Thursday, July 14, 2016

አባ ጊዮርጊስ ዘጋስጫ ያደረጉት ተአምር

አንድ አምላክ በሚሆን በአብ በወልድ በመንፈሰ ቅዱስ ስም አሜን
ዛሬ በዓመታዊ የዕረፍታቸው በዓል ታስበው የሚውሉት አባ ጊዮርጊስ ዘጋስጫ ያደረጉት ተአምር ይህ ነው፡- አምሃራ ሳይንት ቦረና ከአባ ጽጌ ድንግል ገዳም የ5 ሰዓት የእግር መንገድ ከተሄደ በኋላ የአባ ጊዮርጊስ ዘጋስጫ ገዳም ይገኛል፡፡ ይኽ የአቡነ ጽጌ ድንግል ገዳም ከአቡነ ጊዮርጊስ ዘጋስጫ ገዳም ጋር የሚያገናኘው ‹‹የእግዜር ድልድይ›› የተባለ አስገራሚ ታሪክ ያለው ድልድይ አለው፡፡ ሁለቱ ቅዱሳን በመንፈስ ተጠራርተው ለመገናኘት ቢያስቡም ታላቁ የወለቃ ወንዝ ሞልቶ በአካል ሳይገናኙ ቀሩ፡፡ በዚህም ሁለቱ ቅዱሳን አዝነው ከወንዙ ወዲያና ወዲህ ሆነው አፈር ተራጭተው ቢመለሱ ያ የተራጩት አፈር በተአምር ድልድይ ሆነ፡፡ ድልድዩን ሁለቱም በበዓታቸው ሆነው በመንፈስ አዩት፡፡ ጠላት ሰይጣንም ይህንን ሲያይ ድልድዩን በትልቅ ሹል ድንጋይ በስቶ ሊያፈርሰው ሲል አባ ጊዮርጊስ በመንፈስ አዩትና ከጋስጫ ተነሥተው በደመና ተጭነው በመሄድ ሰይጣኑን በግዘፈ ሥጋ ገዝተው ያንን አፈርስበታለሁ ያለውን ትልቅ ድንጋይ አሸክመውት ደብራቸው ጋስጫ ድረስ ወስደውታል፡፡ ያ ድንጋይ ዛሬ በገዳሙ ደወል ሆኖ እያገለግለ ይገኛል፡፡ ድልድዩም እስካሁን ድረስ ለአካባቢው ሙስሊም ማኅበረሰብ ብቸኛው የወለቃ ወንዝ መሻገሪያቸው ሆኖ እያገለገላቸው ይገኛል፡፡

በተአምራት የተሠራው የእግዜር ድልድይ

አባ ጊዮርጊስ የፈለፈሉት ድንቅ ቤተ መቅደስ
 


ሰይጣን ድልድዩን ሊያፈርስበት የነበረው ትልቁ ሹል ድንጋይ አሁን በጋስጫ ገዳም ለመነካካቱ ደወል ሆኖ ያገለግላል
 

ሌላው በእነዚህ ሁለታ ታላላቅ ገዳማት ያየሁት እጅግ አስገራሚ ነገር ቢኖር ሻሾ የሚባለው ነው፡፡ ይኸውም ታማኙ ውሻ ሻሾ በ2006 ዓ.ም እኔ ከአባ ጽጌ ድንግል ገዳም ወደ አባ ጊዮርጊስ ዘጋስጫ ገዳም ለመድረስ የ5 ሰዓት የእግር መንገድ መሄድ ግዴታ በሆነብኝ ሰዓት አሰልቺውን የበረሃ ጉዞ ከአንድ ጓደኛዬ ጋር ስንጓዝ ሙሉውን የ5 ሰዓቱን መንገድ ይመራን የነበረው ታማኙ ውሻ ሻሾ ነበር፡፡ ደክሞን ስናርፍ አብሮን እያረፈ፣ መሄድ ስንጀምርም አብሮን ከፊት ከፊት እየተራመደና መንገዱን እየመራ እዛው ገዳሙ አደረሰን፡፡ ሻሾ ዛሬ ከሰው ይበልጥ ናፈቀኝ፡፡ የጻድቁን የአባ ጊዮርጊስ ዘጋስጫን በረከት አንድም ታማኙን ሻሾን ለማግኘት መስከረም ላይ ከግሸን መልስ ለመሄድ አስቤያለሁና አምላከ ቅዱሳን ይፍቀድልኝ፡፡

ከአባ ጽጌ ድንግል ገዳም እስከ አባ ጊዮርጊስ ገዳም ድረስ ያለውን የ5 ሰዓት የእግር መንገድ ከፊት ከፊት እየመራ በረሃውን አቋርጦ የወሰደኝ የገዳሙ ታማኝ ውሻ ሻሾ- ከገዳሙ በቅርብ ርቀት ላይ ከደረሰ በኃላ ሲያሳርፈን፡፡


የግሸን ተጓዞች ይኽን አጋጣሚ ብትጠቀሙ በረከቱ ዕጥፍ ድርብ ይሆንላችኃል፡፡ ከደሴ በግማሽ ቀን ወግዲ የምትባል ከተማ በማደር በቀጣዩ ቀን በአሕዛብ የተከበቡትንና እጅግ አስገራሚ የሆኑትን የአባ ጽጌ ድንግል ገዳምንና የአባ ጊዮርጊስ ዘጋስጫ ገዳምን መሳለም ይቻላል፡፡ እዛው አካባቢ ደግሞ ጸበላቸው ውስጥ እንጨት ሲነከርበት መቁጠሪያ አድርጎ የሚሰጠውን የአቡነ ገብረ እንድርያስን ገዳም መሳለም ይቻላል፡፡

Wednesday, July 13, 2016

ከሰማይ መና የሚወርድበት ሰረድኩላ ሚካኤል

ከሰማይ መና የሚወርድበት ሰረድኩላ ሚካኤል አስተዋሽ ያጣ ሊታወቅ የሚገባ ብዙ ታሪክ ያለው ቤተክርስቲያኑ ፈርሶ የሚሰራው የሚረዳው የሚያስታዉሰው ያጣ ተምረኝዉ የቅዱስ ሚካኤል ገዳም ::

 
መንዝ እመጋ ቆላ አካባቢ ሰረድኩላ ቅድስ ሚካኤል :-
ይህን ገዳም እስራኤላዎቹ በደመና መጥተዉ ና ክንፍ ያላቸው ከመሰረቱት ከ፬4ቱ ቅዱሳን አንዱ /ናአድ/ የመሰረቱት ገዳም ነው፡፡
ይህ ገዳም ትልቅ ዋሻ በቤተክርስቲያኑ አካባቢ ይገኝል፡፡

ዋሻው ውስጥ ሲገቡ ያልፈረሱ ብዛትያላቸው ክንፍ ያላቸውና ክንፍ የሌላቸዉ አፅመ ቅዱሳን/ይታያሉ፡፡በዚህ ዋሻ ውስጥ ማንም ሰው ሂዶ ሊያየው የሚችል /መና/ ከሰማይ ይወርዳል፡፡በዚያ አካባቢ ታይቶ የማይታወቅ አህል ነገሮችአና መና በዋሻው ውስጥ በብዛት ተንጠልጥለው እና ዙሪያው ሁሉ፡ ሽንብራ;አተር;ባቂላ ና የተለያዩ የማይታወቁ ጥራጥሪዎች ና /የኮክ ፍሬ/ ይታያሉ፡፡ 


የሚገርመው እዚያ አካባቢ ኮክ አያቁም አይበቅልም፡፡አይተውትም አያቁም፡ዋሻው ውስጥ ሲገብ በብዛት የኮክ ፍሬ ይታያል፡፡የተለያዩ ቅርሶች በዋሻው ውስጥ ይታያሉ፡፡ ይህን ቦታ ቤተክርስቲያናችን አለማሳወቋ በጣም ያሳዝናል እግዚአብሔር ግዜ አለው ለዚህ ቦታ ወገኖቺ በቅዱስ ሚካኤል ስም ይህን ቦታ አሳውቁ የማይታወቁ ቅርሶች ያለበት ቦታ ነው፡፡እንጠብቀው፡እንከልለዉ፡እንከባከበው አደራ እላለሁ ፡፡ ቤተክርስቲያኑ አርጅቶ በራሱ ግዜ ፈርሶ አስተዋሽ አጥቶ ፡፡በአዲስ መልክ ለመስራት የአገሩ ሰወች ኮሚቴ አቋቁመው በመለመን ላይ ናቸው፡፡

የሚካኤል ወዳጆች ሚካኤልን የምትወዱ:የምትዘክሩ በቅዱስ ሚካኤል ስም እርዱት እናሰራው በጣም ታዕምር ያየሁበት እና የቅዱሳን ቦታ ነው፡፡/የሰረድኩላ ቅዱስ ሚካኤል በቤታችን ይግባ;ሀሳባችን ያሳካልን፡፡አሜን!!!
ቦታዉ፡-ከአ/አ ሰሜን ሸዋ መንዝ ሞላሌ በእመጋ ኡራኤል ኢየሱስ ገዳም አካባቢ፡መንዝ ከሞላሌ ከተማ የ፭5ሰዓት የእግር መንገድ ሰረድኩላ ሚካኤል ይባላል፡፡

ጩጊ ማርያም- ከጸበሉ ጠጥተው ስጋቸው ያልፈረሰ ፍየሎች

Friday, July 8, 2016

የሸንኮራው ዮሐንስ ተነግሮ የማያልቀው ተአምር!!!!!!!!!



ሰውነቴ በለምጽ የተመታው ነፍስ ሳላውቅ በህጻንነቴ ነው የምትለዋ የጎንደርዋ አጸደ ማርያም ነፍስ ሳውቅ ማፈር ጀመርኩኝ ትምህርቴንም አቁዋርጩ ወደ መሐል ሐገር መጣው ሰው ቤት ለመግባት ማን ይቅጠረኝ ፊቴን ሲያዮ ይደነግጣሉ ከሰው ተጠግቼ በቆሎ መሸጥ ጀመርኩኝ የዛሬ አመት ክረምቱ ሲገባ አንዲት ሴት ልትገዛኝ መጥታ ስለ ሸንኮራ ነገረችኝ አቅም የለኝም ለመሄድ ስላት ጸበልና እምነቱን ሰጠችኝ ማታ ሰውነቴን ተቀብቼው አደርኩኝ አታምኑኝም ለድህነቴ ምክንያት ሁለቱም እጆቼ ጠዋት ስነሳ ሌላ መልክ አምጥተዋል ደነገጥኩኝ ሰው ሲያየኝ ደነገጠ ምን መድሐኒት ነው አሉኝ ጨርቄን ማቄን ሳልል ሸንኮራ መጣው መጥምቁ ምን ተስኖት ሰውነቴ በሙሉ ዳነ ከሰው እኩል አቆመኝ አዲስ አበባ ስመጣ የሚያውቁኝ ጠፋውባቸው መላ አካሌ በለምጽ ተመቶ ነበርና ስድን አዲስ ሌላ ከለር ሌላ ሰው ሆንኩኝ መጥምቅዬ ከጌታው አማልዶ ምንም የማላወቀውን በሸንኮራው የሰርክ ጉባኤ ትምህርት ለንስሐ ለስጋ ወደሙ በቃው እደጁ ያወቁኝ እናት በግል ሆቴላቸው ቀጥረውኝ ጥሩ ደሞዝ አገኛለው ከዝናብና ብርድ ዳንኩኝ ትላንት በበዓሉ ግቢው በእልልታ ስታቀልጥ ነበህ እህታችን እኔን የዳበሰ የዮሐንስ አምላክ ሁላችሁን ይዳብሳችሁ ትላለች አሜን

ተአምር በ አቡነ ገብረ መንፈስ ቅዱስ ቤተ ከርስቲያን /ሽሬ/


Wednesday, July 6, 2016

መጥምቁ ዮሐንስ ከዘመኑ እሳት አወጣኝ


አጸደ ማርያም እህታችን በአዲስ አበባ አንድ ጭፈራ ቤት ውስጥ በዘፋኝነት ትሰራ ነበር የስራ ባልደረባዋ በኤችአይቪ በሽታ ተይዛ
ወደ ሸንኮራ ጸበል ትሄዳለች አጸደ ማርያም እህትዋን ለመጠየቅ ሸንኮራ ወርዳ ሳለ የዮሐንስን ታሪክ አንገቱም በዘፈን ምክንያት እንደተቆረጠ ትሰማለች ይልቁንም ጉዋደኛዋ ያቀረበችላት የተመርመሪ ጥያቄ ያስጨንቃታል አዲስ አበባ መጥታ ስትመረመር የHiv ቫይረስ በደምዋ ይገኛል ደጋግማ ከ3ወራት ቆይታ በሁላ ስትመረመር ለውጥ የለም በመጨረሻ ወደ ሸንኮራ ዮሐንስ ጸበል በመምጣት ንስሐ ገብታ ጸበልዋን ለ1 አመት ስትከታተል ቆይታ ድጋሚ ለምርመራ ስትመጣ ደምዋ ንጹህ እንደሆነ ይነገራታል በስእለትዋ መሰረት ስጋ ወደሙ ተቀብላ ከቀደመው ህይወትዋ እራስዋን አግላለች መጥምቁ የፈወሳት በሽታዋ ብዙ ነው ከዘፋኝነት 13 አመት ሲጋራና ጫት ስትወስድም ነበር ከዝሙት መንፈስ ከጥንቁልና አምልኮ ተላቃለች ያቁዋረጠችውን ትምህርት ቀጥላ ሸንኮራ ባወቀቻት እህት እርዳታ ድግሪዋን ይዛ ትዳር መስርታ ልጅም ወልዳ አዲስ አበባ ቃሊቲ አካባቢ ትኖራለች ያችም ቀድማ የታመመች እህታችን በሽታዋ ድና ሰሜን ወሎ አንድ ገዳም ውስጥ በምናኔ ትኖራለች ክብር ለዮሐንስ


ለክርስትና ስጦታ መተት በአሻንጉሊት ተቀብሮ የተሰጣት እናት - ድንቅ ተዓምር

Friday, June 17, 2016

የሽንቁሩ ቅዱስ ሚካኤል ጠበል ድንቅ ተአምር


እባክሆን ይህን ያላመነ የሚያምንበት ያመነ የሚፅናበትን ተአምር ለወዳጅ ዘመድዋ ያድርሱል...!!!
በስመአብ በወልድ በመንፈስ ቅዱስ አሃዱ አምላክ አሜን
ደዌ ለፈተናም በ ሀጢያት ምክንያትም በብዙ ብዙ ምክንያት ይመጣል እግዚአብሄር አምላክ ፈቅዶ በቸርነቱ ይህን አደረገልኝ እንጂ እንደኔስ ሀጢያት ሌላም በተገባኝ ነበረ ለበሽታዬ ምክንያት ሀጢያት እንደሆነ ስለገባኝ እግዚአብሄርን እየተመላለስኩ በ እንባ ይቅርታ መጠየቅ ጀመርኩ።
ያልሄድኩበት ፀበል ያልያዝኩት ሱባኤ አልነበረም ነገር ግን (የ እግዚአብሔር ምህረት በጊዜዋ ነው ብሎ ነብዩ ቅዱስ ዳዊት እንደተናገረ ሁሉ በመጨረሻ የ ሽንቁሩ ቅዱስ ሚካኤልን ታምር እና ዝና ሰምቼ ወደ ሽንቁሩ መጣሁ እንደቦታው ስርአት ንስሀ ገብቼ ፀበሉን ተጠምቄ መጠጣት ስጀምር ፀበሉን ከጠጣሁ ቡሀላ ባሉ 5 ደቂቃዎች ውስጥ ከሆዴ ውስጥ በስርአት የተከተፈ ስጋ
የሚመስል ነገር ይወጣ ነበር።



በሁኔታው ስደናገጥ በቦታው የቆዩ ፀበልተኞች አይዞህ ይሄ የሚወጣው መርዙ ነው በርታ ይሉኛል ቆይቶ አረንጉዋዴ ፈሳሽ ከሆዴ ወጣ ከዛቡሀላ ከበሽታዬ ሙሉ ለሙሉ ተፈውሻለሁ እኔን የረዳ እናንተንም ይርዳ አሜን።

ይህ የምትመለከቱ ምስል ወንድማችን ባለፈው የሽንቁሩን ደብረ መድሀኒያአለም ቅዱስ ሚካኤል ቦታ ጠይቆኝ በሙሉ እምነት በመሄድ ዕፀበሉ ቦታ በመሄድ ንሰሃ ገብቶ ካንተ በቀር ማንም የለኝ ብሎ በበሽታው ሲጨነቅ ሲጠበብ ይሄው እንደምታዩት ለዘመናት ሲያሰቃየው የነበረውን በሽታ በቅዱስ ሚካኤል ሀይል ፀበሉን በመጠጣት ይሄን ከሆዱ ውስጥ አውቶለታል።

እውነት እንደ ዛሬ የተደሰትኩባት ቀን የለችኝ የሰው ልጅ ስቃይ ሲፈታ ከማየት የበለጠ ምን ደስታ አለ።እንግዲህ እኛ የምናመልከው የምናምነው ፀበል ይሄ ነው ታምሩ ኦርቶዶክስ በማንኛውም በምታደርገው ነገር አትሳሳትም።
ወንድሜ ከዚህ በላይ ታምሩን ለመናገር ያብቃ ለእርሱ የደረሰ አምላክ ስንት በየቤታችን የሚሰቃዩ ያልጋ ቁራኛ ሆነው የሚሰቃዩ እህት ወንድሞች አሉን በምህረቱ አይን ይጎብኝልን።
ታምሩን ሼር በማድረግ ይተባበሩን ሁላችንም ለደጁ አብቅቶ ታምሩን ለመስከር ያብቃን ይችን ቀን በጉጉት እጠብቃት ነበር በእውነት ለእግዚአብሄር የሚሳነው ነገር ምን አለ።