Tuesday, September 3, 2013

በገላን ጉራ ፈለገ ግዮን ቅዱስ ገብርኤል ቤተክርስቲያን የተከሰተ ድንቅ ተአምር

//መስቀሉ ለህዝብ በይፋ የሚታይበት ግዜ ላልተወሰነ ግዜ ተላለፍዋል:: //

ከሰማይ ወረደ ስለ ተባለው መስቀል ከአዲስ አድማስ ጋዜጣ የተገኝኘው መረጃ
 በአቃቂ ቃሊቲ በቅዱስ ገብርኤል ቤተ ክርስቲያን ግቢ ውስጥ፣ ነሐሴ ፳፫ ቀን ፳፻፭ ዓ.ም በቀስተ ደመና፣ በመብረቅ እና በነጎድጓድ ታጅቦ ከሰማይ እንደወረደ የተነገረው መስቀል፣ በጳጳሳት የተጎበኘ ሲኾን፣ ከሁለት ሳምንት በኋላ ለሕዝብ እይታ እንደሚቀርብ ተገለጸ፡፡
መስቀሉን ከወረደበት ለማንሣት የሞከረ ወጣት ተስፈንጥሮ ከወደቀበት ለአራት ቀን ራሱን እንደሳተ የሚናገሩ የቤተ ክርስቲያኑ አገልጋይ፣ ከምሽቱ 9፡00 ከፍንዳታ ጋራ አካባቢው በብርሃን ተሞልቶ ስናይ የእሳት ቃጠሎ መስሎን ነበር ብለዋል፡፡ እያንጸባረቀ በኃይለኛ ግለት ያቃጥል ነበር የተባለው መስቀሉ፣ በጳጳሳት እና በማኅበረ ቅዱሳን መሪዎች የተጎበኘ ሲኾን የኢየሱስን ስቅለት የሚያሳይ ወርቃማ ቅርጽ ያለው ነው፡፡
ወደ አቃቂ ከተማ ከሚያስገባው ዋናው የአስፋልት መንገድ በስተግራ በ10 ኪሎ ሜትር ርቀት ገላን ጉራ በሚባለው ስፍራ የዛሬ አምስት ዓመት የተቋቋመው የቅዱስ ገብርኤል ቤተ ክርስቲያን ውስጥ ነሐሴ ፳፫ ቀን ፳፻፭ ዓ.ም [የቅድስት] ክርስቶስ ሠምራ ክብረ በዓል እየተከናወነ ሳለ ከሌሊቱ 9፡00 የኾነው ክሥተት ነው የዚህ ሁሉ መነሻ፡፡ ከባድ የፍንዳታ ድምፅ የሰሙና የቀስተ ደመና ቀለማትን የተላበሰ ብርሃን የተመለከቱ ነገሩን ከዝናባማው የአየሩ ኹኔታ ጋራ በማያያዝ ብዙም ትኩረት አልሰጡትም ነበር የሚሉት የደብሩ መጋቢ፣ ‹‹በነጎድጓድና በኢትዮጵያ ባንዴራ የታጀበ መስቀል ከሰማይ ሲወርድ አይቻለኹ፤›› ብለዋል፡፡ ከዚያን ጊዜ ወዲህ መስቀሉን ለማየት ወደ ቤተ ክርስቲያኑ የሚጎርፉ ምእመናን በርክተዋል፡፡
ባለፈው ኀሙስ ከአቃቂ ከተማ በማለዳ ተነሥተን ከሁለት ሰዓታት የእግር ጉዞ በኋላ ከቤተ ክርስቲያኑ ስንደርስ፣ ጥቂት ምእመናን በተገኙበት የዕለቱ ቅዳሴ እየተከናወነ ነበር፡፡ ከቆይታ በኋላ ቅጽሩ የመስቀሉን ታሪክ ሰምተው ከአቅጣጫው በሚመጡ ምእመናን ተሞላ፡፡ ‹‹መስቀሉ ከሰማይ ሲወርድ አይቻለኹ›› የሚሉት መጋቤ ሐዲስ ፍሥሓ፣ ስለ መስቀሉ አወራረድ ገለጻ ማድረግ የጀመሩት ከጸሎተ ቅዳሴው ፍጻሜ በኋላ ነው፡፡
በቅጽሩ ከሕንጻ ቤተ ክርስቲያኑ አጠገብ መስቀሉ ወርዶ ያረፈበትን ስፍራ እያመለከቱ ይናገራሉ፡- ቦታው በቆርቆሮ ታጥሮ ድንኳን ተተክሎበታል፡፡ መስቀሉ ዐርፎበታል ከተባለው ስፍራ ‹‹አፈር›› እየተቆነጠረ የሚቀርብላቸው ምእመናን፣ ‹‹አፈሩን›› እየተመለከቱ የመጋቤ ሐዲስን ገለጻ ያዳምጣሉ፡፡
ለቅድስት ክርስቶስ ሠምራ በዓል ነሐሴ ፳፫ ቀን የጸሎት ሥርዐት ከምሽቱ 5፡00 አካባቢ እንደተጀመረ የሚያስታውሱት መጋቤ ሐዲስ፣ ከእኩለ ሌሊት ጀምሮ አካባቢው በቀስተ ደመና ብርሃን ደምቆ እንደነበር ይናገራሉ፡፡ ‹‹የቤተ ክርስቲያኒቱ አገልጋዮችና ምእመናን ለዚህ ልዩ ክሥተት ብዙም ትኩረት አልሰጡትም ነበር፡፡ ከዝናባማው የአየር ጠባይ ጋራ አዛምደው አቅለለው ነው የተመለከቱት፤›› ብለዋል መጋቤ ሐዲስ ፍሥሓ፡፡ የቀስተ ደመናው ብርሃን አንዴ ሲደምቅ፣ አንዴ ሲደበዝዝ መቆየቱን መጋቤ ሐዲስ ጠቅሰው፣ ‹‹ከሌሊቱ 9፡00 ሰዓት ነፋስ ለማግኘት በካህናት መውጫ በር በኩል ስወጣ ግን ደብዛዛ የነበረው ብርሃን የበለጠ ደምቆ እንደ ቀን ብርሃን ወገግ ብሎ ታየኝ፤›› ብለዋል፡፡ ‹‹አሻቅቤ ስመለከት ሰማዩ በነጭ ደመና ተከቦ ተመለከትኩ፡፡ አፍታም አልቆየ፣ በኢትዮጵያ ባንዴራ ቀለማት የተጠቀለለ አንዳች ነገር በዝግታ ከሰማይ እየተገለባበጠ ሲወርድ አየኹ፡፡››
ከቤተ ክርስቲያኑ ቤተ ልሔም አጠገብ ያለውን የአገር አቋራጭ ከፍተኛ የኤሌክትሪክ መሥመር ተሸካሚ ማማ እያመለከቱ፣ ‹‹ከሰማይ እየተጠቀለለ የሚወርደው ነገር ከማማው አካባቢ ሲደርስ ነጎድጎዳማ ድምፅ ማሰማት ጀመረ›› የሚሉት መጋቤ ሐዲስ፣ ‹‹መሬት ላይ ሲያርፍ በከፍተኛ የፍንዳታ ድምፅ አካባቢው የእሳት ንዳድ የመሰለ ብርሃን ሞላው፤›› ይላሉ፡፡ ‹‹ቤተ ልሔሙ ተቃጠለ እያልኹ ብጮኽም ድምፄን የሰማ ሰው አልነበረም፤ ለደቂቃዎች ያህል ለሰዎች እንዳይሰማ ኾኖ ታፍኖ ነበር፡፡ ድምፄ መሰማት ሲችል ግን፣ ካህናቱ ጩኸቱን ሰምተው ተደናግጠው ወደ ውጭ ወጡ፤›› ብለዋል፡፡ አንዳች አደጋ ደርሶ እሳት ተቀጣጥሎ ሊኾን ይችላል በሚል ድንጋጤ ሁሉም እሳቱን ለማጥፋት እንደተሯሯጠ ጠቅሰው፣ ነገር ግን ከአካባቢው ብርሃን በቀር የእሳት ቃጠሎ ማግኘት አልተቻለም ብለዋል፡፡
‹‹አንድ የቤተ ክርስቲያናችን ወጣት አገልጋይ ወደ ደመቀው ብርሃን ተጠግቶ ለማየት ሞከረ፤ አንዳች ነገር ወደላይ አስፈንጥሮ መሬት ላይ ጣለው፤ ምእመናን ተደናገጡ፤ የኤሌክትሪክ መሥመር ተበጥሶ ኮንታክት ፈጥሮ ይኾናል የሚል ጥርጣሬ ነበር ያደረብን›› ሲሉም ተርከዋል፡፡ ‹‹የወደቀው ወጣት ምላሱ ተጎልጉሎ በወደቀበት ራሱን ስቶ ተዘርግቶ ነበር›› የሚሉት መጋቤ ሐዲስ ፍሥሓ፣ ከወደቀበት በጥንቃቄ አንሥተን ጠበልና ቅብዐ ቅዱስ ብናደርግበትም አልተሻለውም ብለዋል፡፡ ከዚያ በኋላ ነው ካህናቱ እንደምንም ወደ ብርሃኑ ተጠግተው የተመለከቱት፡፡ እናም በብርሃን የታጀበ መስቀል መሬት ላይ ዐርፎ አዩ ብለዋል፡፡
ካህናቱና ምእመናኑ በአግራሞት ሲመለከቱ ቢቆዩም የእሳቱ ወላፈን ይፋጃል ያሉት መጋቤ ሐዲስ ፍሥሓ፣ በርቀት መጎናጸፊያ ተወርውሮበት እንዲለብስ እንደተደረገ ይገልጻሉ፡፡ የተቋረጠው ሥርዐተ ማሕሌት ከ10፡00 በኋላ የቀጠለ ሲኾን በካህናቱ ትእዛዝ መስቀሉ ወርዶ ካረፈበት ሥፍራ ላይ ማለዳ 12፡30 ድንኳን ተተከለ፤ ብፁዓን አባቶችም በስልክ እንዲያውቁ ተደረገ ብለዋል፡፡ ይኹን እንጂ በማግስቱ የጻድቁ አቡነ ተክለ ሃይማኖት ክብረ በዓል ስለነበር ብዙዎቹ ጳጳሳት ወደ ደብረ ሊባኖስ፣ ቀሪዎቹም ወደ የአድባራቱ ሄደው ስለነበር በዕለቱ መምጣት አልቻሉም ብለዋል፡፡
‹‹ከበላይ አካላት በተነገረን መሠረት ለወረዳው ፖሊስ ካሳወቅን በኋላ የፖሊስ ኃይል አካባቢውን ተቆጣጠረ፤›› የሚሉት መጋቤ ሐዲስ ቅዳሜ ዕለት የማኅበረ ቅዱሳን አባላት መጥተው መመልከታቸውን ገልጸዋል፡፡ በዚያው ዕለት ከሰዓት በኋላ ለመምጣት ቀጠሮ የሰጡ ጳጳሳት ግን ከአንድ ሰዓት በላይ በረዶ የቀላቀለ ዝናም በመጣሉና ጭቃው የማያስገባ በመኾኑ ከመንገድ ተመልሰዋል፡፡ በማግሥቱ እሑድም አክራሪነትን ለመቃወም ሰልፍ የሚካሄድበት ቀን በመኾኑ መምጣት አልቻሉም፡፡
ሰኞ ዕለት፣ ነሐሴ ፳፯ ቀን በርካታ ጳጳሳት በቦታው ተገኝተው፣ መስቀሉ ዐርፎ ከቆየበት ስፍራ ተነሥቶና በበርካታ ምእመናን ታጅቦ ወደ መቅደስ እንዲገባ መደረጉን መጋቤ ሐዲስ ፍሥሓ ተናግረዋል፡፡ በደረሰበት አደጋ ራሱን ስቶ የቆየው አገልጋይ፣ በአራተኛው ቀን መንቃቱንና በሙሉ ጤንነት ላይ እንደሚገኝ ተነግሯል፡፡ ወጣቱ ሲጠየቅም፡- ሊያነሣው እጁን ሲሰነዝር ከኋላው አንዳች ሕፃን ልጅ የመሰለ ነገር ጎትቶ መሬት ላይ እንደጣለውና ከዚያ በኋላ የኾነውን እንደማያውቅ መግለጹን መጋቤ ሐዲስ ተናግረዋል፡፡
መስቀሉ ከወደቀበት መሬት ተነሥቶ ሲገባ ከፍተኛ ግለት እንደነበረውና [ያከበሩት] አባት ‹‹እያቃጠለኝ ነው›› እያሉ ሲናገሩ እንደነበር ተገልጧል፡፡ መስቀሉ የሰው ሥራ እንዳይኾን የተጠራጠሩ መኖራቸውን የጠቀሱት መጋቤ ሐዲስ ፍሥሓ፣ ‹‹መስቀሉ ከምን እንደመጣ የሚያውቀው ፈጣሪ ነው፤›› ብለዋል፡፡
አቶ እንግዳው የተባሉ የአካባቢው ነዋሪ፣ መስቀሉ ከሰማይ ሲወርድ እንዳልተመለከቱ ጠቅሰው፣ ‹‹በጳጳሳቱ ካረፈበት ተነሥቶ ወደ መቅደስ ሲገባ ወርቃማ ብርሃን ነበረው›› ብለዋል፡፡ አንዳንድ የአካባቢው ሰዎችም ሌሊቱን ነጎድጓዳማ ድምፅ መስማታቸውንና በማግሥቱም ስለ ክሥተቱ ከቤተ ክርስቲያኑ ካህናት እንደተነገራቸው ገልጸዋል፡፡ ለአካባቢው ጸጥታ በማሰብ መስቀሉ በየዕለቱ ለምእመናን እንዳይታይ ከቤተ ክህነት ትእዛዝ እንደተላለፈ ጠቅሰው፣ መስከረም ፲፱ ቀን ፳፻፮ ዓ.ም በቤተ ክርስቲያኑ ቅጽር መስቀሉን ለእይታ ለማወጣት ቀጠሮ መያዙን መጋቤ ሐዲስ አስታውቀዋል፡፡
ጉዞ ተአምሩን ለማየት  

መስቀሉ ያለበት ቦታ






በማሕበራዊ ግጽ ላይ ከቤተክርስቲያን ልጆች የተገኘው መረጃ እንደሚያሳየው ከሰማይ የወረደ መስቀል በቤተ ክርስቲያን መገኘቱን የሚያስረዳ ነው:: ይህም ታማኝ ከሆኑ ሰዎች የተነገረ ስለሆነ እናካፍላችሁ:: ወደፊት ዝርዝር መረጃውን የምናቀርብ ሲሆን ተአምሩን እንዳቀረቡት ይህን ይመስላል::

እነሆ 23/12/2005 . ሀሙስ ለአርብ አጥቢያ ከለሊቱ 900 ሰዓት አከባቢ ካህናት አባቶች እና ምእመናን የክርስቶስ ሳምራን የበአል ዋዜማ ማህሌት ቆመው ሳሉ ድንገተኛ ድምፅ ሲሰሙ ካህናትና የቤተክርስቲያን አስተዳደሩ ከቤተመቅደስ ወጥተው ሁኔታውን ሲመለከቱት ብርሀን ከሰማይ እንደወረደና አከባቢውን በብርሀን እንደሞላው ተመልክተው ሲያዩ የጌታ ስቅለት ያለበት መስቀል ከሰማይ እንደወረደ ተረዱ መስቀሉም በብርሃን ተሞልቶ ነበር እነሱም በመደናገጥ ከቦታው ለጊዜው እራቅ ብለው በመቆም ምህላ አደረሱ::

በቦታው የደረሱ አባት ብርሐኑ ካለፈ በሁዋላ በሞባይል ያነሱት ምስል 


ተአምሩን አሁንም በቦታው ላይ በመገኘት መመልከት ይችላሉ፡፡

አድራሻው ከአቦ ቤተክርስቲያን ወደ ቦሌ ቡልቡላ በሚወስደው መንገድ ዋሻ ተክለሀይማኖትን ካለፉ በኋላ በድልድዩ ላይ ቀጥ ብለው በመውጣት ያገኙታልአድራሻው ከአቦ ቤተክርስቲያን ወደ ቦሌ ቡልቡላ በሚወስደው መንገድ ዋሻ ተክለሀይማኖትን ካለፉ በኋላ በድልድዩ ላይ ቀጥ ብለው በመውጣት ያገኙታል::

ከሰማይ የወረደው ተአምረኛው መስቀል በብፁዕ አቡነ እስጢፋኖስ አማካይነት በቀን 27/12/2005 . ተነስቶ ወደ መቅደሱ ገባ፡፡ ተዓምሩን እያሳየ ያለው ይህ መስቀል የገባበት አድራሻውም አቃቂ ቃሊቲ /ከተማ ወረዳ 10 ገላን ጉራ ፈለገ ግዮን ቅዱስ ገብርኤል ቤተክርስቲያን ሲሆን፡፡ ብፁዕ አቡነ እስጢፋስ መስቀሉን ወደ ቤተመቅደስ እንዳስገቡት መረጃዎች ያመለክታሉ፡፡ 

ባሕታዊ ሕጻነ ማርያም መስቀሉ ይዘውት ሑደት ሲያደርግ

ዝርዝር መረጃው ባይደርሰንም ይህን ተዓምር ያሳየን የቅዱሳን አምላክ ስሙ የተመሰገነ ይሁን፡፡ ‹‹ወወሀብኮሙ ትዕምርተ ለእለ ይፈርሑከ፤ ለሚፈሩሕና ለሚያከብሩህ ምልክትን ሰጠሀቸው›› እንዳለ ቅዱስ ዳዊት ከተሰጡን ምልክቶች አንዱ ቅዱስ መስቀል ነው፡፡ በዚህ ምልክትም ከጠላት ሰይጣን እጅ ልናመልጠበት አርማችንም ልናደርገው ማዕተባችንንም አጥብቀን ልናስር ይገባል፡፡ ይህንም እናደርግ ዘንድ የቅዱሳን አምላክ እግዚአብሔር ይርዳን ለዘለዓለሙ አሜን፡፡

የሸንኮራ ቅዱስ ዮሃንስ ወልደ ነጎድጓድ ጸበል ታምር 

ተአምራት በ በአታ ለማርያም ታህሳስ 3/05

 


Thursday, August 15, 2013

መምህር ግርማ ወንድሙ ከ ለይፍ መጽሄት ጋር ያደረጉት ቃለ ምልልስ

ላይፍ፡- ቅዱስ እስጢፋኖስ ቤተክርስቲያን የጥምቀትና የትምህርት አገልግሎት እንዳይሰጡ የታገዱበት ምክንያት ምንድነው?
መምህር ግርማ፡- ምክንያቱም ሰው በመዳኑ እና የዲያቢሎስ ሚስጥር በመጋለጡ እንዲሁም ህብረተሰቡ ለከፋ መንፈስ ግንዛቤው እየጨመረ መምጣቱ ነው፡፡ የሆነው ሆኖ እኔ እየሩሳሌም አገልግሎት ሄጄ እያለ የቤተክርስቲያኑ አስተዳዳሪ መልክአ ኃይል አባ ሚካኤል የሰንበት ትምህርት ቤት ተማሪዎች ነን በሚሉ ግለሰቦች አማካኝነት ቤተክርስቲያኑ ውስጥ ብዙ ወጪ ወጥቶበት ተገንብቶ የነበረውን መድረክ እና የምዕመና መቀመጫዎች በመንቀልና በመሰባበር ከጥቅም ውጪ አደረጉት፡፡ እነኚህ ሰዎች ያልተረዱት ቢረዱትም ግድ የማይሰጣቸው ያወደሙት ንብረት የእኔ ሳይሆን የእስጢፋኖስ ቤተክርስቲያን መሆኑ ነበር ፤ በቤተክርስቲያን ዙሪያ በሰንበት ትምህር ቤት ብዙ ችግሮች ይሰማሉ፡፡ እነኚህ የሰንበት ትምህር ቤትን ምግባርና ስርዓት ሳይኖራው በስም ብቻ የተጠለሉ አንዳንዶቹ እንደ ክርስቲያን ሳይሆን የእርኩሳን አሰራር የሚፈጽሙ እንደነበር ብዙዎች አገልጋዮች ያውቃሉ፡፡በተጨማሪም ማታ ማታ በድራፍትና በመጠጥ ዙሪያ ሲንካኩና ሲጨፍሩ አምሽተው ጠዋት መጥተው ከበሮ የሚደበድቡ ናቸው፡፡ ጸጉራቸው እንኳን ምስክር ነው፡፡ የተንጨባረሩ ፍጹም ቦዘኔና ዘላን መልክና ገጽታ ያላቸው ናቸው፡፡ ለአባቶቻቸው ክብር የሌላቸው፡፡ ማዋረድ ስራቸው የሆነ ፤ የስነ ምግባር መንፈሳዊ ትምህርትን ከምንም ቦታ ያልያዙ እንደዚሁ የመደዴነት ባህሪ ያላቸው ናቸው፡፡ በእነዚህ ነው የቤተክርስቲያኗ መድረክና ንብረት ያወደሙት፡፡ girma wendimu ላይፍ፡- ከዚህ በፊት በማን ጥሪ መሰረት ነው እስጢፋኖስ ቤተክርስቲያን አገልግሎት ሲሰጡ የነበረው ? መምህር ግርማ፡-  በደብሩ አስተዳዳሪ መላከ ሰላም አማካኝነት ነበር፡፡ ከዚያ በፊት ቦሌ አቦ ፤ ኪዳነምህረት ፤ ፉሪ ሥላሴ ፤ ጭቁኑ ሚካኤል ፤መገናኛ እግዚአብሔር አብ በጠቅላላው በከተማይቱና ወጣ ባሉ ያሉ ደብሮች አገልግያለሁ፡፡
ላይፍ፡- ለስንት ዓመት አገልግሎት ሰጥተዋል? መምህር ግርማ፡-ከ1993 ዓ.ም ጀምሮ እዚህ አዲስ አበባ ያልተቋረጠ አገልግሎት ሰጥቻለሁ፡፡
ላይፍ፡- በእነዚህ አገልግሎት ዘመናት ለቤተክርስቲያን ምን አስተዋጽ አበርክተዋል ? መምህር ግርማ፡-  በእስጢፋኖስ ደብር ጣሪያው ውሃ ያስገባበት ወቅት 3 ሚሊየን ብር ገቢ አሰባስቤ አድሳት አድጌአለሁ፡፡
ላይፍ፡- ለምን ያህል ህሙማን ከህመማቸው የመፈወስ እና ትምህርት አገልግሎት ሰጥተዋል..? መምህር ግርማ፡- ለ4 ሚሊየን ሰው የፈውስ አገልግሎት ሰጥቻለሁ፡፡
ላይፍ፡- በተለይ በምን አይነት ህመም ሲሰቃዩ የነበሩ ሰዎችን አድነዋል ? መምህር ግርማ፡-  አይናቸው የጠፋ ፤ ሰውታቸው አልታዘዝ ብሎ አልጋ ላይ ውለው የነበሩ ፤ እጅና እግራቸው ሽባ የነበሩ ሰዎችን ፈውሻለሁ፡፡
ላይፍ፡- ሁላችሁም የእግዚአብሔር ቃል  የእመቤታንን በረከት የምታስተምሩበት ቤተክርስቲያን ለምን እንዲህ አይነት መከፋፈል መጣ ብለው ያስባሉ ? መምህር ግርማ፡-  በመጽሀፍ ቅዱስ ውስጥ እንክርዳድ በስንዴው መሀል እንደሚዘራው ሁሉ ያም በቤተክርስቲያን ውስጥ አለ፡፡ ገበሬው መልካም ስንዴን ዘራ የሚለው ከውጭ አይደለም፡፡ ዘሩ እዚያው ቤተክርስቲያን ውስጥ ነው፡፡ ስለዚህ በቤተክርስቲያን መንፈሳዊ ህይወትና በልቦና ውስጥ መጀመርና በስጋ ህይወት መጀመር ልዩነት አለው፡፡ አምኖ መጀመርና ሳያምኑ መጀመር የእዚያን ያህል ነው፡፡ ሰሞኑን ወደ ቤተክርስቲያን ገብተው የሚኖሩ በጣም ብዙ ናቸው፡፡ እነዚህ ከተለያዩ የአስማት ስራ ጋር ወደ ቤተክርስቲያን ሲጠጉ ብዙ መልካም ነገር አይጠበቅባቸውምና ይህንን የሚመለከት ‹‹በማለዳ መያዝ›› የሚለው መጽሀፌ ላይ ሰፋ ባለ መልኩ አስቀምጬዋለሁ፡፡ ንጹህ የአምልኮት ፍላጎትና እንዲሁ ደግሞ በደብዛዛው በሚመላለሱ ሰዎች መካከል ዲያቦሎስ በደንብ ይሰራል፡፡ በተለይ ኦርቶዶክስ እምነት ላይ ሰይጣን ከፍተኛ ትኩረት ይሰጣል፡፡ ከታሪክ እውነታም አንጻር እነዚህ ሰዎች ህይወት ውስጥ የተለየ እድል አለ፡፡ ገብቶ ይቀመጥና በጎው መጥላት መልካሙን እንደክፉ ማየት ማሳደድ ያለው መናፍቆች ላይ ሳይሆን እኛ ጋር ነው ያለው፡፡ ይህ ደግሞ የሃይማኖቱ አንዱ በረከት ነው፡፡ ለምን ፈሪሳውያንን ክርስቶስ በመጣ ጊዜ እምነቱን ተራ ወግና ተራ የሆነ የይስሙላ አድርገውት ነበር፡፡ ያ ሂደት ደግሞ እንደዚሁ በቆየን ቁጥር የአዲስ ኪዳንንም ህይወት እንደዚያ ነው የሚሆነው፡፡ ወደ ፈሪሳውያን ጠላት ይሄዳል፡፡ በዚህ ጊዜ እውነቱ እየጠፋ በቤተክርስቲያን ውስጥ  ጣልቃ ይገባሉና ያንን ለመለየት የመንፈስ ቅዱስ ስራም የአጋንንት የቅንነትም ስራ ስለሚያስፈልግ ዛሬ ያ ቅንነቱ እና በጎነቱ በክፋት በተንኮል በምቀኝነት የተሞላ ስለሆነ ያ ሂደት ሊያደርገን አልቻለም፡፡
ላይፍ፡- ብዙ ሰባኪያን ወደ እርስዎ ፕሮግራም የማይመጡት ለምንድነው? መምህር ግርማ፡-  ይህንን የፈውስ ሂደት ስላለመዱት ልክ እንደ መተት እንደ ጠንቋይ አሰራር አድርገው እስከዛሬ ድረስ ሲያወሩ እንደቆዩ ያው የተለመደ ነገር ነው፡፡ስላልተለመደ እንግዳ ነገር ነው የሆነው፡፡ በተለይ በግለሰብ ጸጋ አልተለመደም፡፡ ይህንን ያልተለመደ ነገር እንዲህ ሲወጣ ሁሉም እየተረባረበ ማጨለም ነው የሚፈልገው፡፡ የእግዚአብሔር ስራ ደግሞ ስለማይጨልም ሂደቱን ጠብቆ ይበራል፡፡ ከዚህም በፊትም የተደረጉብኝ ዘመቻዎች ብዙ ናቸው ይህ ብቻ አይደለም፡፡ ይህ እንዲያውም የመጨረሻው ደካማ ነው፡፡ ቤተክርስቲያን ሰዎች መንፈሳዊ አንድነታቸው በክፉ ሰዎች መንፈስ ተመቷል፡፡ በራስ እይታም ተመቷል፡፡ የምቀኝነት መንፈስ አጠናክረው በመያዛቸው ምክንያት የእግዚአብሔር ጸጋ በረከት መለያ መንፈስ አጥተዋል፡፡ አንድነትና ተስማምቶ መዝለቅን በዚህ ዘመን ውስጥ የምንጠብቀው ጉዳይ አይደለም፡፡ ግን እውነት ዞሮ ዞሮ ደረጃዋን ጠብቃ ስለምትወጣ ያን ያህል አስጊ አይደለም ማለቴ ነው፡፡
ላይፍ፡- ከአስተዳዳሪው ጋር የነበራችሁ አለመግባባት ከየት የመጣ ነው? መምህር ግርማ፡-   አስተዳዳሪው መልአከ ኃይል አባ ሚካኤል በአንድ ላይ ቁጭ ብለን በተካፈልንበት ጉባኤ ላይ ሁለት ክፍል ያለው ኮንዶሚኒየም ገዝቼ እንድሰጣቸው ጥያቄ አቅርበውልኛል፡፡
ላይፍ፡-ለቤተክርስቲያን የሚገባውን ሙዳይ ምጽዋት ይካፈላሉ ? መምህር ግርማ፡-  ኧረ በጭራሽ ምጽዋቱ ለቤተክርስቲያን ነው የሚሆነው፡፡
ላይፍ ፡- ታዲያ ከየትኛው ገቢዎ ላይ ነው አስተዳዳሪው ኮንዶሚኒየም ገዝተው እንዲሰጧቸው የጠየቁዎት ? መምህር ግርማ፡-እንዲያው ለትራንስፖርት ፤ ለምንም ወይም ሲዲ ወይም መቁጠሪያ የምሸጠው አለ፡፡ ከእሱ እንደምንም አቻችልና ግዛልኝ ፡፡ አለበለዚያ ደግሞ ሕዝቡን አስተባብረህ የበረከቱ ነገር ወደ እኔ አዙረው ነው ያሉት ሰውየው፡፡
ላይፍ፡- እኛ ከዚህ በፊት ስለዚህ ኮንዶሚኒየም ግዙልኝ ብለው ጠይቀው እንደሆነ ጠይቀናቸው በጭራሽ አልጠየኩም በማለት መልስ ሰጥተው ነበር ? መምህር ግርማ፡- እውነት በቃል ማስተባበር ይቻል ይሆን ?  ከህሊና እና ከእግዚአብሔር መሰወር ግን እንዴት ይቻላል ?
ላይፍ፡- ታዲያ ምን ምላሽ ሰጠዋቸው ? መምህር ግርማ፡-በወቅቱ ያንን ማድረግ አቅሙ ስለሌለኝ ጥያቄያቸውን እንደማልቀበል ገልጬላቸዋለሁ፡፡
ላይፍ፡- ምላሽዎ በግሳጼ ወይስ ሌላ ገጽታ ነበረው…? መምህር ግርማ፡-  በግሳጼ መልኩ አልመለስኩም፡፡ ለምን ያው የሕዝቡ ችግር ስለማውቅ ሁኔታዎችን ስጠብቅ በራሱ ጊዜ ገነፈለና የሰውየው ኃይል ወጣ፡፡ እኔ መገሰጽ አልፈለኩም፡፡ ምክንያቱም ችግሩን አውቃለሁ፡፡ እንዲህ የተወሳሰበ የሙስና አሰራሮች ከመጀመሪያው ጀምሮ በየደረጃው ስር ሰደዱ ናቸው፡፡ በአንድ ዘመን ሳይሆን እየተንከባለሉ የመጡ ችግሮች ናቸው፡፡ ሰውየው ወደ ማዕረጉ እና ወደ አስተዳደሩ ሲመጡ 60 ሺህ ብር ከፍለው ነው ለዚህ የበቃሁት ይላሉ ፤ ያንን በተለያዩ መንገዶች ማቻቻል አለብኝ ማለት ነው፡፡
ላይፍ፡- የኮንዶሚኒየም ግዢ ይህን ያል ያወጣል ብለው ግምቱን ነግርዎት ነበር ? መምህር ግርማ፡-  በቃ ሁለት ክፍል ያለው ኮንዶሚኒም ነው ይገዛልኝ ያሉት ፡፡ ግምቱንም ያውቁታል፡፡
ላይፍ፡-  እርስዎ አለኝ የሚሉት የፈውስ ጸጋ ከየት የመጣ ነው ይላሉ ? መምህር ግርማ፡- ይህ እኮ አንድና ሁለት  ነው እንደሚባለው አይነት ፎርሙላ ወጥ አድርገህ የምታሳየው ነገር አይደለም፡፡ ይህ በጸሎት በስግደት በቅዱስ ቁርባን በመመጽወት ከሰማይ የሚለቀቁት እንጂ ከማንኛውም ሰው የምትገዛው ወይም የምትለውጠው ትርፍ ያለው ነገር አይደለም፡፡ ይህ ከሰማይ የሚሰጥ እንጂ በስጋዊ ጥበብባ ዘዴ ወይም ምርምር ወደ ላብራቶሪ የሚመጣና የሚገኝ አይደለም፡፡ ምክንያቱም የእግዚአብሔር አሰራር ነው፡፡ የእግዚአብሔር አሰራር ደግሞ አለምም ሆነ ስጋውያን አያውቁትም፡፡ መንፈሳውያንም ተቸግረዋል፡፡ በዚህ ዘመን ያሉ የገዛ አባቶቼ እንኳን  ሳይቀሩ ይህንን መንፈሳዊ ጸጋ ለመቀበል በጣም ይቸገራሉ፡፡ ምክንያቱም ከእኛ በኩል ካፈሰሰ ነው እኮ አሁን ችግሩ፡፡ ከእኔ በኩል ካልፈሰሰ እንዴት በዚህ ዘመን ከእግዚአብሔር ይመጣል ፤ የሚል ዋጋ ቢስ እና ተስፋ አስቆራጭ የመንፈሳዊ ህይወት ጉዞን የለመዱት ባህሪ ለማንጸባረቅ ሲሞክሩ ነው አሁን ነገሮች ወደዚህ አይነት አጣብቂኝ ውስጥ የሚገቡት፡፡
ላይፍ፡- እርስዎ ተሰጥቶኛል የሚሉት የመንፈስ ጸጋ ስያሜ ሰጥተውታል ? መምህር ግርማ፡- እንደዚህ ያለ ነገር የለም እንጂ ምን ስሜ ይሰጠዋል ? ክፉ መናፍስን የሚቃወም የእግዚአብሔር መንፈስ ነው፡፡ የእግዚአብሔር መንፈስና ክፉ መንፈስ ደግሞ አይገናኙም፡፡ የእግዚአብሔር መንፈስ የእግዚአብሔር ስጦታ ነው፡፡ የእግዚአብሔር ስጦታ ደግሞ ክፉውን መለየት ፤ ክፉው ማስወገድ ነው፡፡ በመጽሀፍ ቅዱስ ውስጥ አጋንንትን አወጡ ይል የለም እንዴ? በአሁኑ ዘመን አጋንት አስገባ ቢባል ሁሉም ይወደኛል፡፡ አጋንንት ማስወጣት እኮ ነው የተለየ ጠንቋይ ያደረገኝ፡፡
ላይፍ፡-አለኝ የሚሉት የመንፈስ ጸጋ ወደ ሌላ ሰው ማስተላለፍ ይችላሉ ? ወይስ እርስዎ ጋር ነው ሊቀር የሚችለው ? መምህር ግርማ፡- የኤልያስ መንፈስ በኤልሳ እንዳደረ ሁሉ የፈለገው ሁሉ ያገኛል፡፡ እኔም የማስተምረው እኮ ክርስቲያኑ ራሱን ችሎ እንዲቆም ነው፡፡ ጠላቱን እንዲጋፈጥ ፤ ክፉ መንፈስ እንዲያሸንፍ ፤ የዲያቢሎስ ትውልድ መሆኑ እንዲቆም ፤ ከዚያም በላይ የመንፈስ ቅዱስ ስራ የእግዚአብሔር ክብርና ኃይል እየጨመረ እንዲመጣ ፤ የአለም ጥበብ ከእግዚአብሐየር መላዕክ አሰራር ጋር ክርስቲያኖች በረከት ውስጥ እንዲገቡ ነው፡፡፡ አሁን ለምሳሌ በአሜሪካ በስልክ የሚሸኝላቸው ብዙ ሰዎች አሉ፡፡ በእጄ ማስረጃ አለኝ፡፡ በስልክ የሚሸኝላቸው ራዲዮ አቢሲኒያ ላይ ከቁትር 1 ጀምሮ እስከ 34 ድረስ ያለውን ትምህርት በመከታተል እየጸለዩ እየሰገዱ በመቁጠሪያ እየቀጠቀጡ መንፈሱን ያዳክሙታል፡፡ ከዚያ በኋላ መንፈሱ ራሱ እኔ አይ ጥላ ነኝ ፤ ቡዳ ነኝ ፤ አብሬ ነው የተወለድኩት እያለይነግራቸዋል፡፡ በመጨረሻ ከተዳከመ በኋላ አንዳዴ ራሱ ‹‹ሸኙኝ›› ብሎ ይደውላል፡፡ በእጄ የቀረጽኳቸው ከ200 በላይ በስልክ የሸኝሁላቸው ሰዎች አሉ፡፡ አሁን አባቶች ይህ ነገር ሲሰሙ ይደነግጣሉ፡፡ ምክንያም እንዴት በስልክ ሰይጣን ይወጣል  ብለው አንድ ወቅት ላይ አቅርበው ጠይቀውኛል፡፡ ስለዚህ ጸጋው የቤተክርስቲያን እንጂ የእኔ አይደለም፡፡ መቁጠሪያው የቤተክርስቲያን ነው፡፡ ውዳሴው የቤተክርስቲያን ነው፡፡ መላከ ትግሉ የቤተክርስቲያን ነው፡፡ ከዚህ ውጪ የእኔ የያዝኳቸው የምትሀት አሰራር የለም፡፡ ስለዚህም ሁሉም ህዝብ በውጭ አለም ያለው በተለይ ከክፉ መንፈስ ጋር ያለውን ፍልሚያ በሚገባ ስለተገነዘበ እያንዳንዱ ራሱ በመቁጠሪያ እየተጠቀመ የሸኝውም አለ፡፡
ላይፍ፡- አባቶች እርስዎ የሚሰጡት መንፈሳዊ ጉባኤ ተገኝተው በረከት ይሰጡ ነበር ወይ ? መምህር ግርማ፡- እኔ በማገለግለው ላለመገኝት ብዙዎች ይሸሻሉ ተሰልፈው ዝቅ ብለው የህዝብን ችግር ለማየት እስከ አሁን በጎ ህሊና አላገኝሁም፡፡ ሃገር እንደ አቡነ እስጢፋኖስ የጅማው ኃገረ ስብከት ሊቀ ጳጳስ አይነቱ በተደጋጋሚ የህዝቡን ችግር ተረድተው በተደጋጋሚ ወደዚያ እየሄድኩ ሳገለግል መንፈሳዊ ድጋፋቸውን ለህዝቡ ካለው ችግር ለልማቱም ከማሰብ ቢርሌ የሰጡት ቦታና ስራ አለ፡፡
  ላይፍ፡- አባቶች እርስዎ የሚሰጡት መንፈሳዊ አገልግሎት አስተያየታቸው ምንድነው ? መምህር ግርማ፡- ብዙዎች ይህንን መንፈሳዊ ድርሻ ለመወጣት በማደርጋቸው ጥረቶች ላይ በጎ ድጋፍ የላቸውም፡፡ ከተለያዩ አይነት መንገድ ለመዳንም ይሰጣሉ፡፡ ነገር ግን አንዳዶች እንዲያውም የሸናሻም መተት ይህን ያደርጋል፡፡ የሸናሻም አስማት ይህንን ይሰራል እያሉ ለአስት አሰራር ትልቅ ድጋፍና የሰይጣን አሰራር ትልቅ ሞራል ሲሰጡ ነው የሚሰማው፡፡
ላይፍ፡- ይህንን እርስዎ የሚያደርጉትን መንፈሳዊ አገልግሎት ሌሎች አባቶች ያምኑበታል ? መምህር ግርማ፡- እኔም በጣም ግራ የሚገባኝ ዲያቢሎስ የሚያደርገው ጥቃት በመጽሀፍ ቅዱስ በረጅሙ እና በስፋት ጥልቀት ባለው ሁኔታ ገልጿል፡፡ ሐዋርያት አጋንንትን እያወጡ የሰዎችን ደህንነት ሲያበለጽጉ ይታያል፡፡ በቤተክርስያንም እደዚሁ በመንፈሳዊ አገልግሎት በመንፈስ ቅዱስ ስራ እንደሚሰራ ይታወቃል፡፡ እንግዲህ ሰዎች በክፉ መንፈስ አሰራር  ወይም አያምኑም አልያም በእዚአብሔር አሰራር አያምኑም፡፡ በዚህ መንታ መንገድ ላይ መታየት አሁን አይቻልም፡፡ ምክንያም የእግዚአብሔር ሕዝብ በዲያቢሎስ ተጠቅቷል፡፡  ወይ ዲያቢሎስ እንዲበላ ማድረግ ነው አልያም በቤተክርስቲያን መንፈስና ጸጋ ህዝቡ ችግር ውስጥ ገብቶ ችግሩን ማየት ነው፡፡ ገለልተኛ ሆኖ መኖር አሁን አሁን ጊዜው አይደለም፡፡ ስለዚህ ያምናሉ አያምኑም የሚለው ነገር እርሳው እኔን ቢረዱኝ ደስ ባለኝ፡፡ በተሰጣቸው ጸጋ ክፉ መንፈስ ነው ካሉ የእኔን መንፈስ ማወጣት መቻል፡፡ ሁሉም ቢተባበሩኝ መልእክት አስላልፋለሁ ፡፡ እንዲያውም በቤተክርስቲያን ይኖር የነበረ አስማተኛ መንፈሱን አስወጣንለት ብለው ለአለም ዜና ቢያቀርቡ ደስ ባለኝ ነበር፡፡
ላይፍ፡- ቤተክርስቲያኗ ወታደርና ነጋዴ የቤተክርስቲያን አገልጋይ አይሆንም የሚል ሕገ ደንብ አላት፡፡ እርስዎ ግን መንፈሳዊ ሕይወት ውስጥ ከመግባትዎ በፊት ወታደር እንደነበሩና እስጢፋኖስ ቤተክርስቲያን አገልግሎት መስጠት ከጀመሩ በኋላ 1.5 ሚሊየን የሚገመት ቤት ገዝተው እየኖሩ ነው ይባላል በዚህ ላይ ምን ይላሉ ? መምህር ግርማ፡-ዛሬ ሰማዕቱ ሀገር ጠባቂ የምንለው ቅዱስ ጊዮርጊስም የመቶ አለቃ ወታደር ነበር፡፡ ግብጽ ውስጥ ያሉ ብዙ ታላላቅ አባቶችም እንደዚያው ናቸው፡፡ በአሁንም ዘመን ያሉ ብዙ መነኮሳቱ እስከ ጳጳሳቱ ወታደር የነበሩ ናቸው፡፡  ወታደር ማለት የእግዚአብሔርን ስራ አይሰራም ማለት አይደለም ፡፡ እኔ ደግሞ ልቀድስ ላቁርብ አላላኩም ፤ በተሰጠኝ ጸጋ ላገልግል ነው  ያልኩት፡፡ ቤት ምናምን የሚሉት ቤቱን የገዛልኝ የተፈወሰ ሰው ነው፡፡ ቤቱን የገዛልኝ እግዚአብሔር በሰው በኩል ነው ፡፡ ቤቱን የገዙልኝ ሰው በተጨባጭ ከጎኔ አሉ፡፡ ይህንን እንደ አንድ እንደ ትልቅ ነገር ማንሳት በራሱ ምንን ያመለክታል ፤ ምቀኝነትን ነው ፤ ያው ከደማችን ውስጥ የተለመደ ምቀኝነት ስላለ እንጂ ከነዚህ ሁኔታዎች በሙሉ እንዳሰራ የሚያደርጉ አይደሉም፡፡
ላይፍ፡- እርስዎን አስማተኛ እና ጠንቋይ ናቸው የሚሉዎት ሰዎች ምላሽ ምንድነው ? መምህር ግርማ፡- እኔ አስማተኛ ከሆንኩ እኔ ጋር መጥተው አስማቱን ማውጣት ነው፡፡ እኔ ጋር መጥተው አስማቴ የት ጋር እንደተቀበረ ፈልገው ማውጣት ነው፡፡ ክንዴ ላይ ወይም እግሬ ላይ ወይም ጭንቅላቴ ላይ እንዳለ ደንበኛ ራጅ ይዘው መጥተው ፈልገው ማውጣት፡፡ ወይም መንፈስ ከሆነ ያስወጡልኝ፡፡ ቢረዱኝ እኮ ለእኔም ደስ ይለኛል፡፡ ግልግል ነበር፡፡ እስቲ አስማቴን ኑ እና አስወጡልኝ እባካችሁ ስለ እግዚአብሔር ስለ ቅድስት ድንግል ማርያም ብዬ እለምናችኋለሁ፡፡

Thursday, May 9, 2013

መላከ ሰላም ዘላለም እሰይ ስለ መምህር ግርማ ምን ይላሉ?

የቅዱስ እስጢፋኖስ አስተዳዳሬ አቶ ሚካኤል ታደሰ የሃሰት የምልኩስና ስሙ ኃይለ ኢየሱስ/ ከአርባምንጭ የተባረረበት ደብዳቤ





የመምህር ግርማ ወንድሙ እገዳ በተመለከተ የቀድሞው የቅዱስ እስጢፋኖስ ቤ/ክ አስተዳዳሪ መላከ ሰላም ዘላለም እሰይ የሰጡት  አስተያየት እና ከ እገዳው ጀርባ ያሉ  እውነቶች




 የ እገዳ ደብዳቤውን ከቤተ ክርስቲያኑ ሰንበት ትምህርት ቤት የፌስ ቡክ ገጽ ይመልከቱ

Who is priest/Exorcist Memeher Girma Wondimu?