Wednesday, January 4, 2017

የሰማዕቱ የቅዱስ ጊዮርጊስ ፀበል

ይህ የምታዩት የተአምረኛው የሰማዕቱ የቅዱስ ጊዮርጊስ ፀበል ነው። ይህ ፀበል ብዙ ድውያንን ከተለያዩ ሀገራት ዝናውን ታሪኩን በመስማት እየመጡ ከበሽታቸው ፀበሉን በመጠመቅ፣በመጠጣት ብዛት ያላቸው ሰወች ከስቃያቸው ተፈውሰዋል።

ፀበሉ የሚገኝበት አካባቢ በአማራ ክልል በሰሜን ጎንደር ዞን  በቋራ ወረዳ በበርሚል ቀበሌ ይገኛል። ሽር በማድረግ በሰማዕቱ ስም ይተባበሩን የሰማዕቱ በረከት ከሁላችን ጋር ይሁን አሜን።

Tuesday, December 27, 2016

በሻሌ ንቡ ቅ/ሚካኤል - Video

ዋካ ቅድስ ጊዮርጊስ ገዳም

በ15ክ/ዘመን የተመሰረተው አብነ ጵጥሮስ የቀደሱበት የባረኩት በደመና የመጣ ታቦት ቀድሞ ከ15ክ/ዘመን በፊት/ መንዝ ዋካየአብይ ገብረመንፈስቅድስ ገዳም/ ሲሆን 15ክ/ዘመን ላይ ዋካ ቅድስ ጊዮርጊስ ገዳም ተብላል፡፡በጣም ስለት ሰሚ ነው፡ጣልያን በወረረን ግዜ ቦንብ ጥለው ቤተክርስቲያኑን ሊያቃጥሉ ቢወረወሩ ቤተክርስቲያኑ አልቃጠል ሲላቸው ሰውን ፡ካህኑን እየገደሉ ቤተክርስቲያኑ አልቃጠል ሲላቸው የታቦቱን መጎናጸፍፊያ ለብሰው ሲሂድ ከዋካ ከቦታ አልፈው ሂደው ጉርሙኝ ቆላውየ4ሰዓት መንገድ ልብሱን ለብሶ ለብሰው ጣሊያኖቹ ሲሂድየአካባቢው ሰው /አቶ ተገኝ/የሚባሉ ሰው ይህ በምታዩት ጋሻ በመከት ጣሊያኖቹን በመግደልና ገደል በመክተት የጊዮርጊስ መጎናጸፊያ አስመልሰው መጎናጸፊያው(ልብሱ ):በዋካ ጊዮርጊስ ይገኝል፡፡

 




አቶ ተገኝ ጀግና ተብለው የደጃዝማች መሀረግ ሲሰጣቸው ቁረብ ሰጋወ ደሙ ተቀበሉ ሲላቸው በመንዝ አካበቢ ጀግና ሲሞት ቀረርቶ ;ይሸለላል;ይፎከራል ይህ ሳይደረግ ጀግና አይቀበርም፡፡እና አቶ ተገኝ ቁረብ ሲባሉ እኔን ጊዮርጊሰ ጀግና አርጎ ጠላቱን ገድይ ልብሱን አስመልሻለሁ እና ቁርባኑን ሰጋ ደሙን ጊዮርጊሰ ያቀዋል፡ሳይሸለልልኝ ሳይፋከርልኝ ብለው በ110አመታቸው ሞቱ፡፡ የሚገርሙአባት ናቸው በጀግና አሟሟትየተፋከረ፡እየተሸለለ በጀግና አቀባበር በ110አመታቸው አርፈዋል፡፡ስለት ሰሚው ዋካ ጊዮርጊስ የዱሮው ቤተክርስቲያንሳይፈርስ ሌላ ቤተክርስቲያን በመሰራት ላይ ሲሆን መርዳት ለእግዚአብሔር ማበደር ሲሆን ስለት ሰሚውን ዋካን በምንችለው አቅም እንርዳ የቤተክርስቲያኗ መሰረቱ በመሠራት በመውጣት ላይ ነው፡፡በረከቱ በያለንበት ከጊዮርጊሰ ይደርብን፡፡አሜን
ቦታው-+መንዝ ዘብር ገብርኤል ከአ/አ 260ኪሜ ሲሆን ከዘብር የ4ሰዓት መንገድ ሲሆን 4wdመኪና ቦታው ድረስ ይገባል ሜዳ ቀላል መንገድ ነው፡፡

Sunday, November 27, 2016

በራእይ አዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ እንደሚገኝ የታየው ታቦት ተገኘ

ቅ/ሚካኤል ሚዛንና ሰይፍ ይዞ በዩኒቨርሲቲው ፩ኛ በር በኩል እየወሰደ ያሳየኛል፡፡”
/ታቦቱ መኖሩን የጠቆሙት ባለራእዩ ባሕታዊ በለጠ ዘነበ/
*                    *                    *
aau-st-michael-ark
 
(አዲስ አድማስ፤ ዓለማየሁ አንበሴ፤ ቅጽ ፲፮ ቁጥር ፭፻፹፤ ቅዳሜ፣ ኅዳር ፲፯ ቀን ፳፻፱ ዓ.ም.)
በአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ 6 ኪሎ ካምፓስ ሙዝየም ውስጥ፣ ከግማሽ ክፍለ ዘመን በላይ ያስቆጠረ ታቦት የተገኘ ሲኾን፤ ታቦቱ ለኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን እንደተመለሰ ታውቋል፡፡
በዩኒቨርሲቲው ግቢ ታቦት ስለመኖሩ፣ “ራእይ ታይቶኛል” የሚሉ ባሕታዊ ለጠቅላይ ቤተ ክህነት ባስታወቁት መሠረት፣ ጥናት ተደርጎ መኖሩ በመረጋገጡ፤ ከዩኒቨርሲቲው ጋር ብዙ ድርድር ከተደረገ በኋላ፣ ኅዳር 10 ቀን 2009 ዓ.ም.፣ ታቦቱ ለጠቅላይ ቤተ ክህነት መመለሱን በጉዳዩ ተሳታፊ የነበሩት መጋቤ ምሥጢር ቡሩክ አሣመረአዲስ አድማስ ተናግረዋል፡፡
“ታቦቱ በዐፄ ኃይለ ሥላሴ ጥያቄ እንደተቀረፀና የቅዱስ ሚካኤል ታቦት መኾኑን የሚገልጽ ማስታወሻ ተገኝቷል፡፡ ታቦቱ ከ68 ዓመት በላይ ዕድሜ እንዳለውም ታውቋል፤” ብለዋል – መጋቤ ምሥጢር ቡሩክ፡፡
ታቦቱ በዩኒቨርሲቲው ስለመኖሩ፣ ባሕታዊ በለጠ ዘነበ የተባሉ በራእይ ታይቶኛል በሚል በተደጋጋሚ ሲናገሩ እንደነበር የጠቆሙት መጋቤ ምሥጢር ቡሩክ፤ “ቅዱስ ሚካኤል ሚዛንና ሰይፍ ይዞ በዩኒቨርሲቲው ካምፓስ አንደኛ በር በኩል እየወሰደ ያሳየኛል፤” እያሉ ይናገሩ እንደነበርና፣ ይህንንም በ2003 ዓ.ም. አካባቢ ለፓትርያርክ አቡነ ጳውሎስ መግለጻቸውን፤ ነገር ግን ትኩረት የሚሰጣቸው ሳያገኙ መቅረታቸውን ያስታውሳሉ፡፡

ባሕታዊው፣ በ2007 ዓ.ም. ይህንኑ ራእይ ለብፁዕ ወቅዱስ ፓትርያርክ አቡነ ማትያስ ማሳወቃቸውንና የሚመለከታቸው የጠቅላይ ቤተ ክህነቱ የሥራ ሓላፊዎች ጉዳዩ እንዲጠና ማዘዛቸውን መጋቤ ምሥጢር ቡሩክ አውስተው፣ በጥናቱም ጽላቱ በዩኒቨርሲቲው ውስጥ መኖሩ መረጋገጡን ገልጸዋል፡፡ ይህን ተከትሎም ታቦቱ ለቤተ ክርስቲያንዋ እንዲመለስ ከዩኒቨርስቲው ጋር በርካታ የደብዳቤ ልውወጦች ተደርገዋል፡፡
መጀመሪያ ላይ ዩኒቨርሲቲው የጥናትና ምርምር ተቋም እንደመኾኑ፣ ቅርሶችን ተከባክቦ የመያዝና ለትውልድ የማስተላለፍ ሓላፊነት እንዳለበት በመግለጽ፣ ታቦቱን ለቤተ ክርስቲያንዋ ለመመለስ በእጅጉ ተቸግሮ ነበር፤ ይላሉ መጋቤ ምሥጢር ቡሩክ፡፡ ኾኖም ጽላት ለቱሪስቶች(ለጉብኝት) ክፍት ኾኖ መታየት የሌለበት የሥርዓተ አምልኮ መፈጸሚያና  መግለጫ በመኾኑ፣ በዩኒቨርሲቲው ሙዝየም ውስጥ ቢቀመጥ ትርጉም እንደሌለው ስምምነት ላይ በመደረሱ፣ የመንበረ ልዑል ቅዱስ ማርቆስ ቤተ ክርስቲያን በአደራ ተረክቦ እንዲያስቀምጥ መደረጉን ለማወቅ ተችሏል፡፡

ታቦቱ፣ አልተረስቶን በሚል ስያሜ፣ በመዝገብ ቁጥር 1761 ተመዝግቦ የተገኘ ሲኾን፣ ሚስተር ስቴፈን ራይት በተባለ ሰው፣ እ.አ.አ ሰኔ 12 ቀን 1961 ወደ ሙዝየም መግባቱን መጋቤ ምሥጢር ይናገራሉ፡፡ ነገሥታት ታቦት አስቀርፀው በቤተ መንግሥታቸው በሚገኙ አብያተ ጸሎታት(ሥዕል ቤቶች) የማስቀመጥ ልምድ እንደነበራቸው የጠቀሱት መጋቤ ምሥጢር ቡሩክ፤ ምናልባትም ዐፄ ኃይለ ሥላሴ ይህን የቅዱስ ሚካኤል ታቦት ሳያስቀርፁት እንዳልቀረ ግምት መኖሩን አመልክተዋል፡፡ “ታቦቱ በዩኒቨርሲቲው ሙዝየም 3ኛ ምድር ቤት ውስጥ ለብቻው በተሠራ ቤት ውስጥ ተደብቆ ነው የተገኘው፤ የሙዝየሙ ሠራተኞች እንኳን ታቦት መኖሩን አያውቁም ነበር፤” ብለዋል መጋቤ ምሥጢሩ፡፡
ከሰኔ 12 ቀን ጀምሮ፣ ከመልአኩ ቅዱስ ሚካኤል ጋር ይገናኙ እንደነበር የገለጹት ባለራእዩ ባሕታዊ በለጠ ዘነበ፣ በተደጋጋሚ ወደ ፓትርያርኩ ጽ/ቤት እየሔዱ ቢናገሩም ትኩረት አለማግኘታቸውን ጠቅሰው፣ በኋላ የቤተ ክርስቲያኒቱ የልማትና ክርስቲያናዊ ተራድኦ ኮሚሽንና የቤተ መዛግብትና ቅርስ ክፍል ሓላፊዎች ባደረጉት ከፍተኛ ጥረት ታቦቱን ከዩኒቨርስቲው ለመረከብ መቻሉን ለአዲስ አድማስ አስረድተዋል፡፡

በአዲስ አበባ ዩኒቨርስቲ የታሪክ ምሁር የኾኑትን ፕ/ር አሕመድ ዘካርያን ስለ ጉዳዩ ጠይቀናቸው ምላሽ ለመስጠት ፈቃደኛ ሳይኾኑ ቀርተዋል – “አኹን ብዙም የምገልጸው ነገር የለም፤” በማለት፡፡
the-imperial-genete-leul-palace-and-menbere-leul-st-mark-church
የቀድሞው ገነተ ልዑል ቤተ መንግሥት(የአኹኑ የአ.አ.ዩ. የኢትዮጵያ ጥናትና ምርምር ተቋም – በግራ) 
እና የመንበረ ልዑል ቅዱስ ማርቆስ ቤተ ክርስቲያን(በቀኝ)
በዩኒቨርሲቲው ሙዝየም የተገኘውን የቅዱስ ሚካኤል ታቦት አስመልክቶ፣ ለብዙኃን መገናኛ እና ለሕዝብ ይፋ ለማድረግ፣ ለጥር 8 ቀን 2009 ዓ.ም. መርሐ ግብር መያዙን መጋቤ ምሥጢር ቡሩክ አስታውቀዋል፡፡
አኹን በ6 ኪሎ የሚገኘው የአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ ዋናው ግቢ፣ የግርማዊ ቀዳማዊ ንጉሠ ነገሥት ዐፄ ኃይለ ሥላሴ ገነተ ልዑል ቤተ መንግሥት የነበረ ሲኾን፣ ታቦቱን በአደራ የተረከበው የመንበረ ልዑል ቅዱስ ማርቆስ ቤተ ክርስቲያንም፣ የንጉሠ ነገሥቱና ቤተሰቦቻቸው ሥዕል ቤት(ጸሎት ቤት) ኾኖ ያገለገለ ነው፡፡ የ1953 ዓ.ም. መፈንቅለ መንግሥት ተከትሎ የንጉሡ ቤተ መንግሥት ወደ ኢዮቤልዩ በመዛወሩ፣ የገነተ ልዑል ቤተ መንግሥትን ለትምህርት ተቋምነት በስጦታ አበርክተዋል፤ ጸሎት ቤት የነበረው የመንበረ ልዑል ቅዱስ ማርቆስ ቤተ ክርስቲያንም ለሕዝብ አገልግሎት የሚሰጥ ኾኗል፡፡

በአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ: ከግማሽ ክፍለ ዘመን በላይ ያስቆጠረ ታቦተ ቅዱስ ሚካኤል ተገኘ

የቅዱስ ገብርኤል ጽላት በአንድ አባት ራእይ ተገኘ