Tuesday, February 7, 2017

የቁልቋል በር ማርያም ቤተክርስቲያን


እነሆ ከተወለደ ጀምሮ 15 ዓመት ሙሉ በአልጋ ቁራኛ ተይዞ ይኖር የነበረ ወንድማችን በእናታችን ጸበል እነሆ ከደዌው ተፈውሷል እንዲሁም ተነግሮ የማያልቅ ድንቅ ታምራት በእመቤታችን ተደርጓል የእናታችን የቁልቋል በር ማርያም ወዳጆች እንደሚታወቀው የእናታችን ቤት ለመጨረስ የተለያዩ ገቢ ማሰባሰቢያ እያደረግን እንገኛለን የተለያዩ ጉዞዎች ፣ ትኬቶችን በመሸጥ ላይ ነን፤ ይህን መልካም ስራ ለመስራት እናቴ ቤትሽ በፍሶ እኔ እንዴት በተደላደለ ቤት እኖናራለን ብለን ከሀገርም በውጪም የምንኖር እጆቻንችን ዘርግተናል በመዘርጋት ላይም ነን ታዲያ ቤተክርስቲያኑ በአሁኑ ሰዓት ስራው የጀመረ ሲሆን ነገር ግን አሁን ሙሉ ለሙሉ ስራውን ለመስራት እነዚ ነገሮች ይጎድላሉ እንደ አሽዋ ሲሚንቶ ፌሮ፣ እና ህንፃ ቤተክርስቲያኗን ለመጨረስ የሚያስፈልጉ ነገሮች በጣም ይጎድላሉ ከዚህ በተጓዳኝ ደግሞ ይህን ስራ የሚሰሩ ሳተኞች የሚከፈላቸው ብር ሙሉ ለሙሉ ባለመገኘቱ በተወሰነ ሰራተኛ ነው አሁን ስራው የተጀመረው በሀገርም በውጪም የምንገኝ እህት ወንድሞቼ አንዳችን ባንችል እንኳ ሁለት ሦስት ከዛ በላይ በጋራ በመሆን ያለንን በማዋጣት የእናታችን የቁልቋል በር ማርያምን ቤት እንስራ ከዛ ባሻገር ደግሞ ብዙ ምህመን እንደዚ ያለ ቤተክርስቲያን የለም እናንተ በስሟ ልትነግዱ ነው የሚል ሃሳብ ነበር ነገር ግን እውነታን ቦታው ድረስ ሄዳችሁ ያያችሁ እህት ወንድሞቼ ምስክር ናችሁ ከእናታችን ጎን በመሆን እጅ ለእጅ ተያይዘን የጀመርነው ከግብ እናድርስ፤ እማማ ወላዲተ አምላክ ያሰብነውን መልካም ነገሮች ሁሉ በምልጃዋ ታስፈጽምልን የባንክ አካውንት ቁጥሩ kuli kual ber d/m/k mariam b/k commercial bank of Ethiopia Acc/no 1000167540949 ለበለጠ መረጃ ደግሞ በህነዚህ ስልክ ይደውሉ 09 38 59 49 03/0911 76 28 72 / 0913 67 78 91 ደውለው ስለ ቤተክርስቲያኗ ያለችበት ሁኔታ ደውለው መጠየቅ ይችላሉ ፡፡
‹‹ በእውነቱ ይህ ቤት ፈርሶ እናንተ በተሸለሙ ቤቶቻችሁ ልትኖሩ ጊዜው ነውን? ›› ሀጌ 1፡4

Monday, February 6, 2017

ፃድቃኔ ማሪያም ድንቅ ታምር

የእናታችን የፃድቃኔ ማሪያም ድንቅ ታምር ትላንት ለሊት እለተ ቅዳሜ ከለሊቱ 8:--- ገደማ እህታችን ጉሮሮዬን ተናነቀኝ ብላ መፀዳጃ ቤት ሄደች አብረዋት ያሉትም ሰዎች ተከትለዋት ይወጣሉ ታዲያ ያልታሰበ ክስተት ተፈጠረ አነቀኝ ባጠጠኝ ያለችው ይህ የምታዩት ቁወቱ አንድ ስንዝር የሚሆን እባብ ከሆዷ ወጣላት የድንግል ማሪያም ስም ይመስገን ክብር ለስሟ ይሁን ይህ ድንቅ ታምር የተደረገው በትላንትናው ለሊት እለተ ቅዳሜ ለእሁድ አጥቢያ ከለሉቱ 8:19 /26/5/2009 ነው እኔም ድንግል ማሪያም የዘረያእቆብ እመቤት ስውሯ ፅላት የአይን ምስክር ስላደረገችን ድንቅ ታምሯን እንድመሰክር ስላደረገችኝ ምስጋና ይድረሳት ለተጨነቅነው ሁሉ ትድረስልን አሜን


Wednesday, February 1, 2017

የእመቤታችን ድንቅ ተአምር

ከዚህ በታች የምታነቡትን ድንቅ ተአምር ያደረገችው የእመቤታችን ስዕለ አድህኖ በሀገራችን በኢትዮጵያ ሰበታ ቤተ ደናገል ጠባባት አንድነት ገደም (ጌቴሰማኔ ማርያም) የሚገኝ ሲሆን ምስለ ስእሏን በ ፎቶም ሆነ በቪድዮ ማንሳት ለክብሯ ሲባል የተከለከለ ነው፡፡ ይህ የምታዩት ግን እዛው ሰበታ መድኃኒአለም ቤተክርስትያን ውስጥ ይገኛል፡፡ ይህችን ተአምረኛ ምስለ ስእል እንዴትና ማን እንዳመጣት እንዲሁም የሰራችውን ተአምር እዛው ሄደው እንዲሰሙና እንዲያዩት እጋብዛለሁ፡፡
(በድጋሜ ፨ እባካችሁ አንተ ታዲያ ፎቶውን እንዴት አነሳኽው ለምትሉ፤ ይሄኛው ሌላ ነው አሳሳሉ ግን ይሄን ታሪክ መሰረት አድርጎ ነው። ተአምረኛዋ ምስለ ስዕል ግን አንድ አጥማቂ አባት (ቡኃላ አቡነ የተባሉ) በቦርሳቸው ይዘዋት ይዞሩ የነበሩ የጣሊያን ጦር ኢትዮጵያን በወረረ ጊዜ ጥይት ያልጎዳት መጽሐፍ ቅዱስ ነው ምታክለው። ገዳማውያን እናቶች አክብረው አስቀምጠዋታል)

ተአምሪሃ ለእግዝዕትነ ቅድስት ድንግል በ ፪ኤ ማርያም ወላዲተ አምላክ ጸሎታ ወበረከታ የሃሉ ምስሌነ ለዓለመ ዓለም አሜን ልመናዋ ክብሯ በእኛ ለዘላለም በውነት ይደርብንና አምላክን የወለደች በድንጋሌ ሥጋ በድንጋሌ ነፍስ የፀናች ክብርት እመቤታችን ያደረገችው ተዓምር ይህ ነው። አምላክን የወለደች በድንጋሌ ሥጋ በድንጋሌ ነፍስ የፀናች ክብርት እመቤታችን በሥዕሏ አድራ ያደረገችውን ተዓምር ስሙ ።
ከአፍርንጊያ አገር ( ከአፍሪካ )ማለት ነው በከበረ ልብስና በወርቅ በብርም እጅግ የከበረ አንድ ነጋዴ ነበር ። ያም ሰው ሥጋ የለበሰች የምትመስለውን አምላክን የወለደች በድንጋሌ ሥጋ በድንጋሌ ነፍስ የፀናች የክብርት እመቤታችንን ሥዕል ዜና በሰማ ጊዜ ፈጽሞ ደስ አለው ። ገንዘቡን ሁሉና ንግዱንም ትቶ ደኃ መስሎ ወደ ጼዴንያ አገር ሄደ ሥዕሏንም ሠርቆ ወደ አገሩ አፍርንጊያ (አፍሪካ) ይወስዳት ዘንድ ይህንን ምክኒያት አደረገ ሥዕሊቱንም አግኝቶ ወደ አገሩ ይወስዳት ዘንድ የተጠረገ መንገድን ሊያገኝ ደጅ እየጠና በጼዴንያ የተሠራች የእመቤታችንን ቤተ ክርስቲያን ለሁለት ዓመት ያህል ሲያገለግል ኖረ ። እመምኔቲቱ ግን የመነኮሳቱን በር በፍፁም ትጋት ትጠብቅ ነበርና ሥዕሊቱን ይወስዳት ዘንድ እንዳልተቻለው ባወቀ ጊዜ ሾተልን ይዞ እጁን በመስኮት አዝልቆ ከሥዕሊቱ የሥጋ ቁራጭን ያህል ቆረጠ ያን ጊዜም ከሥዕሊቱ ደም ወጣ ። እርሱም የሥጋ ቁራጭን ያህል ይዞ ወጥቶ ተሠወረ ። ያን ጊዜም ሰዎች አውቀው በጭንቅ ፈልገው አግኝተው ያዙት ይገድሉትም ዘንድ ወደዱ ። ያን ጊዜም ከሥዕሊቱ እንዲህ የሚል ቃል ተነገረ "" እኔን ስለ መውደዱ ክብር ሊሆነው ወስዷል እንጂ ይህንንስ በክፋት አላደረገውምና ተዉት አትግደሉት ነገር ግን የተቆረጠውን ሥጋ ከእርሱ ወስዳችሁ ከተቆረጠበት ቦታ ግጠሙት "" ያን ጊዜም እንዲሁ አድርገው አኖሩትና ሥጋው ተጣብቆ ቀድሞ እንደነበረ ሆነ ነገር ግን የደምና የሾተሉ ፍለጋ ምልክቱ እስከዛሬም ድረስ ታውቆ ታይቶ ይኖራል ። በአርያም ለሚመሰገን አምላክን በወለደች በድንጋሌ ሥጋ በድንጋሌ ነፍስ በፀናች በክብርት እመቤታችን አማላጅነትም ይህንን ተዓምር ለገለጸ ለእግዚአብሔር ምስጋና ይገባል ። ልመናዋ ክብሯ አማላጅነትዋ የልጅዋ የወዳጅዋም ቸርነት በእኛ ለዘለዓለም በውነት ይደርብን ። አሜን

የእመቤታችን መቃብርና ያረገችበት ጣራ - Tomb of The Virgin Mary

"የጎጆዋ አርሴማ" - ድንቅ ነገር


☞ እንሆ በአዲስ አበባ በቦሌ ቡኒ ቅዱስ እግዚአብሔር አብ እና ቅድስት አርሴማ ቤተክርስቲያን የተከናወነ ድንቅ ነገር !!!!!! እንዲህ ሆነ በ ጥር 10 2009 ዓ ም የጥምቀት በዓለ ክብር ከተራውን ፈጽመን እንሆ በ 13 የቅዱስ እግዚአብሄር አብ , ቅድስት ኪዳነምህረት ,ተክልዬ, አና አርሴምዬን አጅበን ወደ መንበረ ክብሩ ደረስን ስርአተ ቤተክርስቲያኑን አከናውነን በእግዚአብሔር ፈቃድ እና በአባቶች ራዕይ ጽላቷ የመጣችው ቅድስት አርሴማ በድጋሚ ከገዳማውያን አባቶች የተነገሩትን መልእክት በአውደ ምህረት ተናገሩ እንዲህ አሉ "ሰማዕቷ ቅድስት አርሴማ ጥንታዊ ለዛ ያለው ጎጆ ቤተክርስቲያን ሰርታችሁ በዛ አስገቡኝ " ብላለች ብለው ራዕዩን ተናገሩ ፡፡





ከዚህ በኀላ ማሳረጊያ ጸሎት ተደርጎ ታቦታቱ ወደመንበረ ክብራቸው ሲገቡ የቅድስት አርሴማን ያከበሩት አባት ተፍገመሙ ምን አልባት እረጅም መንገድ ስለተጓዙ ይሆናል በሚል ሌላ ካህን ተቀየሩ እንዲሁ እኒህ አባት ተንቀጠቀጡ በዚህ ጊዜ ምዕመናን በለቅሶ በዋይታ ተንበርክከው ማልቀስ ጀመሩ በዚህ ጊዜ ካህኑ ወደ ኀላ መልሳቸው እኛም ታቦቱን በማጀብ በእግዞታ ተከተልን በቅጽረ ቤተክርስቲያኑ ውስጥ በስተ ምስራቅ በኩል በጣም ቆንጆና ደልዳላ ቦታ ላይ ስትደርስ ካህኑን አቆመቻቸው በዚያች ቦታ ጸሎት ተደርጎ መሰረት ተጣለ ፡፡ ከዚህ በኀላ በነባሩ ቤተክርስቲያን በረንዳ ላይ ድንኳን ተጥሎ ታቦቷ በዛ አደረች እስካሁን በዛው ትገኛለች ፡ በአለቱ በተገኘው ገቢ እና በበጎ አድራጊዎች ታግዞ ጎጆ ቤትዋ በመሰራት ላይ ትገኛለች እንግዲህ በሰማዕቷ መልካም ፈቃድ በቀን 28/05/09 ዓም ጸሎተ ምህላ አድርሰን ቅዳሴ ቤቷን ለማክበር በዝግጅት ላይ እንገኛለን የሰማዕቷ ወዳጅ የሆነ ሁሉ በቤቷ እንድትገኙ ጥሪዋን ታስተላልፋለች ፡፡ታዋቂው እና ፈዋሹ የሰማዕቷ የማር ጸበል እንዳያመልጣችሁ ይህም ከመቅደሳ የተገኘ ነው ፡፡እንዲሁም ሀብተ ፈውስ ባላቸው አባት በመምህር አብርሃም የጸበል አገልግሎት ይሰጣል ፡፡ አድራሻ ከጎሮ ወደ ቱሉዲምቱ በሚወስደው መንገድ ላይ ሁለተኛውንና ትልቁን ድልድይ ሳይሻገሩ አስፋልቱ ዳር ላይ ይገኛል እግዚአብሔር አብ እና ቅድስት አርሴማ ቤተክርስቲያን ፡፡ለበለጠ መረጃ 0913511802 ወይም 0936451511ይደውሉ፡፡ በተጨማሪ ☞መንፈሳዊ ጉዞ የምታዘጋጁ መንፈሳዊ ማህበራት አና የቤተክርስቲያን ልጆች ወር በገባ በ 6 ወደዚህች የበረከት ደብር በሆነች ምዕመናንን እንድታስጎበኙልን እና ምዕመናንን የበረከቱ ተካፋይ ታደርጓቸው ዘንድ ቤተክርስቲያን ጥሪዋን ታስተላልፋለች ቤተክርስቲያናም ማንኛውንም መንፈሳዊ ተግባራት ታከናውናለች ፡፡የሰማዕቷ ቅድስት አርሴማ በረከት ይደርብን አሜን፡፡
ጸሐፊ ዲ/ን ኤርምያስ ግርማ


የቅድስት አርሴማ አዲስ ፀበል