Tuesday, August 19, 2014

የዘማሪ አለማየሁ ኡርጌ ምስክርነት- በፀበል ኃይል ከሞት መዳን

ዘማሪ አለማየሁ ኡርጌ ከአገልግሎት መልስ ባላወቀው ሁኔታ ከባድ ሕመም አጋጠመው::ያጋጠመው ሕመም ግን መፍትሔ እንደሌለው እና እግሩ መቆረጥ እንዳለበት ተነገረው:: በፀበል ኃይል እግዚያብሔር ያደረገለትን ድንቅ ተዓምር ከምስለ ወድምጹ ይከታተሉ::

 

ወንቅእሸት - ሙት አንሳው- ቅዱስ ገብርኤል ገዳም
ሸንኮራ ዩሐንስ ጸበል; አንጀት ካንሰር; ፍቅርተ; የእግር እብጠት

Wednesday, July 30, 2014

ድንቅ ተዓምር በሸንኮራ ቅዱስ ዩሐንስ ጸበል


የተወደዳችሁ የእግዚያብሔር ቤተሰቦች ዛሬ የምንመሰክራላችሁ ተዓምር ለወንድም አንተነሕ ኃይሌ የተደረገለት ሲሆን: ይህ ወንድም በ2005 ዓ.ም ታሞ ወደ ሕክምና ጣቢያ በመሔድ ምርመራ ያደርጋል:: ነገር ግን ውጤቱ አስደንጋጭ ብሎም ያልተጠበቀ ነበር:: የሕክምና ዶክተሩ የአንጀት ካንሰር እንዳለበት ይነግሩታል:: ይህ ብቻ አደለም ሌላ በጣም ተስፋ አስቆራጭ ነገርም ነገሩት እርሱም በዚች አለም በህይወት ሊቆይ የሚችለው ቢበዛ ለ 3ወር ብቻ እንደሆነም ጭምር ያስረዱታል:: በዚህም አስደንጋጭ ዜና ተስፋ መቁረጥ ቢደርስበትም የተለያዩ ሆስፒታሎች ጋር በመሔድ የሕክምና እርዳታን ይሞክር ጀመር:: ለምሳሌ ኮርያ ሆስፒታል: ተክለሐይማኖት ሆስፒታል: ብሩክ ክሊኒክ ላንድ ማርክ እና ጥቁር አንበሳ ሆስፒታል ከሔደባቸው የተወሱኑ የሕክምና ጣቢያዎች ሲሆኑ የተሻላ ነገርን ግን ማግኘት አልቻለም:: በስተመጨረሻ ላይ ግን ወደ እግዚያብሄር መፍትሔዎች አዳኝነት በመመለስ በሸንኮራ ዩሐንስ ጸበል በመጠጣት የእግዚያብሔር አዳኝነትን መጠባባቅ ያዘ:: በዚህ አመት ባደረገው ምርመራ በአሁኑ ግዜ በጥሩ የጤና ሁኔታ ላይ ሲሆን "የካንሰር ስፔሻሊስት" እና የቅዱስ ዩሐንስ ሸንኮራ ጸበል ረድተውኛል" ሲል ቃል በቃል ተናግሯል:: ከዚህ በታች በምታዩት ፎቶ ላይ ዶክመንቶቹን እያሳየ እንዳለ እናያለን::

"እግዚያብሄር በጻድቁ እንደተገለጠ እወቁ..":: መዝ 4:3




Friday, April 25, 2014

ከአፄ ዋሻ ማርያም ገዳም የተሰረቀው ታቦት ከጅቡቲ በተዓምራት ተመለሰ



የእስራኤልን አምላክ ታቦት ስደዱአት፤ እኛንና ሕዝባችንን እንዳትገድል በስፍራዋ  ትቀመጥ፡፡ /1ኛ ሳሙ. 5፤ 12/
በሰሜን ሸዋ ሀገረ ስብከት በደብረ ብርሃን አካባቢ ከአፄ ዋሻ ማርያም ገዳም የተሰረቀው የመድኀኔዓለም ታቦት ከጅቡቲ በተዓምራት ተመለሰ፡፡

ከአፄ ዋሻ ማርያም ገዳም የተሰረቀው የመድኀኔዓለም ታቦት ጅቡቲ ውስጥ ለ17 ዓመታት በአንድ ግለሰብ ቤት ተደብቆ ከቆየበት ተዓምራቱን በመግለጡ በተደናገጠው ቤተሰብ ጠቋሚነት፤ ጅቡቲ ለሚገኘው ለምሥራቀ ጸሐይ ቅዱስ ገብርኤል ቤተ ክርስቲያን  በማስረከብ ሚያዚያ 17 ቀን 2006 ዓ.ም. ወደ ኢትዮጵያ ተመልሷል፡፡

“በ1938 ዓ.ም. የተቀረጸውና በአፄ ዋሻ ማርያም ገዳም የነበረው የመድኀኔዓለም ታቦት ሐምሌ 28 ቀን 1989 ዓ.ም. የቤተ ክርስቲያኑን በርና መስኮት ተሰብሮ  መሰረቁን ለወረዳው ቤተ ክህነትና ለፖሊስ በወቅቱ አሳውቀን ነበር፡፡ ለማፈላለግ ያደረግነው ጥረት ሁሉ መና ሆኖብን ቆይቷል፡፡ እግዚአብሔር በወደደ ጊዜ ወደ ቤቱ ይመለስ ዘንድ ፈቀደ፡፡” ይላሉ የገዳሙ አስተዳዳሪ ቄስ ኃይለ ጊዮርጊስ መኮንን፡፡

ጅቡቲ እንዴት እንደተወሰደ እስካሁን በግልጽ የታወቀ ነገር እንደሌለ የሚገልጹት የጅቡቲ ምሥራቀ ጸሐይ ቅዱስ ገብርኤል ቤተ ክርስስቲያን አስተዳዳሪ ቆሞስ አባ ዮናስ መልከ ጼዲቅ “ታቦቱ በግለሰቡ ቤት ታላቅ ተዓምራትን ነው ያደረገው፡፡ በቤቱ ውስጥ ደብቆ ያስቀመጠው ግለስብ ሚስት ስታብድ ልጁ ሞቶበታል፡፡ በዚህ የተደናገጠው ሌላው የሰውየው ልጅ በቤታቸው ውስጥ ታቦት እንዳለና ወደ ቤተ ክርስቲያን እንዲወሰድ ባቀረበው ጥያቄ መሠረት ጉዳዩን በመከታተል ከጠቅላይ ቤተ ክህነት፤ ከውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር፤ በጅቡቲ የኢትዮጵያ ኤምባሲና ከሌሎችም ጋር መረጃ በመለዋወጥ ወደ ኢትዮጵያ ለማምጣት ችለናል” ብለዋል፡፡

ምንጭ