛሮች አሉ:: ተጸልዮበት ሽቶ ብንጠቀም ሽቶ የሚወዱ ዛሮችን መከላከል ይቻላል : 
የመንበርከኪያ ቦታ ደረቅ ያለ የጥጥ ፍራሽ ቢሆን ይመረጣል:: ግልበት በሚሰግድበት ግዜ መመቻቸት አለበት ነገር ግን
 በጣም የሚመች ሥፕንጅ መሆን የለበትም: ስንፍና እንዳይሰማው: የሚሞቅ ነገር መሆን የለበትም መቀዝቀዝም 
የለበትም:: 
በሚሰግድበት ግዜ በስእሎቹ ፊትለፊት  መስገድ ሲጀምር የሚከተሉትን ምልክቶች ያያል:- መዛል:መድከም መልፈስፈስ 
:: በሚጸልይበት ግዜ ከስእሎቹ የሚወጣ መንፈሳዊ እሳት አለ:: በሰውነቱ ላይ ከስእሎቹ ተጠግቶ ሲጸልይ መውረር 
መቅበጥበጥ:ማቃጠል የሚታይበት ይሆናል:: አንዳንዱም መንፈሱ ወዲያው መገለጥ ጠባይ አለው:: መንፈሱ ጸሎት በከፍተኛ
 ሁኔታ ጸሎት እየከለክለው የሚያጠቃው ከሆነ የቅዱስ ሚካኤልን ስእል በፍሬም በጥሩ ሁኔታ ሰርቶ  መሬቱ ላይ አድርጎ
 
እጁ ላይ እና ሰይፉ ላይ በሚሰግድበት ግዜ መንፈሱ ሊጥለው ይችላል:: በዚህ ግዜ መቁጠርያ ያስፈልጋል::ጸጥ በል 
በጌታየ በየሱስ ክርስቶስ ስም ብሎ ሲመታው ቅዱስ ሚካኤል ሆይ እሰርልኝ ሲለው  በስእሉ ፊት ያለው ሐይል እየተገለጠ
 ቅዱስ ሚካኤል ሊያስርለት ይችላል:: ሰውየው እየሰማም እያወቀም መንፈሱን ሊያስርለት ይችላል:: በዚህ ግዜ 
ፕሮግራም ይዞ ወድ  እኔ ደውሎ አንዳንድ መረጃ እንለዋወጣለን:: የሚደክም ከሆነ ይደክማል የሚሸኝም ከሆነ 
ይሸኛል:: ሆኖም ግን  እነዚህን ልምምዶች በቀላሉ የሚመጡ  አደሉም:: ሰውየው በጥሩ የበረከት መንፈሳዊ ህይወት 
ለማለፍ እራሱን ማዘጋጀት አለበት:: ጸሎትን እንደ ደስታ አምላክን እንደማማረርያ ጎዳና ሳይሆን "ሁል ግዜ በጌታ 
ደስ ይበላችሁ:ደግሜ እላለሁ ደስ ይበላችሁ::ገርነታችሁ ለሰው ሁሉ ይታወቅ::" እንዲል ገራገር መሆን አለበት:: 
"ጌታ ቅርብ 
ነው::በነገር ሁሉ በጸሎትና በምልጃ ከምስጋና ጋር በእግዚአብሔር ዘንድ ልመናችሁን አስታውቁ እንጂ በአንዳች 
አትጨነቁ::" ፊልጵስዮስ 4:4-6
 
ራእይን
 ምሪቱን ለማግኘት ደግሞ የጸሎት ቦታችን ላይ ለባልና ሚስት የመኝታ ያህል መኖር አለበት: ቤተሰብ ካለው ከሌለው