Sunday, January 25, 2015
Wednesday, January 14, 2015
ሙስሊሙ ያገኘው የቅድስት ሥላሴ ቤተክርስቲያን
በ02/05/07የየረር በር ጽርሐ አርያም ቅድስት ሥላሴ ቤተክርስቲያን ሰንበት ትምህርት ቤት የጥምቀት
አገልግሎትን ምክንያት በማድረግ ለአገልጋዮችየጥምቀት በዓልን መሠረታዊ ምንነት፣ ትውፊታዊ አከባበርና የወጣቶች
ተሳትፎን የሚዳስስ ትምህርት/ሥልጠና እንድሰጥ ጠቁመውኝ በታሪካዊውቤተክርስቲያን ተገኝቼ ነበር፡፡
የሥልጠናውን/ትምህርቱን ሙሉ ይዘት ከዚህ በፊትም በዚሁ በክታበ ገፄ/ፌስቡክ/ ላይ ለጥፌው ስለነበርከይዘቱ ይልቅ
ዛሬ የቤተክርስቲያኑንና የሰንበት ትምህርት ቤቱን አንዳንድ አስገራሚ እውነታዎች ላካፍላችሁ፡፡
የየረርበር
ጽርሐ አርያም ቅድስት ሥላሴ ቤተክርስቲያን በተለይ ከዛሬ አሥር ዓመታት በፊት ድፍን አዲስ አበባ የሚያወራለት፣
ሕዝብ የሚጎርፍበትቤተክርስቲያን ነበር፡፡ ቤተክርስቲያኑ የመወያያ ርእስ እንዲሆን ያደረገው ደግሞ አንድ ሙስሊም
በራእይ ተገልጦለት አገኘው መባሉነበር፡፡ ሙስሊሙ ራሱ እንደሚተርከው አሁን ቤተክርስቲያኑ ያለበትን ቦታ
ገዝቶ ይኖርበት ነበር፡፡ አንድ ቀን ቤት ሊሠራ ድንጋይ ሊያነሣ ሲል “ድንጋዩየኔ ነውና አስቀምጥ” የሚል ድምጽ
ይሰማል፡፡ ሌሊት ሌሊትም በግቢው ውስጥ የዝማሬ ድምጽ እየሰማ ወደ ውጭ ሲወጣ ሕፃናት እየዘመሩይመለከታል፡፡ በዚህም
ምክንያት ቦታው እንዲቆፈር ያደርግና ቤተክርስቲያኑ ተገኘ፡፡አሁን ሙስሊሙ ከእስልምናም ከክርስትናም ነፃ ሆኜጥቂት
መቆየት እፈልጋለሁ በማለቱ በዚያው አካባቢ እንዲሁ እየኖረ ሲሆን የእርሱ ልጆች ግን ተጠምቀው ወደ ክርስትና
መመለሳቸውንናበቅዳሴ ጊዜና ዘወትር ከቤተክርስቲያኑ እንደማይጠፉ የሰንበት ትምህርት ቤቱ አባላት አጫውተውኛል፡፡
ከዚህታሪክ
ባሻገር መጀመሪያ የቤተክርስቲያኑ መኖር የተገለፀው በገዳም ለሚኖሩ አባቶች እንደ ነበር የሚናገሩ ሰዎች በተለይ
ከቅርብ ጊዜወዲህ ያሉ ሲሆን በጉዳዩ ላይ ጥናት እየተካሄደ መሆኑንም አገልጋዮቹ ጠቁመውኛል፡፡ በምስሉላይ
የሚታየው ሕንፃ ቤተክርስቲያን ተቆፍሮ በተገኘው ላይ የተገነባ ሲሆን ወደ ውስጥ ለገባ ሰው የተገኘው ጥንታዊው
ቤተክርስቲያንበውስጡ ይታያል፡፡ ከቤተክርስቲያኑጋር ከ300 በላይ የቅዱሳን አፅምና ሌሎች ቅርሶችም አብረው ተገኝተው
በዚያው የሚገኙ መሆናቸውተጠቁሟል፡፡
ቤተክርስቲያኑከቅድስት ሥላሴ ታቦት በተጨማሪ የአቡነ አረጋዊ ታቦትም አለው፡፡
ከዚህበላይ የሚታየው የቤተክርስቲያኑ የድንጋይ ደወል ሲሆን ታሥረው የሚታዩት ድንጋዮች በሚያስደንቅ ሁኔታ እንደ
ብረት ድምጽን የሚያወጡናቸው፡፡ አብሮኝ የነበረው አገልጋይ በእጁ ነካ ሲያደርጋቸው ከድንጋይ የማይገኝ ድምጽን
ማውጣታቸውን አስተውያለሁ፡፡ ቤተክርስቲያኑበመጀመሪያ እስካለፉት ጥቂት ዓመታት ድረስ እንደገዳም ይተዳደር
ነበር፡፡ እንደገዳም ይተዳደር በነበረበት ወቅት ማንም ሰው ገናቅጽሩ ውስጥ ሳይገባ በሩቁ ጫማውን እንዲያወልቅ ሕግ
ነበር፡፡ አሁን ግን ጉዳዩ በፍላጎት ሆኖ ጫማ የሚወለቀው ወደ መቅደስ ሲገባሆኗል፡፡ አንዳንድ አገልጋዮችና ምዕመናን
ግን አሁንም ድረስ ጫማቸውን እያወለቁ ወደ ግቢው ሲገቡ አስተውያለሁ፡፡
የደብሩሰንበት ትምህርት ቤት አባላት በአብዛኛው በምስሉ ላይ እንደሚታየው ወደ ግቢው ሲገቡ ጫማቸውን አውልቀው
ነው፡፡ ላገለግል የሄድኩበትጉባኤ እስኪጀመር ድረስ ሁሉም በባዶ እግራቸው መሆናቸው አስገርሞኝ ስጠይቃቸው ይህንን
በውስጠ ደንብም ሆነ ሕግ ተገደው ሳይሆንበፍቅርና በፍላጎት የቦታውን ቅድስና ለመዘከር የሚያደርጉት መጽሐፍ ቅዱሳዊ
ተግባር መሆኑን ገልፀውልኛል፡፡
Tuesday, November 25, 2014
መንግስተ ሰማያት እውን ናት - እማሆይ ወለተ ጊዮርጊስ - Heaven is for real -Near death experience
መንግስተ ሰማያት እውን ናት - እማሆይ ወለተ ጊዮርጊስ በኦፕራሲዮን ግዜ መንግስተ ሰማያት እና ሲኦልን እንዳዩ ይመሰክራሉ::
Heaven is for real - Emahoy Welete Giorgis- Near death experience
Heaven is for real - Emahoy Welete Giorgis- Near death experience
ባሕታዊ አባ ገብረ ጊዮርጊስ
Subscribe to:
Posts (Atom)