Monday, June 13, 2016

ተነግሮ የማያልቀው የሸንኮራ ዮሐንስ ድንቅ ተአምር

ስለ ሸንኮራ ቅዱስ ዮሐንስ ጸበል ምን ያህል ያዉቃሉ? የሸንኮራ ዮሐንስ ፀበል በአማራ ክልል በሰሜን ሸዋ ዞን በምንጃር ሸንኮራ ወረዳ ንዑስ ከተማ በሆነችዉ በባልጪ ከተማ አጠገብ በርካታ ተገልጋዮች ከተለያዩ ቦታዎች በመምጣት ፈውስ የሚያገኙበት ፀበል ነው፡፡ ፀበሉ በፈዋሽነቱ በይፋ መታወቅ የጀመረዉ:- አባ ካሳ የሚባሉ መናኝ ባህታዊ በሸንኮራ ቅ/ዮሐንስ ቤ/ክ መቃብር ቤት ዉስጥ ዘግተዉ ይኖሩ ነበር፡፡ ከእለታት አንድ ቀን በህልማቸዉ ከቤተ ክርስቲያኑ በስተምስራቅ ከወንዙ ዉስጥ ጸበል ፈልቋልና ወርደህ አይተህ ለህዝቡ ንገር እዉራን የሚያበራ፣ ለምፅ የሚያነፃ፣ ጎባጣ የሚያቀና ጸበል ፈልቋል በልና ንገር ብሎ በህልማቸዉ ነገራቸዉ፡፡

ሲነጋ ጠዋት በተነገራቸዉ መሰረት ወደ ወንዝ ወርደዉ ጸበሉን ሲፈልጉ አላገኝ አሉት፡፡ አባ ካሳ የዕድሜ ባለፀጋ ሲሆኑ ሲፈልጉ ዉለዉ በድካም ወደ ቤታቸዉ ተመለሱ፡፡ እንደገና ሌሊት በህልማቸዉ "ጠዋት ተነሣና ወደ ጸበሉ ዉረድ ጸበሉ ከጫካ ዉስጥ ፈልቆ ታገኘዋለህ ከፊ ከፊትህ የምትመራህ ርግብ ታሳይሃለች"አላቸዉ፡፡ በታዘዙት መሰረት ከጠዋት ተነስተዉ ወደ ወንዝ ሲሄዱ ርግብ ከፊት ከፊት እየመራቻቸዉ ከወንዙ ዉስጥ ሲደርሱ ጸበሉ ከፈለቀበት ገደል ላይ ክንፏን ዘርግታ አረፈች፡፡ከዚያም አባ ካሣም እግዚአብሔርን አመስግነዉ የፈለቀዉን ጸበል ጠጥተዉ እግራቸዉን ክፉኛ በሽታ ያማቸዉ ስለነበር ጸበሉን ሲያስነኩት ከያዛቸዉ በሽታ ወዲያዉኑ ተፈዉሰዋል፡፡ ከዚህ በኋላ አባ ካሳ የፈለቀዉን ጸበል ለህዝቡ ነግረዉ ሚያዝያ 30 ቀን ታቦተ ህጉ ወደ ጸበሉ ወርዶ በደማቅ ሁኔታ ተክብሯል፡፡ ይህንን ራዕይ ያዩት ሚያዝያ 15ቀን 1654 ዓ.ም ገደማ ሲሆን 354 ዓመት ያስቆተረ ጸበል ነዉ ተብለዉ ይገመታል፡፡ የቅዱስ ዮሐንስ በረከት ከሁላቸን ጋር ይሁን አሜን ።


ቤቱ ከአፋፍ ላይ ጸበሉ ከጅረት የድውያን ዳባሽ መጥምቀ መለኮት የስሙ ትርጉዋሜ ፍስሐ ወሐሴት በልደቱ የፈታ የአባቱን አንደበት እማሆይ ሂሩተ ገብርኤል ይባላሉ ተወልደው ያደጉት እዚሁ አዲስ አበባ ነው ትምህርታቸውን ጨርሰው ዮንቨርስቲም የሁለተኛ አመት ተማሪ ሳሉ በደረሳቸው መለኮታዊ ጥሪ በምናኔ ወደ ገዳም በመግባት ለ5 አመታት አገልግለው ደጅ ጠንተው በገዳሙ ማህበር ፈቃድ ምንኩስናቸውን ተቀብለው አገልግሎታቸውን በሰፊው በመስጠት ላይ ሳሉ ድንገት ባላሰቡት ሁኔታ በጡት ካንሰር በሽታ ይለከፋሉ አዲስ አበባ ለህክምና በመምጣት በጥቁር አንበሳ ሆስፒታልና በሌሎችም የግል ህክምና መስጫ ምርመራ ቢያደርጉም የታመመው አካል በአስቸኩዋይ ካልተቆረጠ ካንሰሩ ይሰራጫል ይባላሉ ህመሙ ከባድና ጽኑ ነበር በተለይ የጨረር ህክምና ተብለው የባሰ ተሰቃዮ እማሆይ ምርር ብለው ያለቅሳሉ ገና በማለዳ ነፍሴን ለገነት ስጋዬን ለአራዊት ብዬ መንኜ እንዴት ገላዬ ተገልጦ ክብሬ ይቃለላል ይህስ እንዲሆን አምላኬ ለምን ፈቀድክ ብለው ያዝናሉ የታመመ አካላቸውን ለማስቆረጥ ቀጠሮ ይይዛሉ እማሆይ እንደተናገሩት ፒያሳ አካባቢ ነዳይ መስለው ተሰውረው የሚኖሩ ባህታዊ ከጊዮርጊስ ቤተክርስቲያን ስወጣ "ሸንኮራ ዮሐንስ ሂጂ አንቺ ፈላሲ "ይሉኛል የምን እብድ ነው ብዬ አለፍኩት ክንክን አደረገኝና ተመልሼ ባይ ጠፉብኝ ልቤ ተነሳሳ ስቃዮ ደግሞ ረፍት ነሳኝ ደምና መግል ከታመመው አካሌ ይወርዳል እንደምንም ሸንኮራ መሪ ሰው ይዜ ገባው እምነቱን ጸበሉን ስቀባው ከረምኩኝ ይፈስ የነበረው የደም ጎርፍ ጠፋ ህመሜም ቀነሰ እንቅልፍም በደንብ እተኛ ጀመር ሰላሜ ተመለሰ የቀጠሮውም ቀን አለፈ ፍጹም ጤነኛ ሆንኩኝ የአይነ ከርሙ ባህታዊ ነብየ ልኡል ሰማእቱ መጥምቁ የጌታዬ የአምላኬ ወዳጅ በአድያመ ዮርዳኖስ በሸንኮራ ምድር በስሙ በፈለቀው ጸበል ጡቴን ከመቆረጥ አዳነኝ ዳግም ተመርምሬ ፍጹም ጤነኛ ነሽ ተብያለው ወደምወደው ገዳሜ በደስታ ተመልሻለው ብለዋል እናታችንይህን ያደረገ የዮሐንስ አምላክ ክብር ይግባው ይግባው ከኛም የማይበጀንን ነገር ቆርጦ ይጣልልን አሜን

Thursday, June 9, 2016

ተአምራት በሸንኮራ ደብረ መንክራት ቅዱስ ዮሐንስ - 2

ሸንኮራው ቅዱስ ዮሐንስ ጸበል እጹብ ድንቅ ተአምራት የተደረገላቸው ግብጻዊትዋ እናቴ
ወ/ሮ ናዲያ ሁለተኛዋ እናቴ ኢትዮጵያ አቡነ ዘበሰማያት ብለህ እራይ የምታይባት ቅድስት ምድር ናት የሚሉ ከ40 አመት በላይ የሚኖሩት እዚሁ አዲስ አበባ ነው እኔ የማውቃቸው አፍ ከፈታው ከህጻንነት እድሜዬ ጀምሮ ነው በአፍሪካ ህብረት ከወላጅ እናቴ ጋር ረጅም አመት ሰርተዋል ዛሬም በመስራት ላይ ይገኛሉ እኝህ እናት ግብጽ ደማንሁር የምትኖር አብሮ አደግ እህታቸው በማህጸንዋ ውስጥ ምን እንደሆነ ያልታወቀ ነገር ተገኝቶ ለ5አመታት ስትሰቃይ ልጅ ነው አንዳንዴምን እጢ ነው ስትባል በመጨረሻ ወደ አውስትራሊያ ሄዳ ኦፕራሲዮን ብትደረግም ምንም ማህጸንዋ ውስጥ አልተገኘም በቅድመ ምርመራ ዶክተሮቹ ምንነቱ ያልተለየ ነገር አለ መውጣት አለበት ብለው ነው የከፈትዋት በመጨረሻም ወደ ግብጽ ተስፋ ቆርጣ ተመልሳ ሳለ ወ/ሮ ናዲያ የቀድሞውን ፓትርያርክ አቡነ ጳውሎስን ከቅድስት ስላሴ ቀዳሽ እያሉ ከ60ቹ ጀምሮ ይተዋወቃሉና ቡራኬ ለመቀበል ሄደው ችግራቸውንም አውርተው ሲጨርሱ ፓትርያርኩ የዮሐንስን ጸበል ላኩላት ብለዋቸው ኖሮ እኔን ይጠይቁኛል ግዜ ስላልነበረ ከወ/ሮ ሳባ ሐብቶም ቤት ጸበሉን ተቀብዬ ሰጠዋቸው ታማሚዋ ጸበሉ ግብጽ ደርሶ በቀመሰችበት ደቂቃ ያ ያሰቃያት ለሐኪሞች ከአእምሮ በላይ የነበረው ነገር እንደ ልጅ 5አመት ይዛው የተንከራተተችው ማህጸዋ ተከፍቶ የተሰወረው 2ኪሎ እጢ ወጣ እላይዋ ያደረው እርኩስ መንፈስም ታሪኩን ለፈለፈ ዛሬ እህታችን ትዳር ይዛ የ1 ልጅ እናት ሆና ካናዳ ትኖራለች መጥምቁንና ያከበረውን አምላኩን ሸንኮራ ድረስ መጥታ ደጁን ስማ ስጦታዋን አስገብታለች ለናዲያ ያደረገውን አስደናቂ ተአምር ወደፊት እናወራዋለን የመጥምቁ አምላክ ክብር ምስጋና ይግባው አሜን

 
የመጥምቁ ዮሐንስን ድንቅ ተአምር በህጻን አንደበቱ የመሰከረው ህጻን ፍቅረ ዮሐንስ ናዝሬት ከተማ ተወልዶ ያደገው ይህ ልጅ ባጋጠመው የአጥንት ካንሰር ምክንያት በህክምና መፍትሔ ሲጠፋ ወላጅ እናቱ ወደሸንኮራ ዮሐንስ ይዛው ትመጣለች ክብር ምስጋና ለዮሐንስ አምላክ ካርድ አውጣ ኤክስሬ ተነሳ መድሐኒት ግዛ የለ የመጥምቁ ጸበል የታመመ እግሩ ሲመታው ያሰቃየው የነበረው በነቀርሳ(ካንስር)የተበላው አጥንቱ ስጋውን ዘንጥሎ ወጥቶ ጤናውን አግኝቶዋል ቆሜ እራመዳለው ኩዋስ እጫወታለው ትምህርቴንም ጀምሬያለው ብሎ በህጻን በሚጣፍጥ አንደበቱ የወጣለትን አጥንት ይዞ ከወላጅ እናቱ ጋራ ምስክርነቱን በአወደ ምህረቱ ሰጥቶዋል የዮሐንስ አምላክ ክብር ይግባው
 
 

Wednesday, June 8, 2016

ተአምራት በሸንኮራ ደብረ መንክራት ቅዱስ ዮሐንስ

ሸንኮራ ዮሐንስ ከአየር ላይ ሲታይ የገደሉ መሐል ጸበሉ ያለበት ነው ያች 8የማይበልጡ የጭራሮ ጎጆ የነበረች መንደር ዛሬ የፈውስ መዲና ሆና ዘምናለች 20 ሰው የምትይዘው ቤተክርስቲያን ዛሬ ታላቅ ህንጻ ተገንብቶባታል የነፍስም የስጋም ሆስፒታል ሆናለች አጥቢያዋ



















አቶ በላይ ደምሴ የተባሉ አባት ከባሌ ክፍለሐገር
ሁለቱም ጆሮዋቸው መስማት አይችልም ነበር አባታችን የመጥምቁን የፈውስ ዝና ቢሰሙም ወደ ሸንኮራ ለመምጣት አቅም ያጣሉ አንድ በአካባቢያቸው የሚያውቁትን ወጣት ጸበል አምጣልኝ ብለው 500 ብር ለትራንስፓርት ሰጥተው ይሸኙታል ልጁ እዛው ሲያውደለድል ተደብቆ ከርሞ ከወንዝ ውሐ ቀድቶ ይሰጣቸዋል አቶ በላይም የተሰጣቸውን ውሐ በእምነት ሲጠጡት ጆሮዋው ተከፈተ ድንቅ ነው በዚያው ቅጽበት የወጣቱ ሁለቱም ጆሮ መስማት አቆመ ይህ ወጣት ጥፋቱን ያውቃልና በንስሐ አባቱ አማካኝነት ወደ ሸንኮራ መጥቶ ለነፍስም ለስጋው ንስሐ ገብቶ ቀኖና ተቀብሎ ይፍታህ በሚባልበት 14ኛ ቀኑ ላይ ጆሮው ተከፍቶ በአንደበቱ የሰራውን ጥፋትና የተደረገውን ድንቅ ተአምር መስክሮዋል ይህን ያደረገ የመጥምቁ አምላክ ክብር ይግባው አሜን

ወ/ሮ ሐዱሽ ገ/ዋህድ ይባላሉ ከገጠሪቱ ኢትዮጵያ 16 አመት የታወረ አይናቸውን ለመታከም ነው ወደ መሐል ሐገር የመጡት አዲስ አበባ ኦፕራሲዮን ቢያደርጉም ተስፋ የለውም እንዲሁ ይኑሩ ይባላሉ ቤተክርስቲያን ለመሳለም ሄደው የሸንኮራን ታሪክ ሰዎች ሲያወሩ ሰምተው አድራሻ ጠይቀው መሪ አስታማሚ ይዘው ጉዞ ወደመጥምቁ ቤት ተከራይተው ጸበሉን መጠመቅ ይጀምራሉ 8ኛ ቀን ላይ ወደ ጸበሉ መውረጃ ገደሉን መንገድ ከመሪያቸው ጋር ይጀምራሉ መሪያቸው ድንገት ወደ ጫካ ለሽንት ትገባለች እሳቸውም ከምቆም ብለው መንገድ ይጀመራሉ በምርኩዛቸው ድንገት ያላሰቡት ነገር ተከሰተ የለበሱትን ነጠላ ቆንጥር ያዘብኝ መንገዱም ቁልቁለት ላይ ነበርና የያዝኩትምርኩዜም ከእጄ አምልጦ ተንሸራቶ ርቆ ወደቀ በቆምኩበት ደነገጥኩኝ ተማረርኩኝ ሞቴን ተመኘው አዘንኩኝ ምነው ዮሐንስ ብዬ ነጣላዬን ከእሾኩ ለማላቀቅ ፊቴን ሳዞር የጠፋው አይኔ ቦግ አለ ማመን አልቻልኩም እየተመራው የወረድኩትን ገደል ህዝቡን እየመራው በእልልታ በሆታ ወጣውት ብለው መስክረዋል እኝህ እናት በወቅቱ ከደስታቸው ብዛት ግቢው ውስጥ ይንከባለሉ ነበር ይህን ያደረገ የመጥምቁ አምላክ ክብር ይግባው አሜን

ሸንኮራን የሚያውቅ ሁሉ ምንትዬ ዮሐንስ ምን እንዳደረገላት የማያውቅ የለም በስምዕ ጽድቅ ጋዜጣ በዜና ቤተክርስቲያን በደብሩ መጽሔት ታሪክዋ በሰፊው ተመዝግቦዋል ስቃየ ብዙዋ እህታችን አዲስ አበባ ጎፋ መካነ ህያዋን ቅዱስ ገብርኤል ሰንበት ተማሪ የሆነችው ምንትዬ ታሪክዋ ሰፊ ስቃይዋ ዘግናኝ ነበር አትተኛም አትቀመጥም አትራመድም የዮሐንስ ያለህ ያዮ ይመስክሩ በልብ በኩላሊት በደም ብዛት እረ የበሽታዋ አይነት ብዛቱ መለኮትን ባጠመቀበት እጁ ዮሐንስ የታሰረችበትን ደዌ ሁሉ ፈታት ከሰውነትዋ የሚወደው ደምና መግል ተወግዶ ሞትሽን ጠብቂ በሳጥር ተቁዋጥረሽ ልትጣይ ነው የተባለችው ምንትዬ ይህው ዛሬ በእግርዋ ቆማ የመጥምቁን ደጅ ጥዬ አልሄድም ብላ እንግዳ ተቀባሪ ጸበልተኛ አጉራሽ ሆናለች እስቲ ሰኔ 30 ኑና የመጥምቁን ታሪክ ጽናት ትእግስትዋን ተማሩ ህወታችሁን አለምልሙ የምስጋናን ህይወት እንድትጀምሩ የቀጠሮ ሰው ይበለን አሜን

እናታችን ከባሌ ነው የመጡት ያወኩዋቸው ጫካ ጸበል ለመጠጣት ወጥቼ ነው ወይዘሮ ደሜ ይባልሉ ከንፈራቸው ላይ በወጣ ቁስል ምክንያት መላ ፊታቸው ይቆስልና ሽታም ያመጣል በሐኪም ብዙ አቅሜን ጨረስኩኝ ጠንቁዋይም ገንዘቤን ጨረሰብኝ የሸንኮራ ዮሐንስን ድንቅ ተአምር ሰማው ተነስቼ መጣው ጠረኔ ከሰው ስለማያቀላቅልና የቆሰለው ፊቴንም ደፍሮ የሚያይ ስለሌለ ጫካ እውላለው ጸበልም ሰው ሳይኖር እወርዳለው አሉኝ በእውነት ዘግናኝ አጋጣሚ ነበር 8አመታት የተሰቃዮበት ያ የቆሰለው ፊት እንደ ሰንኮፍ ውልቅ ብሎኝ በቁስል የነፈረው ከንፈራቸው ደርቆ ጠረን መአዛቸው ተለውጦ በዛ ህመምተኛ በነበረ አንደበታቸው እልልታን ብቻ ሳይሆን ንስሐ ገብተው ስጋ ወደሙም ተቀብለው ብጽአታቸውን በእጃቸው የፈተሉትን ግምጃ ስእሉን ሲጋርዱ አይቻለው እኝህ ምስኪን እናት ሸንኮራ ለጥቂት ሳምንታት ተቀምጠው ነው ፈውስን ያገኙ ዛሬ በየአመቱ ሰኔ 30 ከደጁ አይቀሩም የኛንም ክፉ መአዛ አምላከ ዮሐንስ ያጣፍጥልን አሜን

በሸንኮራው ዮሐንስ ጸበል ከጡት ካንሰር የዳነችው
የአጥቢያችን ብስራተ ገብርኤል ነዋሪ ሳባ ሐብቶም እህቴም እናቴም የሆነችው ሳባ ወደ ሸንኮራ ከመሄድዋ በፊት በጽኑ ስቃይ በካንሰር በሽታ ትሰቃይ ነበር በወቅቱ የነበራት ስቃይ ከቃላት በላይ ነበር አቅሙም ነበራትና ያልደረስችበት ህክምና የለም በተለይ የግል ሐኪምዋ ፕሮፌሰር ታዬ እንዲሁም በጥቁር አንበሳ ብሩክ ክሊኒክ ህክምናዋን ብትከታተልም ካንሰሩ ወደ መላ አካላትዋ ተሰራጭቶ ሞትዋን ስትጠብቅ ወደ ምንጃር ሸንኮራ ጸበል በመምጣት ሸንኮራ በወቅቱ ጥቂት ጎጆዎች ብቻ የነበረባት ትንሽ መንደር ነበረች ከሞላ ቤትዋ ወጥታ የጭራሮ ጎጆ ተከራይታ ጸበልዋን ጀመረች ጽናትዋ ትእግስትዋ ይደንቅ ነበር ቅዱስ ዮሐንስ ደጅ ጥናትዋን ስቃይዋን ተመልክቶ ከአምላኩ አማልዶ በህልም በራእይ ሳይሆን በገሐድ በመገለጥ እንደዳበሳትና 4አመት በዘግናኝ ሁኔታ ያበጠው ሰውነዋ ፈንድቶ ብዙ ደምና መግል ከሰውነትዋ ወጥቶ ፈውስን ተቀዳጅታለች አዲስ አበባ መጥታ ተመርምራ ሙሉ ጤናማ መሆንዋን አረጋግጣለች ይህው 17 አመት ሆናት የቀብር ማስፈጸሚያ በርበሬ የተፈጨላት ጤፍ የተሸመተላት የንፍሮ እህል የተለቀመላት መግነዝ ጨርቅዋን ከቤት ብሞትም ብላ ይዛ የወጣችው ሳባ መጥምቁ ዳብሶ ፈውስን አግኝታ ለእንባ አድርቅ የታሰበው እህል ለዝክር ሆነንዋል ሳባቆማ ትሆዳለች በእለተ ፋሲካ በየአመቱ ቤትዋን በአወደ አመት ዘግታ የአክፋይዋን በመጥምቁ ደጅ ላሉ ካህናት ጸበልተኞች ነዳያን ይዛ ጾም ታስፈታለች መጥምቀ መለኮት ነብየ ልኡል እኛ ከማናውቀው የታሰርንበት ክፉ ነገር ይፍታን አሜን

ነቢየ ልኡል ሐዋርያው ሰማእቱ መጥምቀ መለኮት ድንግላዊው ባህታዊው ካህኑ ከሴት ከተወለደ የሚተካከለው የሌለ ቅዱስ ዮሐንስ በልደቱ የአባቱን የታሰረ አንደበት የፈታ የስሙ ትርጉዋሜ የሁሉ ደስታ የሆነ ዛሬም በደዌ የታሰረውን በጸበሉ የሚፈታ ቃልኪዳኑ ዛሬም ያልተሻረ በመጥምቁ ደጃፍ ያገናኘን በፎቶ የምናየው ወንድም በሸንኮራ ጸበል የተፈወሰ ነው
የቀጠሮ ሰው ይበለን አሜን



ፀበሉ ፈዋሽ ዘብር ቅድስ ገብርኤል


 ምንጭ