በአቡነ መልከ ጸዴቅ ገዳም የተደረገውን ተዓምር ብጹእ አቡነ ዲዮስቆሮስ እንዲህ ይመሰክራሉ::
የሚዳ አቡነ መልከ ጼዴቅ ገዳም (Mida Abune Melketsedek Monastry)
የጸሎት
አቅጣጫ ምስራቅን የተመለከተ መሆን አለበት:: በመንበርከክ በግንባር ልክ የእመቤታችን የቅዱስ ሚካኤል የቅዱስ እና
የቅዱስ ገብርኤል በግራና ቀኝ : በመቆም ልክ የስላሴ የመድኃኔአለም ስእል ይደረጋል:: ከስእሉ ራቅ የሚባለው
ክፍተቱ
የመጽሐፍ መግለጫ ያህል ነው:: ስእሎቹ ተጸልዮባቸው ቅባ ቅዱስ ይቀባሉ ቢቻል ቤተ ክርስቶያን ተባርካው በቅዳሴ ግዜ
ቅባ ቅዱስ ተቀብተው መሆን አለበት:: ስእሎቹ በጥሩ ፍሬም የተሰሩ ስእሎች መሆን አለባቸው:: ከስራቸው የጸሎት
ወሃ : እጣን: እምነት:የወይራ ዘይት: የመጽሀፍ ማስቀመጫ: የምንጠቀምባቸው እንደ ሽቶ ዎች ካሉ አጠገብ መሆን
አለባቸው:: ሽቶ የሚወዱ ዛሮች አሉ:: ተጸልዮበት ሽቶ ብንጠቀም ሽቶ የሚወዱ ዛሮችን መከላከል ይቻላል :
የመንበርከኪያ ቦታ ደረቅ ያለ የጥጥ ፍራሽ ቢሆን ይመረጣል:: ግልበት በሚሰግድበት ግዜ መመቻቸት አለበት ነገር ግን
በጣም የሚመች ሥፕንጅ መሆን የለበትም: ስንፍና እንዳይሰማው: የሚሞቅ ነገር መሆን የለበትም መቀዝቀዝም
የለበትም::
በሚሰግድበት ግዜ በስእሎቹ ፊትለፊት መስገድ ሲጀምር የሚከተሉትን ምልክቶች ያያል:- መዛል:መድከም መልፈስፈስ
:: በሚጸልይበት ግዜ ከስእሎቹ የሚወጣ መንፈሳዊ እሳት አለ:: በሰውነቱ ላይ ከስእሎቹ ተጠግቶ ሲጸልይ መውረር
መቅበጥበጥ:ማቃጠል የሚታይበት ይሆናል:: አንዳንዱም መንፈሱ ወዲያው መገለጥ ጠባይ አለው:: መንፈሱ ጸሎት በከፍተኛ
ሁኔታ ጸሎት እየከለክለው የሚያጠቃው ከሆነ የቅዱስ ሚካኤልን ስእል በፍሬም በጥሩ ሁኔታ ሰርቶ መሬቱ ላይ አድርጎ
እጁ ላይ እና ሰይፉ ላይ በሚሰግድበት ግዜ መንፈሱ ሊጥለው ይችላል:: በዚህ ግዜ መቁጠርያ ያስፈልጋል::ጸጥ በል
በጌታየ በየሱስ ክርስቶስ ስም ብሎ ሲመታው ቅዱስ ሚካኤል ሆይ እሰርልኝ ሲለው በስእሉ ፊት ያለው ሐይል እየተገለጠ
ቅዱስ ሚካኤል ሊያስርለት ይችላል:: ሰውየው እየሰማም እያወቀም መንፈሱን ሊያስርለት ይችላል:: በዚህ ግዜ
ፕሮግራም ይዞ ወድ እኔ ደውሎ አንዳንድ መረጃ እንለዋወጣለን:: የሚደክም ከሆነ ይደክማል የሚሸኝም ከሆነ
ይሸኛል:: ሆኖም ግን እነዚህን ልምምዶች በቀላሉ የሚመጡ አደሉም:: ሰውየው በጥሩ የበረከት መንፈሳዊ ህይወት
ለማለፍ እራሱን ማዘጋጀት አለበት:: ጸሎትን እንደ ደስታ አምላክን እንደማማረርያ ጎዳና ሳይሆን "ሁል ግዜ በጌታ
ደስ ይበላችሁ:ደግሜ እላለሁ ደስ ይበላችሁ::ገርነታችሁ ለሰው ሁሉ ይታወቅ::" እንዲል ገራገር መሆን አለበት::
"ጌታ ቅርብ
ነው::በነገር ሁሉ በጸሎትና በምልጃ ከምስጋና ጋር በእግዚአብሔር ዘንድ ልመናችሁን አስታውቁ እንጂ በአንዳች
አትጨነቁ::" ፊልጵስዮስ 4:4-6