በሸንኮራው ቅዱስ ዮሐንስ ጸበል እጹብ ድንቅ ተአምራት የተደረገላቸው ግብጻዊትዋ እናቴ
ወ/ሮ ናዲያ ሁለተኛዋ እናቴ ኢትዮጵያ አቡነ ዘበሰማያት ብለህ እራይ የምታይባት ቅድስት ምድር ናት የሚሉ ከ40 አመት በላይ የሚኖሩት እዚሁ አዲስ አበባ ነው እኔ የማውቃቸው አፍ ከፈታው ከህጻንነት እድሜዬ ጀምሮ ነው በአፍሪካ ህብረት ከወላጅ እናቴ ጋር ረጅም አመት ሰርተዋል ዛሬም በመስራት ላይ ይገኛሉ እኝህ እናት ግብጽ ደማንሁር የምትኖር አብሮ አደግ እህታቸው በማህጸንዋ ውስጥ ምን እንደሆነ ያልታወቀ ነገር ተገኝቶ ለ5አመታት ስትሰቃይ ልጅ ነው አንዳንዴምን እጢ ነው ስትባል በመጨረሻ ወደ አውስትራሊያ ሄዳ ኦፕራሲዮን ብትደረግም ምንም ማህጸንዋ ውስጥ አልተገኘም በቅድመ ምርመራ ዶክተሮቹ ምንነቱ ያልተለየ ነገር አለ መውጣት አለበት ብለው ነው የከፈትዋት በመጨረሻም ወደ ግብጽ ተስፋ ቆርጣ ተመልሳ ሳለ ወ/ሮ ናዲያ የቀድሞውን ፓትርያርክ አቡነ ጳውሎስን ከቅድስት ስላሴ ቀዳሽ እያሉ ከ60ቹ ጀምሮ ይተዋወቃሉና ቡራኬ ለመቀበል ሄደው ችግራቸውንም አውርተው ሲጨርሱ ፓትርያርኩ የዮሐንስን ጸበል ላኩላት ብለዋቸው ኖሮ እኔን ይጠይቁኛል ግዜ ስላልነበረ ከወ/ሮ ሳባ ሐብቶም ቤት ጸበሉን ተቀብዬ ሰጠዋቸው ታማሚዋ ጸበሉ ግብጽ ደርሶ በቀመሰችበት ደቂቃ ያ ያሰቃያት ለሐኪሞች ከአእምሮ በላይ የነበረው ነገር እንደ ልጅ 5አመት ይዛው የተንከራተተችው ማህጸዋ ተከፍቶ የተሰወረው 2ኪሎ እጢ ወጣ እላይዋ ያደረው እርኩስ መንፈስም ታሪኩን ለፈለፈ ዛሬ እህታችን ትዳር ይዛ የ1 ልጅ እናት ሆና ካናዳ ትኖራለች መጥምቁንና ያከበረውን አምላኩን ሸንኮራ ድረስ መጥታ ደጁን ስማ ስጦታዋን አስገብታለች ለናዲያ ያደረገውን አስደናቂ ተአምር ወደፊት እናወራዋለን የመጥምቁ አምላክ ክብር ምስጋና ይግባው አሜን

የመጥምቁ ዮሐንስን ድንቅ ተአምር በህጻን አንደበቱ የመሰከረው ህጻን ፍቅረ ዮሐንስ ናዝሬት ከተማ ተወልዶ
ያደገው ይህ ልጅ ባጋጠመው የአጥንት ካንሰር ምክንያት በህክምና መፍትሔ ሲጠፋ ወላጅ እናቱ ወደሸንኮራ ዮሐንስ ይዛው
ትመጣለች ክብር ምስጋና ለዮሐንስ አምላክ ካርድ አውጣ ኤክስሬ ተነሳ መድሐኒት ግዛ የለ የመጥምቁ ጸበል የታመመ
እግሩ ሲመታው ያሰቃየው የነበረው በነቀርሳ(ካንስር)የተበላው አጥንቱ ስጋውን ዘንጥሎ ወጥቶ ጤናውን አግኝቶዋል ቆሜ
እራመዳለው ኩዋስ እጫወታለው ትምህርቴንም ጀምሬያለው ብሎ በህጻን በሚጣፍጥ አንደበቱ የወጣለትን አጥንት ይዞ
ከወላጅ እናቱ ጋራ ምስክርነቱን በአወደ ምህረቱ ሰጥቶዋል የዮሐንስ አምላክ ክብር ይግባው