Wednesday, January 14, 2015

ሙስሊሙ ያገኘው የቅድስት ሥላሴ ቤተክርስቲያን

በ02/05/07የየረር በር ጽርሐ አርያም ቅድስት ሥላሴ ቤተክርስቲያን ሰንበት ትምህርት ቤት የጥምቀት አገልግሎትን ምክንያት በማድረግ ለአገልጋዮችየጥምቀት በዓልን መሠረታዊ ምንነት፣ ትውፊታዊ አከባበርና የወጣቶች ተሳትፎን የሚዳስስ ትምህርት/ሥልጠና እንድሰጥ ጠቁመውኝ በታሪካዊውቤተክርስቲያን ተገኝቼ ነበር፡፡ የሥልጠናውን/ትምህርቱን ሙሉ ይዘት ከዚህ በፊትም በዚሁ በክታበ ገፄ/ፌስቡክ/ ላይ ለጥፌው ስለነበርከይዘቱ ይልቅ ዛሬ የቤተክርስቲያኑንና የሰንበት ትምህርት ቤቱን አንዳንድ አስገራሚ እውነታዎች ላካፍላችሁ፡፡

የየረርበር ጽርሐ አርያም ቅድስት ሥላሴ ቤተክርስቲያን በተለይ ከዛሬ አሥር ዓመታት በፊት ድፍን አዲስ አበባ የሚያወራለት፣ ሕዝብ የሚጎርፍበትቤተክርስቲያን ነበር፡፡ ቤተክርስቲያኑ የመወያያ ርእስ እንዲሆን ያደረገው ደግሞ አንድ ሙስሊም በራእይ ተገልጦለት አገኘው መባሉነበር፡፡ ሙስሊሙ  ራሱ እንደሚተርከው አሁን ቤተክርስቲያኑ ያለበትን ቦታ ገዝቶ ይኖርበት ነበር፡፡ አንድ ቀን ቤት ሊሠራ ድንጋይ ሊያነሣ ሲል “ድንጋዩየኔ ነውና አስቀምጥ” የሚል ድምጽ ይሰማል፡፡ ሌሊት ሌሊትም በግቢው ውስጥ የዝማሬ ድምጽ እየሰማ ወደ ውጭ ሲወጣ ሕፃናት እየዘመሩይመለከታል፡፡ በዚህም ምክንያት ቦታው እንዲቆፈር ያደርግና ቤተክርስቲያኑ ተገኘ፡፡አሁን ሙስሊሙ ከእስልምናም ከክርስትናም ነፃ ሆኜጥቂት መቆየት እፈልጋለሁ በማለቱ በዚያው አካባቢ እንዲሁ እየኖረ ሲሆን የእርሱ ልጆች ግን ተጠምቀው ወደ ክርስትና መመለሳቸውንናበቅዳሴ ጊዜና ዘወትር ከቤተክርስቲያኑ እንደማይጠፉ የሰንበት ትምህርት ቤቱ አባላት አጫውተውኛል፡፡



ከዚህታሪክ ባሻገር መጀመሪያ የቤተክርስቲያኑ መኖር የተገለፀው በገዳም ለሚኖሩ አባቶች እንደ ነበር የሚናገሩ ሰዎች በተለይ ከቅርብ ጊዜወዲህ ያሉ ሲሆን በጉዳዩ ላይ ጥናት እየተካሄደ መሆኑንም አገልጋዮቹ ጠቁመውኛል፡፡ በምስሉላይ የሚታየው ሕንፃ ቤተክርስቲያን ተቆፍሮ በተገኘው ላይ የተገነባ ሲሆን ወደ ውስጥ ለገባ ሰው የተገኘው ጥንታዊው ቤተክርስቲያንበውስጡ ይታያል፡፡ ከቤተክርስቲያኑጋር ከ300 በላይ የቅዱሳን አፅምና ሌሎች ቅርሶችም አብረው ተገኝተው በዚያው የሚገኙ መሆናቸውተጠቁሟል፡፡
ቤተክርስቲያኑከቅድስት ሥላሴ ታቦት በተጨማሪ የአቡነ አረጋዊ ታቦትም አለው፡፡

ከዚህበላይ የሚታየው የቤተክርስቲያኑ የድንጋይ ደወል ሲሆን ታሥረው የሚታዩት ድንጋዮች በሚያስደንቅ ሁኔታ እንደ ብረት ድምጽን የሚያወጡናቸው፡፡ አብሮኝ የነበረው አገልጋይ በእጁ ነካ ሲያደርጋቸው ከድንጋይ የማይገኝ ድምጽን ማውጣታቸውን አስተውያለሁ፡፡ ቤተክርስቲያኑበመጀመሪያ እስካለፉት ጥቂት ዓመታት ድረስ እንደገዳም ይተዳደር ነበር፡፡ እንደገዳም ይተዳደር በነበረበት ወቅት ማንም ሰው ገናቅጽሩ ውስጥ ሳይገባ በሩቁ ጫማውን እንዲያወልቅ ሕግ ነበር፡፡ አሁን ግን ጉዳዩ በፍላጎት ሆኖ ጫማ የሚወለቀው ወደ መቅደስ ሲገባሆኗል፡፡ አንዳንድ አገልጋዮችና ምዕመናን ግን አሁንም ድረስ ጫማቸውን እያወለቁ ወደ ግቢው ሲገቡ አስተውያለሁ፡፡

የደብሩሰንበት ትምህርት ቤት አባላት በአብዛኛው በምስሉ ላይ እንደሚታየው ወደ ግቢው ሲገቡ ጫማቸውን አውልቀው ነው፡፡ ላገለግል የሄድኩበትጉባኤ እስኪጀመር ድረስ ሁሉም በባዶ እግራቸው መሆናቸው አስገርሞኝ ስጠይቃቸው ይህንን በውስጠ ደንብም ሆነ ሕግ ተገደው ሳይሆንበፍቅርና በፍላጎት የቦታውን ቅድስና ለመዘከር የሚያደርጉት መጽሐፍ ቅዱሳዊ ተግባር መሆኑን ገልፀውልኛል፡፡

Tuesday, November 25, 2014

መንግስተ ሰማያት እውን ናት - እማሆይ ወለተ ጊዮርጊስ - Heaven is for real -Near death experience

መንግስተ ሰማያት እውን ናት - እማሆይ ወለተ ጊዮርጊስ በኦፕራሲዮን ግዜ መንግስተ ሰማያት እና ሲኦልን እንዳዩ ይመሰክራሉ::
Heaven is for real - Emahoy Welete Giorgis- Near death experience

ባሕታዊ አባ ገብረ ጊዮርጊስ

Wednesday, November 12, 2014

ጸሎት ሰሚዋ ኩክ የለሽ ማርያም እና አባ ኃይለ ጊዮርጊስ ዘብሔረ ቡልጋ


አባ ኃይለ ጊዮርጊስ ዘብሔረ ቡልጋ የኩክ የለሽ ማርያም ገዳምን የመሰረቱ ሲሆን በመስከረም 23 ቀን 1908 በቡልጋ ወረዳ ተወለዱ፡፡እግዚአብሔር አምላክ በእርጅና ጊዜአቸው በ64 ዓመታቸው ለመንፈሳዊ አገልግሎት ወደ ቤቱ የጠራቸው በአካለ ሥጋ በነበሩበት ጊዜም ነበር ከቅድስት ድንግል ማርያም ከቅዱሳን መላእክት ከጻድቃን ሰማዕታት ጋር ለመነጋገር የበቁ ታላቅ አባት ነበሩ፡፡
እግዚአብሔር ያከበረውን ማን ያዋርደዋል እንዳለ መጽሐፉ እኚህ ታላቅ አባት በሣርያ ቅዱስ ሚካኤል ቤተክርስቲያን ሲያገለግሉ ቤተክርስቲያን ሲረዱ የቀዩ አባት ሲሆን ከዕለታት አንድ ቀን የቅዱስ ሚካኤልን በዓል ሲያከብሩ በዋዜማው ከቅዱስ ሚካኤል ጋር በመነጋገር የሥላሴን ዙፋን ገንትንና ሲኦልን ለማየት የበቁ አባት ናቸው፡፡

ከዚህ ጊዜ ጀምሮ አባ ኃይለ ጊዮርጊስ በእግዚአብሔር አጋዥነት በቅዱሳን መሪነት ገዳሙን የመሰረቱት ሲሆን ከድንጋይ ፍልፍል አራት / 4 / ቤተመቅደሶችንና ሌሎች የባህታውያን መኖሪያ ዋሻዎች የፈለፈሉ ሲሆን አብረዋቸው ቅዱሳን መላእክት እንደሚያግዟቸው በህይወት በነበሩበት ሰዓት ይናገሩ እንደነበር የገዳሙ አገልጋዮች ይናገራሉ፡፡አራቱ ቤተመቅደሶች፡-

1. የቅዱስ እግዚአብሔር አብ ፍልፍል ዋሻ፡- ይህ ገዳም አባ ኃይለ ጊዮርጊስ በ1972 ዓ.ም ጀምረው በ1976 ዓ.ም ነው ያጠናቀቁት ሲሆን ይህን ያህል ጊዜ ለምን እንደፈጀ የራሱ የሆነ ምክንያት አለውና በቦታው ተገኝተው ሚስጢሩን እንዲያውቁ ይመከራሉ

2. ኩክ የለሽ ማርያም ፍልፍል ዋሻ፡- በ1984 ዓ.ም ጀምረው በአንድ ዓመት ጊዜ ውስጥ ነው ያጠናቀቁት፡፡ኩክ የለሽ ማርያም ማለት የጆሮ ኩክ የሌላት ቶሎ የሰዎችን ችግር የምትሰማ ለጠየቋትም ቶሎ ምላሽ የምትሰጥ እናት ማለት ነው፡፡ይህ ማለት ግን ሌሎች ቅዱሳን አይሰሙም ማለት አይደለም ፡፡ እመቤታችን ወላዲተ አምላክ ድንግል ማርያም አባ ኃይለ ጊዮርጊስ እጅግ አብዝታ ስለምትወዳቸው ኩክ የለሽ ማርያም ገዳምን እንዲመሰረቱ አድርጋቸዋለች፡፡ በጸበሏ በእምነቷ ብዙ ተዓምራቶችን እያደረገች ትገኛለች፡፡

3. የቅድስት ሥላሴ ፍልፍል ዋሻ፡- በ1984 ዓ.ም ጀምረው ከኩክ የለሽ ማርያም ፍልፍል ዋሻ ጋር አብሮ በአንድ ዓመት ውስጥ ነው የተጠናቀቀው ድንቅ ተዓምር እየተደረገም ይገኛል፡፡

4. ምን ያምር ቅዱስ ገብርኤል፡- በ1986 ዓ.ም ጀምረው በአንድ ዓመት ጊዜ ውስጥ ነው ያጠናቀቁት፡፡ይህ ገዳም በቅዱስ ገብርኤል መሪነትና አጋዥነት በአባ ኃይለ ጊዮርጊስ ተፈለፈለ፡፡በዚህ ቤተመቅደስ ውስጥ ጸበል ፈልቆ ብዙ ተዓምራትን እያደረገ ይገኛል፡፡በአጠቃላይ በአራቱም ቤተመቅደስ በየእለቱ ማይጠንት ይታጠናል፡፡እንዲሁም በየወሩ ቅዳሴ ይቀደስባቸዋል፡፡ገዳሙ በ1972 ዓ.ም ተጀምሮ በ1986 ዓ.ም መጨረሻ ተጠናቆ በ1987 ዓ.ም በአባቶች ተባርኮ መለኮሳት በምነና ሕይወት ገብተዋል፡፡

እኚህ አባት ገዳሙን መስርተው ብዙ መንፈሳዊ አገልግሎት ካገለገሉ በኃላ በ1997 ዓ.ም መጋቢት 19 ቀን በዓለ እረፍታቸውን ካደረጉ በኃላ አጽማቸው በገዳሙ በጸሎት በአታቸው ውስጥ ይገኛል፡፡ይህ ገዳም ከ25 በላይ መለኮሳት የሚኖሩበት ሲሆን በሽመናና በልማት ስራ ከጸሎት ጎን ለጎን እየሰሩ ይገኛሉ፡፡ ይህን ታላቅ ገዳም የረገጠ ወንደ የ40 ቀን ህጻን ሴት የ80 ቀን ህጻን ይሆናል ተብሎ ቃል ኪዳ ተገብቶለታል እንዲሁም በቦታው የበረከት ሥራ የሰራ ጸሎት ያደረገ እስከ ሰባት ትውልድ ድረስ ምህረት እንደሚደረግለት ቃል ኪዳን ተገብቶለታል እርሶም በቦታው በመገኘት ለቦታው የተገባለትን ቃል ኪዳን ይሸምቱ እኔ ኃጢአተኛ ባሪያችሁ የዚህ ቃል ኪዳን ተካፋይ ሆንኩ ምዕመናንና ምዕመናትም የዚህ ቃል ኪዳን ተካፋይ ይሆን ዘንድ ብዕሬን አንስቼ አካፈልኳችሁ፡፡

ወስብሐት ለእግዚአብሐር
ምንጭ፡-ገዳሙ ያሳተመው ብሮሸር
ለበለጠ መረጃ ፡- የቅዱስ እግዚአብሔር ማህበር 0911 133944 ፤ 0922 461145
አድራሻ፡- ደብረ ብርሃን በስተሰሜን ምስራቅ በኩል 5 ኪሎ ሜትር ርቀት ላይ ትገኛለች