Wednesday, November 12, 2014

ጸሎት ሰሚዋ ኩክ የለሽ ማርያም እና አባ ኃይለ ጊዮርጊስ ዘብሔረ ቡልጋ


አባ ኃይለ ጊዮርጊስ ዘብሔረ ቡልጋ የኩክ የለሽ ማርያም ገዳምን የመሰረቱ ሲሆን በመስከረም 23 ቀን 1908 በቡልጋ ወረዳ ተወለዱ፡፡እግዚአብሔር አምላክ በእርጅና ጊዜአቸው በ64 ዓመታቸው ለመንፈሳዊ አገልግሎት ወደ ቤቱ የጠራቸው በአካለ ሥጋ በነበሩበት ጊዜም ነበር ከቅድስት ድንግል ማርያም ከቅዱሳን መላእክት ከጻድቃን ሰማዕታት ጋር ለመነጋገር የበቁ ታላቅ አባት ነበሩ፡፡
እግዚአብሔር ያከበረውን ማን ያዋርደዋል እንዳለ መጽሐፉ እኚህ ታላቅ አባት በሣርያ ቅዱስ ሚካኤል ቤተክርስቲያን ሲያገለግሉ ቤተክርስቲያን ሲረዱ የቀዩ አባት ሲሆን ከዕለታት አንድ ቀን የቅዱስ ሚካኤልን በዓል ሲያከብሩ በዋዜማው ከቅዱስ ሚካኤል ጋር በመነጋገር የሥላሴን ዙፋን ገንትንና ሲኦልን ለማየት የበቁ አባት ናቸው፡፡

ከዚህ ጊዜ ጀምሮ አባ ኃይለ ጊዮርጊስ በእግዚአብሔር አጋዥነት በቅዱሳን መሪነት ገዳሙን የመሰረቱት ሲሆን ከድንጋይ ፍልፍል አራት / 4 / ቤተመቅደሶችንና ሌሎች የባህታውያን መኖሪያ ዋሻዎች የፈለፈሉ ሲሆን አብረዋቸው ቅዱሳን መላእክት እንደሚያግዟቸው በህይወት በነበሩበት ሰዓት ይናገሩ እንደነበር የገዳሙ አገልጋዮች ይናገራሉ፡፡አራቱ ቤተመቅደሶች፡-

1. የቅዱስ እግዚአብሔር አብ ፍልፍል ዋሻ፡- ይህ ገዳም አባ ኃይለ ጊዮርጊስ በ1972 ዓ.ም ጀምረው በ1976 ዓ.ም ነው ያጠናቀቁት ሲሆን ይህን ያህል ጊዜ ለምን እንደፈጀ የራሱ የሆነ ምክንያት አለውና በቦታው ተገኝተው ሚስጢሩን እንዲያውቁ ይመከራሉ

2. ኩክ የለሽ ማርያም ፍልፍል ዋሻ፡- በ1984 ዓ.ም ጀምረው በአንድ ዓመት ጊዜ ውስጥ ነው ያጠናቀቁት፡፡ኩክ የለሽ ማርያም ማለት የጆሮ ኩክ የሌላት ቶሎ የሰዎችን ችግር የምትሰማ ለጠየቋትም ቶሎ ምላሽ የምትሰጥ እናት ማለት ነው፡፡ይህ ማለት ግን ሌሎች ቅዱሳን አይሰሙም ማለት አይደለም ፡፡ እመቤታችን ወላዲተ አምላክ ድንግል ማርያም አባ ኃይለ ጊዮርጊስ እጅግ አብዝታ ስለምትወዳቸው ኩክ የለሽ ማርያም ገዳምን እንዲመሰረቱ አድርጋቸዋለች፡፡ በጸበሏ በእምነቷ ብዙ ተዓምራቶችን እያደረገች ትገኛለች፡፡

3. የቅድስት ሥላሴ ፍልፍል ዋሻ፡- በ1984 ዓ.ም ጀምረው ከኩክ የለሽ ማርያም ፍልፍል ዋሻ ጋር አብሮ በአንድ ዓመት ውስጥ ነው የተጠናቀቀው ድንቅ ተዓምር እየተደረገም ይገኛል፡፡

4. ምን ያምር ቅዱስ ገብርኤል፡- በ1986 ዓ.ም ጀምረው በአንድ ዓመት ጊዜ ውስጥ ነው ያጠናቀቁት፡፡ይህ ገዳም በቅዱስ ገብርኤል መሪነትና አጋዥነት በአባ ኃይለ ጊዮርጊስ ተፈለፈለ፡፡በዚህ ቤተመቅደስ ውስጥ ጸበል ፈልቆ ብዙ ተዓምራትን እያደረገ ይገኛል፡፡በአጠቃላይ በአራቱም ቤተመቅደስ በየእለቱ ማይጠንት ይታጠናል፡፡እንዲሁም በየወሩ ቅዳሴ ይቀደስባቸዋል፡፡ገዳሙ በ1972 ዓ.ም ተጀምሮ በ1986 ዓ.ም መጨረሻ ተጠናቆ በ1987 ዓ.ም በአባቶች ተባርኮ መለኮሳት በምነና ሕይወት ገብተዋል፡፡

እኚህ አባት ገዳሙን መስርተው ብዙ መንፈሳዊ አገልግሎት ካገለገሉ በኃላ በ1997 ዓ.ም መጋቢት 19 ቀን በዓለ እረፍታቸውን ካደረጉ በኃላ አጽማቸው በገዳሙ በጸሎት በአታቸው ውስጥ ይገኛል፡፡ይህ ገዳም ከ25 በላይ መለኮሳት የሚኖሩበት ሲሆን በሽመናና በልማት ስራ ከጸሎት ጎን ለጎን እየሰሩ ይገኛሉ፡፡ ይህን ታላቅ ገዳም የረገጠ ወንደ የ40 ቀን ህጻን ሴት የ80 ቀን ህጻን ይሆናል ተብሎ ቃል ኪዳ ተገብቶለታል እንዲሁም በቦታው የበረከት ሥራ የሰራ ጸሎት ያደረገ እስከ ሰባት ትውልድ ድረስ ምህረት እንደሚደረግለት ቃል ኪዳን ተገብቶለታል እርሶም በቦታው በመገኘት ለቦታው የተገባለትን ቃል ኪዳን ይሸምቱ እኔ ኃጢአተኛ ባሪያችሁ የዚህ ቃል ኪዳን ተካፋይ ሆንኩ ምዕመናንና ምዕመናትም የዚህ ቃል ኪዳን ተካፋይ ይሆን ዘንድ ብዕሬን አንስቼ አካፈልኳችሁ፡፡

ወስብሐት ለእግዚአብሐር
ምንጭ፡-ገዳሙ ያሳተመው ብሮሸር
ለበለጠ መረጃ ፡- የቅዱስ እግዚአብሔር ማህበር 0911 133944 ፤ 0922 461145
አድራሻ፡- ደብረ ብርሃን በስተሰሜን ምስራቅ በኩል 5 ኪሎ ሜትር ርቀት ላይ ትገኛለች

Tuesday, November 4, 2014

ተዓምረኛው በሻሌ ንቡ ቅ/ሚካኤል እና ሰማዕቱ እስጢፋኖስ ቤተክርስቲያን


በስመ አብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ አሐዱ አምላክ አሜን
“የእግዚአብሔርን ሥራ በምድር ያደረገውን ታምራት እንድታዩ ኑ” መዝ. 45፡8
በንብ መንጋ የተከበበው የበሻሌ (ንቡ) ቅ/ሚካኤል፣ ቅ/እስጢፋኖስ እና ወአባ ሰላማ ከሳቴ ብርሃን ቤተክርስቲያን አመሰራረትና ገቢረ ተዓምራት አጭር መግለጫ
ቤተክርስቲያኑ ከመመስረቱ በፊት በቦታው ላይ ሲከናወኑ የነበሩ ልዩ ልዩ ታምራት፡-
1. ለብዙ ዓመታት ከተለያየ ቦታ ተጣልተው የነበሩ ምዕመናን ቦታው ላይ እየመጡ እርቀ ሰላም ሲፈጽሙበት ኖረዋል፤
2. ቤተክርስቲያኑ ከተተከለበት ቦታ ትልቅ የጽድ ዛፍ ላይ የሚወጣው ሙጫ እንደ እጣን ጢስ ሽታ ለብዙ ዓመታት አካባቢውን መዓዛው (ሽታው) ያውድ ነበር፡፡
3. በዚሁ ቦታ ላይ ሌሊት ሌሊት የመላዕክት ዝማሬ (ጣዕመ ዜማ) የከበሮ ድምጽ ይሰማ እንደነበረ በዕድሜ የገፉ የአካባቢው አዛውንቶች ተናግረዋል፡፡
4. በአካባቢው ከሚኖሩ ምዕመናን መካከል በመልካም ስራቸው የታወቁና ከ90 ዓመት በላይ ዕድሜ የነበራቸው እናት የቅዱስ ሚካኤል ታቦት (ጽላት) እንደሚተከል በተደጋጋሚ ለሕዝበ ክርስቲያኑ ይናገሩ ነበር፡፡
5. ቀደም ሲል በእነ አብርሃ ወአጽብሃ ዘመነ መንግሥት አካባቢ ጀምሮ ከተለያየ አካባቢ የሞቱ አባቶች አስከሬናቸው እየመጣ
በቤተመቅደሱ ስለሚገኘው የንብ መንጋ አገባብ (አመጣጥ)
እግዚአብሔር አስቀድሞ ቦታውን ስለመረጠው፡-
1. ሕዳር 12 ቀን 2002 ዓ.ም የቅዱስ ሚካኤል በዓል ሲከበር በዋዜማው ሊቃውንቱ በአገልግሎት ላይ እንዳሉ ማለትም ሕዳር 11 ቀን 2002 ዓ.ም ከቀኑ 9፡00 ሰዓት ገደማ ከምስራቅ አቅጣጫ የንብ መንጋ መጥቶ የቃል ኪዳኑ ታቦት በሚገኝበት በመንበሩ ውስጥ ገብቶ ካደረ በኋላ በነጋታው ታቦቱ ወጥቶ በሚከበረበት ጊዜ ንቡ ከመንበሩ ወጥቶ እንደ ደመና ረቦ ካሉት ምዕመናን ጋር ታቦቱን ዙሮ አክብሯል፡፡ በዕለቱም ይህን አስደናቂ ታምር ያዩና የተመለከቱ ምዕመናንም በከፍተኛ ድምጽ እግዚአብሔርን አመስግነዋል፡፡
2. ሕዳር 11 ቀን 2004 ዓ.ም የድንግል ማርያም ዕለት ካህናቱ ቅዳሴ ገብተው በሚቀድሱበት ጊዜ ቅዱስ ወንጌል ሲነበብ የንብ መንጋ መጥቶ ከቤተክርስቲያኑ ጉልላት ላይ የመስቀል ምልክት ሰርቶ ከሰፈረ በኋላ ከቀኑ 11፡00 ሰዓት ላይ ተነስቶ ቤተክርስቲያኑን ዙሮ ወደ ቤተልሔም ውስጥ ገብቶ እስከአሁን ድረስ ሰፍሮ ይገኛል፡፡
3. ታህሳስ 9 ቀን 2004 ዓ.ም ከቀኑ 9፡00 ሰዓት የንብ መንጋ መጥቶ ከቤተክርስቲያኑ ጎን ላይ ከሰፈረ በኋላ ከቀኑ 11፡30 ተነስቶ ቤተክርስቲያኑን ዙሮ ወደ ግብር ቤት ገብቶ እስከአሁን ድረስ ሰፍሮ ይገኛል፡፡

Saturday, October 25, 2014

የእመቤታችን የቅድስት ድንግል ማርያምና የአርባ ሓራ መድኃኒዓለም ተዐምር

የእመቤታችን የቅድስት ድንግል ማርያምና የአርባ ሓራ መድኃኒዓለም ተዐምር
   ከጌታቸው ገብሬ እንግዳ
       አንድ አምላክ በሚሆን በአብ፣ በወልድ፣ በመንፈስ ቅዱስ ስም በቅድሚያ መንፈሳዊ ሰላምታዬን አቀርባለሁ። ኗሪነቴ በዋሽንግተን ዲሲ ከእመቤታችን ቅድስት ማርያም ቤተ ክርስቲያን አጠገብ ነው። ባለትዳርና የሁለት ልጆች አባት ነኝ።ጥቅምት 18 ቀን 2005 .. እምሽቱ ላይ በሥራ ገበታ ላይ እያለሁ ራሴንና መላ ሰውነቴን ስላመመኝ አለቃዬን አስፈቅጄ ወደ ቤቴ ሄድኩ። ቤቴም እንደደረስኩ የቤቴን በር ለመክፈት ስታገል ስልክ ተደወለልኝ። ከዚህ በኋላ የሆነውን ብዙውን ስለማላስታውስ በባለቤቴ በወ/ ታሪክ አንደበት የተተረከውን ላቅርብላችሁ።

        ባለፈው ጥቅምት ወር የቅዱስ ገብርኤል ዋዜማ ዕለት ከምሽቱ አምስት ሰዓት ላይ ባለቤቴ ከሥራ ከሚመጣበት ከተለመደው ሰዓት አንድ ሰዓት ቀደም ብሎ በራችንን ለመክፈት የሚታገል ሰው እንዳለ ስለሰማን እኔና ልጆቼ የምናደርገው ቢቸግረን ለባለቤቴ ስልክ ደወልንለት። ስልኩንም እንደደወልን እቤታችን በር ላይ የባቤቴ ስልክ ሲያቃጭል ሰማን። በዚህም በሩን ለመክፈት የሚታገለው ባለቤቴ እንደሆነ አወቅን። ወዲያውም እኔና ልጆቼ ተሯሩጠን ሄደን በሩን ስንከፍት ባለቤቴ እንደሰከረ ሰው እየተንገዳገደ ራሱን ችሎ መቆም አቅቶት አየነው። ግራ ተጋብተን ምን እንደሆነ እንኳ ሳንጠይቀው ዝም ብለን ደግፈነው ወደ ቤት አስገባነው። ኃይለኛ ራስ ምታት እንዳለበት ሲነግረን ይሻለዋል ብለን የራስ ምታት መድኃኒት ሰጥተን አስተኛነው። በማግስቱም የቅዱስ ገብርኤል ዕለት በዋሽንግተን ኃይለኛ አውሎ ነፋስ ይነፍሳል ተብሎ ስጋት ስለነበር /ቤት ሁሉ ዝግ እንደሚሆን በመገናኛ ብዙኃን ተነግሮ ነበር። እኔም አጋጣሚውን በመጠቀም ቤተሰቡ በሙሉ ቁርስ አብረን እንድንበላ ልጆቼን ቀሰቀስሁና አባታቸውን አስነስተው ወደ ገበታው እንዲቀርቡ ነገርኳቸው። ባለቤቴ ከመኝታው ተነስቶ ከተጣጠበ በኋላ ወደ ገበታው ለመቅረብ ሲመጣ መራመድ አልቻለም። ዝልፍልፍ አለ። ሁላችንም ተደናገጥን። ልጆቼም ስልክ ደውለው አምቡላንስ ጠሩ። ባለቤቴም በአስቸኳይ ለሕክምና ወደ ዋሺንግተን ሆስፒታል ማዕከል ተወሰደ። እዚያም እንደደረሰ ሐኪሞቹ በሚያውቁት መንገድ ሁሉ መርምረው ምንም ሕመም ሊያገኙ አልቻሉም። ሊነጋጋ ሲል ጧት ላይ ለሕመሙ ማስታገሻ ብለው መርፌ ሲወጉት አንቀጠቀጠውና ደካከመው። መተንፈስ አቃተው፣ አንደበቱም ተያዘ።እንደሞተ ሁሉ ሰውነቱ ቀዘቀዘ በዚህን ጊዜ በመሳሪያ ኃይል እንዲተነፍስና ደሙም እንዲጣራ አደረጉ። ሆዱን ከፍተው ለማየት ቢሞክሩ ሰውነቱ ከፍሎሪዳ እንደመጣ ገና ከማቀዝቀዣ እንደወጣ ሥጋ ድርቅ ብሎ ስለት የማይደፍረው ሆነ። ሐኪሞቹ የሚያደርጉት መላው ጠፋቸው። አንድ ጊዜ ሳንባው ተቃጥሏል፣ ትንሽ ቆይተው ጉበቱ ተበላሽቷል፣ ከዚያም ኩላሊቱ አይሠራም ሲሉ ጥቂት ቀናት አለፉ።



አንድ ቀን ከሐኪሞቹ አንደኛውበኛ በኩል ምንም ልንረዳው የምንችለው የለም፤ ወደ ማገገሚያ ቤት ሄዶ በእዚያ ቢቆይ ነው የሚሻለው፤ ስለዚህ ወደዚያ እንድንልከው ፈርሚ አሉኝ።እኔምአልፈርምም፤ በእናንተ በኩል ምንም ዕርዳታ ማግኘት ካልቻለ እዚያስ ሄዶ ምን ያደርጋል? ለመሞት ለመሞት እዚሁ ሆኖ ቢሞት ይሻላል አልኳቸው። ይህንን የሰሙ ወዳጆቻችን በጣም አዘኑ። አንዳንዶቹ ለሚቀርቡት ታቦት ተሳሉ። አንዳንዶቹ ደግሞ ኢትዮጵያ ለሚገኙ ለበቁ አባቶች በፀሎታቸው እንዲራዱ በስልክ አሳሰቡ። የሚጨነቁልን የሚያውቁን ብቻ ሳይሆኑ ባጋጣሚ ሁኔታውን የሰሙ የማያውቁንም ነበሩ። አንድ ቀን ባለቤቴ ከተኛበት ክፍል ውጭ በእንግዶች ማረፊያ ቤት ተቀምጨ እያለሁ አንዲት እናት ጋር እየተጨዋወትን እያለን ስለባለቤቴ ጭንቀቴን ስነግራቸው አንዲት የጸሎት መጽሐፍ (የሰኔ ጎልጎታ የእመቤታችን ፀሎት መጽሐፍ በክታብ መልክ የተዘጋጀች) ከቦርሳቸው አወጡናእንቺ በዚህ አሻሺው፤ እመቤታችን ታድነዋለችአሉኝ። እኔም ተቀበልኳቸውና ባለቤቴ ወደተኛበት ክፍል ገብቼ (በገባሁ ቁጥር እየፈረምኩ ነው። ቁጥጥሩ ጥብቅ ነው። ዝም ብሎ እንደፈለጉ መግባት መውጣት የለም።) ሴትየዋ እንደነገሩኝ ባለቤቴን ላሻሸው ብዬ መጽሐፏን ገና ግንባሩ ላይ ሳስነካ የመተንፈሻውና ደም የማጣሪያው መሣሪያ ሁሉ ይንጫጫ ጀመር። እኔ ወደ ማሽኑ አልደረስኩም። ማሽኑ ጋር የተያያዘ ገመድ አልነካሁም። ግን ማሽኑ ያለማቋረጥ እሪታውን ቀጠለ። ሕብረ-ቀለማት እያወጣ ተብለጨለጨ። ሐኪሞቹና ነርሶቹ እየተሯሯጡ መጡናማሽኑን ለምን ነካሽ?” ብለው ተቆጡኝ። እኔም የሆነውን ነገርኳቸው። እነሱም የጸሎት መጽሐፏን እንዳሳያቸው ጠየቁኝና ሰጠኋቸው። አገላብጠው አዩና ሳቁብኝ። ውሸት የነገርኳቸው መስሏቸዋል።እመቤቴ ሆይ አታሳፍሪኝ፤ ኃይልሽን ግለጪላቸውብዬ እነሱም እንዲሞክሩት መጽሐፏን ሰጠኋቸው። እነሱም የጸሎት መጽሐፏን ወደግንባሩ ሲያስጠጓት ማሽኑ ተንጫጫ። እነሱም ተደናገጡ። በሁኔታው ግራ ተጋቡ። ከአቅማቸው በላይ የሆነ የማይመረመር ኃይል አጋጠማቸው። አንደኛውም ሐኪምበኛ በኩል ምንም ልንረዳው እንደማንችል ገልጸንልሻል። ትልቅ እምነት አላችሁ። በእምነታችሁ ተስፋ የምታገኙ ከመሰላችሁ እሱን ሞክሩ። የሚጸልይላችሁ ከሌለ እኛ እናመጣላችኋለንአለኝ።የሚፈቀድልን ከሆነማ የራሳችንን ቄሶች አስመጥተን እናጸልያለን አልኩት። በልቤሌላማ ከእምነቴ ውጭ የሆነ መጥቶ አይዘባርቅብኝምአልኩ። ይህንን የእመቤታችንን ተዐምር የሰሙ ሰዎች ወደ ሆስፒታሉ መጉረፍ ጀመሩ። ከላይ እንዳልኩት ጸሎቱ በያለበት ተጠናከረ። ከኡራኤልም የሚጸልዩልን ቄስ መጡ። እሳቸው የመጡ ዕለት።ማሽኑ መሥራት አቁሟል፤ ሕመምተኛው አርፏል፤ ከዚህ በላይ የምንነግራችሁ የለም። አስከሬኑን እስከምናስረክባችሁ እኛን ምንም ነገር ልታነጋግሩን አትችሉምብለውን እየተላቀስን ነበር። በመላቀስ ላይ እያለን ቄሱ ለቅሷችንን አስቆሙንና የሚያጽናናንን የእግዚአብሔር ቃል ተናገሩ። እሳቸውምአትዘኑ፣ ለእግዚአብሔር የሚሳነውነገር የለም። አልአዛርን በሞተ በአራተኛው ቀን ያስነሳ አምላክ ወንድማችንንም ሊያስነሳ ይችላል። ባይነሳም እንኳ ማዘን አይገባም። ክርስቲያን ሞተ አይባልም። ያውም ዘር የተካ፣ ማስታወሻ ትቶ የሄደ ወንድም ሞተ አይባልም።እያሉ ሲናገሩ አንደኛዋ አስታማሚ መጣችናእስቲ ተረጋጉ፣ መሣሪያው መስራት ጀምሯል። ሕመምተኛውም ትንፋሹ ተመልሷል። አታልቅሱ እስቲ መጨረሻውን ጠብቁአለችን። ቄሱምእግሬን ለምለም ያድርገው፤ እግዚአብሔር ፍጻሜውን ያሳምረውብለው ሄዱ።  


ከዚያ በፊት አንድ ቀን ቀደም ብሎ አንዲት ጓደኛዬ (ከኔ ጋር አብራ ስትጨነቅ፣ እኔን ታበረታታ የነበረች) “ዛሬ ትልቅ ሕልም አየሁ።እግዚአብሔር ጠባቂ መልአኬን እልክለታለሁ፤ አይሞትምየሚል መልዕክት ሰማሁብላ ነግራኝ ነበር። ላምናት ግን አልቻልኩም። በማግስቱ የጥቅምት መድኃኒዓለም በሚውልበት ዋዜማ ሲመሻሽ (እርግጠኛ ነኝ በኢትዮጵያ የመድኃኒዓለም ማኅሌቱ ደምቋል።) አንዲት ጓደኛዬ ደውላጸሎት የሚያደርጉ ካህን አንዲት ልጅ ይዛቸው እየመጣች ነውና እበሩ ድረስ ሄደሽ ተቀበያቸውአለችኝ። እኔም እንደተባልኩት እውጭ በር ድረስ ሄጄ ብጠብቅ ቄሱንና ልጅቱን አላገኘኋቸውም። ተመላላሹ ሰው ብዙ ስለሆነ እንኳን የማላውቃቸውን የማውቃቸውንም ለማግኘት ይከብድ ነበር። ከብዙ ጥበቃ በኋላ ተስፋ ስቆርጥ ለጓደኛዬ ደውዬ ልጅቱን ላገኛት እንዳልቻልኩ ነገርኳት። እሷምእስካሁን እንዴት አልደረሱም?” ብላቆይ ልደውልላትና እሷ እንድትደውልልሽ አደርጋለሁአለችኝ። እኔም ብዙ ጠበቅሁ፤ ግን ስልክ ሳይደወልልኝ ቀረ። በኋላ ላይ ጓደኛዬ ደወለችልኝናለምን እንደሁ እንጃ ስልኳን አታነሳም። መልዕክት ትቸላታለሁ ለእኔ ወይም ላንቺ ትደውላለችአለችኝ። እኔም ተመልሼ ወደ ባለቤቴ ክፍል ስሄድ ቄሱ ከሌሎች ሰዎች ጋር ሆነው ይጸልያሉ። ብዙ ከጸለዩ በኋላ ከአርባ ሓራ በመጣው ቅቤ ባለቤቴን ግንባሩን ሲቀቡት ዓይኑን ገለጠ። ቄሱም ጥያቄ ሲጠይቁት በዓይኑ ይመልስላቸው ጀመር። አምላካችንን አመሰገንን። ምስጋና አንዲት ናት። የሱ ግን ቸርነት ብዙ ነው። እሱ ሌላ አይፈልግም፤ ምስጋና ብቻ። ግን ምስጋና ያንሰዋል። መድኃኒዓለም በዕለተ ቀኑ ባለቤቴን ከሞት መለሰው። የባለቤቴ የሰውነቱ ሙቀት ተመለሰ። ሐኪሞቹም በማግስቱ መጥተው ሲያዩት ዓይኑን ቁልጭ ቁልጭ ሲያደርግ አላመኑም። በራሱ መተንፈስ ይችል እንደሁ ብለው የተሰካካውን ገመድ ነቀሉለት። ያለ መሣሪያው መተንፈስ ቻለ። ተቃጥሏል ያሉት ሳንባ ይሰራል። ኩላሊቱም ደሙን ማጣራት ይችላል። ሌሎቹም እነሱ ተበላሽተዋል ያሏቸው የሰውነቱ ክፍሎች በሙሉ ንጹሕ ሆነው አገኟቸው። ባለቤቴን እግዚአብሔር እንደገና ፈጠረው። ይህን ድንቅ ለሠራ፣ ከዚያ ከባድ ጭንቀት ለገላገለኝ አምላክ አንዲት ምስጋና ብቻ እንዴት ትበቃዋለች? የሆኖ ሆኖ፣ አሁን እኔ ለሌላም ተርፌአለሁ።


 አንዲት ሴትእህቴ አትናገርም፣ እጇም በድን ሆኗልብትለኝ ትንሽ የተረፈችኝ ከአርባ ሓራ የመጣች ቅቤ ነበረችኝ እሷኑ ሰጠኋት። ያችን ተቀብታ እጇንም ማንቀሳቀስ፣ መናገርም እንደጀመረች እህቷ አበሰረችኝ። ክብር ምስጋና ለመድኃኒዓለም ይሁን። እኛ ልባችን ጠጣር ሆኖ ብናስቸግረውም በምህረቱ እየጎበኘን፣ ቸርነቱን እየገለጸልን ይገኛል። ባለቤቴ ስለመዳኑ ሕልም ያየችውም ጓደኛዬ አርባ ሓራ መድኃኒዓለም (መንዝ ማማ ምድር) ድረስ ሄዳ ስዕለቷን አግብታ ተመልሳለች። ይህ ከዚህ በላይ  ቀረብኩላችሁ ባለቤቴ የዘገበችውን ታሪክ ነበር። ይኸ ሁሉ ሲሆን እኔ ምንም የማውቀው ነገር አልነበረም። እኔ የነበርኩት በደስታ ዓለም ውስጥ ነበር። በሀገራችን ኦጋዴን አካባቢ እንዳለው ዓይነት ጣራውም ግድግዳውም በአፈር በተሠራ ቤት ውስጥ በተከመረ የስንዴ ምርት ላይ ስሮጥ ነበር የቆየሁት። ቤቱ ብዙ በሮች ስላሉት በአንዱ በር ገብቼ በሌላው እወጣለሁ። እንደገና ተመልሼ እገባና በእህሉ ላይ እሮጣለሁ። ቤቱ ውስጥ ደማቅ ብርሃን አለ። ብርሃን ከየት እንደሚበራ አይታወቅም። መቆም የለም መሮጥ ብቻ። እረፍት አልነበረኝም። ሆኖም ከደስታ በስተቀር ድካምአይሰማኝም ነበር። ከነቃሁ በኋላ ወደ ቤቴ እንዲወስዱኝ ነበር የጠየቅሁት። በሆስፒታል አልጋ ላይ መቆየቱ ደስ አላለኝም። ከደስታ ዓለም ተመልሼ እንደገና ወደ ጭንቀት መግባት አልፈለግሁም። በእግዚአብሔር ደግነት ፍጹም ጤነኛ ሆኜ ከሆስፒታል ከወጣሁ በኋላ አሁን ወደ ሥራዬ ተመልሻለሁ። ቢገርማችሁ በቀን እስከ አስራ ስድስት ሰዓት ድረስ እየሰራሁ ነው።



በቅዱሱ ሥፍራ በአርባ ሓራ መድኃኒዓለም ገዳም ተገኝቼ እግዚአብሔርን ለማመስገን እንድበቃ በዝግጅት ላይ  እገኛለሁ። ሐኪሞቹ በኔ ነገር እስከ አሁን ድረስ ግራ እንደተጋቡ አሉ።ምን ዓይነት እምነት ነው ያላችሁ!” በማለት  በተደጋጋሚ ይደነቃሉ። የመንፈስ ቅዱስን ሥራ ሊመረምሩትና ሊደርሱበት እንደማይችሉ የታወቀ ነው። አንድ ከፍተኛ  ትምህርት ግን አግኝተዋል ብዬ እገምታለሁ። ሳይንስ ሊደርስበት የማይችል የመንፈስ ቅዱስ ኃይል እንዳለ። ሰው ከሞተ  በኋላ እንደገና መነሳት እንደሚችል። እግዚአብሔር አልዐዛርን በሞተ ከአራት ቀናት በኋላ ያስነሳው ከሞት ስለመነሳቱ  ተጠራጣሪዎች ጥያቄ እንዳያነሱ ነበር። አልዐዛርን እንደሞተ ዕለቱን ቢያስነሳው ኖሮአልሞተም፣ መች ሞተና ነው?” ብለው ይከራከሩ ነበር። እኔንም እግዚአብሔር የመለሰኝ (ያስነሳኝ) በሐኪሞች ግምት እንደገና በሕይወት ለማንሰራራት  ከማልችልበት ሁኔታ ነው። እግዚአብሔር በኔ በኃጢአተኛው አድሮ ክብሩ