ሸንኮራ ዮሐንስ ከአየር ላይ ሲታይ የገደሉ መሐል ጸበሉ ያለበት ነው ያች 8የማይበልጡ የጭራሮ ጎጆ የነበረች
መንደር ዛሬ የፈውስ መዲና ሆና ዘምናለች 20 ሰው የምትይዘው ቤተክርስቲያን ዛሬ ታላቅ ህንጻ ተገንብቶባታል
የነፍስም የስጋም ሆስፒታል ሆናለች አጥቢያዋ
አቶ በላይ ደምሴ የተባሉ አባት ከባሌ ክፍለሐገር
ሁለቱም ጆሮዋቸው መስማት አይችልም ነበር አባታችን የመጥምቁን የፈውስ ዝና ቢሰሙም ወደ ሸንኮራ ለመምጣት አቅም ያጣሉ አንድ በአካባቢያቸው የሚያውቁትን ወጣት ጸበል አምጣልኝ ብለው 500 ብር ለትራንስፓርት ሰጥተው ይሸኙታል ልጁ እዛው ሲያውደለድል ተደብቆ ከርሞ ከወንዝ ውሐ ቀድቶ ይሰጣቸዋል አቶ በላይም የተሰጣቸውን ውሐ በእምነት ሲጠጡት ጆሮዋው ተከፈተ ድንቅ ነው በዚያው ቅጽበት የወጣቱ ሁለቱም ጆሮ መስማት አቆመ ይህ ወጣት ጥፋቱን ያውቃልና በንስሐ አባቱ አማካኝነት ወደ ሸንኮራ መጥቶ ለነፍስም ለስጋው ንስሐ ገብቶ ቀኖና ተቀብሎ ይፍታህ በሚባልበት 14ኛ ቀኑ ላይ ጆሮው ተከፍቶ በአንደበቱ የሰራውን ጥፋትና የተደረገውን ድንቅ ተአምር መስክሮዋል ይህን ያደረገ የመጥምቁ አምላክ ክብር ይግባው አሜን
ወ/ሮ ሐዱሽ ገ/ዋህድ ይባላሉ ከገጠሪቱ ኢትዮጵያ 16 አመት የታወረ አይናቸውን ለመታከም ነው ወደ መሐል ሐገር
የመጡት አዲስ አበባ ኦፕራሲዮን ቢያደርጉም ተስፋ የለውም እንዲሁ ይኑሩ ይባላሉ ቤተክርስቲያን ለመሳለም ሄደው
የሸንኮራን ታሪክ ሰዎች ሲያወሩ ሰምተው አድራሻ ጠይቀው መሪ አስታማሚ ይዘው ጉዞ ወደመጥምቁ ቤት ተከራይተው ጸበሉን
መጠመቅ ይጀምራሉ 8ኛ ቀን ላይ ወደ ጸበሉ መውረጃ ገደሉን መንገድ ከመሪያቸው ጋር ይጀምራሉ መሪያቸው ድንገት ወደ
ጫካ ለሽንት ትገባለች እሳቸውም ከምቆም ብለው መንገድ ይጀመራሉ በምርኩዛቸው ድንገት ያላሰቡት ነገር ተከሰተ
የለበሱትን ነጠላ ቆንጥር ያዘብኝ መንገዱም ቁልቁለት ላይ ነበርና የያዝኩትምርኩዜም ከእጄ አምልጦ ተንሸራቶ ርቆ
ወደቀ በቆምኩበት ደነገጥኩኝ ተማረርኩኝ ሞቴን ተመኘው አዘንኩኝ ምነው ዮሐንስ ብዬ ነጣላዬን ከእሾኩ ለማላቀቅ ፊቴን
ሳዞር የጠፋው አይኔ ቦግ አለ ማመን አልቻልኩም እየተመራው የወረድኩትን ገደል ህዝቡን እየመራው በእልልታ በሆታ
ወጣውት ብለው መስክረዋል እኝህ እናት በወቅቱ ከደስታቸው ብዛት ግቢው ውስጥ ይንከባለሉ ነበር ይህን ያደረገ
የመጥምቁ አምላክ ክብር ይግባው አሜን
ሸንኮራን የሚያውቅ ሁሉ ለምንትዬ ዮሐንስ ምን እንዳደረገላት የማያውቅ የለም በስምዕ ጽድቅ ጋዜጣ በዜና
ቤተክርስቲያን በደብሩ መጽሔት ታሪክዋ በሰፊው ተመዝግቦዋል ስቃየ ብዙዋ እህታችን አዲስ አበባ ጎፋ መካነ ህያዋን
ቅዱስ ገብርኤል ሰንበት ተማሪ የሆነችው ምንትዬ ታሪክዋ ሰፊ ስቃይዋ ዘግናኝ ነበር አትተኛም አትቀመጥም አትራመድም
የዮሐንስ ያለህ ያዮ ይመስክሩ በልብ በኩላሊት በደም ብዛት እረ የበሽታዋ አይነት ብዛቱ መለኮትን ባጠመቀበት እጁ
ዮሐንስ የታሰረችበትን ደዌ ሁሉ ፈታት ከሰውነትዋ የሚወደው ደምና መግል ተወግዶ ሞትሽን ጠብቂ በሳጥር ተቁዋጥረሽ
ልትጣይ ነው የተባለችው ምንትዬ ይህው ዛሬ በእግርዋ ቆማ የመጥምቁን ደጅ ጥዬ አልሄድም ብላ እንግዳ ተቀባሪ
ጸበልተኛ አጉራሽ ሆናለች እስቲ ሰኔ 30 ኑና የመጥምቁን ታሪክ ጽናት ትእግስትዋን ተማሩ ህወታችሁን አለምልሙ
የምስጋናን ህይወት እንድትጀምሩ የቀጠሮ ሰው ይበለን አሜን
እናታችን ከባሌ ነው የመጡት ያወኩዋቸው ጫካ ጸበል ለመጠጣት ወጥቼ ነው ወይዘሮ ደሜ ይባልሉ ከንፈራቸው ላይ በወጣ
ቁስል ምክንያት መላ ፊታቸው ይቆስልና ሽታም ያመጣል በሐኪም ብዙ አቅሜን ጨረስኩኝ ጠንቁዋይም ገንዘቤን ጨረሰብኝ
የሸንኮራ ዮሐንስን ድንቅ ተአምር ሰማው ተነስቼ መጣው ጠረኔ ከሰው ስለማያቀላቅልና የቆሰለው ፊቴንም ደፍሮ የሚያይ
ስለሌለ ጫካ እውላለው ጸበልም ሰው ሳይኖር እወርዳለው አሉኝ በእውነት ዘግናኝ አጋጣሚ ነበር 8አመታት የተሰቃዮበት
ያ የቆሰለው ፊት እንደ ሰንኮፍ ውልቅ ብሎኝ በቁስል የነፈረው ከንፈራቸው ደርቆ ጠረን መአዛቸው ተለውጦ በዛ
ህመምተኛ በነበረ አንደበታቸው እልልታን ብቻ ሳይሆን ንስሐ ገብተው ስጋ ወደሙም ተቀብለው ብጽአታቸውን በእጃቸው
የፈተሉትን ግምጃ ስእሉን ሲጋርዱ አይቻለው እኝህ ምስኪን እናት ሸንኮራ ለጥቂት ሳምንታት ተቀምጠው ነው ፈውስን
ያገኙ ዛሬ በየአመቱ ሰኔ 30 ከደጁ አይቀሩም የኛንም ክፉ መአዛ አምላከ ዮሐንስ ያጣፍጥልን አሜን
በሸንኮራው ዮሐንስ ጸበል ከጡት ካንሰር የዳነችው
የአጥቢያችን ብስራተ ገብርኤል ነዋሪ ሳባ ሐብቶም እህቴም እናቴም የሆነችው ሳባ ወደ ሸንኮራ ከመሄድዋ በፊት በጽኑ ስቃይ በካንሰር በሽታ ትሰቃይ ነበር በወቅቱ የነበራት ስቃይ ከቃላት በላይ ነበር አቅሙም ነበራትና ያልደረስችበት ህክምና የለም በተለይ የግል ሐኪምዋ ፕሮፌሰር ታዬ እንዲሁም በጥቁር አንበሳ ብሩክ ክሊኒክ ህክምናዋን ብትከታተልም ካንሰሩ ወደ መላ አካላትዋ ተሰራጭቶ ሞትዋን ስትጠብቅ ወደ ምንጃር ሸንኮራ ጸበል በመምጣት ሸንኮራ በወቅቱ ጥቂት ጎጆዎች ብቻ የነበረባት ትንሽ መንደር ነበረች ከሞላ ቤትዋ ወጥታ የጭራሮ ጎጆ ተከራይታ ጸበልዋን ጀመረች ጽናትዋ ትእግስትዋ ይደንቅ ነበር ቅዱስ ዮሐንስ ደጅ ጥናትዋን ስቃይዋን ተመልክቶ ከአምላኩ አማልዶ በህልም በራእይ ሳይሆን በገሐድ በመገለጥ እንደዳበሳትና 4አመት በዘግናኝ ሁኔታ ያበጠው ሰውነዋ ፈንድቶ ብዙ ደምና መግል ከሰውነትዋ ወጥቶ ፈውስን ተቀዳጅታለች አዲስ አበባ መጥታ ተመርምራ ሙሉ ጤናማ መሆንዋን አረጋግጣለች ይህው 17 አመት ሆናት የቀብር ማስፈጸሚያ በርበሬ የተፈጨላት ጤፍ የተሸመተላት የንፍሮ እህል የተለቀመላት መግነዝ ጨርቅዋን ከቤት ብሞትም ብላ ይዛ የወጣችው ሳባ መጥምቁ ዳብሶ ፈውስን አግኝታ ለእንባ አድርቅ የታሰበው እህል ለዝክር ሆነንዋል ሳባቆማ ትሆዳለች በእለተ ፋሲካ በየአመቱ ቤትዋን በአወደ አመት ዘግታ የአክፋይዋን በመጥምቁ ደጅ ላሉ ካህናት ጸበልተኞች ነዳያን ይዛ ጾም ታስፈታለች መጥምቀ መለኮት ነብየ ልኡል እኛ ከማናውቀው የታሰርንበት ክፉ ነገር ይፍታን አሜን

ነቢየ ልኡል ሐዋርያው ሰማእቱ መጥምቀ መለኮት ድንግላዊው ባህታዊው ካህኑ ከሴት ከተወለደ የሚተካከለው የሌለ ቅዱስ
ዮሐንስ በልደቱ የአባቱን የታሰረ አንደበት የፈታ የስሙ ትርጉዋሜ የሁሉ ደስታ የሆነ ዛሬም በደዌ የታሰረውን በጸበሉ
የሚፈታ ቃልኪዳኑ ዛሬም ያልተሻረ በመጥምቁ ደጃፍ ያገናኘን በፎቶ የምናየው ወንድም በሸንኮራ ጸበል የተፈወሰ ነው
የቀጠሮ ሰው ይበለን አሜን
የቀጠሮ ሰው ይበለን አሜን
ፀበሉ ፈዋሽ ዘብር ቅድስ ገብርኤል
ምንጭ