የኢንተርኔት አገልግሎት ፈጣን ባልሆነበት ቦታ
በአማራጭነት ይህንን በጽሑፍ መልክ ያንብቡ:: ረጅም ትምሕርት ሲሆን በተቻለ መጠን በቂ መልክቱን በጽሑፍ
አቅርበናል:: የቃላት ግድፈት ካለ እያረሙ እንዲያነቡ እንጋብዛለን::
የጸሎት ቦታ እንዴት ላዘጋጅ?
ክፉንና
ደጉን ለመለየት አምልኮ ያስፈልጋል:: አምልኮ የሌለበት ህይወት አለም ላይ የወደቀ ነው ስለዚህም የአምልኮት ራእይ
አንድ ክርስቲያን ሊኖረው ይገባል:: ማምለክ ማለት እግዚያብሔርን ከልብ መውደድ: ቃሉን በልቦና ማኖር: እና መጠበቅ:
እርሱን ተስፋ ጉልበታችንን ማድረግ ነው:: በተግባር ደግሞ ኑሮን ጠባይን ለእግዚያብሔር መስጠት: ውስጣዊ ህይወታችንን
ለክብሩ የተዘጋጀ ማድረግ :: ስለ ሐጢአታችን ንሰሐ ገብተን ሥጋውና ደሙን መውሰድ: እለት እለት ስለበደላችን
ስለሐጢአታችን ለእግዚያብሔር መንገር:: እለት እለት እግዚያብሔርን የምናመሰግንበትን ግዜ ካገኘን የአምልኮት
ሕይወት ገበና አለን ማለት ነው:: ሰብአ ሰገል ክርስቶስን በፍቅር ፈልገው እንደመጡ አንድ ክርስቲያንም ክርስቶስን
ፈልጎ መምጣት አለበት:: በአምልኮት ባሕርይ ሔሮድስን ማለፍ ቅድሚያ የሚሰጠው ነገር ነው:: ሔሮድስ ማለት የዚህ
አለም ነገሮች ናቸው እነዚህም :የአለምን ሰዎች እውቀት: ሳይንስ እግዚያብርሔን የሚከለክል : የድንግል ማርያም ልጅ ክርስቶስን
የሚከለክል ነው:: ሔሮድስ ማለት ሐብት : ስልጣን: ማዕረግ የመሳሰሉት እነዚህ ሁሉ የሔሮድስ መንገድ ጠቋሚ
ናቸው:: ሰዎች የጥፋት ሞት ውስጥ የሚገቡት የአምልኮት ሕይወት በማጣት ነው:: እግዚያብሔርን የሚፈልጉ ሰዎች ሔሮድስ
ጋር መቅረት የለባቸውም:: ኮከቡን ማየት አለባቸው ኮከቡም ያለው በሰማይ ነው::
ብዙ
ክርቲያኖች ወደ እግዚያብሔር ቤት አይሔዱም ወይም ወደ ሰማይ ቀና አይሉም:: በዚህም ወደ ልባቸው የሚሔድባቸው
መጣባቸው:: ሰይጣን ወደ ቤታቸው ወደ ኑሮአቸው ወደ ሕይወታቸው መጣ:: በዚህ ዓለም ገለልተኛ ሆኖ መኖር አይቻልም:: በዚህ
አለም ሁለት ነገር ነው ያለው:: ጽድቅና ኩነኔ: ጨለማና ብርሃን: ሓጢአትና ጽድቅ: ሰላምና ጦርነት::ከፈለክ ወደ
ብርሃን ካልፈለክ ወደ ጨላማ: ከፈለክ እውነት ካልፈለክ ሐሰት: እንዲህ በጥንድ የተያያዘ ነው:: የእግዚያብሔርን
በቅድምያ ከሰማን የእግዚያብሔር ጽድቅ ይገለጥልናል: የሰዎችን ከሰማን ሁል ግዜ እንደተደናገግርን ተስፋችንን
በአልሆነ አቅጣጫ እየጠበቅን እንኖራለን:: ሔሮድስ ክፉ መሆኑን የምናውቀው ስናመልክ ነው::
የጸሎት ቦታ

ራእይን
ምሪቱን ለማግኘት ደግሞ የጸሎት ቦታችን ላይ ለባልና ሚስት የመኝታ ያህል መኖር አለበት: ቤተሰብ ካለው ከሌለው