Wednesday, June 8, 2016

ተአምራት በሸንኮራ ደብረ መንክራት ቅዱስ ዮሐንስ

ሸንኮራ ዮሐንስ ከአየር ላይ ሲታይ የገደሉ መሐል ጸበሉ ያለበት ነው ያች 8የማይበልጡ የጭራሮ ጎጆ የነበረች መንደር ዛሬ የፈውስ መዲና ሆና ዘምናለች 20 ሰው የምትይዘው ቤተክርስቲያን ዛሬ ታላቅ ህንጻ ተገንብቶባታል የነፍስም የስጋም ሆስፒታል ሆናለች አጥቢያዋ



















አቶ በላይ ደምሴ የተባሉ አባት ከባሌ ክፍለሐገር
ሁለቱም ጆሮዋቸው መስማት አይችልም ነበር አባታችን የመጥምቁን የፈውስ ዝና ቢሰሙም ወደ ሸንኮራ ለመምጣት አቅም ያጣሉ አንድ በአካባቢያቸው የሚያውቁትን ወጣት ጸበል አምጣልኝ ብለው 500 ብር ለትራንስፓርት ሰጥተው ይሸኙታል ልጁ እዛው ሲያውደለድል ተደብቆ ከርሞ ከወንዝ ውሐ ቀድቶ ይሰጣቸዋል አቶ በላይም የተሰጣቸውን ውሐ በእምነት ሲጠጡት ጆሮዋው ተከፈተ ድንቅ ነው በዚያው ቅጽበት የወጣቱ ሁለቱም ጆሮ መስማት አቆመ ይህ ወጣት ጥፋቱን ያውቃልና በንስሐ አባቱ አማካኝነት ወደ ሸንኮራ መጥቶ ለነፍስም ለስጋው ንስሐ ገብቶ ቀኖና ተቀብሎ ይፍታህ በሚባልበት 14ኛ ቀኑ ላይ ጆሮው ተከፍቶ በአንደበቱ የሰራውን ጥፋትና የተደረገውን ድንቅ ተአምር መስክሮዋል ይህን ያደረገ የመጥምቁ አምላክ ክብር ይግባው አሜን

ወ/ሮ ሐዱሽ ገ/ዋህድ ይባላሉ ከገጠሪቱ ኢትዮጵያ 16 አመት የታወረ አይናቸውን ለመታከም ነው ወደ መሐል ሐገር የመጡት አዲስ አበባ ኦፕራሲዮን ቢያደርጉም ተስፋ የለውም እንዲሁ ይኑሩ ይባላሉ ቤተክርስቲያን ለመሳለም ሄደው የሸንኮራን ታሪክ ሰዎች ሲያወሩ ሰምተው አድራሻ ጠይቀው መሪ አስታማሚ ይዘው ጉዞ ወደመጥምቁ ቤት ተከራይተው ጸበሉን መጠመቅ ይጀምራሉ 8ኛ ቀን ላይ ወደ ጸበሉ መውረጃ ገደሉን መንገድ ከመሪያቸው ጋር ይጀምራሉ መሪያቸው ድንገት ወደ ጫካ ለሽንት ትገባለች እሳቸውም ከምቆም ብለው መንገድ ይጀመራሉ በምርኩዛቸው ድንገት ያላሰቡት ነገር ተከሰተ የለበሱትን ነጠላ ቆንጥር ያዘብኝ መንገዱም ቁልቁለት ላይ ነበርና የያዝኩትምርኩዜም ከእጄ አምልጦ ተንሸራቶ ርቆ ወደቀ በቆምኩበት ደነገጥኩኝ ተማረርኩኝ ሞቴን ተመኘው አዘንኩኝ ምነው ዮሐንስ ብዬ ነጣላዬን ከእሾኩ ለማላቀቅ ፊቴን ሳዞር የጠፋው አይኔ ቦግ አለ ማመን አልቻልኩም እየተመራው የወረድኩትን ገደል ህዝቡን እየመራው በእልልታ በሆታ ወጣውት ብለው መስክረዋል እኝህ እናት በወቅቱ ከደስታቸው ብዛት ግቢው ውስጥ ይንከባለሉ ነበር ይህን ያደረገ የመጥምቁ አምላክ ክብር ይግባው አሜን

ሸንኮራን የሚያውቅ ሁሉ ምንትዬ ዮሐንስ ምን እንዳደረገላት የማያውቅ የለም በስምዕ ጽድቅ ጋዜጣ በዜና ቤተክርስቲያን በደብሩ መጽሔት ታሪክዋ በሰፊው ተመዝግቦዋል ስቃየ ብዙዋ እህታችን አዲስ አበባ ጎፋ መካነ ህያዋን ቅዱስ ገብርኤል ሰንበት ተማሪ የሆነችው ምንትዬ ታሪክዋ ሰፊ ስቃይዋ ዘግናኝ ነበር አትተኛም አትቀመጥም አትራመድም የዮሐንስ ያለህ ያዮ ይመስክሩ በልብ በኩላሊት በደም ብዛት እረ የበሽታዋ አይነት ብዛቱ መለኮትን ባጠመቀበት እጁ ዮሐንስ የታሰረችበትን ደዌ ሁሉ ፈታት ከሰውነትዋ የሚወደው ደምና መግል ተወግዶ ሞትሽን ጠብቂ በሳጥር ተቁዋጥረሽ ልትጣይ ነው የተባለችው ምንትዬ ይህው ዛሬ በእግርዋ ቆማ የመጥምቁን ደጅ ጥዬ አልሄድም ብላ እንግዳ ተቀባሪ ጸበልተኛ አጉራሽ ሆናለች እስቲ ሰኔ 30 ኑና የመጥምቁን ታሪክ ጽናት ትእግስትዋን ተማሩ ህወታችሁን አለምልሙ የምስጋናን ህይወት እንድትጀምሩ የቀጠሮ ሰው ይበለን አሜን

እናታችን ከባሌ ነው የመጡት ያወኩዋቸው ጫካ ጸበል ለመጠጣት ወጥቼ ነው ወይዘሮ ደሜ ይባልሉ ከንፈራቸው ላይ በወጣ ቁስል ምክንያት መላ ፊታቸው ይቆስልና ሽታም ያመጣል በሐኪም ብዙ አቅሜን ጨረስኩኝ ጠንቁዋይም ገንዘቤን ጨረሰብኝ የሸንኮራ ዮሐንስን ድንቅ ተአምር ሰማው ተነስቼ መጣው ጠረኔ ከሰው ስለማያቀላቅልና የቆሰለው ፊቴንም ደፍሮ የሚያይ ስለሌለ ጫካ እውላለው ጸበልም ሰው ሳይኖር እወርዳለው አሉኝ በእውነት ዘግናኝ አጋጣሚ ነበር 8አመታት የተሰቃዮበት ያ የቆሰለው ፊት እንደ ሰንኮፍ ውልቅ ብሎኝ በቁስል የነፈረው ከንፈራቸው ደርቆ ጠረን መአዛቸው ተለውጦ በዛ ህመምተኛ በነበረ አንደበታቸው እልልታን ብቻ ሳይሆን ንስሐ ገብተው ስጋ ወደሙም ተቀብለው ብጽአታቸውን በእጃቸው የፈተሉትን ግምጃ ስእሉን ሲጋርዱ አይቻለው እኝህ ምስኪን እናት ሸንኮራ ለጥቂት ሳምንታት ተቀምጠው ነው ፈውስን ያገኙ ዛሬ በየአመቱ ሰኔ 30 ከደጁ አይቀሩም የኛንም ክፉ መአዛ አምላከ ዮሐንስ ያጣፍጥልን አሜን

በሸንኮራው ዮሐንስ ጸበል ከጡት ካንሰር የዳነችው
የአጥቢያችን ብስራተ ገብርኤል ነዋሪ ሳባ ሐብቶም እህቴም እናቴም የሆነችው ሳባ ወደ ሸንኮራ ከመሄድዋ በፊት በጽኑ ስቃይ በካንሰር በሽታ ትሰቃይ ነበር በወቅቱ የነበራት ስቃይ ከቃላት በላይ ነበር አቅሙም ነበራትና ያልደረስችበት ህክምና የለም በተለይ የግል ሐኪምዋ ፕሮፌሰር ታዬ እንዲሁም በጥቁር አንበሳ ብሩክ ክሊኒክ ህክምናዋን ብትከታተልም ካንሰሩ ወደ መላ አካላትዋ ተሰራጭቶ ሞትዋን ስትጠብቅ ወደ ምንጃር ሸንኮራ ጸበል በመምጣት ሸንኮራ በወቅቱ ጥቂት ጎጆዎች ብቻ የነበረባት ትንሽ መንደር ነበረች ከሞላ ቤትዋ ወጥታ የጭራሮ ጎጆ ተከራይታ ጸበልዋን ጀመረች ጽናትዋ ትእግስትዋ ይደንቅ ነበር ቅዱስ ዮሐንስ ደጅ ጥናትዋን ስቃይዋን ተመልክቶ ከአምላኩ አማልዶ በህልም በራእይ ሳይሆን በገሐድ በመገለጥ እንደዳበሳትና 4አመት በዘግናኝ ሁኔታ ያበጠው ሰውነዋ ፈንድቶ ብዙ ደምና መግል ከሰውነትዋ ወጥቶ ፈውስን ተቀዳጅታለች አዲስ አበባ መጥታ ተመርምራ ሙሉ ጤናማ መሆንዋን አረጋግጣለች ይህው 17 አመት ሆናት የቀብር ማስፈጸሚያ በርበሬ የተፈጨላት ጤፍ የተሸመተላት የንፍሮ እህል የተለቀመላት መግነዝ ጨርቅዋን ከቤት ብሞትም ብላ ይዛ የወጣችው ሳባ መጥምቁ ዳብሶ ፈውስን አግኝታ ለእንባ አድርቅ የታሰበው እህል ለዝክር ሆነንዋል ሳባቆማ ትሆዳለች በእለተ ፋሲካ በየአመቱ ቤትዋን በአወደ አመት ዘግታ የአክፋይዋን በመጥምቁ ደጅ ላሉ ካህናት ጸበልተኞች ነዳያን ይዛ ጾም ታስፈታለች መጥምቀ መለኮት ነብየ ልኡል እኛ ከማናውቀው የታሰርንበት ክፉ ነገር ይፍታን አሜን

ነቢየ ልኡል ሐዋርያው ሰማእቱ መጥምቀ መለኮት ድንግላዊው ባህታዊው ካህኑ ከሴት ከተወለደ የሚተካከለው የሌለ ቅዱስ ዮሐንስ በልደቱ የአባቱን የታሰረ አንደበት የፈታ የስሙ ትርጉዋሜ የሁሉ ደስታ የሆነ ዛሬም በደዌ የታሰረውን በጸበሉ የሚፈታ ቃልኪዳኑ ዛሬም ያልተሻረ በመጥምቁ ደጃፍ ያገናኘን በፎቶ የምናየው ወንድም በሸንኮራ ጸበል የተፈወሰ ነው
የቀጠሮ ሰው ይበለን አሜን



ፀበሉ ፈዋሽ ዘብር ቅድስ ገብርኤል


 ምንጭ

Wednesday, June 1, 2016

መጻሕፍቶቻችን ስለ ቅ/ያሬድ ምን ይላሉ?

መጻሕፍቶቻችን ስለ ቅ/ያሬድ ምን ይላሉ?
ኢትዮጵያ ተለይታ ከምትታወቅባቸው እና ቤተ ክርስቲያናችንም ለሀገሪቱ ካበረከተቻቸው ብዙ ነገሮች አንዱ ያሬዳዊ ዜማ ነው። የዚህ ልዩ ሀብት ጀማሪ የሆነው ግንቦት ፲፩ ቀን ክብረ በዓል የሚደረግለት ቅ/ያሬድ ኢትዮጵያዊ ቅዱስ፣ ካህን፣ ሊቅ፣ መዓርዒረ ዜማ፣ ደራሲ (የዜማ እና የመጻሕፍት)፣ የመጻሕፍት መምህር
፣ ባለቅኔ (በድጓው ውስጥ ያሉ ቅኔዎችን መዘርዘር ይቻላል)፣ ሰማዕት (ያሬድ ማኅሌተ እግዚአብሔርን ሲያደርስ ንጉሡ ገብረ መስቀል ተመስጦ እግሩን ስለወጋው ደሙን አፍስሷልና) ወዘተ. የሚሉት ስለ ክብሩ የሚቀጸሉ መጠሪያዎቹ ናቸው።
ቅ/ያሬድ ሲነሳ ሁሌም ቀድሞ በአእምሯችን የሚመጣው በኢትዮጵያ ውስጥ ዜማን የጀመረ መሆኑና ግእዝ፣ ዕዝል፣ አራራይ ብሎ በሦስት መደብ መክፈሉ ነው። ዜማው ከዛሬ 1500 ዓመታት በፊት ተጀምሮ እስከ ዛሬ ድረስ የማይሰለችና ልዩ መንፈሳዊ ሐሴትን የሚያጎናጽፍ ሰለሆነ በእርሱ ዜማ የመመሠገነው ልዑል አምላክ፣ አመሥጋኞቹ ካህናትንም ምድራውያን መላእክት የሚያሰኝ ነው። ቅ/ያሬድ ከመነሳቱ በፊት በኢትዮጵያ ውስጥ እንደ ውርድ ንባብ ያለ ትሑት ቃል እንጂ ምልክት ያለው በዜማ የሚደርስ ማሕሌት አልነበረም። ስለዚህ ዜማ ሲነሳ ያሬድ መጠራቱ አይቀሬ መሆኑን ሁሉም የሚስማማበት ነው። ሌላው የቅ/ያሬድ አስተዋጽኦ እና በብዙዎች ዘንድ የማይታወቀው ሥራው በኢትዮጵያ ውስጥ የመጀመሪያው ደራሲ እሱ መሆኑ ነው። እስካሁን በተደረገው ጥናት የኢትዮጵያ ጽሑፎች እስከ ያሬድ መነሳት ድረስ ትርጉሞች (በተለይ ከግሪክ ቋንቋ) ነበሩ። ብሔራዊ ድርሰትን (ሀገር በቀል) በኢትዮጵያ የጀመረ ያሬድ ነው። ለዛሬ የማቀርበው ጽሑፍ ቅ/ያሬድ የደረሳቸውን መጻሕፍትና የኋላ ሊቃውንት ስለ እርሱ ክብር የጻፉትን በመጠኑ ይመለከታል። (ስለ ሕይወት ታሪኩ በብዙ ቦታ ስለተጻፈ ብዙም አልዳስሰውም።)
በሀገራችን ከሚገኙት መጻሕፍት ስለ ቅዱስ ያሬድ የሚናገሩ መጻሕፍት በርካታ ናቸው፤ በጥቅሉ በሦስት ዋና ዋና ክፍሎች እንመድባቸዋለን። የመጀመሪያዎቹ ራሱ ቅ/ያሬድ የጻፋቸው የዜማ መጻሕፍት ሲሆኑ፤ ሁለተኛዎቹ ስለ ቅ/ያሬድ ክብር የተደረሱ የምሥጋና ድርሰቶች፤ ሦስተኞቹ የቅ/ያሬድን ታሪክ የያዙ ሌሎች መጻሕፍት ናቸው። ዝርዝራቸውን ቀጥሎ እንመልከት።

ሀ) እርሱ የጻፋቸው፤
ከላይ በመግቢያው እንዳልነው ቅ/ያሬድ የምሥጋና እና የአምልኮ መግለጫ የሆኑ የዜማ መጻሕፍትን በግዕዝ ቋንቋ ጽፏል። እነዚህም በስፋት የሚታወቁት አምስቱ የዜማ መጻሕፍቱና በታሪክና በትውፊት የተቀበልናቸው ሌሎች መጻሕፍት ናቸው። እነርሱም፥
1) ድጓ - ከቅ/ያሬድ ድርሰቶች ውስጥ ትልቁ የዜማ መጽሐፍ ድጓ ሲሆን በሦስት ዋና ዋና ክፍሎች የተከፈለና በቤ/ክ ከዓመት እስከ ዓመት የሚደርስ ምስጋና ነው። በተለያዩ ዘመናት የተገለበጡ የድጓ ቅጂዎች በኢትዮጵያ የሚገኙ ሲሆን አንዳንድ ጠቃሚ እና ትክ የማይገኝላቸው ቅጂዎች ከባሕር ማዶ ተሻግረው ይገኛሉ (ለምሳሌ ቫቲካን [Vat. Aeth. 28]፣ በርሊን [Orient. 1000])። በሀገራችን ከሚገኙት ዕድሜ-ጠገብ ድጓዎች መካከል በላሊበላ ቤተ-ጊዮርጊስ የሚገኘው (12ኛ መ/ክ/ዘ)፣ በጣና ቂርቆስ የሚገኘው (13 መ/ክ/ዘ)፣ በደብረ ብርሃን የሚገኘው (16ኛመ/ክ/ዘ)፣ የሐይቁ ድጓ (17መ/ክ/ዘ)) ይጠቀሳሉ። “መጽሔተ፡ ጥበብ” በመባል የሚታወቀው የቅ/ቤተልሔም (ደ/ጎንደር) ድጓ ለምስክር አብነት ነው።
2) ጾመ ድጓ - በዐቢይ ጾም የሚደርስ ምሥጋና ነው። ጾመ ድጓ በዋናው ድጓ (ከአስተምህሮ ድጓ) ክፍል ተካቶ ይገኛል። ክፍሉ በዓቢይ ጾም ውስጥ ባሉት ሰንበታት ልክ ሲሆን ተራቸውም፤ ዘወረደ፣ ቅድስት፣ ምኵራብ፣ መጻጕዕ፣ ደብረ፡ ዘይት፣ ገብር፡ ሔር፣ ኒቆዲሞስ እና ሆሣዕና የሚል ነው።
3) ምዕራፍ - ይህ የዜማ መጽሐፍ ከመዝሙረ ዳዊት የተውጣጡት ምሥጋናዎችን በመስመር በመስመር እየከፈለ የሚደርስ የስብሐተ እግዚአብሔር መጽሐፍ ነው።
4) ዝማሬ - ማሕሌት ሲቆም የሚደርስ ሆኖ በጊዜ ቅዳሴ ከድርገት በኋላ የሚቀርብ ምሥጋና ነው። ዝማሬ አምስት ክፍሎች ያሉት ሲሆን እነዚህም ኅብስት፣ ጽዋ፣ መንፈስ፣ አኮቴት እና ምስጢር የሚባሉት ናቸው። የዚህ የዝማሬና የመዋሥዕት ማስመስከሪያ ቤተ ጉባኤው ቅ/ያሬድ ባስተማረበት ቦታ በዙርአባ አረጋዊ ቤ/ክ (ደቡብ ጎንደር) ነው።
5) መዋሥዕት - ካህናት በተዋሥኦ (በመቀባበል) የሚያዜሙት ሲሆን በተለይ በጸሎተ ፍትሐት ጊዜ እና በቀዳም ሥዑር ዕለት የሚደርስ ምሥጋና ነው።
6) አንቀጸ ብርሃን - ቅ/ያሬድ ይህን የእመቤታችንን ምሥጋና ያደረሰው በአክሱም ጽዮን ቤ/ክ ውስጥ ከታቦተ ጽዮን ፊት ቆሞ ሲሆን ድርሳኑ ይህንን እንዲህ ይገልጻል “ወሶቤሃ፡ ቦአ፡ ያሬድ፡ ውስተ፡ ታቦተ፡ ሕጉ፡ ለእግዚአብሔር፡ እንተ፡ ይእቲ፡ ገበዘ፡ አክሱም፡ ወአንበረ፡ ፪እደዊሁ፡ ውስተ፡ ርእሰ፡ ታቦት፡ ወከልሐ፡ በልዑል፡ ቃል፡ እንዘ፡ ይብል፡ ቅድስት፡ ወብፅዕት፡ ስብሕት፡ ወቡርክት፡ ክብርት፡ ወልዕልት፡ አንቀጸ፡ ብርሃን፡ መዓርገ፡ ሕይወት፡ እስከ፡ ተፍጻሜቱ። ..... ።” ገድሉ እና ተአምሩ (ሦስተኛው) እመቤታችንን እየለመነ አንቀጸ ብርሃንን በዕዝል ዜማ ሲያደርስ ቁመቱ አንድ ክንድ ያህል (“ተለዓለ፡ መጠነ፡ እመት፡”) ከምድር ወደ ላይ ከፍ ይል እንደነበር መዝግበውታል። ለዚህ ጸሎት ምላሽ እመቤታችንም ተገልጻ በቃል ታናግረው ነበር።
7) የሦስት ቅዱሳንን ገድል ጽፏል፤ በትውፊት እንደሚታወቀው ቅ/ያሬድ ከዘጠኙ ቅዱሳን መካከል የሦስቱን ቅዱሳን ገድል ጽፏል። እነዚህም ገድለ አረጋዊ፣ ገድለ ጽሕማ እና ገድለ ይምአታ ናቸው።
8) ቅዳሴ - የታተሙት ቅዳሴያት 14 በብዛት ይታወቃሉ፤ ነገር ግን ያልታተሙ ሌሎች ስድስት ቅዳሴያትም አሉ፤ የቅ/ያሬድ ቅዳሴም ካልታተሙት አንዱ ነው።

ለ) ስለ ቅ/ያሬድ ክብር የተጻፉ
ከኢትዮጵያ ቅዱሳን ሊቃውንት ግንባር ቀደም የሆነው ማሕሌታይ ያሬድ በዜማ ደራሲነቱ በዓለም ደረጃ የሚታወቅ ሲሆን ካበረከተው ዘመን ተሻጋሪ ሥራ አኳያ ስናየው ግን ስለ እርሱ ክብር የተጻፈው አነስተኛ ነው። ድርሳን እና ገድል ተጽፎለታል ሆኖም በጣም አጫጭር ናቸው። እስካሁን ከተገኙት ውስጥ ዕድሜ ጠገብ የሆነው በሐይቅ ገዳም (ደቡብ ወሎ) ከሚገኘው “ገድለ ቅዱሳን” ውስጥ የሚገኘው “ድርሳን ወገድል ዘቅ/ያሬድ” ሲሆን የተጻፈበት (የተቀዳበት) ዘመኑም በ16ኛው መ/ክ/ዘ ነው። በሁለተኛ ደረጃ ጥንታዊ የሚባለው የቅ/ያሬድ ድርሳን እና ገድል በ17ኛው መ/ክ/ዘ/ የተጻፈው እና በሀገረ እንግሊዝ የሚገኘው ሲሆን፤ ሦስተኛው ደግሞ በዘመዶ ማርያም (ሰሜን ወሎ) የሚገኘው ሲሆን ዘመኑም በ18ኛው መ/ክ/ዘ ነው። በ19ኛው እና በ20ኛው መ/ክ/ዘ ሌሎች በርካታ ቅጂዎች በብዙ ቦታዎች ይገኛሉ። በውጭ ሀገር ከሚገኙት ቅጂዎች ውስጥ በፓሪስ ቤ/መጻሕፍት የሚገኘውን ገድል ኮንቲ ሮሲኒ የሚባል ምሁር ከግዕዝ ወደ ላቲን ተርጉሞ እ.ኤ.አ. በ1904 አሳትሞታል። ድርሳን፣ገድል፣ ተአምር እንዲሁም መልክአ ያሬድን ይዟል። ቀጥለን በዝርዝር እንመልከታቸው፤ 


1) ድርሳነ ያሬድ - ለቅዱስ ያሬድ ታሪክ ዋና ምንጭ ሆኖ የሚጠቀሰውና ከገድሉ ይልቅ ስፋት ያለው ድርሳኑ ነው። ሲጀምር እንዲህ ይላል፥ “በስመ፡ አብ፡ ወወልድ፡ ወመንፈስ፡ ቅዱስ፡ ፩አምላክ። ድርሳን፡ ዘቅዱስ፡ ያሬድ፡ ካህን፡ ቀርነ፡ ቤተ፡ ክርስቲያን፡ ዘይጼውዖሙ፡ ለመሃይምናን፡ ከመ፡ ይሴብሕዎ፡ ለእግዚአብሔር፡ በክላሕ፡ ወበዓቢይ፡ ቃል፡ ከመ፡ ሱራፌል። ....”

2) ገድለ ያሬድ - የቅ/ያሬድን የሕይወት ታሪኩንና ተጋድሎውን ዜና በአጭሩ የሚዘክር ሲሆን ሲጀምር እንዲህ ይላል፥ “በስመ፡ አብ፡ ወወልድ፡ ወመንፈስ፡ ቅዱስ፡ ፩አምላክ። ገድል፡ ወስምዕ፡ ዘቅዱስ፡ ወንጹሕ፡ ወብፁዕ፡ ወኅሩይ፡ ያሬድ፡ ካህን፡ ጸሎቱ፡ ወበረከቱ፡ ወሀብተ፡ ረድኤቱ፡ የሀሉ፡ ምስሌነ፡ ....” 

3) ተአምረ ያሬድ - ካህኑ ያሬድ የፈጸማቸው ገቢረ ተአምራት በርካታ ቢሆኑም በገድሉ ላይ ተመዝግበው የምናገኛው ግን ሦስት ናቸው። 

4) መልክአ ያሬድ - የኋላ ሊቃውንት ስለ ቅ/ያሬድ ክብር እንዲሆን “መልክእ” ደርሰውለታል። ሲጀምር እንዲህ ይላል፥ “በስመ፡ እግዚአብሔር፡ ሥሉስ፡ ዘበሰማያት፡ አቡነ። በምግባር፡ ወግዕዝ፡ ዘወለደነ። ያሬድ፡ ወጠንኩ፡ ለመልክእከ፡ ድርሳነ። አብርህ፡ ኅሊናየ፡ ወዘልብየ፡ ዓይነ። ወበልሳንየ፡ ጸሐፍ፡ ሐዲሰ፡ ልሳነ።” ... ይህ መልክእ በብዙ ቦታ የሚገኝ ሲሆን እኔ ማስተያየት የቻልኩት ፓሪስ ከሚገኘው እና ኮንቲ ሮሲኒ (1904) ካሳተመው ነው። 

5) የግንቦት ፲፩ ስንክሳር ንባብ - የግዕዙ ስንክሳር (እንዲሁም የባጅ - እንግሊዝኛ ትርጉም 1928፣ የኮሊ - የፈረንሳይኛ ትርጉም 1997፣ የትንሣኤ ማሳተሚያ ድርጅት ሕትመት - የአማርኛ ትርጉም 1993 ዓ.ም.) ስለ ቅ/ያሬድ ሕይወት ይዘረዝራል። ሲጀምር እንዲህ ይላል፤ “ወበዛቲ፡ ዕለት ካዕበ፡ አዕረፈ፡ ያሬድ፡ ማኅሌታይ፡ አምሳሊሆሙ፡ ለሱራፌል። ወዝንቱ፡ ቅዱስ፡ እምአዝማዲሁ፡ ለአባ፡ ጌዴዎን፡ ውእቱ፡ እምካህናተ፡ አክሱም፡ ....” 

6) ነግሥ ዘያሬድ - ለቅ/ያሬድ ካተደረሱት የ“ነግሥ” ምሥጋናዎች መካከል አንዱ አባ ጊዮርጊስ ዘጋሥጫ የደረሰው ብሎ ይጀምራል፥ “ያሬድ፡ ቀሲስ፡ መዓርዒረ፡ ዜማ፡ ማኅሌታይ። መዓንዝር፡ ከመ፡ ወልደ፡ ዕሴይ። .....” ሁለተኛው ደግሞ አፄ ዘርአ ያዕቆብ የደረሰው ምሥጋና ሲሆን እንዲህ ይላል “ሰላም፡ እብል፡ ለያሬድ፡ ቀሲስ፡ ምሉዐ፡ መንፈስ፡ ለኢትዮጵያ፡ ነደቀ፡ በሃሌ፡ ሉያ፡ ምድራስ። አስተባልሐ፡ ደቂቃ፡ በዜማ፡ ሠላስ። መኃልይሁ፡ ውዱስ። በስብሐት፡ ሐዲስ።”

7) አርኬ - ፓሪስ የሚገኘው (ኮንቲ ሮሲኒ ያሳተመው) እና በትንሣኤ ማሳተሚያ የታተመው የስንክሳሩ አርኬ ስለ ቅ/ያሬድ ምሥጋናውን እንዲህ ብሎ ይጀምራል - “ሰላም፡ ለያሬድ፡ ስብሐተ፡ መላእክት፡ ለሕዋጼ። እንተ፡ አዕረገ፡ በልቡ፡ ሕሊና፡ መንፈስ፡ ረዋጼ።...”። በ17 መ/ክ/ዘ የተጻፈውና ለንደን (ብሪቲሽ ቤ/መ) የሚገኘው የስንክሳር አርኬ እንዲህ ይላል፤ “ሰላም፡ ለዝክረ፡ ስምከ፡ ዘተጸውዖቱ፡ መዓር።...”

ሐ) ስለ ቅ/ያሬድ የሚያስረዱ ሌሎች መጻሕፍት
1) ገድለ አረጋዊ - ከላይ እንዳየነው በትውፊት የገድለ አቡነ ጸሐፊ ቅ/ያሬድ እንደሆነ ይነገራል። የታተመው ገድለ አረጋዊ የጸሐፊነቱን ሚና ለሌላ ይሰጠዋል፤ ሁለቱን ሃሣቦች ስናገናዝባቸው ሊሆን የሚችለው መጀመሪያ ያሬድ ጽፎት በኋላ ሌሎች ገልብጠውታል ማለት ነው። ወደ ገድለ አረጋዊ ስንዘልቅ በርካታ ቦታዎች ላይ የቅዱስ ያሬድን ታሪክ መዝግቦት ይገኛል። ያሬድ በዘመነ ገብረ መስቀል ማሕሌቱን እንደጀመረ፣ ድርሰቱን ከብሉይ ከሐዲስ እንዳውጣጣው፣ ዜማውን ከመላእክት እንደሰማው፣ ወዘተ.... ይዘረዝራል። እንዲሁም ወደ ደብረ ዳሞ ወጥቶ ሕንጻ ቤ/ክ ሲመለከት “ወከልሐ፡ በቃለ፡ መዝሙር፡ ወይቤ፡ ይሔውጽዋ፡ መላእክት፡ እስመ፡ ማኅደረ፡ መለኮት፡ ይእቲ፡ ዖድክዋ፡ ዖድክዋ፡ ዖድክዋ፡ ወርኢኩ፡ ሥነ፡ ሕንጼሃ፡ ለቅድስት፡ ቤተ፡ ክርስቲያን።” ብሎ እንደዘመረ፡ ይናገራል።
2) ድርሳነ ዑራኤል - የቅ/ያሬድን ታሪክ ከያዙት የቤ/ክ መጻሕፍት መካከል አንዱ ድርሳነ ዑራኤል ሲሆን እመቤታችን ተገልጻ ቅ/ኤፍሬምንና አባ ሕርያቆስን “ዜማ እንዲደርስልኝ ውዳሴዬንና ቅዳሴዬን ለያሬድ ስጡት” ብላ እንዳዘዘቻቸውና ቅ/ያሬድም በተሰጠው ሀብተ ዜማ እንደዘመረ ይናገራል። ለቅ/ያሬድ ጽዋዓ ልቡና ያጠጣው መራሔ ብርሃናት ዑራኤል እንደሆነ ድርሳነ ዑራኤል ይገልጻል።
3) መጽሐፈ አክሱም - ይህ መጽሐፍ የአክሱም ጽዮንን ታሪክ እና የርስት ጉልቷን ሥሪት የሚናገር ሲሆን ስለ ቅ/ያሬድ ዜማ ድርሰት ይናገራል። እንዲሁም ከላይ በድርሳነ ዑራኤል የተገለጸውን ታሪክ (እመቤታችን ተገልጻ ቅ/ኤፍሬምንና አባ ሕርያቆስን “ዜማ እንዲደርስልኝ ውዳሴዬንና ቅዳሴዬን ለያሬድ ስጡት” ያለችውን) መዝግቧል።
4) ታሪከ ነገሥት - የኢትዮጵያን ታሪክ ከያዙት መጻሕፍት አንዱ የሆነው የዙርአባ (ዙራምባ) ታሪከ ነገሥት የቅ/ያሬድን ታሪክ የያዘ ሲሆን በተለይ በዑራኤል መሪነት ከአጼ ገ/መስቀልና አባ አረጋዊ ጋር ወደ ዙርአባ ተራራ እንደወጡ፣ በዙርአባ ለሦስት ዓመታት ቅ/ያሬድ ዝማሬና መዋሥዕትን እንዳስተማረ ይናገራል።

የቅዱስ ያሬድ በረከት ከሁላችን ላይ ይደርብን፤

ግንቦት ፳፻፰

Monday, May 30, 2016

ፖርት ሳይድ ማርያም ፡ ዘይት የምታፈልቀው ስእል

እህታችን ማሕሌት መኮንን  በግብጽ ፖርት ሳይድ ማርያም ተገኝታ ዘይት የምታፈልቀውን የእመቤታችንን ስእል ተኣምሩን በ ምስል ወድምጽ ታቀርብልናለች፥፥  ከዚህ በፊት ስለዚህ ተኣምር በሚከተሉት ፖስቶች ኣስነብበን ስለነበር በተያይዝነት ብታነቡት ሙሉ ተኣምሩን ትረዳላችሁ::


ከእጇ ዘይት የሚፈልቅ የቅድስት ኤልሳቤጥ አስገራሚ ታሪክ

ፖርት ሳይድ ማርያም በግብጽ

 

 

የእመቤታችንን ተአምር - ዲያቆን ሳሙኤል


የእመቤታችንን ተአምር ልንገራችሁ ማለትም ለእኔ ያደረገችልኝ ስሜ ዲያቆን ሳሙኤል ሀ'/ማርያም ይባላል የተወለድኩት በምስራቁ የሀገራችን ክፍል ሲሆን በዛ አካባቢ ኢ አማንያን ይበዛሉ ተወልጄ አንድ ዓመት ሲሞላኝ በፀና መታመሜን እና እናቴ ለድንግል ማርያም ተስላ እንደተረፍኩኝ ትነግረኛለች ከዛም 5 ዓመት እንደሞላኝ እናቴ ስዕለቷ ለቤተክርስቲያን ብፅዓት አድርጋ መስጠት ስለነበረ ወደ ታላቁ ገዳም አሰቦት ደብረ ወገግ ገዳም ወስዳ ለአበ ምኔቱ አስረከበችኝ ልብ በሉ ይህ ገዳም ወንዶች ብቻ የሚኖሩበት ገዳም ነው እኔም ገና ብላቴና ሳለሁ ከአባቶች ጋር ተቀላቀልኩኝ በመቀጠልም ካለ ወጥ የሚበላውን የቃል ኪዳን ዳቤ እየበላሁ የቆሎ ትምህርቴን ጀመርኩኝ ህፃን ስለነበርኩኝ አዕምሮዬ ያስተማሩኝል ሁሉ ይቀበል ነበር በእንደዚህ ያለ ህይወት እየኖርኩኝ የግብረ ዲቁና ትምህርቴን አጠናቀቁኝ ከዛም ማዕረገ ዲቁና ተቀበልኩኝ አሁን ላይ ልብ በሉ ገዳሙ የዓንድነት ገዳም ስለሆነ የቀንድ ከብቶች እና የጋማ ከብቶች አሉት ስለዚህም ባህታውያን መናኞች እንዚህን ከብቶች በየተራ ወደ ጫካ በማሰማራት ይጠብቃሉ በተጨማሪም ለተላላኪነት ሁለት ሁለት ህፃን ይመደብላቸዋል በእንደዚህ ዓይነት ሁኔታ እኔም በ1991 ዓ.ም ምደባው ደረሰኝ ግንቦት 21 የመቤታችን ዕለት ማለትም 20 ለ21 አጥቢያ ህልም አየሁ አስደንጋጭ ህልም በወቅቱ ያሳድጉኝ የነበሩ አባት ባህታዊ ኀይለ ሚካኤል ስነግራቸው ገባድ ነገር ይገጥማሀል ግን ምን አትሆንም አሉኝ እሺ አባቴ ፀልዩልኝ ብዬ አብረን ከተመደብነው ልጅ ጋር ወደ ጫካ ሄድን የሄድንበት ጫካ በአካባቢው ስም ሶራ ይባላል ብዙ ኢ አማንያን ዘላኖች ያሉበት ቦታ ነው ከዛም ልክ ከኑ 6 ሰዓት ግንቦት 21 1991 ዓ.ም አስደንጋጭ ነገር ተከሰተ ሽፍቶች ማለትም በአጋባቢው አጠራር ኢሳዎች ያዙን እጃችንን የፍጥኝ አሰሩን ልብ በሉ እኛ ገና ያልጠነከርን ጨቅላዎች ነበርን ኡኡኡ ብለን ጮህን ከተራራው ድምፅ በስተቀር የደረሰልን የለም ሊያርዱን ቢላዋ ከሰገባቸው መዘዙ ጭንቀት ተፈጠረ አስተውሉ የሞት አፋፍ ላይ ነው ይህ በእንዲህ እዳለ በደመነፍስ እየታገልኩኝ ወደ ሰማይ ቀና አልኩኝ አንድ ነገር በአፌ ወጣ በታፈነ ድምፅ የአምላኬ እናት የጭንቅ አማላጇ ማርያም ሆይ እባክሽ ከልጅሽ ጋር ድረሽልኝ ከዚህ ጭንቅ ካወጣሽኝ በእራሴ እጅ የተሰራ ሰሌን (ማለትም የዘንባባ ሥሪት ምንጣፍ) ለቤተክርስቲያንሽ አስገባለሁ ብዬ ድምፄን ከፍ አድርጌ ጮኩኝ እመቤቴ በፍጥነት ደረሰችልኝ ሊያርደኝ የሚታገለኝ ሰው ከመቅፅበት ለቀቀኝ እኔም እሮጨ ነጭሎ የሚባል ዛፍ ስር ተደበኩኝ እመቤቴ በውስጤ ገባች አንዱ ጓደኛዬም እንዲሁ ተሳለ ደረሰችለት እነኛ አራጆች የእኛን ፊት ማየት አቅቷቸው ከብቶቹን በመያዝ ወደ ገላግሌ የሚባል አካባቢ ሮጡ እኔም በእመቤቴ ምልጃ ከሞት ተርፌ ወደ ገዳሙ እሮጥኩኝ የአደጋ ደወልም ደወልኩኝ ሁሉም መናንያን ምንድነው ብለው ተሰበሰቡ የሆነውን ነገርኳቸው ሁሉም በህብረት እንባቸውን አውጥተው አለቀሱ ከሞት የአተረፈኝን የድንግል ማርያምን ልጅ አመሰገኑ ከዛ ከብቶችን የዘረፉት ሰዎች ሲካፈሉ እርስ በእርስ ተገዳደሉ የአካባቢው ሽፍቶችም ወተቱን ሲጠጡ በተቅማጥ መሞት ጀመሩ የሚያደርጉት ሲጠፋቸው ገዳሙ ይቅርታ ያድርግልን ብለው ከብቶቹን መለሱ እናም ዛሬ ላይ ዓለም የእመቤታችንን ምልጃ ይሰማ ዘንድ ውስጤ አስገደደኝ ይህ ታሪክ ህያው እግዚአብሔር ያውቃል እሙን ነው ሼር በማድረግ ለዓለም እናድርስ የገዳሙ ታሪክ በዘሁ አምድ ይቀጥላል ለእኔ የደረሰች ድንግል ማርያም የአምላክ እናት ለእናንተም ትድረስላችሁ
አሜን
አሜን
አሜን
ያነበበው ሁሉ ሼር እንዲያደርግ በድንግል ማርያም ስም እጠይቃለሁ
ለበለጠ መረጃ 0911072282 ዲያቆን ሳሙኤል

ድንቃ ድንቅ ተኣምራት በቅዱሳን ገዳማት

Wednesday, May 18, 2016

ተዐምረኛው ጅሩ ሥላሤ ገዳም

ይህ የምታዩት ጅሩ ሥላሤ ገዳም ይባላል አሣሮ ወረዳ ወቅሎ ጊዮርጊሥ ቤ/ክ ጅሩ አርሤማ መንገድ ላይ ይገኛል:: ገዳሙ በብዙ ህዝበ ክርሥቲያን ያልታወቀ እና ያልተጎበኘ ነው:: ብዙ በረከት እና ተአምራት ያለበት ገዳም ሢሆን የጉዞ ማህበራት ወደዚ ገዳም ጉዞ በማዘጋጀት ምዕመናኑን የበረከቱ ተካፋይ እንድታረጉ እና ገዳሙንም እንድትደግፉ ሥል በሥላሤ ሥም ጠይቃለው:: ወሥብሃት ለእግዚዐብሄር::



ድንቅ ተዓምር በ ለጀት ኪዳነምህረት

Tuesday, May 10, 2016

የጠቋር መንፈስ ጠባያትና አያያዝ .

የጠቋር መንፈስ ጠባያትና አያያዝ .
የጠቋር መንፈስ ከሌሎች ክፉ መንፈሶች ሁሉ እጅግ በጣም ለየት የሚያደርገው ስዎችን ከአቅም በላይ በሆነ መንገድና ሁኔታ ውሰጥ በእጅጉ የሚፈትን አሮጌውን በአዲስ ለመተካት የሚያስችል የተለያዩ የጥቃት ሥልቶች ያሉትና በአንድ ጊዜ በርካታ የጥቃት ግንባሮችን በሰው ህይወት ላይ መክፈት የቻለ ወይም የሚችል አደገኛ መንፈስ መሆኑ ነው ፡፡ በህብረተሰቡ ውስጥ መንፈሳዊ መልአክ ጠባቂና ጸሎተኞ የሚል ስያሜ ተሰጥቶት ይህንን ስም ተከትሎ የሚሄድ ማንኛውምንም ሌላ መንፈስ በመጫን ለራሱ የተሻለ ቦታ በመስጠት እልከኞ የመሆን ከፍተኛ አቅም ያለውና የመሪነት ስሜት የሚታይበት መንፈሰ ነው ፡፡
. .
መንፈሱ የህንን ሥያሜውን ያገኘው ለብዙ ዘመናት በኮከብ ቆጠራ ሲያሟርቱ በሚኖሩ ሰዎች አማካኝነት ነው ፡፡ የመጠሪያውንም ጠባይ ተከትሎ ጠቋር የሚለው ቃል አፍሪካዊ መንፈሰ መሆኑን ለማሳየት ነው ፡፡ በመሆኑም ሥያሜው ጂኦግራፊያዊ አቀማመጥና ይዘት ያለው ሆኖ የሚንቀሳቀስ መንፈስ ነው ፡፡
. .
ከዚህ በተጨማሪም ሥራው የጠቆረ ህይወት የጨለማ ኑሮን የሚገልጥ የሚያመለክትና የሚያጎናጽፍ ነው ፡፡ ግብር ስጦታውና ሽልማቱ ጥቁር ቀለም ያለበት እንስሳም ይሁን አልባሳት የፍላጎቱ መለያ ነው ፡፡ በአብዛኛው ለማለት ይቻላል ጥቁር ቀለም የጠቋር ዋነኞ መገለጫ ነው ፡፡
. .
ጠቋር በግራ እጁ ለሚሰራ ሰው ግራውን በቀኝ ለሚሰራውን ሰው ደግሞ ቀኙን ይይዛል ፡፡ ሰው እንደ ልቡ ተንቀሳቅሶ እንዳይሠራ ዋናውን ሀይሉን ክንዱንና ሕሊናውን በሥውር ይቋጣጠራል ፡፡ ሴቷ አጋንንት ሻንቂት ስትባል ወንዱ ደግሞ ጠቋር ሻንቆ ይባላል ፡፡ መንፈሱ ስያሜውን ያገኘው በአውደ ነገሥት ውስጥና ቀደም ሲል ሌዋውያን አይሁዶች ኢትዮጵያ በመጡበት ወቅት ሲሆን በዚሁ ጊዜም ሁለት ዓይነት ደብተራዎች አብረው መጥተው ነበር ፡፡
. .
የመጀመሪያዎቹ ታቦተ ጽዮንን የሚያገለግሉ የምሥጋናና የአምልኮት እግዚአብሔር ደብተራዎች (መንፈሰሳዊ ሊቃውንት) ሰሆኑ ሁለተኞቹ ደግሞ ምትሀታዊውን ትምህርት ከአረማውያን የተማሩ ሌዋያን ማለትም የእስራኤል ነገዶች ነበሩ ፡፡ ሁለቱም አገራችን ከገቡ ጊዜ ጀምሮ ሰፋ ያለ ቦታ ከማግኘታቸው ጋር ተያይዞ ሁለተኛው ወገን በቀጥታ የክፉው መንፈስ አካል ሆኖ በአውደ ነገሥቱ ምሪት ውስጥ ጠቋር የምለውን ስያሜ አገኘ ፡፡
. .
በመጽሐፍ ቅዱስ ውስጥ እንዲህ ዓይነቱ መንፈስ በገዢነት ላይ ሆኖ ከላይ እንደቆየ የሚያሳየን በዮሐንስ ወንጌል ፰ : ፴፱ ላይ የአብርሃም ዘር ነን የሚሉትን ተቆጣጥሮአቸው ነበር ጌታ ኢየሱስም ለመንፈሳዊ በረከት ተዘጋጁ ሲላቸው እኞ የቃል ኪዳን ተስፋና የአብርሃም ልጆች ነን ፡፡ እኞ ቀደም ሲል አምልኮት ራእይ ተስፋና የተሻለ እድል ከነበራቸው ዘሮች ውስጥ ነን እያሉ ይመጻደቁ ነበር ፡፡
. .
በቀደሙት አባቶች አምልኮት እየተኩራሩና እየተመኩ አስተሳሰባቸው ተግባራቸው ግን ተግባር የሌለው የወግ አምልኮትን መንገድን የተከተለ ነበር ፡፡ በቀደመው በአብርሀም ስም ሰማያዊ ተስፋን የሚያገኙ መሥሏቸው ኑሮአቸውን ግብዝነት በተመላ ፈሪሳውያንነት ይመሩ ነበር ፡፡
. .
በዮሐንስ ወንጌል ፰ : ፴፱
" መልሰውም። አባታችንስ አብርሃም ነው አሉት። ኢየሱስም። የአብሃም ልጆች ብትሆኑ የአብርሃምን ሥራ ባደረጋችሁ ነበር ፡፡ ነገር ግን አሁን ከእግዚእብሔር የሰማሁትን እውነት የነገርኋችሁን ሰው ልትገድሉኝ ትፈልጋላችሁ፤ አብርሃም እንዲህ አላደረገም። እናንተ የአባታችሁን ሥራ ታደርጋላችሁ አላቸው። እኛስ ከዝሙት አልተወለድንም አንድ አባት አለን እርሱም እግዚአብሔር ነው አሉት፡፡ ኢየሱስም አላቸው። እግዚአብሔርስ አባታችሁ ከሆነ በወደዳችሁኝ ነበር፤ እኔ ከእግዚአብሔር ወጥቼ መጥቻለሁና፤ እርሱ ላከኝ እንጂ ከራሴ አልመጣሁምና ። ንግግሬን የማታስተውሉ ስለ ምንድር ነው? ቃሌን ልትሰሙ ስለማትችሉ ነው።እናንተ ከአባታችሁ ከዲያብሎስ ናችሁ ፡፡" አላቸው ዲያብሎስ አባት ሊሆን የሚችልበት መንገድና አጋጣሚ በጣም ሰፊ ነው ፡፡ ከዚህ አንጻር ጠቋር የሚባለው መንፈስ ይህንኑ መንገድ ያጠናክራል ፡፡
. .
የፈሪሳውያን መንፈስና የጠቋር ሥልት በብዙ መንገድ ተመሳሳይነት ያለው ሲሆን የሁለቱም መግለጫ በማስመሰል ዘመንና ጌዜን ጨርሶ ከእግዚአብሔር ክብር መለየት ነው ፡፡ መጽሐፍ ቅዱስ ሲነግረን
. .
"ጻድቃን እንደ ሆኑ በራሳቸው ለሚታመኑና ለሎቹን ሁሉ በጣም ለሚንቁ ይህን ምሳሌ ነገራቸው፥ እንዲህ ሲል። ሁለት ሰዎች ሊጸልዩ ወደ መቅደስ ወጡ፥ አንዱ ፈሪሳዊ ሁለተኛውም ቀራጭ። ፈሪሳዊም ቆሞ በልቡ ይህን ሲጸልይ ። እግዚአብሔር ሆይ፥ እንደ ሌላ ሰው ሁሉ፥ ቀማኞችና ዓመፀኞች አመንዝሮችም፥ ወይም እንደዚህ ቀራጭ ስላልሆንሁ አመሰግንሃለሁ፤ በየሳምንቱ ሁለት ጊዜ እጦማለሁ፥ ከማገኘውም ሁሉ አሥራት አወጣለሁ አለ። ቀራጩ ግን በሩቅ ቆሞ ዓይኖቹን ወደ ሰማይ ሊያነሣ እንኳ አልወደደም፥ ነገር ግን ። አምላክ ሆይ፥ እኔን ኃጢአተኛውን ማረኝ እያለ ደረቱን ይደቃ ነበር ። እላችኋለሁ፥ ከዚያ ይልቅ ይህ ጻድቅ ሆኖ ወደ ቤቱ ተመለሰ፤ ራሱን ከፍ የሚያደርግ ሁሉ ይዋረዳልና፥ ራሱን ግን የሚያዋርድ ከፍ ይላል።"
. የሉቃስ ወንጌል ፲፰ : ፱
በማለት የሚገልጸው ቃል ክፉ መንፈስ በሰዎች ላይ ሲያድር እንዲህ ዓይነት የውስጥ ትዕቢት በማሳደር ፈረሐ እግዚአብሔር በማራቅ እምነትን የሚፈትን መሆኑንን ከፊሪሳዊው የጸሎት ልምድ መገንዘብ እንችላለን ፡፡ በመሆኑም ጠቋር በመንፈሳዊ ሥፍራና በጸሎት ወቅት በትቢት ሰዎችን ሊያስትና አቅጣጫቸውን ሊያስለውጥ ይችላል ፡፡ በአገራችን ልማዳዊ አነጋገር ጠቋር ዳዊት ደጋሚ አሸዋ ቃሚ ቅጠል ለቃሚ የባላል ፡፡ እናቶች በዚህ መንፈስ በጣም ተታለዋል ፡፡ መንፈስ ውስጣቸው እያለ አብረው ይመነኩሳሉ < የእኔ እኮ...ዳዊት ደጋሚ ነው ! እንዲህ ቀላል አይደለም ቤተክርስቲያን ሳሚ ገዳማዊ መነኩሴ ነው ...ወዘተ እያሉ በስፋት እንዲቀበሉት የሚደርጋቸው ሲሆን አውደ ነገሥቱም ይህንን መንፈስ ያጠናክረዋል ፡፡
. .
. .
. የጠቋር መንፈስ ሥልቶች .
ይህ የጠቋር መንፈስ ከፍተኛ የማስገደድ ኃይል ስላለው ራሱን ትልቅ አድርጎ በማሳየት ሌሎች በግድ በትልቅነት እንዲቀበሉት ያደርጋል ፡፡
. .
• በሕልም በማስፈራራት
• ያሳየውን ራእይ በሚቀጥለው ቀን ተግባራዊ በማድረግ
• በሰውነት ውስጥ የተለያዩ ምልክቶች በመስጠት ነው ፡፡
. .
ጠቋር ሰዎችን በቀላሉ ለመያዝ የሚከተለው ሥልት ከሌሎች በላቀ ሁኔታ የተለያየና የበለጠ ነው ፡፡ከእነዚም ውስጥ በገባበት አጭር ጊዜ ውስጥ በአስገዳጅነት ከፍተኛ ሀይልን ተጠቅሞ በፍጥነት ልቡናን ሰውሮ ሕሊናን በማስጨነቅ ወደፈለገው አቅጣጫና በሚፈልገው መንገድ መምራት መቻሉ አንድ ነው ፡፡ ይህን ክፉ መንፈስ ብዙ አባቶችና እናቶች ለምደውታል ፡፡ ልምምድም በባሕር ውስጥ ካለው መሸነፍ ጋር የያይዞ ለአምልኮት ከሚሰጡት ቦታና በጸሎት ከሚቃወሙት ተግባራዊ እንቅስቃሴ ደካማነት የተነሳ በቀላሉ ተቀብለውት እንዲኖሩ ያደርጋል ፡፡
. .
ጠቋር ከሕቡዓን (ከተሰወሩ) ቅዱስ ጋር ያገናኛል በማለት የመናፍስቱ ሹክሹክታ እንደዚ ቅዱሳን ድምፅ ምናባዊ ውልብታውን ደግሞ እንደ ፃድቃን ብርሃናዊ ገጽ በመቁጠር ለማሳመን የሚሞክር መንፈስ ነው ፡፡
በባሕርይ ውስጥ አባት ሆኖ የመቀመጥ የመያዝ ጠባዩ በሥፋት የታወቀ ነው ፡፡ ብዙዎች ጠቋርን መንፈሳዊ ነው! ምንም ጉዳት አያመጣም እንዲያውም ጠባቂ ረዳትና አጋዥ ነው ይሉታል ፡፡ ከዚህ በተጨማሪም ራእይን ይገልጣል ተብሎ የተለያዩ መሻቶችን የሚጠይቅና ባመኑትና በሰገዱለት ዘንድ የሚገበርለት መንፈስ ነው ፡፡
. .
. ጠቋር በጸሎት ሥፍራ የጸሎቱን ባሕርይ በዝማሬ ቦታ የዝማሬውን ባሕርይ ወዘተ ... ይከተላል ፡፡ መንፈሱ በጣም ጥንቃቄ የሚያደርገው በቅዱስ ቁርባን አምልኮት ላይ ብቻ ነው፡፡ በዚህ በኩል የሚመጣበትን የእግዚአብሔር መንፈሰ ጨርሶ ሊቋቋመው ስለማይችል ሰዎች ወደ ቅዱስ ቁርባንና ወደ እግዚአብሔር አምልኮተ እንዳይገቡ የመጀመሪያውን የመዘግየትና የመጎተት ውጊያ ይከፍታል ፡፡ ኑሮአቸውን የተሟላና የተሳካ እንዳይሆን አስሮ በመያዝ በእግዚአብሔር አምላክ እንዲማረሩ ያደርጋል ፡፡ በቤተሰብ ምሥረታ ውስጥም ገብቶ በልጆች አእምሮና ሕሊና ውስጥ አፍዝ አደንግዝ ለመሆን ጊዜ አይፈጅበትም ፡፡ ምክንያቱም አባት ተብሏልና በመጽሐፍ ቅዱስ ውስጥ "እናንተ ከአባታቸው ከዲያብሎስ ናችሁ " ተብሏል ፡፡ ከላይ የሚነሳ ወንዝ ወደታች ለመውረድ ምን ያስቸግረዋል ? ጠቋር ከላይ ያለውን አጥብቆ ያዘ ማለት ታች ያለውን መቆጣጠር ይችላል ፡፡
. .
ጠቋር ሥልታዊ መንፈስ በመሆኑ ወደ ሰውነት ለገብ ሌሎች መንፈሶች የአሥራር ሥልቱን ያስተምራል ፡፡ ወደ እግዚአብሔር ቤት ወደ ጸሎተና ጸበል ሥፍራ ሰንሄድ ውጭ ተለይቶ የሚጠብቁንን መንፈሶች ሥልታቸውን ለውጠው ከጸሎትና ከጸበል መልስ ወደ ሰውነት ውስጥ በመግባት በልብ ውስጥ የነበረውን ሠላምና ጤና ማወክ እንዲጀምሩ ያበረታታል ፡፡
ሌሎች መንፈሶች እንዲደበቁ ተራ በተራ እንዲጨው ጊዜ እንዲያባክኑና ያስከተሉት ችግር እንዲባባስ ከማድረጉም በላይ የጠቋር መንፈስ ቶሎ እዳይያዝ በዋላ የገባውን መንፈስ አጋፍጦ በመስጠት ራሱን ደብቆ መንፈሶቹ ከወጡ በዋላ ተመልሰው እንዲገቡ ደጋግሞ በሌላ ዓይነት አቀራረብ እንዲናገሩና እንዲጮዉ በማድረግ ዘዴውን ይቀይሳል ፡፡
" የአማልክት አምላክ፥ የነገሥታትም ጌታ፥ ምሥጢርም ገላጭ ነው። "
( ትንቢተ ዳንኤል ፪ : ፵፯)
ጠቋርን በሁለት መንገድ እናገኘዋለን
1'ወደ አውደ ነገስት የኮከብ ቆጠራ ውስጥ ስንገባ
2'ጊዜና ዘመኔን ፍታልኝ ብለን ወደ ጠንቋይ ቃልቻው አስማተኛውና መተተኞው ዘንድ ስንሄድ ነው ፡፡
. .
. 'ከጠቋር የረቀቀ ምሥጢራዊ የጥቃት ዘዴዎች መካከል .
. .
• ሰዎችን በፍጥነት የመልመድ ጠባዩና በከፍተኛ ደረጃ ተመሳስሎ የመኖርና የማድፈጥ ችሎታው
• አንዳንዴ የምታያቸውን ራእዮች እውነተኞ ለማስመሰል ሰፋ ያለ ጊዜና መንገድ በሕይወትህ ውሰጥ መምራት መቻሉ
• ባሕርይህን የመምሰል ጠባዩ የተዋጣለት መሆኑ
'ለጸሎት ስትዘጋጅና ስትጸልይ የሚያመጣው ፈተና '
• የትግሉ ሥልት በኑሮህ ውስጥ ያሉትን ጎዶሎዎች በሙሉ በልብህ ላይ ይጽፍልሃል በዚህም ሃሳብህ ይከፈልና ጸሎትህን ያሰናክላል
• ባለፋ ጉዳዮች ላይ እንድትጨነቅና ምነው እንዲህ ባረኩት ኖሮ ብለህ እንድታስብ በጸልሎትህ ሰዓት ሃሳብ ያመጣልሃል
• ወደፊት የምትሠራቸውን ሥራዎች ከፊትህ ያመጣብህና እንከኖችን በመደርደር በሀሳብ እንድትዋጥ ያደርግሃል በዚህ ጊዜ ፍንጭ ሳይሰጥህና የማንነቱ ጠባይ ሳይታወቅ በመንፈሳዊ ሕይወትህ ውስጥ ባሉት ርምጃዎች ሁሉ ብዙውን መንገድ አብሮህ ስለሚጓዝ አታውቅውም ፡፡ ምክንያቱም ማንነቱና ምንነቱ በአንተ ባሕርይ ውስጥ የተደበቀ ነው ፡፡
. .
ይህ መንፈስ በጠበል ቦታ ራሱን የመደበቅና የመሰወር ከፍተኛ ችሎታ የለው ብቻ ሳይሆን የሚያስገርመው በጠበልና በተለያየ የአገልግሎት ሥፍራዎች ላይ እየጮኸና ወጥቶ የሄደ እየመሰለ በማዘናጋት የተዳፈነ እሳት ሆኖ ለጊዜው ውስጣችን ተረጋግቶ ጸጥ ብሎ መቀመጥ የሚችል መንፈስ መሆኑ ነው ፡፡
. .
ሌላው የረቀቀ ሥልቱ ደግሞ ራሱን በማመሳሰል እንደ ቅዱስ መልአክም ለመሆን እየቃጣው ንስሐ ግቡ ጫማ ከመግቢያ በር አውልቁ እያለ በጠበል ቦታና በአንዳንድ የጥምቀት ቦታዎች ገላጭ በመሆን የብዙ ክርስቲያኖችን ልቦና በመሳብ ውስጣዊውን የእግዚአብሔር አምልኮ
ጥንካሬያቸውን ያጠናል ይሰልላል ፡፡
. .
. ውጫዊ እይታን ማደናገር .
. .
የጠቋር መንፈስ ካሉት ክፉ ጠባያት መካከል አንዱና ዋናው ውጫዊ እይታን በማዘበራረቅ ልቦናን መረበሽ ነው ፡፡ ክፉው መንፈስ በዓይንና በልብ ውስጥ በማድፈጥ መንፈሱ ያለበት ሰው ለሚያየው ነገር ትኩረት እንዳይኖረው አድርጎ ያንን የተመለከተውን ነገር አዛብቶ በማቅረብ ልቦናውን በመረበሽ አእምሮውን ይበጠብጣል ፡፡
. .
. ውጫዊ ድምጾችን አጣሞ ማሰማት .
. .
ዘመድ ቤተሰብ ጎረቤት ጓደኛ ውስጥ ተንኮል እንደሚፈጽሙ አድርጎ ማሳየት ሳይናገሩ እንደተናገሩ አድርጎ ማሰማት ያላወሩትን እንደ አወሩ አድርጎ በማሳመን በክፉ እንድናስባቸውና እንደናያቸው ያደርጋል ፡፡
. .
, የእንስሳትን ድምጽና ጩኸት መተርጎም .
. .
. ከመንፈሱ ሥውር ወጥመዶች መከላከል ለምሳሌ : ጅብ ሲጮህ መቁጠር ወፏ ያለ ወትሮዋ ለየት ያለ ዝማሬ አሰማች ውሻው እንዲህ ብሎ አላዘነ ጉንዳን በስልፍ ሆኖ ወደ ቤት ገባ ወዘተ ... በማለት እየተረጎምን የሚመጣውን ጊዜ ከክፉ ነገር ጋር በማዛመድ በሥጋትና በፍርሃት ተቆራመደን እንድንኖር ማድረጉ አንዱ ነው ፡፡
. .
. . . ሌላ ሰው የማያየውን መመልከት .
. .
ጠቋር ዓይን ላይ በመቀመጥ በአንድ ሰው ላይ ያደረን ክፉመንፈስ በማሳየት ያስደምመዋል አንዳንዴም መላእክትን አስመስሎ በመናገር በብዥታ ውስጥ መልእክት ያስተላልፍለታል ፡፡
. .
. የሸክም ጫና መፍጠር .
" ጫንቃውን ከሸክም፥ እጆቹንም በቅርጫት ከመገዛት አራቅሁ።"
(መዝሙረ ዳዊት ፹፩:፮)
. .
የጠቋር ክፉ መንፈስ ከሌሎች ውቃቢዎች አውሊያዎችና ዛሮች ለየት የሚያደርገው በቀኝ ትከሻ ላይ ተቀምጦ ትልቅ ድንጋይ ወይም ከባድ ዕቃ የተሸከምን ያህል እንዲሰማን በማድረግ ብርቱ በትከሻ ላይ ድበታና ጫናን መፍጠር ሌላው የሚታወቅበት ገጽታው ነው ፡፡ ሌላው ችግር በትከሻ ላይ ወይም በጀርባ በኩል ሆኖ በብዥታ የቆመ ሰው መስሎ ገጽታውን ማሳየት የተለመደ ልዩ ተግባሩ ነው ፡፡ አንዳንድ ጊዜ ደግሞ በአውላላ ሜዳ ላይ የቡና ሽታ ወይም የሽቶ መዓዛ በማምጣት የመንፈሱን የሽታ ፍላጎት ከሚሸተው ሰው ስሜት ጋር በማስተሳሰር የልብን አምሮትና መሻትን በሽታው መዓዛ አማካይነት እንዲናፍቅ ያደርገዋል ፡ ፡
. .
- ውስጥን ማድመጥ .
ውስጥን አዳምጦ በጎውን ነገር መሸሽ ፣ ውስጥን አዳምጦ ክፋትን መለማመድ ፣ ውስጥን አዳምጦ የሌሎችን ሕይወት ለመተናኮል መመልከት ፣ ውስጥን አዳምጦ አጋንንቱን ማገልገል እነዚህ ውጥን የማድመጥ ልምምዶች በብዙዎቻችን ሕይወት ውስጥ ሥር ሰደው ከተቀመጡ ቆይተዋል ፡፡ ምክንያቱም ቤተሰባችን ከቅዱስ ቁርባን ሀይልና ከመንፈሳዊ በረከት በመውጣቱና በመራቁ ነው ፡፡ በሌላ አነጋገር በዘራችን ውስጥ ዘልቀው ጣልቃ የገቡ ርኩሳን መናፍስት አብረውን ዘር ሆነዋል ፡፡ ስለዚህ ውስጣችን ስናዳምጥ ብዙ እንጎዳለን ፡፡
. .
ጠቋር ከውስጥ ሆኖ የነገረህን ሀሳብ የበለጠ እንድታምነው በሕልም አሳምሮና አስተካክሎ ያሳያል ፡፡ ከዚህ መተጨማሪም በስው ላይ አድሮ ያንኑ ሀሳብ ከሌላ ሰው አንደበት እንድትሰማው ሰው የዘጋጅልሃል ፡፡
. .
, የጠቋር መንፈስ በአውደ ነገሥቱ ከፍተኛ ቦታ የተሰጠውና ከስያሜው የተነሳ ታላቅ የተባለ ቆየት ብሎ ቀኝን በመያዝ ጠባቂ መልአክ የሚባል ልዩ ስያሜና ክብር የተሰጠው ነው ፡፡ ብዙዎች ሳያውቁት ተከትለውታል የአምልኮት ክብር ሰጥተውት በውስጥ በኩል የሚነግራቸውን እያዳመጡ ችግራችንን ይቀርፋልናል ብለው በጨላማው የአስተሳሰብ ስሜት ይመሩበታል ፡፡ ይህ የተሳሳተ የጥፋት መንገድ በትውልዳቸውም ውስጥ ቀጣይ ሆኖ አብሮ በመወለድ በተለያየ ዓይነት ሁኔታ ልጆቻቸው በመንፈሱ እርግማን እንዲፈተኑ ያደርጋቸዋል ፡፡
. .
'የጠቋር መንፈሰ ለሰዎች የሚያወርሳቸው አንዳንድ ጠባያት
. .
የጠቋር መንፈሰ አጋንንት እና ሰይጣን ቢሆንም ንግሥናውና የሚጠራበት ስም በዛሮችና በውቃቢዎች ዘንድ እንደ ትልቅ ማዕረግ ስለሚታወቅለት ራሱን ታላቅና ሀያል አድርጎ ይቆጥራል ፡፡
. . . መንፈሱ የሰው ልጆችን ሕይወትና ኑሮ የሚፈትንና ለፈተና አሳልፎ የሚሰጥ ወይም የሚዳርግ ክፉ የዲያብሎስ መንፈስ በመሆኑ አንዴ ውስጣችን ከገባ ባሕርያችንን ለውጦ እልከኛ ፣ ደፋር ፣ ጉልበተኛ ጠበኞ ትዕቢተኛ ቁጡና ሀይለኞ .. ወዘተ ስለሚያደርገው ሕይወታችንን ከሌሎች ሰዎች ጋር ያለንን መልካም ግንኙነት ሁሉ አደጋ ላይ በመጣል ያበላሻል ፡፡
. .
. ጭንቀትን መፍጠር .
" በተጨነቁ ጊዜ ወደ እግዚአብሔር ጮኹ፥ ከመከራቸውም አዳናቸው፤" (መዝሙረ ዳዊት ፻፯:፮)
አእምሮአችን ውስጥ የእርሱን ውሳኔ የራሳችን ውሳኔ እንዲመስለን ያደርጋል ውሎ ሲያድር ግን ምን ሆኜ ነው እንደዚህ ዓይነት ውሳኔ የደረኩት ብለን እንድንጨነቅና ሕሊናችንን ክፉኞ እንድንወቅስ ያደርጋል ፡፡ በዚህ ሁኔታ መንፈሱ ከአእምሮ ከሕሊህና ከልቦናህ በአጠቃላይ ከራስህ ጋር እየተጣላህ እንድትኖር ስለሚያደርግህ ጭንቀት የማይለየው ሰው ትሆናለክ ፡፡
• የጭንቀቱ ዓይነቶች •
ሀ.ራስህ የምትደብቀው ጭንቀት ፣ የሚያስጨንቀው ጉዳይ የሚታወቅ ይሆንና ለምሳሌ ባል ለሚስቱ ሚስት ለባልዋ የማይገልጹት ይሆናል ፡፡
ለ.የተሰወረ ጭንቀት ፣ አስጨናቂው ፡ ጭንቀት ጭንቀት ይልሃል ፡፡
ሐ.የተገለጠ ጭንቀት ፣ የጭንቀቱ ጉዳይና ሁኔታ በደንብ ልታውቀውና ልትገልጸው ትችላለህ ፡፡ ነገር ግን ወደ መፍትሔ እንዳትሄድ ጭንቀትህን የሚያባብስ የሚጫንህ መንፈስ ይኖራል ፡፡
• የፍርሀት መንፈስን ማንገሥ •
" በሞት ጥላ መካከል እንኳ ብሄድ አንተ ከእኔ ጋር ነህና ክፉን አልፈራም። " ( መዝሙረ ዳዊት ፳፫ : ፬ )
. .
ሀ.የሥጋ ፍርሃት (ውጫዊ ) ለምሳሌ አውሬ ስናይና ከፍተኛ ድምፅ ሲጮህብን የሚፈጠርብን ድንጋጤ ከነባራዊው ዓለም ወይም አውጭ የሚመነጭ የሥጋ ፍርሃት ነው ፡፡ ዲያብሎስን ብዙ ጊዜ በሥጋዊ ዓይናችን የምንገነዘበውን ከመንፈሳዊ ጉዟችን ለማደናቀፍ ይህን ዓይነቱን ፍርሃት ያመቻችልናል ፡፡
ለ.የነፍስ ፍርሀት ( ውስጣዊ ) ከውስጣችን የሚመነጭ የፍርሀት አየነት ነው ፡፡ ነፍስን የሚያስፈራው ሀይል ደግሞ ዲያብሎስና ሠራዊቱ ነው ፡፡ቤታችንን ኑሮችንን ሀብታችንን ጤናችንን ... በአጠቃላይ ሕልውናችንን ረግጦ የያዘው ዲያብሎስ የውስጥ ፍርሀታችንና ጭንቀታችን ሁሉ መሠረት ነው ፡፡ ሐኪሞቻችንና ሌሎች የመስኩ ሙያተኞች ለሁሉም የፍርሃት ዓይነቶች ፎቢያ የሚል የጋራ መጠሪያ አበጅተውለታል፡፡
. .
. ለምሳሌ aqua phobia - ውሃን መፍራት
. Achluo phobia - ጭለማን መፍራት
. Avio phobia - የአውሮፕላን ጉዞን መፍራት
. gamo phobia - ጋብቻን መፍራት
. Ecclesio phobia - ቤተክርስቲያን መፍራት
. .
. የጠቋር መንፈስ የፍርሀት ጥላዎች .
. ይህ መንፈስ መንፈሳዊ መሠረት የሌላቸውንና ጾም ጸሎት ስግደት የማያውቁትን እንዲሁም ልማዳዊ አምልኮት የሚከተሉትን ሰዎች በማስፈራራት የሚበረታ ሲሆን በዓይን-ሕሊናቸው በፍርሃት እንዲዋጡ በብዥታ ማደናገርና ከዋላቸው ጥላ መስሎ በመቆም በመክበድ በበላያቸው በማንዣበብ ሰውነታቸውን በመጎንተልና ማስደገጥ የልብ መራድና የአእምሮ መጨነቅን በመፍጠር ወደ እብደት የሚወስደውን የአእምሮ ሕመም እንዲፈጠርባቸው ያደርጋል ፡፡
. .
. በአጠቃላይ ይህ የድፍረት መንፈስ የሰው ልጆችን ሕይወትና ኑሮ እየፈተነ በስኬት በእድገት ጎዳና ላይ እንዳይረማመዱ አድርጎ ወደ ጨለማ የሚመራ ቢሆንም በእምነት ሀይል እግዚአብሔር በሰጠን የእግዚአብሔር ልጅነት በምሕረቱና በቸርነቱ ጥላ እየታገዝን በቅዱሳን መላእክት እርዳታ በፃድቃን መንፈስ ምልጃ እየተረዳን በቅዱስ ወንጌል የቃሉ ብርሃን እየተመራን በክርስቶስ ሥጋና ደም ስንታተም ይህንን ጠላታችንን ከሕይወታችንና ከዙሪያችን ልናስወግድበት የምንችልበት ሀይል እግዚአብሔር ይሰጠናል ፡፡
" አንተ መብራቴን ታበራለህና፤ እግዚአብሔር አምላኬ ጨለማዬን ያበራል።በአንተ ከጥፋት እድናለሁና በአምላኬም ቅጥሩን እዘልላለሁ።"
. መዝሙረ ዳዊት ፲፰ : ፳፰ - ፳፱
ምንጭ "በማለዳ መያ`ዝ መጽሐፍ" ✞ በመልአከ መንክራት ግርማ ወንድሙ
!!! እንደ እግዚአብሔር ፍቃድ በቅርቡ ቀን !!!
☞ ክፉ መናፍስቶችን የማዋረስ ምሥጢራዊ ጥበብ

የዝሙት መንፈስ ምንድነው? አይነጥላ ምንድነው?

Friday, April 15, 2016

ወንጌላዊው ሉቃስ የሣላት ሥዕለ ማርያም ተአምራት

ጼዴንያ በምትባል ሀገር ውስጥ የነበረች ማርታ የምትባል የከበረችና የተመረጠች አንዲት ሴት ነበረች። ከዕለታት አንደ ቀንም የሷ ገንዘብ እንደ ሰው ገንዘብ ሁሉ እንደሚጠፋና ከንቱ እንደሆነ በማሰብ ሰፊ የእንግዳ ማረፊያ በማዘጋጀት እንግዶች መቀበል ጀመረች። አብልታ አጠጥታ ከጨረሰች በኋላ ስለመለኮትና ስለቀደሙት አባቶች ትጠይቅ ነበረ። ከእለታት አንድ ቀንም  አብልታ አጠጥታ ከጨረሰች በኋላ ለእርሷ የሚጠቅማትን ነገር እንግዶችን ስትጠይቅ በኢየሩሳሌም ሀገር ውስጥ የእመቤታችንን ሥዕል የሚሥሉ እንዳሉ ያቺም ሥዕል የለመኑትን ሁሉ እንደምታደርግላቸው ነገሯት።
ይህንንም ነገር ሰምታ በድንግል ማርያም ፍቅር ልቧ ተነካ። ሰለሥዕሉ የነገሯትንም ሰዎች ‹‹ገንዘብንና ወርቅን ሰጥቼው ከሚሥሉት ሰዎች የድንግል ማርያም ሥዕልን ይገዛልኝ ዘንድ ከእናንት ወደ ኢየሩሳሌም የሚሄድ አለን?››  ብላ ጠየቀቻቸው። አንድ መነኩሴም ያቺ ሴት ድንግል ማርያምን የመውደዷን ነገር ሰምቶ ‹‹አኔ እሄደለው በራሴው ወርቅም ገዝቼልሽ እመጣለው በተመለስኩ ጊዜም የገዛሁበትን ወርቅ ያህል ካንቺ እቀበላለው›› አላት።
ማልዶም ተነሥቶ ወደ ኢየሩሳሌም ሄደ በደረሰ ጊዜም ያቺን ሴት ይገዛላት ዘንድ ያማጸነችውን በዚያ አሰበ። አስቦም አልቀረም መልኳ ያማረ ሥዕል ገዛ።
ቅድስት ድንግል ማርያም ከተወደደው ልጇ ጋር (አቡነ የምዓታ ገዳም የሚገኝ ሥዕል ?15 ኛው መ.ክ.ዘ.)
ይህችውም ሥዕል ወንጌላዊው ሉቃስ የሣላት ናት ትባላለች። ያም መነኩሴ ሥዕሏን በደረቱ ታቅፎ ወደ ጸዴኔያ በሚወስደው መንገድ ሔደ።  እየሄደ ሳለም አንበሳ ይገድለው ዘንድ እየጮኸ በጠላትነት ተነሣበት። ያ መነኩሴ አንበሳውን ከመፍራቱ የተነሳ ደነገጠ ተንቀጠቀጠ። ደንግጦ ቁሞ ሳለም ያቺ ሥዕል ከአንበሳው ጩኸት ሰባት እጅ በሚበልጥ በፍጹም መፍራት ጮሀ ተናገረች። ያን ጊዜም ፈረሰኛ ተከትሎ ለሞት እንዳደረሰው ያ አንበሳ ደንግጦ ፈጥኖ ሸሸ። ያም መነኩሴ የሥዕሊቱን ድምጽ ከመስማቱ የተነሣ እያደነቀ ሄደ።
ሁለተኛም መቀማት መግደል ልማዳቸው የሚሆን ወንበዴዎች በከበቡት ጊዜ አስቀድመን እንደተናገርን ያች ሥዕል እንደመብረቅ ባለ በታላቅ ቃል አሰምታ ተናገረች። ከመፍራትም ብዛት የተነሳ እነዚያ ወንበዴዎች ያ ጩኸት  ከየት እንደመጣ (እንደተደረገ) ሳያውቁ ሸሹ። ያም መነኩሴ እነዚህን የሚያስደንቁ ተአምራት በሰማና ባየ ጊዜ አሰበ። ረዳት ትሆነኝ ዘንድ ወደ አገሬ ኢትዮጵያ ይዣት እሄዳለውም አለ።
እሱ ግን ይህችን ሥዕል በፍጹም  ልቦናዋ ከምትወዳት ሴት ጋር ትኖር ዘንድ በራሷ ፈቃድ እንደመጣች አላወቀም። ነገር ግን ለነጋዶች እንደሚሸጧቸው እንደሌሎች ገንዘቦች ያለ ፈቃዷ በገንዘቡ ዋጅቶ ያመጣት መስሎት ነበር። ስለዚህች ነገር ለዚህች ሴት እንዳልሰጣት ባገሬ መንገድ እሄዳለው እንጂ በቤቷ መንገድ አልሄድም አለ። እንዲህም ሲያስብ በልቦናውም ሲመክር ከባህር ዳርቻ ደረሰ። ብዙ መርከቦች ነበሩ ወደ ወደብ በማናቸው መንገድ ትወጣለችሁ አላቸው። አንዱ ወደ ጸዴንያ አለው፣ተወው። አንዱ ግን በሌላ ቦታ ወደ ኢትዮጵያ አገር እወጣለው አለው።
በዚያች መርከብም ሄደ ነገር ግን ግማሽ( ከባህር መካከል) ሲደርስ ጥቅል ነፋስ ተነስቶ ያለፈቃዱ ጼዴንያ ወደሚያወጣ ወደብ ወሰደው። በዚያች መንገድ ወጥቶ በልቡ “ሥዕል እገዛላት ዘንድ ያመጸነች እኔ እንደሆንሁ በወዴት ታውቀኛለች ብሎ ወደ ማርታ ቤት ሄደ ወደ ቤቷ ገብቶም ከመንገደኞች ጋር አደረ።
ሲነጋ ከሳቸው ጋር ወደ ውጭ ወጥቶ መንገዱን ይሔድ ዘንድ ወዶ  ከእንግዶች ጋር ወደ ቅጽር በር ደረሰ እነሱም ወጡ። ይህ መነኩሴ ግን ወጥቶ መሄድ ተሳነው በእመቤታችን በድንግል ተአምር መዝጊያው በፊቱ ተዘግቶበታል። የቅጽሩ በር ግን ከፊቱ ለሌሎቹ አለተለወጠም ለሚገቡ ለሚወጡም የተከፈተ ነበር። የማርታም ልማድ ስንቅ ለሌላቸው ለመንገድ የሚያሻቸውን እየሰጠች ወደ ቅጽሩ በር እንግዶችን ዘወትር መሸኘት ነበር።
ያንም መነኩሴ በዚያ ለመውጣት ሲተጋ ሳይቻለው ባየች ጊዜ አባቴ ሆይ በታመመ ሰው አምሳል አይሃለሁ እደር ነገ ትሄዳለህ ቤቴም ለእንግዶች ማደሪያ የተሠራ ነውና አለችው እሱም እሺ አላት። በነጋውም ሁለተኛ ይሔድ ዘንድ በወደደ ጊዜ እንደ ትናንት መሔድ ተሳነው። እሷም ሁለተኛ ጊዜ አሳደረችው። ዳግመኛም በሶስተኛው ቀን ይወጣ ዘንድ ሲሞክር ልማድ አልተወውም መውጣትንም አልቻለም።
ማርታም ሦስት ቀን እንደዚህ ሆኖ እንደ በሽተኛ ሳይተኛ እንደ ደህና ሳይሄድ ባየችው ጊዜ ‹‹አባቴ ሆይ ይህ ባንተ ላይ ያለነገር ምንድን ነው ተናገር›› አለችው። ያም መነኩሴም በማፈር መናገር ጀመረ። ‹‹ወደ ኢየሩሳሌም በሔድሁ ጊዜ የእመቤታችን ድንግል ማርያም ሥዕል አመጣልሽ ዘንድ ያማጸንሽኝ እኔ እንደሆንሁ አላወቅሽምን?›› አላት። ከቤቴ የሚገቡና የሚወጡ ብዙዎች ናቸውና በምን አውቅሃለሁ አለቸው። ከዚህም በኋላ የተደረገውን ተአምራት ሁሉ ነገራት።
ይህንንም ተናገሮ ያችን ሥዕል ከክንዱ አውጥቶ ሁለንተናዋ ድንቅ የሚሆን ያችን ሥዕል እነሆ ለማርታ ሰጣት። ማርታም ይህን ነገር ሰምታ ድንግልን ስለወደደች ከእግሩ በታች ሰገደች። ሥዕሉን ከእጁ ተቀብላ በታላቅ ምስጋና አመሰገነች ሰገደችም። ሰለሞን ለታቦተ ጽዮን ማደሪያ ቤተመቅደስን እንዲሠራ ያመረ ቤትን አሠራችላት። እሷንም የሚቻላትን ያህል አክብራ አኖረቻት። ከሥዕሏም እንባና ወዝ ይወጣ ነበር። ከወዟም የተቀቡት ከሚያስጨንቅ ደዌያቸው ይፈወሱ ነበር። በዓሏም መስከረም 10 ቀን ነው። ማርታም በፊቷ እጅ ትነሣና ትሰግድ እንደነበረ በተአምረ ማርያም ላይ 8 ተአምር ላይ ተገልጿል።

ንብ በሚያረባ ሰው ላይ የተደረገ ተአምር

Friday, April 1, 2016

ምድር ውስጥ ያለችው የታች ጋይንቷ ሰጎዳ ማርያም

አርብ ገበያ ነን፡፡ አርብ ገበያ የታች ጋይንት ወረዳ ዋና ከተማ ናት፤ አዲስ አበባ ከአርብ ገበያ 775 ኪሎ ሜትር ትርቃለች፡፡ የታች ጋይንት ብዙው የአየር ንብረት ወይና ደጋማ ነው፡፡ እንደ ቤተ ልሔም ያሉ ጥንታዊ መንፈሳዊ ስፍራዎች የሚገኙባት ወረዳ ከልዳ ጊዮርጊስ እስከ ደቃ ቂርቆስ አስደናቂ የሆኑ መንፈሳዊ መዳረሻዎች ቢኖሩባትም ብዙም አትታወቅም፡፡ ከራሷ ተሻግሮ የሀገር ልጅ ሊኮራበት የሚገባውን ቀደምት ቅርስ ፍለጋ መጥተናል፡፡ 
ሰጎዳ ማርያም ከአርብ ገበያ 11 ኪሎ ሜትሮች ያክል ትርቃለች፡፡ የደብሯ የጽሑፍ ሰነዶችና የሀገሬው ቃል ጥንታዊነቷን ይገልጻል፡፡ የተተከለችው በአብርሐ አጽበሐ ሲሆን የሰነዶቹ ምስክርነት በ330 ዓ.ም. እንደተሰራች ያትታል፡፡ አቡነ ሙሴ የተባሉ ከግብጽ የመጡ ቅዱስ አባት የተከሏት እንደሆነች ታሪኳ የሚያስረዳው ሰጎዳ ማርያም አስገራሚ በሚባል አሰራር የታነጸችና ከመሬት ተገናኝታ በልዩ ሁኔታ የተፈጠረች ደብር ናት፡፡
ዘመኗን ወደ ኋላ ቆጥሮ ከ 1600 ዓመታት በፊት ይህንን ትሰራ የነበረች ሀገር ለሰራቸው የምትሰጠው ቦታ ምን እንደሆነ ከሚያሳብቁ የሀገራችን መስህቦች አንዷ ናት፡፡ የተነጠፈ ዐለት ድንቅ ቤተ ክርስቲያን የሆነባት ሰጎዳ ማርያም ውስጧ በማህሌትና በመቅደስ የተከፋፈለ ነው፡፡


ምድር ውስጥ ብትሆንም ቀደምት ጥበበኞች የኪነ ህንጻ ጥበበኛነታቸውን ዘመን አሻግረው ማሳየት የቻሉበት አሰራርን ተላብሷል፡፡ ከአናትና በጎን በኩልና በላይኛው ክፍል ለብርሃን ማስገቢያ የተተው መስኮቶች አሉ፡፡ የእነኚህ መስኮቶች አቀማመጥና አቅጣጫ ትክክል መሆኑን በውስጠኛው ክፍል ያለውን በቂ ብርሃን በመመልከት ይደመሙበታል፡፡
የውስጥ ስዕሎቿ ከዐለቱ ህንጻ እኩል ዘመን ባይኖራቸውም እድሜ ያስቆጠሩ ናቸው፡፡ በርካታ ጥንታዊ ቅርሶች የሚገኙባት ሰጎዳ ማርያም የሚበልጠው መገለጫዋ ምንፍስና በመሆኑ ከነገስታት ስጦታዎች ይልቅ የቀደሙት የበቁ አባቶቿ መገልገያ ቁሳቁሶች በክብር ተይዘው የሚጠበቁባት ታሪካዊና መንፈሳዊ ስፍራ ናት፡፡



የኪዳነ ምሕረት ተዓምር 

በደሴ ቁስቋም ማርያም የተደረገ እጅግ ድንቅ ተአምር

 

Friday, March 25, 2016

የእመቤታችን መቃብርና ያረገችበት ጣራ - Tomb of The Virgin Mary

ትውልድ ሁሉ ብፅእት የሚላት በተለይ እኛ ኢትዮጵያውያን እንደ ነብሳችን የምንሳሳላት የእናታችንና የእመቤታችን የቅድስት ድንግል ማርያም ቅዱስ መካነ መቃብርና የተነሳችበት/ያረገችበት ቅዱስ ጣራ ከታች በፎቶ እንደምታዩት ይህን ይመስላል። የሚገኘውም እየሩሳሌም ውስጥ በቄድሮን ሸለቆ አካባቢ ነው።የእመቤታችን ምልጃና ፀሎት በረከትና ረድኤት ከኛ ከምንወዳት ልጆቿ ጋር ለዘላለም ይኑር! በረከቱ ለእናንተም ይድረስ። 


ድንግል በእውነት ተነስታለች ምስክሩም ይኸው ያረገችበት ቅዱስ ጣራ በቄድሮን ሸለቆ (Kidron Valley) ይህን ይመስላል። ይህንን ቅዱስና ድንቅ ቦታ ለሌሎች ሼር በማድረግ እናንተም የበረከቱ ተካፋዬች ሁኑ! እኛ የድንግል ልጆች ስለምናምነው ቀጥተኛና እውነተኛ የተዋህዶ ሀይማኖት ትክክለኛ መረጃና ከልብ ስለምንወዳት ድንግል ማርያም የማንጠራጠርበት ምክንያት አለን። በዚህ ለማያምኑትና አማላጂነቷን ለሚክዱ እመቤታችን ልቦናቸውን ትመልስልን!!! 



የቅድስት ድንግል ማርያም በዘይቱን መገለጽ - በአማርኛ ትርጉም


Monday, March 21, 2016

መልዐከ መንክራት ግርማ ወንድሙ ከገጠመኛቸው

በስመአብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ አሃዱ አምላክ አሜን፡፡
.
መልዐከ መንክራት ግርማ ወንድሙ ከገጠመኛቸው አንዱን ሲናገሩ በሬድዮ አቢሲንያ ቁጥር 22 ካስተማሩት የተሰደ…
.
አንድ ቦታ ላይ አከራዩኝ ብየ ኪራዩ እንደ ጠያቂ ሆኜ ሄድኩኝ፡፡ ከገባሁ በኋላ ዕቃየን አጓጉዤ፡፡ አንድ መኪና ሙሉ አጓጌዤ ማለት በፒክ አፕ ገባሁና ቤት አገኘሁ ብየ ነው፡፡ ለዛዉም እኮ ደግሞ ደግሞ አንድ ክፍል ናት፡፡ በጣም አስቸጋሪ ናት ደግሞ በዛ ላይ ጥበትዋ፡፡ ግን ትበቃኛለች እኔ ምን አለኝ ገብቸ መዉጣት ነው፤ ጸሎት ማድረስ ነው ብየ መሬት አደላድየ አንጥፌ ምን ብየ ጥዋት ለአገልግሎት ልብሴን ለብሼ፤ መጸሐፌን በሻንጠየ ይዤ ስወጣ፡፡ የት ነው የሚሄዱት? አለችኝ ሴትየዋ፡፡ ወደ መሪ አቦ፡፡ እንዴ፤ እንዴ፤ እንዴ መሪ አቦ ሰው የሚያንጫጩት እርስዎ ነዎት? አለችኝ፡፡ አዎ ነው እናትየ፡፡ እኔ ደግሞ በቅን የምታይ መስሎኝ ነው፡፡ እ..ም… አለች፡፡
.
አረረረ..በቃ ሐበሻ እንዲህ ሲል ችግር አለ ማለት ነው፡፡ ሆዴን እየቆረጠኝ ነገሩን እየበላሁ እ..ም… የምትለዋን ቃል ይዤ መጓዝ ጀመርኩ፡፡ እንግዲህ እ..ም… ማከት በሐበሻ ነገር የመብላት ዋዜማ ወይም በልቡ ዉስጥ የቆረጠው ነገር በቅፅበት አለ ማለት ነው፡፡ ይህቺ ነገር ሳስተምር ሁሉ ሆዴን ትበላኛለች፡፡ ስመለስ መጡ እንኳን ደህና መጡ፡፡ ስጠብቆት ነበረ፡፡ ገና ምሳ ሳልበላ፤ አረፍ ሳልል ቤት ይፈልጉ፡፡ ልጄ ከአሜሪካ ትመጣለች ስልክ ተደዉሎልኛልና ሰሞኑን ቤቱን አፀዳድቼ፣ ቀለም ቀብቼ ልጄ ልጠብቃት ስለሆነ ዛሬዉኑ ቤት ይፈልጉና በሦስት ቀን ውስጥ እንዲወጡ እባክዎትን ይተባበሩን አሉና ቁጭ፡፡
.
ጉድ ፈላ፡፡ ይህ ሁሉ ታድያ ይቺ ቀሚሴ አይደለች ጉድ ያፈላች አልኩና ቀሚሴ ላይ አፈጠጥኩ ሳቅ…፡፡ ወይ ቀሚሴ አልኩ በቃ፡፡ ወይ ይቺ የቤተክርስትያን ቀሚስ ይገርማል አልኩና፡፡ ከዛ ደግሞ ስሜ ነው አንዱ ችግሩ ደግሞ የሚያንጫጫው ከተማውን የሚለው ደግሞ የተለመደ ነው እስከ ቅርብ ግዜ ድረስ፡፡ እንደዉም የሚያሳዝነኝ እስካ አሁን ድረስ በጣም አሁንም የምያሳዝነኝ እንዲህ አይነት ጭዋታ፤ እንዲህ አይነት የእርግማን መንፈስን የሚያስፋፉ በቤተ ክርስትያን ያሉ ጉብል ሰባኪዎች ናቸው፡፡ እነዚህ ጉብልዎቹ፡፡ አዳዲስ ጉብልዎቹ ሰባኪዎች እስካ አሁን ድረስ አሁን አሉ መጸሓፍ መውጣቱን እንኳ አላወቁም፡፡ መጥተው የዳነዉን ህዝብ፤ የዳነዉን ህዝብ አይጠይቁም፡፡ አሁን በያዙት ቦታና በተመደቡበት ቦታ ላይ እስካሁን ድረስ እኔን እያሳደዱ ነው፡፡ ለምሳሌ በሳሊተ ምህረት ሲኤምሲ ይሰብካሉ፤ በጥንት የነበረው በጣም የታወቀው ቦታ ላይ የካ ሚካኤል ይሰብካሉ፡፡ ግርማ የሚባል አስማተኛ ከተማ በጠበጠው እያሉ ሰሙኑን ሁሉ ይሰብካሉ፡፡ የካ ሚካኤል ትልልቅ ሰው ባለበት፤ አባቶች የሚባሉ ባሉበት በዛ ቦታ ላይ ትልልቅ ደህንነት፤ ዓይነ ስዉር በበራበት ቦታ ላይ ሲያሽካኩ መድረኩን ሲጫወቱበት ይዉላሉ፡፡ ህዝቡ አይ የምታውቁት ነገር የለም ዝም በሉ እስኪላቸው ድረስ የሚያሳፍር ነው በጣም፡፡ እና የሚያሳፍሩ ናቸው፡፡
.
እና እነዚህ አዳዲሶቹ ጉብልዎች የፈጠሩት ችግርና በዓውደ ነገስቱ ዓለም ይኖሩ የነበሩት አባቶች የንስሐ ልጆቻቸውን እያወገዙ እርሱ ጋር ከሄዳችሁ የተረገማችሁ ናችሁ፤ እርሱ ጋር ከሄዳችሁ ውጉዝ ከመ አርዮስ እያሉ ህዝበ ክርስትያኑን ብጥብጥ አድርገው ትልልቅ የሆኑ ውርደቶችን እያስተላለፉ ከቤተ እግዚአብሔር ያሉት አባቶች ናቸው፡፡ እነርሱ ባደረጉት ትግባርና በቀሰቀሱት ቅስቀሳ መኖርያ ቤት እምከራየው ቤት እስከማጣ ድረስ፡፡ ከዛ በኋላ በኋላ ሴትየዋ አጣደፈችኝ፡፡ በሦስት ቀን እለቅሎታለው አልኩኝ፡፡ አሁንም ፍለጋ ጀመርኩ፡፡ ስንፈልግ፤ ስንፈልግ እኔን ከሚያውቁኝ ደላላዎች ጋር ስንፈልግ እባካችሁ ጉባኤ ላይ ተናገርኩ እባካችሁ የቤት ደላላዎች የላችሁም ብየ ሰው ፊት ተናገርኩ፡፡ መጡ እኔ አውቃለሁ አለ፡፡ ከዛ በኋላ እስኪ ቤት ፈልግልኝ አልኩ፡፡ አሁንም ስንፈልግ ሄድን አሁንም አንድ ቦታ ተገኘ አለ፡፡ ትልቁ ቤት ላይ ሳሎን አለ፡፡ ከሳሎኑ ኋላ ያለቹው ጓሮ ነው ያከራየው፡፡ አሷም ደግሞ 500 ብር አለችኝ፡፡ እሺ ጥሩ ችግር ለም አልኩ፡፡ ያኔ ምንም የለንም፡፡ በጣም ተወዶብኛል፡፡ ሆኖም ከቤተሰብ ጋራ ማለት ነው፡፡ ደሞዝ የለም ምን የለም፡፡ እሺ በ 500 ብር ተስማማሁ ወዴት ልሂድ ታድያ ለመሪ ቅርብ ነው፡፡ ከዛ በኋላ ሄድንና ሰዉየው ሲያዩኝ ምነው የሚከብዱ ይመስላሉ?፡፡ እንዴት?፡፡ ሳዮት ከበድበድ ያሉ ነዎት ለኛ ቤት አይመጥንም፡፡ እንዴ ለመኖርያ ቤትዎ ለዚህ ለሚያከራዩኝ?፡፡ አይ ማለቴ የኛ ቤት ለርስዎ የሚሆኖት መስሎ አልታየኝም፡፡ ተለቅ ያሉ ሰው ነዎት ማለቴ ነው፡፡ አረ እኔ የምታዩኝ ምን ለራሴ ኩርማም ጭባጥ እማልሞላ፡፡ አይይ ግድ የሎትም የኛ ቤት አይመጥንዎትም ለፊቴ ደግሞ እርስዎ ከብደዉኛል አለና ቁጭ፡፡ ከሸፈ ይሄም ከሸፈ፡፡
.
በኋላ አንዱ ጉባኤ ላይ አረ እባካችሁ በመኖርያ ምክንያት ለቅቄ ልሄድ ነው እንዴ አዲስ አበባ ትቻቹ ልሄድ ነው ስል፡፡ አይ የኔ እናት ታማለች በዛው እገዛ እያደረግክልን ትቀመጣለህ አለኝ እና አንድ ወንድም፡፡ እዛ ቤት ገባሁ፡፡ ከዉስጧ የተከፈለች ነች፡፡ በከፊል ደግሞ ለሌላ የጸሎት መገልገያ የምትሆን ቦታ አደረግኩና ቁጭ አልኩ፡፡
.
በነሱ ላይ የመተተችባቸው ሴት ደግሞ በጓሮ በኩል አለች፡፡ በዛ ስወጣ ስገባ መተተኛ መጥፎ ደሮ ትላለች ደሮዋን እያየች እኮ ነው፡፡ ኮቴሸን መስበር ነበረ እያለች የገዛ ደሮዋን በኔ እያሳበበች አኔን ትራገማለች፡፡ ልክ መውጭያ ሳዓቴን ታውቃለች የታባትዋ ይህችን ደሮ እዚህ ከገባች ጀምሮ እንዲሁ አታክልቱ መሬቱን ቦታው ሁሉ ተግማማኮ ትላለች፡፡ እኔ ጸሎት ሳደርስ እንግዲህ ዕጣኑ እየሸተታት ነው መሰለኝ፡፡
.
እንደገና በሌላው ቀን ደግሞ ቆይ አንቺን ከዚህ ሳላጠፋ ይህቺን ደሮ የሚያርድልኝ እንደዉም ምንም ሰውና ቢላዋ ላጣ ነው ትላለች፡፡ የፈረደባት ደሮ ግን ደሮዋ የለችም፡፡ እኔ ነው ደሮው ሳቅ ሳቅ…፡፡ የሚገርም ነው እንዲህ ያለች እያለች ደግሞ ከቤት ውስጥ ደግሞ አንድ መንፈስ ያለባት ልጅ አለች፡፡ ለሷ መንፈስ ነፃ እንድወጣ ስታገል ደግሞ የሷ መንፈስ እሷን ገለበጠና ደግሞ እሷ ከጎኔ ነበረች፡፡ ግድግዳዉን ትደበድባለች፡፡ የታባቱ ይሄ ሰዉየ ከዚህ ካተነቀለ የአባቴን ቤት ይዞ፤ የአባቴን ቦታ፤ ይዞ እናቴን እያስቸገረ እያለ ደግሞ እሱ ደግሞ ሌሊት ከእንቅልፍ ይከለክለኛል፡፡ በዚህ ላይ ደግሞ አይጦቹ ይንጋጋሉ፡፡ በመጨረሻ አንድ አይጥ ጣቴን ስጋ ያገኘ መስሎት ቦድሶ ለቀቀው፡፡ አባቶች አይጥ ሲነክስህ ያሰብከው ይሳካል ይላሉ፡፡ ዎው አልኩና ቢቸግረኝ በጣም ተስፋ አደረግኩኝ ሳቅ ሳቅ…፡፡ ምክንያቱማ አይጥ ሲበዛ በረከት ይመጣል ይባላልና የቀደሙ አባቶች የሚናገሩት ነው፡፡ አይጥ ምቀኛ ነው፡፡ ምቀኛ ሲበዛ እግዚአብሔር ከአንተ ጋር ሆኖ በረከት ይሰጣል እንደ ማለት ነው ትርጉሙ፡፡ ጎሽ እንግዲህ አባቶች የተናገሩት የአይጥዋ ድርሻ በእጄ ላይ ስላረፈ እግዚአብሔር አንድ ነገር ያደርጋል ብየ ጠበቅኩኝ፡፡ እዛው ቤት እንዲሁ መንከራተት፤ መንከራተት በአንድ በኩል ሌባውም ደጅ ሲጠና፡፡ አንዳንድ ዕቃዎችን ደግሞ ከዛ አሽሼ ዘግቼ ወደ ዝዋይ ወደ ቤተሰብ ሄጀ ስመለስ፤ መጣ እንዲህ ይቺ መጥፎ ደሮ ስባል ምን በቃ እንግዳው ሲመጣ ደሮ እንግዲህ ይግበሰበሱ ጀመር እነዚህ ግብስብሶች መምጫቸው መሄዳቸው የማይታወቅ ድራሻቸው ይጥፋ ስንባል፡፡ ልክ እንግዳው ሲመጣ ያቺ መታችዋ በጎረቤት በኩል ትጮሃለች ኡ ኡ ነው የምትለው፡፡ እንግዳው ሲመጣ ትራገማለች፤ ትታገላለች፡፡ ይሄ መተተኛ ደብተራ ትላለች፡፡ ከዛ እንግዶች ሁሉ፡፡
.
በጣም የሚያሳዝነኝ ደግሞ ሞራሌን የነካው፡፡ አንድ ሴት አሜሪካ ቪሲዲዉን ተለቆ ነበር ያን ግዜ ደግሞ፡፡ አይታ ልጅዋን ልታድን ወደኔ ትመጣለች፡፡ ደህና ሰው ተብሎ እንግዲህ የእግዚአብሔር ጸጋ ተገልጦለት ተብሎ በሷ አስተሳሰብ እንግዲህ በጣም የተሻለ ቤት፣ የተሻለ ኑሮ ብላ ነው የምትጠብቀው፡፡ ከዛ መጣች ሳጥን ሰጠኋት መቀመጫ፡፡ ወንበር የለኝም፡፡ እኔ እዚህ የምጸልይበት ቦታ መሬት አለች እዛች ላይ ቁጭ አልኩኝ፡፡ ልጇን ይዛ መጣች፡፡ ቤቱን ታያለች፡፡ እንዲህ እንዲህ ብላ ወደ ላይ ጣራዉን ታያለች፤ ግድግዳው ታያለች፡፡ ግድግዳው ጭቃ ነው በአንድ በኩል ከኋላ በኩል ደግሞ ጭቃው ተገርስሶ አፉ ከፍተዋል፡፡ አንዳንዴ ዝናብ ሲመጣ በዛ በኩል ይመጣል፡፡ ከነካሁት ሊፈርስ ነው፡፡ ይወድቅና እንደገና ደግሞ ኦና ሊሆን ነው፡፡ እና ዝም ብየዋለው ምን ላድርግ ሲወድቅ ድረስ፡፡ ከዛ ግድግዳዉን ከአሁን ከአሁን አትውደቅ እያልኩ እቀመጣለውና መጥታ ሳጥን ላይ ቁጭ አለች፡፡
.
ቤቱን ታያለች፤ ታያለች፤ ታያለች ይሄው የመጣሽበት ጉዳይ እንግዲህ ልጅሽ ነው ጸሎት እናድርስ ስል፡፡ እየፈፋት ነው ቤቱ እሷ ከአሜሪካ ነው የመጣችው፡፡ በማቴርያልም ጭምር ያመልካሉ፡፡ እንግዲህ ይሄ በዓለም የታወቀ ሰዉየ ይዚህ ቆሻሻ መንደር ውስጥ ምን ያደርጋል ብላ ነው እሷ፡፡ ስለዚህ የመጣሁት ወደ ጠንቋይ ሰው ነው ብላ ነው የገመተቹው በቃ፡፡ ያው ቤቱ ደግሞ የጸሎት ዕጣን ስለሚደረስበት እሷ የምታውቀው አይነት ባይሆንም ዕጣን ዕጣን ይሸታል፡፡ አሃ ብላ በስጋት ዓይን ታየኛለች፡፡ ከዛ ልጅቱ ላይ ያለው መንፈስ ተያዘ፡፡ ቡዳ፣ መተትና ዓይነ ጥላ ነበረ፡፡ ይሄ መያዙ አላስገረማትም፡፡ ያስገረማት የምኖርበት ቤት የቀፈፈው መሆኑ ነው፡፡ እና አላስደሰታትም፡፡ ከዛ ይሄው ይሄው ተያዘልሽ አልኩኝ፡፡ ቅር እያላት ሳይ በኋላ እየጸለይኩ ከመንፈሱ ጋር እየታገልኩ በስዕሉ መስታዎት ሳያት ላይ ጣራ ጣራዉን ታያለች፡፡ እንደ አጋጣሚ ሆኖ አይጥ በላይ በጣራው በኩል ስትመጣ በርግጋለች፡፡ ዘንዶ የተቀመጠ መስሏታል፡፡ ይሄው በቃ ተይዘዋል ስላት፡፡ ተያዘ እንዴ? ይሄ ነበረ ችግርዋ አለችና እግዚአብሔር ይስጥለኝም አላለችም ቀስ ባላ ሹልክ ብላ ስትሄድ እንዴ ገረመኝ፡፡ ምን መሆኗ ነው የሷ ደንብሮ ነው እንዴ ብየ በኋላ ሳስተዉለው ቤቱ ቀፏት ነው፡፡ የምኖርበት ቤት ቀፏት ነው፡፡ በስልክም ያለችው ነገር የለም፡፡ እኔ ታግየ ብቻ ከልጂቱ ጭንቀትና ችግር ጋር ተካፍየ ነው ሂጂ በቃ እና ነገ ትመለሻለሽ፡፡ እንግዲህ ተመልከት ስትቀር ስጠብቃት ስልክ ስደዉል ዝግት ታደርገዋለች፡፡ ለልጂትዋ አስቤ እናትየዋ እንግዲህ ለልጂትዋ ማሰብ አቅትዋት ነው፡፡ ያንን የመሰለ ዉርደት፣ ያን የመሰለ ክፉ መንፈስ ለዘመናት ያደቀቃት ልጂቱን የጎዳት እንዳታገባ ዓይነጥላው አለ፤ እንዳትወልድ ዓይነጥላው አለ፤ ሥራው እንዳትሰራ መተቱ አለ፡፡ እቤት ጉልት ልጅ ይዛ መንፈሱ ተጋልጦ በዛች ኮሳሳ ቤት ምክንያት ቀረች፡፡
.
ከዛ በኋላ እሷ ላመጣች እናት ስደዉልላት ምን አይነት ፍንጭ ሰጠችኝ፡፡ የሚኖሩበት ቤት ዓይን የማይገባ ነው፡፡ እንደተባለው ሰዉየው አስማተኛ ሳይሆኑ አይቀሩም አለችና ቁጭ፡፡ ብላለች የሚለው መልዕክትን እንደገና፡፡ በቃ በቃ አልኩ ይህን ለተናገረችው ሴት ስልኩም አጠፋሁ የሷንም ይዚህችኛዉም አጠፋሁና፡፡ ወይ ጉድ ብየ ጸሎቴን ጸልየ፤ ለእግዚአብሔር ተናግሬ የዛን ቀን ያለምኩት ህልም ምን ግዜም የማይረሳኝ ነው፡፡ በደንብ ለአምላኬ ተናገርኩና መቼ ነው ከኢኮኖሚ ነጻ የምታወጣኝ፡፡ ከኢኮኖሚ ባርነት ከዚህ ከቤት ክፉ አገዛዝ፤ ከመኖርያ ቤት፤ ከእርግማን መቼ ነው የምታወጣኝ፡፡ ጠንቋዩና ቃልቻው እዚህ ባለ ሦስትና ባለ አራት ፎቅ ሆኖ የአዲስ አበባ፡፡ የአዲስ አበባ ህዝብ ለጠንቋይና ለቃልቻ ቤት የሚሰራ፡፡ ለመተተኛና ለሟርተኛ ህንፃ የሚገነባ ህዝብ ለኔ አንድ ንፁህ የምከራይበት ቤት አጣሁ ብየ ለእግዚአብሔር ተናገርኩኝና፡፡ ከሌሊቱ አስር ሰዓት ተኩል ለጸሎት ልነቃ ስል የተለየ የጸሎት ቤት ቦታ ያለው፡፡ እጅግ ሰፋ ያለ ብዙ ክፍሎች ያለት እና እጅግ በጣም ብዙ የበረከት ምንጭ ያለው ቤት የሚመስል ራዕይ አየሁና ብንን አልኩ፡፡ በጣም ደስ አለኝ፡፡ በቃ ራዕየይ አመንኩት፡፡ እግዚአብሔር ተናገረ፡፡ ትላንት ባለቀስኩት ዛሬ መልስ ሰጠኝ ብየ እንደገና ጸሎቴን አድርሼ ወደ ቦሌ መድኃኔ ዓለም ሄጄ ተሳልሜ ዙርያዉን ዞሬ ክብርህ፣ ደስታህ፣ ኃይልህ ከኔ ጋር ይን ብየ ደስ ብሎኝ ስጠብቅ፡፡
.
ያው ከአሜሪካ አንድ ታላቅ በሃገሩ መንግስት የታወቀ ፕሮፌሰርና ሳይንቲስት ወደ ኢትዮጵያ መጣ፡፡ በስድስት ወር ውስጥ እኮ ነው፡፡ ከዛች ቤት በነገራችን ላይ ከአንድ ከተወሰነ ወራት በኋላ ወጣሁኝ፡፡ ለሦስት ዓመት አራት ወር የቀረው ኖሬበታለሁኝ ማለት ነው እዛች ቦታ ደሳሳ ጭቃው ሁሉ እየገባ፤ ዉሃ እየተከላከልን ዙርያዉን እየገደልን ዉሃው ሲመጣ አንዳንዴ ውሃ እንዳይስደን እየተጠነቀቅን ቦይ እያወጣንለት እዛ ቆየን፡፡ ይህንን በማድረጋቸው እግዚአብሔር ይስጣቸው፡፡ እነርሱም ታላቅ ውለታ ነው እንጂ አዲስ አበባ ለቅቄ ለመውጣት ሞክሬ ነበረ፡፡ በዚች ሃገር ውስጥ የተለየ አስማተኛ እንደሆንኩ ተደርጎ የሚነገረው የንስሐ አባቶች ድምፅ በከፍተኛ ትንቅንቅ ነበር፡፡ ዲያብሎስ የተዋጋኝ በነሱ በኩል ነበር፡፡
.
ያው ዛሬ በአያት ምድር ላይ አሉ ከሚባሉ አንዱ ቤት ውስጥ እገኛለው፡፡ ያ ሳይንቲስትና ባለቤቱ ቤቱን ገዝተዉልኝ ደስ ብሎኝ እግዚአብሔር ይመስገን ከመንከራተት ድኜ እግዚአብሔር ስሙ የተመስገን ይሁን፡፡ ጸሎቴን በአንድ ቀን ውስጥ ምላሽ ሰጠ እግዚአብሔር፡፡ እዚህ ያለው ህዝብ እንዲህ ሲያደርገኝ ለኔ የሚግዘኝን ከዉጪ አመጣኝ፡፡ ዛሬም የሚለወጡት እዚህ ያሉት በብዛት አይደሉም፡፡ ከዉጪ ያሉት ናቸው የሚለወጡት፡፡ እግዚአብሔር መባረክ ጀመረው የውስጡ ሳይሆን የዉጩዉን ነውና እግዚአብሔር አምላክ ለዘልዓለም ስሙ የተመስገን ይሁን፡፡ ይህንን የሚመስል ብዙ የተንከራተተ ህይወት አሳልፍያለው፡፡ ዘፋኝ ብሆን እኮ እሸለም ነበረ፡፡ ሬድዮ ጣብያዉም፤ ቴሌቪዥኑም፤ ካድሬዉም ትልልቁም ትንንሹም ያጨበጭብልኝ ነበር፡፡ ግን እግዚአብሔር በተረገመበት፤ እግዚአብሔር የለም በተባለበት ሃገር ውስጥ እግዚአብሔር አለ የሚል ከሆነ፤ እግዚአብሔር ቅዱስ ነው የሚል ከሆነ አንተ እርኩስ ነህ የሚለው ነው የሚበዛውና እውነታው ይሄ ነው፡፡ ይሄን የሚመስል ሁኔታ ውስጥ ነው ያሳለፍነው፡፡ አልጋ በአልጋ የሆነ መንፈሳዊ ህይወት የለም፡፡ አልጋ በአልጋ የሚሆነው ለአርቲስቶች ብቻ ነው፡፡ እግዚአብሔር ማስተዋሉን ይስጠን፡፡

Thursday, February 25, 2016

ድንቅ ተዓምር በ ለጀት ኪዳነምህረት

ማክሰኞ 16/06/2008 ዓ.ም የመቤታችንን ክብረ በዓል ለማክበር ወደ ለጀት ኪዳነምህረት ሂጀ ሳለ ትልቅ ተዓምር አየሁ ። እግዚዐብሔር ይመስገን ደስ ይበላችሁ ። ስሟ ቃልኪዳን የምትባል ሰው ታማ ያልሄደችበት ሐኪም ፀበል የለም እና አሁን ሰልችቷት እቤቷ ዋድ አካባቢ ነበር ያለች። የህመሙ አይነት ከሆዷ ከጉልበቷ አካባቢ ሁሌ የሚቆርጣት ሳይታይ ደም ይፈሳት ነበር።የፈሰሰው/የተቆረጠው/ ለምጡ አሁንም አለ።ነገር ግን ዛሬ ታሪክ ተለወጠ ክብር ለናታችን ቅድስት ድንግል ማረያም።አንድ በፀበል የምታውቃት ጓደኛዋ ደውላ ዛሬ ኪዳነምህረት ንግሷ ስለሆነ ነይ አክብሪስትለት እሷም ከዋድ መጣች።መጥታ ታቦት እንደገባ ፀበል እንድትጠጣ በትንሽ ሀይላንድ ስጥተዋት ከቤተክርስትያን አጥር ወጥታ ስትጠጣ በትውኪያ 2/ሁለት/ምላጭ ወጥቶላታል። ክብርምስጋና ለአምላክ እናት።ስለ ታምሩማወቅ የሚፈልግ። 0911593144 ይደውሉ።በበለጠ መሔድ የሚችል እሁድ እቦታው ሒዶ ታምሩን ይስማ። ኦርቶዶስ ለዘላለም ትኑር

አንዲት እህት ከሆዷ ውስጥ ጥቁር ወፍ ወጣላት




የኪዳነ ምሕረት ተዓምር

የካቲት 16/2008 ዓም ኪዳነ ምሕረት በዓል ቀን አረብ አገር የምትኖር እህታችን የተደረገውን ተዓምር እንዲህ አቅርባዋላች:: ከሆዷ የወጣላት አውሬ ምስል ከነድምጹ አቅርባለች:: ድንቅ ስራውን ይመስከሩ::

የሸንኮራ ቅዱስ ዮሃንስ ወልደ ነጎድጓድ ጸበል ታምር 

 

Wednesday, February 24, 2016

መምሕር ግርማ ከአገልግሎት የታገዱበት ደብዳቤ

መምህር ግርማ ወንድሙ
ከ ላይፍ መጽሄት ጋር ያደረጉት ቃለ ምልልስ
የኤልያስ መንፈስ በኤልሳ እንዳደረ ሁሉ የፈለገው ሁሉ ያገኛል፡፡ እኔም የማስተምረው እኮ ክርስቲያኑ ራሱን ችሎ እንዲቆም ነው፡፡ እኔ ነገ የማልፍ ሰው ነኝ ዘላለም አልኖርም ግን ክርስትያኑ ጠላቱን እንዲጋፈጥ ፤ ክፉ መንፈስ እንዲያሸንፍ ፤ የዲያቢሎስ ትውልድ መሆኑ እንዲቆም ፤ ከዚያም በላይ የመንፈስ ቅዱስ ስራ የእግዚአብሔር ክብርና ኃይል እየጨመረ እንዲመጣ ፤ የአለም ጥበብ የእግዚአብሔር ልዩ አሰራር አውቀው ክርስቲያኖች በረከት ውስጥ እንዲገቡ ነው፡፡ ፍላጎቴ ግን እግዚአብሔር በተረገመበት፤ እግዚአብሔር የያድንም የለም በተባለበት ሃገር ውስጥ እግዚአብሔር አለ የሚል ከሆነ፤ እግዚአብሔር አዳኝ ቅዱስ ነው የሚል ከሆነ አንተ እርኩስ ነህ የሚለው ነው የሚበዛውና እውነታው ይሄ ነው፡፡ ይሄን የሚመስል ሁኔታ ውስጥ ነው ያሳለፍነው አሁንም እያሳለፍን ያለነው
ያደረጉት ቃለ ምልልስ..
ላይፍ፡- ሁላችሁም የእግዚአብሔር ቃል የእመቤታንን በረከት የምታስተምሩበት ቤተክርስቲያን ለምን እንዲህ አይነት መከፋፈል መጣ ብለው ያስባሉ ?
መምህር ግርማ፡- በመጽሀፍ ቅዱስ ውስጥ እንክርዳድ በስንዴው መሀል እንደሚዘራው ሁሉ ያም በቤተክርስቲያን ውስጥ አለ፡፡ ገበሬው መልካም ስንዴን ዘራ የሚለው ከውጭ አይደለም፡፡ ዘሩ እዚያው ቤተክርስቲያን ውስጥ ነው፡፡ ስለዚህ በቤተክርስቲያን መንፈሳዊ ህይወትና በልቦና ውስጥ መጀመርና በስጋ ህይወት መጀመር ልዩነት አለው፡፡ አምኖ መጀመርና ሳያምኑ መጀመር የእዚያን ያህል ነው፡፡ ሰሞኑን ወደ ቤተክርስቲያን ገብተው የሚኖሩ በጣም ብዙ ናቸው፡፡ እነዚህ ከተለያዩ የአስማት ስራ ጋር ወደ ቤተክርስቲያን ሲጠጉ ብዙ መልካም ነገር አይጠበቅባቸውምና ይህንን የሚመለከት ‹‹በማለዳ መያዝ›› የሚለው መጽሀፌ ላይ ሰፋ ባለ መልኩ አስቀምጬዋለሁ፡፡ ንጹህ የአምልኮት ፍላጎትና እንዲሁ ደግሞ በደብዛዛው በሚመላለሱ ሰዎች መካከል ዲያቦሎስ በደንብ ይሰራል፡፡ በተለይ ኦርቶዶክስ እምነት ላይ ሰይጣን ከፍተኛ ትኩረት ይሰጣል፡፡ ከታሪክ እውነታም አንጻር እነዚህ ሰዎች ህይወት ውስጥ የተለየ እድል አለ፡፡ ገብቶ ይቀመጥና በጎው መጥላት መልካሙን እንደክፉ ማየት ማሳደድ ያለው መናፍቆች ላይ ሳይሆን እኛ ጋር ነው ያለው፡፡ ይህ ደግሞ የሃይማኖቱ አንዱ በረከት ነው፡፡ ለምን ፈሪሳውያንን ክርስቶስ በመጣ ጊዜ እምነቱን ተራ ወግና ተራ የሆነ የይስሙላ አድርገውት ነበር፡፡ ያ ሂደት ደግሞ እንደዚሁ በቆየን ቁጥር የአዲስ ኪዳንንም ህይወት እንደዚያ ነው የሚሆነው፡፡ ወደ ፈሪሳውያን ጠላት ይሄዳል፡፡ በዚህ ጊዜ እውነቱ እየጠፋ በቤተክርስቲያን ውስጥ ጣልቃ ይገባሉና ያንን ለመለየት የመንፈስ ቅዱስ ስራም የአጋንንት የቅንነትም ስራ ስለሚያስፈልግ ዛሬ ያ ቅንነቱ እና በጎነቱ በክፋት በተንኮል በምቀኝነት የተሞላ ስለሆነ ያ ሂደት ሊያደርገን አልቻለም፡፡
ላይፍ፡- ብዙ ሰባኪያን ወደ እርስዎ ፕሮግራም የማይመጡት ለምንድነው?
መምህር ግርማ፡- ይህንን የፈውስ ሂደት ስላለመዱት ልክ እንደ መተት እንደ ጠንቋይ አሰራር አድርገው እስከዛሬ ድረስ ሲያወሩ እንደቆዩ ያው የተለመደ ነገር ነው፡፡ስላልተለመደ እንግዳ ነገር ነው የሆነው፡፡ በተለይ በግለሰብ ጸጋ አልተለመደም፡፡ ይህንን ያልተለመደ ነገር እንዲህ ሲወጣ ሁሉም እየተረባረበ ማጨለም ነው የሚፈልገው፡፡ የእግዚአብሔር ስራ ደግሞ ስለማይጨልም ሂደቱን ጠብቆ ይበራል፡፡ ከዚህም በፊትም የተደረጉብኝ ዘመቻዎች ብዙ ናቸው ይህ ብቻ አይደለም፡፡ ይህ እንዲያውም የመጨረሻው ደካማ ነው፡፡ ቤተክርስቲያን ሰዎች መንፈሳዊ አንድነታቸው በክፉ ሰዎች መንፈስ ተመቷል፡፡ በራስ እይታም ተመቷል፡፡ የምቀኝነት መንፈስ አጠናክረው በመያዛቸው ምክንያት የእግዚአብሔር ጸጋ በረከት መለያ መንፈስ አጥተዋል፡፡ አንድነትና ተስማምቶ መዝለቅን በዚህ ዘመን ውስጥ የምንጠብቀው ጉዳይ አይደለም፡፡ ግን እውነት ዞሮ ዞሮ ደረጃዋን ጠብቃ ስለምትወጣ ያን ያህል አስጊ አይደለም ማለቴ ነው፡፡
ላይፍ፡- እርስዎ አለኝ የሚሉት የፈውስ ጸጋ ከየት የመጣ ነው ይላሉ ?
መምህር ግርማ፡- ይህ እኮ አንድና ሁለት ነው እንደሚባለው አይነት ፎርሙላ ወጥ አድርገህ የምታሳየው ነገር አይደለም፡፡ ይህ በጸሎት በስግደት በቅዱስ ቁርባን በመመጽወት ከሰማይ የሚለቀቁት እንጂ ከማንኛውም ሰው የምትገዛው ወይም የምትለውጠው ትርፍ ያለው ነገር አይደለም፡፡ ይህ ከሰማይ የሚሰጥ እንጂ በስጋዊ ጥበብባ ዘዴ ወይም ምርምር ወደ ላብራቶሪ የሚመጣና የሚገኝ አይደለም፡፡ ምክንያቱም የእግዚአብሔር አሰራር ነው፡፡ የእግዚአብሔር አሰራር ደግሞ አለምም ሆነ ስጋውያን አያውቁትም፡፡ መንፈሳውያንም ተቸግረዋል፡፡
ለዛ ነው እምያሳድዱኝ በዚህ ዘመን ያሉ የገዛ አባቶቼ እንኳን ሳይቀሩ ይህንን መንፈሳዊ ጸጋ ለመቀበል በጣም ይቸገራሉ፡፡ ምክንያቱም ከእኛ በኩል ካፈሰሰ ነው እኮ አሁን ችግሩ፡፡ ከእኔ በኩል ካልፈሰሰ እንዴት በዚህ ዘመን ከእግዚአብሔር ይመጣል ፤ የሚል ዋጋ ቢስ እና ተስፋ አስቆራጭ የመንፈሳዊ ህይወት ጉዞን የለመዱት ባህሪ ለማንጸባረቅ ሲሞክሩ ነው አሁን ነገሮች ወደዚህ አይነት አጣብቂኝ ውስጥ የሚገቡት፡፡
ላይፍ፡- እርስዎ ተሰጥቶኛል የሚሉት የመንፈስ ጸጋ ስያሜ ሰጥተውታል ?
መምህር ግርማ፡- እንደዚህ ያለ ነገር የለም እንጂ ምን ስያሜ ይሰጠዋል ? ክፉ መናፍስን የሚቃወም የእግዚአብሔር መንፈስ ነው፡፡ የእግዚአብሔር መንፈስና ክፉ መንፈስ ደግሞ አይገናኙም፡፡ የእግዚአብሔር መንፈስ የእግዚአብሔር ስጦታ ነው፡፡ የእግዚአብሔር ስጦታ ደግሞ ክፉውን መለየት ፤ ክፉው ማስወገድ ነው፡፡ በመጽሀፍ ቅዱስ ውስጥ አጋንንትን አወጡ ይል የለም እንዴ? በአሁኑ ዘመን አጋንንት አስገቢ ቢባል ሁሉም ይወደኛል፡፡ አጋንንት ማስወጣት እኮ ነው የተለየ ጠንቋይ ያደረገኝ፡፡
ላይፍ፡-አለኝ የሚሉት የመንፈስ ጸጋ ወደ ሌላ ሰው ማስተላለፍ ይችላሉ ? ወይስ እርስዎ ጋር ነው ሊቀር የሚችለው ?
መምህር ግርማ፡- የኤልያስ መንፈስ በኤልሳ እንዳደረ ሁሉ የፈለገው ሁሉ ያገኛል፡፡ እኔም የማስተምረው እኮ ክርስቲያኑ ራሱን ችሎ እንዲቆም ነው፡፡ እኔ ነገ የማልፍ ሰው ነኝ ግን ክርስትያኑ ጠላቱን እንዲጋፈጥ ፤ ክፉ መንፈስ እንዲያሸንፍ ፤ የዲያቢሎስ ትውልድ መሆኑ እንዲቆም ፤ ከዚያም በላይ የመንፈስ ቅዱስ ስራ የእግዚአብሔር ክብርና ኃይል እየጨመረ እንዲመጣ ፤ የአለም ጥበብ ከእግዚአብሔር ልዩ አሰራር አውቀው ክርስቲያኖች በረከት ውስጥ እንዲገቡ ነው፡፡ ፍላጎቴ
ላይፍ፡- አባቶች እርስዎ የሚሰጡት መንፈሳዊ ጉባኤ ተገኝተው በረከት ይሰጡ ነበር ወይ ? መምህር ግርማ፡- እኔ በማገለግለው ላለመገኝት ብዙዎች ይሸሻሉ ተሰልፈው ዝቅ ብለው የህዝብን ችግር ለማየት እስከ አሁን በጎ ህሊና አላገኝሁም፡፡ እንደ አቡነ እስጢፋኖስ የጅማው ኃገረ ስብከት ሊቀ ጳጳስ አይነቱ በተደጋጋሚ የህዝቡን ችግር ተረድተው በተደጋጋሚ ወደዚያ እየሄድኩ ሳገለግል መንፈሳዊ ድጋፋቸውን ለህዝቡ ካለው ችግር ለልማቱም ከማሰብ ቢርሌ የሰጡት ቦታና ስራ አለ፡፡
ላይፍ፡- አባቶች እርስዎ የሚሰጡት መንፈሳዊ አገልግሎት አስተያየታቸው ምንድነው ? መምህር ግርማ፡- ብዙዎች ይህንን መንፈሳዊ ድርሻ ለመወጣት በማደርጋቸው ጥረቶች ላይ በጎ ድጋፍ የላቸውም፡፡ ከተለያዩ አይነት መንገድ ለመዳንም ይሰጣሉ፡፡ ነገር ግን አንዳዶች እንዲያውም የሸናሻም መተት ይህን ያደርጋል፡፡ የሸናሻም አስማት ይህንን ይሰራል እያሉ ለአስት አሰራር ትልቅ ድጋፍና የሰይጣን አሰራር ትልቅ ሞራል ሲሰጡ ነው የሚሰማው፡፡
ላይፍ፡- ይህንን እርስዎ የሚያደርጉትን መንፈሳዊ አገልግሎት ሌሎች አባቶች ያምኑበታል ?
መምህር ግርማ፡- እኔም በጣም ግራ የሚገባኝ ዲያቢሎስ የሚያደርገው ጥቃት በመጽሀፍ ቅዱስ በረጅሙ እና በስፋት ጥልቀት ባለው ሁኔታ ገልጿል፡፡ ሐዋርያት አጋንንትን እያወጡ የሰዎችን ደህንነት ሲያበለጽጉ ይታያል፡፡ በቤተክርስያንም እደዚሁ በመንፈሳዊ አገልግሎት በመንፈስ ቅዱስ ስራ እንደሚሰራ ይታወቃል፡፡ እንግዲህ ሰዎች በክፉ መንፈስ አሰራር ወይም አያምኑም አልያም በእግዚአብሔር አሰራር አያምኑም፡፡ ይናገሩታል ያስተምሩታል ግን ይህው እግዚአብሔር አዳነ ሲባል ግን አያምኑትም በዚህ መንታ መንገድ ላይ መታየት አሁን አይቻልም፡፡ ምክንያም የእግዚአብሔር ሕዝብ በዲያቢሎስ ተጠቅቷል፡፡ ወይ ዲያቢሎስ እንዲበላ ማድረግ ነው አልያም በቤተክርስቲያን መንፈስና ጸጋ ህዝቡ ችግር ውስጥ ገብቶ ችግሩን ማየት ነው፡፡ ገለልተኛ ሆኖ መኖር አሁን አሁን ጊዜው አይደለም፡፡ ስለዚህ ያምናሉ አያምኑም የሚለው ነገር እርሳው እኔን ቢረዱኝ ደስ ባለኝ፡፡ በተሰጣቸው ጸጋ ክፉ መንፈስ ነው ካሉ የእኔን መንፈስ ማወጣት መቻል፡፡ ሁሉም ቢተባበሩኝ መልእክት አስላልፋለሁ ፡፡ እንዲያውም በቤተክርስቲያን ይኖር የነበረ አስማተኛ መንፈሱን አስወጣንለት ብለው ለአለም ዜና ቢያቀርቡ ደስ ባለኝ ነበር፡፡
ላይፍ፡- ቤተክርስቲያኗ ወታደርና ነጋዴ የቤተክርስቲያን አገልጋይ አይሆንም የሚል ሕገ ደንብ አላት፡፡ እርስዎ ግን መንፈሳዊ ሕይወት ውስጥ ከመግባትዎ በፊት ወታደር እንደነበሩናይውራል ስለዚህ ምን ይላሉ ?
መምህር ግርማ፡-ዛሬ ሰማዕቱ ሀገር ጠባቂ የምንለው ቅዱስ ጊዮርጊስም የመቶ አለቃ ወታደር ነበር፡፡ ግብጽ ውስጥ ያሉ ብዙ ታላላቅ አባቶችም እንደዚያው ናቸው፡፡ በአሁንም ዘመን ያሉ ብዙ መነኮሳቱ እስከ ጳጳሳቱ ወታደር የነበሩ ናቸው፡፡ ወታደር ማለት የእግዚአብሔርን ስራ አይሰራም ማለት አይደለም ፡፡ እኔ ደግሞ ልቀድስ ላቁርብ አላላኩም ፤ በተሰጠኝ ጸጋ ላገልግል ነው ያልኩት፡፡ ይህንን እንደ አንድ እንደ ትልቅ ነገር ማንሳት በራሱ ምንን ያመለክታል ፤ ምቀኝነትን ነው ፤ ያው ከደማችን ውስጥ የተለመደ ምቀኝነት ስላለ እንጂ ከነዚህ ሁኔታዎች በሙሉ የእግዚአብሔር ስራ እንዳይሰራ የሚያደርጉት አይደለ። ፡፡ ዘፋኝ ብሆን እኮ እሸለም ነበረ፡፡ ሬድዮ ጣብያዉም፤ ቴሌቪዥኑም፤ ካድሬዉም ትልልቁም ትንንሹም ያጨበጭብልኝ ነበር፡፡ ግን እግዚአብሔር በተረገመበት፤ እግዚአብሔር የያድንም የለም በተባለበት ሃገር ውስጥ እግዚአብሔር አለ የሚል ከሆነ፤ እግዚአብሔር አዳኝ ቅዱስ ነው የሚል ከሆነ አንተ እርኩስ ነህ የሚለው ነው የሚበዛውና እውነታው ይሄ ነው፡፡ ይሄን የሚመስል ሁኔታ ውስጥ ነው ያሳለፍነው፡፡ አልጋ በአልጋ የሆነ መንፈሳዊ ህይወት የለም፡፡ አልጋ በአልጋ የሚሆነው ለአርቲስቶች ብቻ ነው፡፡
ላይፍ፡- እርስዎን አስማተኛ እና ጠንቋይ ናቸው የሚሉዎት ሰዎች ምላሽ ምንድነው ?
መምህር ግርማ፡- እኔ አስማተኛ ከሆንኩ እኔ ጋር መጥተው አስማቱን ማውጣት ነው፡፡ እኔ ጋር መጥተው አስማቴ የት ጋር እንደተቀበረ ፈልገው ማውጣት ነው፡፡ ክንዴ ላይ ወይም እግሬ ላይ ወይም ጭንቅላቴ ላይ እንዳለ ደንበኛ ራጅ ይዘው መጥተው ፈልገው ማውጣት፡፡ ወይም መንፈስ ከሆነ ያስወጡልኝ፡፡ ቢረዱኝ እኮ ለእኔም ደስ ይለኛል፡፡ ግልግል ነበር፡፡ እስቲ አስማቴን ኑ እና አስወጡልኝ እባካችሁ ስለ እግዚአብሔር ስለ ቅድስት ድንግል ማርያም ብዬ እለምናችኋለሁ፡፡እንኳን እኔ ይልቅ እና እኔ ባስተማርኩት መስረት እንኳን ብዙዎች ሲፀልዩ ጎደኞቻችው እየራቅዋቸው እንደሆነ ይነግሩኛል 2ተኛው የመምህር ግርማ አስማተኛ የሚባል ቅፅል ስም ይሰጣቸዋል ለምን የመንፍስ አንድነት የላቸውም እርኩሱ ከ ቅዱሱ እንደማይስማማው ሁሉ መባረክ ስትጀምር ለእግዚአብሔር መንበርከክ ስትጀምር ለማይንበረከኩት በቃል ብቻ ለሚኖሩት እራስ ምታት ትሆንባቸዋለህ ይሄ ነው እውነታው!





ኢትዮጵያዊ 350 ሺህ ብር ከኦስትሪያ ለወደቁትን አንሱ የአረጋውያንና የአእምሮ መርጃ ማዕከል ድጋፍ አደረጉ! ድጋፍ ያደረጉት መንበረ አብርሃም የተሰኙ ኢትዮጵያዊ ከኦስትሪያ ሲሆን ከዚህ ቀደም መምህር ግርማ ወንድሙ ለበጎ አድራጎት ድርጅት ድጋፍ ያደረጉትን ፕሮግራም ከተመለከቱ በሆላ እንዲሁም በአባታችን አስተባባሪነት የአባታችን የወንጌል ተማሪ የሆነችው በተወካያቸው በአቶ ታሪኩ ተገኝ አማካይነት ተናግረዋል፡፡ በዚህም አማካይነት 350ሺህ ብር የሚያወጣ ዘመናዊ 65 አልጋዎችን ከነሙሉ ፍራሾች ለአረጋውያኑ ተወካይ በዛሬው ዕለት አስረክበዋል!






ዝቅ ብሎ መምሕር ግርማ ወደ አገልግሎት የተመለሱበት ደብዳቤ ይታያል:: በቅርብ ግን ይህ አገልግሎታቸው በ አባ ማቲያስ 30-06-2008 የተጻፈ የ እገዳ ደብዳቤ እንደሚከተለው ነው::




መምሕር ግርማ ወደ አገልግሎት የተመለሱበት ደብዳቤ

መምህር ግርማ ወንድሙ በደርሰባቸው ክስ ምክኒያት አገልግሎት ተቋርጦ እንደነበር የሚታወስ ነው:: መምህር ግርማ በወስ ጥቅምት 30/2008 ከተለቀቁ በኃላ የካቲት 9/2008 ከ ከደቡብ ም እራብ ሸዋ ሀገረ ስክበት የሥራ ምደባ ተደርጎላቸዋል:: በዚህም ምክኒያት የካቲት 19/20 በ ጀሞ ቅዱስ ኡራኤል ቤተክርስቲያን አገልግሎት ይሰጣሉ::

ጥቅምት 30 ፣ 2008 ከደቡብ ምእራብ ሸዋ ሀገረ ስብከት የካቲት 9/2008 የተጻፈላቸው ደብዳቤ እንደሚያሳየው ወደ አገልግሎት ተመልሰዋል::

Wednesday, February 10, 2016

በንብና ነብር የምትጠበቀው ሥዕለ ማርያም “ወይኑት”

ኅዳር 10 ቀን 2006 ዓ.ም. 
በእንዳለ ደምስስ

ከኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን ታላላቅ ገዳማት መካከከል በምሥራቅ ጎጃም ሀገረ ስብከት ውስጥ የሚገኙት የመርጡለ ማርያም እና ደብረ ወርቅ ገዳማት በግንባር ቀደምትነት ይጠቀሳሉ፡፡ ሁለቱም ገዳማት ጥንት መሥዋዕተ ኦሪት ይከናወንባቸው የነበረና ታላላቅ ታሪካዊ ቅርሶችንም ለትውልድ በማስተላለፍ ረገድ ትልቁን ድርሻ ከያዙት ቅዱሳት መካናት መካከል ይመደባሉ፡፡

መስከረም 29 ቀን 2006 ዓ.ም. በምሥራቅ ጎጃም ሀገረ ስብከት ሊቀ ጳጳስ አቡነ ማርቆስ ጥሪ መሠረት በብፁዕ ወቅዱስ አቡነ ማትያስ ፓትርያርክ ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት ዘኢትዮጵያ ሊቀ ጳጳስ ዘአክሱም ወእጨጌ ዘመንበረ ተክለ ሃይማኖት የሚመራና ብፁዓን አበው ሊቃነ ጳጳሳት የሚገኙበት የልዑካን ቡድን መርጡለ ማርያም ገዳም አዲስ ለሚሠራው ሕንፃ ቤተ ክርስቲያን የመሠረት ድንጋይ ለማኖር፤ እንዲሁም በደብረ ወርቅ ማርያም ገዳም የተገነባውን መንበረ ጵጵስና ለመመረቅና ለዘመናዊ ትምህርት ቤት ግንባታ የመሠረት ድንጋይ ለማኖር ከሄደው ልዑክ ጋር ተጉዣለሁ፡፡
በመርጡለ ማርያም ገዳም የነበረን ቆይታ አጭር በመሆኑ መረጃዎችን ለማሰባበሰብ የጊዜ እጥረት ስላጋጠመኝ አልተሳካልኝም፡፡ በደብረ ወርቅ ገዳም ቆይታዬ ከቋጠርኳቸው መረጃዎች መካከል ቅዱስ ሉቃስ ከሣላቸውና ኢትዮጵያ ውስጥ ከሚገኙት ቅዱሳት ሥዕላት መካከል በንብና ነብር የምትጠበቀው ሥዕለ ማርያም /ምስለ ፍቁር ወልዳ/ “ወይኑት” ስለተሰኘችው ሥዕል ጥቂት ላካፍላችሁ፡፡ ደብረ ወርቅ ማርያም ገዳምን ላስቀድም፡፡

ደብረ ወርቅ ማርያም ገዳም
ደብረ ወርቅ ማርያም ገዳም በምሥራቅ ጎጃም ሀገረ ስብከት በእናርጅና እናውጋ ወረዳ ከአዲስ አበባ 290 ኪሎ ሜትር ርቀት ላይ ትገኛለች፡፡ የኦሪት መሥዋዕት ሲሰዋባቸው ከቆዩት ቅዱሳት መካናት አንዷ ናት፡፡ በተለይም ከ250-351 ዓ.ም. መሥዋዕተ ኦሪት ሲሰዋባት እንደቆየች የጽሑፍ መረጃዎች ያመለክታሉ፡፡

የጎጃም አፈ ጉባኤ በነበረው ምሑረ ኦሪት ያዕቆብ አማካይነት መሥዋዕተ ኦሪት ሲሰዋባት የቆየ መሆኑን በገዳሟ የሚገኙ የኦሪት ሥርዓት ማከናወኛ የነበሩ እንደ መቅረዝ፤ ስንና ብርት የመሳሰሉ ቅርሶች ከመመስከራቸውም በላይ በገዳሟ ውስጥ የሚገኘው የቤተ ክርስቲያኗ የታሪክ መዝገብ ያስረዳል፡፡

weyenuteእመቤታችን ቅድስት ድንግል ማርያም ከልጇ ከወዳጇ ጋር ወደ ምድረ ግብፅ ስትሰደድ ካረፈችባቸው ቅዱሳት መካናት መካከል አንዷ ደብረ ወርቅ መሆኗንም በድርሳነ ኡራኤል ላይ ተጽፎ ይገኛል፡፡ በ4ኛው መቶ ክፍለ ዘመን በኢትዮጵያ የነገሡት ወንድማማቾቹ አብርሃና አጽብሃ ክርስትናን እያስፋፉ ከቦታ ቦታ ይዘዋወሩ በነበረበት ወቅት መርጡለ ማርያምን አቅንተው ክርስትናን መሥርተው ወደ ደብረ ወርቅ በመምጣት ከምሁረ ኦሪት ያዕቆብ ጋር ተገናኝተዋል፡፡ ያዕቆብን ክርስትናን አስተምረው የአዲስ ኪዳን ሥርዓትን በመመሥረት “ያዕቆብ ኤጲስ ቆጶስ ዘኢየሩሳሌም ደብረ ወርቅ” ብለው ሾመውታል፡፡

አብርሃና አጽብሃ ደብረ ወርቅ ላይ ቤተ ክርስቲያን ሳይሠሩ ዐረፍተ ሞት ስለገታቸው በእግራቸው የተተካው ዐፄ አስፍሐ ያልዝ በ351 ዓ.ም. ወደ ደብረ ወርቅ በመምጣት ቤተ ክርስቲያኗን አሰርቷል፡፡ የደብረ ወርቅ ማርያም ገዳም በዮዲት ጉዲት በመቃጠሏ በ1372 ዓ.ም. በዐፄ ዳዊት የገንዘብ ድጋፍ አባ ሰርፀ ጴጥሮስ በተባሉ አባት አማካይነት በድጋሚ ተሠርታለች፡፡ ከጊዜ በኋላም ቤተ መቅደሷን ዐፄ ገላውዴዎስ በኖራና ድንጋይ ሲያሠሯት፤ ቅኔ ማኅሌቷ ደግሞ በስክ እንጨት ካለምንም ምሥማር በዐፄ ተክለ ጊዮርጊስ ተሠርታለች፤ በ1963 ዓ.ም. ዐፄ ኃይለ ሥላሴም አሳድሰዋታል፡፡

ቤተ ክርስቲያኗ 44 ቆመብዕሴ/አምድ/፤ የውጪና የውስጥ 11 በሮች፤ 36 መስኮቶች ሲኖሯት የግድግዳ ላይ ሥዕሎቹ ዐፄ ዮስጦስ /1704 ዓ.ም./፤ 1873 ዓ.ም. የንጉሥ ተክለ ሃይማኖት ልጅ የሆኑት ራስ ኃይሉ አስለውታል፡፡ በቤተ ክርስቲያኗ ዘመናዊ ሙዚየም ውስጥ በርካታ ታሪካዊና ጥንታዊ ቅርሶችም ይገኛሉ፡፡

“ወይኑት” ቅዱስ ሉቃስ የሣላት ሥዕለ ማርያም
ዐፄ ዳዊት ጌታችን መድኀኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ከተሰቀለበት መስቀል ጋር ወደ ኢትዮጵያ ካመጧቸው የቅዱስ ሉቃስ ሥዕላት መካከል “ወይኑት” የተሠነችው ሥዕል አንዷ ስትሆን ዐፄ ዘርዓweyenute 2 ያዕቆብ ለደብረ ወርቅ ማርያም ገዳም አበርክተዋል፡፡ እስከ ዛሬ ድረስም ተጠብቃ ትገኛለች፡፡ በ1660ዎቹ ዓ.ም. በዐፄ አእላፍ ሰገድ /ፃድቁ ዮሐንስ/ ለወይኑት ማስቀመጫ እቃ ቤት ይሆን ዘንድ ባለ ሁለት ፎቅ ሕንፃ በድንጋይና በኖራ በማስገንባት ጣሪያውን የሣር ክዳን በማልበስ አሠርተውላታል፡፡ ፎቁ ላይ ትናንሽ 8 መስኮቶችም ይገኛሉ፡፡

ሥዕለ ሉቃስ “ወይኑት”ን የሚጠብቁ ነጫጭ ንቦች የሚገኙ ሲሆን ጥቋቁር ንቦቹ ደግሞ ከመስኮቶቹ እየወጡና እየገቡ መመልከት የተለመደ ነው፡፡ ንቦቹ ከሕንፃው መሠራት ጋር እንደገቡ የሚነገር ሲሆን ማሩ እስካሁንም ተቆርጦ አያውቅም፡፡ ወይኑት በዓመት ለሦስት ጊዜያት ሕዝቡን ለመባረክ ወደ ቤተ መቅደስ ትወሰዳለች፡፡ መስከረም 21፤ ጥር 21 እና ነሐሴ 16፡፡ ሥዕሏ ወደ ቤተ መቅደስ ሥትወሰድ ንቦቹ አጅበዋት የሚሄዱ ሲሆን ስትመለስም አብረዋት ይመለሳሉ፡፡ ንቦቹ ሕዝቡን የማይተናኮሉ እንደመሆናቸው በተንኮል ወይም ለሥርቆት የመጣ ሰው ካለ ግን እየነደፉ እንደሚያባርሩ ከዚህ በፊት ከተደረጉት ገቢረ ተዓምራት በመነሳት ይገለጻል፡፡

ወይኑትን የሚጠብቁ ከንቦቹ በተጨማሪ ነብሮችም በሕንፃው ጣሪያ ላይ ይገኛሉ፡፡ ቀን እዚያው ተኝተው የሚውሉ ሲሆን ምሽት ላይ ምግብ ፍለጋ እንደሚወጡ ይነገራል፡፡ በአካባቢው የሚገኙ በጎች ወደ ቤተ ክርስቲያኗ ቅጥር ከገቡ ከነብሮቹ ጋር እንደሚጫወቱና እንደማይተናኮሏቸው የዓይን እማኞች ያስረዳሉ፡፡

የዐፄ ዮሐንስ 4ኛ ወታደር ሥዕለ ሉቃስ /ወይኑትን/ ለመሥረቅ ሞክሮ ንቦቹ ነድፈው እንዳባረሩት፤ እንዲሁም ዐፄ ዮሐንስ ከደርቡሽ ጋር ባደረጉት ጦርነት ሥዕለ ማርያምን /ወይኑት/ ይዘው ለመዝመት ባደረጉት ጥረት ንቦቹ ወታደሮቻቸውን- በመንደፍ አስጥለዋታል፡፡ የእግዚአብሔር ፈቃድ እንዳልሆነ የተረዱት ዐፄ ዮሐንስ ሥዕሏን ወደነበረችበት መልሰው እንደዘመቱ የቤተ ክርስቲያኗ የታሪክ መዝገብ ያስረዳል፡፡ የፋሺስት ኢጣሊያ ጦር ኢትዮጵያን በወረረበት ወቅት የደብረ ወርቅ ማርያም ገዳምን ለመዝረፍ ዕቃ ቤቱን ሰብረው ለመግባት ያደረጉት ጥረት እንዳይሳካ በማድረግ ጠባቂ ንቦቹ ወታደሮቹን በመንደፍ እንዳባረሯቸው መረጃዎች ያመለክታሉ፡፡ 

ይቆየን

Friday, February 5, 2016

Monday, January 4, 2016

ፃድቃኔ ማርያም - ድንቅ ተአምር

ዛሬ ፃድቃኔ ማርያም ሄጄ በአይኔ ያየሁትን ተአምር ልፅፍላችሁ ወደድኩኝ፡፡ ቀኑ ቅዳሜ ነው ፤ ሰዎች አብዛኛውን ጊዜ ወደ ፃድቃኔ ለመሄድ የሚነሱበት ቀን ስለሆነ መጀመሪያ የሚወጣው አውቶቡስ እንዳያመልጠን ከባለቤቴ ጋር በጠዋት ነበር አውቶቡስ ተራ የደረስነው ፤ ነገር ግን ሰው እዛ ያደረ ይመስል 12፡00 ላይ አውቶቡሱ ሞልቶ መንቀሳቀስ ጀምሮ ነበር፡፡ ባለቤቴም ‹‹አይ በዚህም ሰዓት ደርሰን አመለጠን ይገርማል ተወው ባክህ እመቤቴ እንደፈቀደች›› አለችኝና ሁለተኛው አውቶቡስ ላይ ገባን፡፡ ይህኛው ደግሞ ቀጥታ ዘላቂ ሰው ስላጣ የመንገድ ሰዎችንም በመጫን ነበር የሞላው፡፡ ጉዞ ወደ ፃድቃኔ ማርያም ፤ ውዳሴዋን ደግመን ጉዞ ጀመርን፡፡ መኪናው ሲያወርድ ፤ ሲጭን 9፡00 አካባቢ ደብረ ምጥማቅ ደረስን ፤ እዚህ እንውረድና በአቋራጭ እንሂድ ተባብለን ሰላ ድንጋይ ሳንደርስ ወረድን ፡፡ እቃችንን ለአንድ የሀገሬው ሰው አሸክመን አቋራጩን ተያያዝነው ፡፡ ልጁ እንዲህ አለን ‹‹ ዛሬ ግን ማደሪያ የምታገኙ አይመስለኝም በጣም ብዙ ሰው ነው የመጣው አለን›› :: ‹‹ችግር የለውም ውጪ አንጥፈን እናርፋለን ለመተኛት መች መጣን›› አልነው፡፡

ደጇን ስንረግጥ ልጁ ያለው አልቀረ የወንዶች ማረፊያ ሁለቱም አዳራሽ ከአፍ እስከ ገደቡ ሞልቷል ፤ በረንዳውን ላይ ብናይ የበረንዳው ይብሳል ፡፡ የኔን ማረፊያ ውጭ አነንጠፍንና የእሷን ለማየት ወደ ሴቶች ማረፊያ እያቀናን ሳለ ፤ አንዲት መንፈስ ያደረባት ሴት ፤ እጇም እግሯም በሰንሰለት ታስራ እንዲ እያለች የእመቤታችንን ማዳን ትመሰክራለች ‹‹ ዛሬ ደግሞ ኪዳነምህረት ድንቅ ነገር ሰርታለች ሂዱነና እዩ›› እያለች ለሰዎች ስትናገር እንደ አጋጣሚ እኔም ሰማሁ፡፡ እሷ የጠቆመችን ቦታ ላይ ስንሄድ አንዲት የ12 ዓመት ህፃን ልጅ እና እህትየዋ አንድ ላይ ቆመው ተመለከትን ፡፡ ጠጋ ብለን ምን ተደርጎላቸው ነው ስል ስጠይቅ ‹‹ የዚች ህፃን አይኗ በራላት›› ሲሉ ነገሩን፡፡ ለኔ የተደረገልኝን ያህል ደነገጥኩኝ፤ በጣምም ደስ አኘኝ፡፡ እህትየዋ የምትይዘውን የምትጨብጠውን ነገር አጥታ ነበር ፡፡ ታናሽ እህቷ የተደረገላትን ነገር እያየች ከአእምሮዋ በላይ ስለሆነ እና ደስታው ፈንቅሏት ታለቅሳለች ፤ እኛም ገርሞን ማደሪያችንን ትተን ልጅቷ ጋር ረዥም ደቂቃዎች ስለሁኔታ ለመስማት እዛው አረፍ አልን ፡፡ እህትየዋም ሰዎች ጥያቄዎችን ሲጠይቋት እንዲህ አለች ፡-

‹‹ ቤት ውስጥ ከእኩያዎቿ ጋር ስትጫወት የበረንዳ ብረት አይኗን መታት ፤ ለጊዜው ከማበጥ ውጪ ምንም አልሆነም ነበር ፤ ነገር ግን በጊዜ ሂደት አይኗ እያበጠ መጣ ፤ እይታዋንም ጋረዳት ፤ ትምህርቷንም አቋርጣ ለ6ወር ያህል ህክምና ፍለጋ አሉ የተባሉ የአይን ስፔሻሊስቶች ጋር ብራችንን አውጥተን ሄድን ፤ መፍትሄ ግን ሊመጣ የልጅቷም አይን ማየት ግን አልቻለም ፤ ቤተሰባችን ጭንቅ ውስጥ ገባ ፤ በመጨረሻ እመቤቴ እንዳደረገች ታድርጋት ብይ እዚህ ይዣት መጣሁ ዛሬ ሶስተኛ ቀናችን ነው ፤ ለሶስት ቀን ያህል ፤ ጠዋት ተሸክሜአት ጸበል እወስዳታለሁ ፤ እምነቱን ከፀበል ጋር ደባልቄ አይኗ ዙሪያው ላይ እቀባታለሁ ፤ ይህው እናንተ እንደምታዩት እግዚአብሄር ፈቅዶ ዛሬ አይኗ ሊያይ ችሏል›› ብላ ለቅሶ፡፡

‹‹ሁሉን የምትገዛ ጌታ አምላክ ሆይ፥ ሥራህ ታላቅና ድንቅ ነው›› ዮሀንስ ራዕይ 15 3-4 ፤ ‹‹ይህች ከእግዚአብሔር ዘንድ ሆነች፥ ለዓይናችንም ድንቅ ናት።›› መዝሙረ ዳዊት118፥23 ከማለት ውጪ ሌላ ምን ይባላል፡፡አምኖ የመጣ እንዲህ ይደረግለታል ፤ ብዙዎቻችን ግን እግዚአብሔር ቤት ስንሄድ በሁለት ልብ ሆነን ነው ፤ ስንመለስም ከሁለት ያጣ የምንሆነው ለዚህ ይመስለኛል፡፡
ያየነውን ነገር ማመን እስኪያቅተን ድረስ እየተገረምን ማረፊያ ፍለጋ ስንንቀሳቀስ ሰዎች ተሰብስበው አየን ፡፡ ሁሌ ማታ 11፡00 ላይ በወንዶች ማረፊያ አካባቢ እና በሴቶች ማረፊያ አካባቢ አዲስ ለመጡ ሰዎች የቦታውን ስርዓት ፤ ምን እንደሚደረግ ፤ ምንስ እንደማይደረግ አባቶች ለ30 ደቂቃ ያህል ያስረዳሉ፡፡ ጠጋ ስንል ተረኛው አባት እንዲህ ሲሉ ነገሩን፡-

‹‹ ይህውላችሁ ልጆች ሀገር አቋርጣችሁ ከተለያየ ቦታ እዚ የመጣችሁት እናንተ ፈልጋችሁ ብቻ አይደለም ፤ እግዚአብሔርም ፈቅዶላችሁ ጭምር ነው፡፡ ስለዚህ እሱ ፈቅዶ እና ወዶ እስካመጣችሁ ድረስ የመጣችሁበትን አላማ የሚያስተጓጉል አንዳች ነገር ማድረግ የለባችሁም ፤ ይህ ቦታ የምህላ ፤ የፀሎት ፤ የሱባኤ ቦታ ነው ፤ እዚህ ቦታ ላይ ከእናንተ የሚጠበቅባችሁ ነገር አለ እርሱም ፡- ወደ ገዳም ስትወርዱ ጫማችሁን አድርጋችሁ መግባት አይቻልም ፤ ሴቶችም ወንዶችም በገዳም ውስጥ ስትመላለሱ ክርስትያናዊ አለባበስ መልበስ አለባችሁ ፤ በማደሪያችሁም ሆነ ገዳም ስትወርዱ ጮክ ብሎ መነጋገር አይቻልም ፤ ብዙ ሰዎች አርምሞ ስለሚይዙ እነሱንም መረበሽ ስለሆነ ይህ አጥብቆ የተከለከለ ነው ፤ የቻለ በቀን ሰባት ጊዜ ፀሎት ማድረስ አለበት፤ ካልቻለህ ግን ሶስቱን ጸሎት ማስተጓጎል የለበትም ፤ ከሰኞ እስከ አርብ ድረስ በሽተኛ ካልሆነ በቀር ምግብ 12 ሰዓት ላይ ነው መብላት የሚቻለው እስከዚያ ሁሌ ጾም ነው(ከበዓለ 50 በቀረ) ፤ የተፈቀዱት ምግቦች ቆሎ ፤ባቄላ ፤ ጥጥሬዎች እና በሶ ከሰኞ እስከ አርብ ሲሆን ቅዳሜ እና እሁድ ዳቦ መብላት ይፈቀዳል ፤ እንጀራ እና ወጥ ገዳም ውስጥ ባላችሁበት ጊዜ መብላት አይቻልም ፤ ጸበል ጠዋ በ11 ይከፈታል ከዚያ በፊት ጸበል መውረድ አይቻልም እስከ ሰባትም ስንትም ሰዓት ይቆያል ፤ እዚህ ቦታ ላይ በዓመት 1ጊዜ ብቻ ነው ቅዳሴ ያለው ፤ ጠዋት ሊነጋ ሲል 11 ሰዓት ላይ ኪዳን ማድረስ ፤ ሲነጋ ትምህርተ ወንጌል መሳተፍ ፤ከ ሰዓት ከ9፡40 ጀምሮ ምህላ ማድረስ አለባችሁ የዛኔ ነው የመጣችሁበትን አላማ እና እናንተ የምትገናኙት ›› እያሉ ብዙ ነገር ነገሩን መከሩን፡፡

እኛ እንኳን ለ3 ቀን ነው የመጣነው ገዳም ውስጥ የሚኖሩ መነኮሳት ይህን ሁሉ ችለው ነው የሚኖሩት? ይገርማል ፤ እግዚአብሔርም አለምን ትተው እሱን ብለው የመጡትን ያስችላቸዋል:: በመጨረሻም ፀሎት አድርገውልን ወደ ማደሪያችን ሸኙን፡፡ ይህን ስመለከት ብዙ ቦታዎች ስንሄድ የቦታውን ስርዓት ሳናውቅ የምናጠፋ ሰዎች እንበዛለን ፤ ልክ እንደ ፃድቃኔ ማርያም ገዳም ቀን በቀን ሳይሰለቹ እንደዚህ አይነት ነገሮች ሁሉም ቦታ ቢለመድ ጥሩ የሚል ሀሳብ አለኝ፡፡

የሚቀጥለው ቀን ጠዋት
ለሊት ኪዳን አድርሰን ወረፋው እንዳይበዛ ፀበል ወረድን ፤ ፀበል ተጠምቀን ስናበቃ ለመጠጣት አንዱ ልጅ ጋር ጠጋ ብዬ ቁጭ አልኩ ፤ ጎንበስ ብዬ ሳየው አንዳች ነገር ጉልበቱ ላይ ትልቅ እጢ ቋጥሮ ተመለከትኩኝ ፤‹‹ወንድሜ ምን ሆነህ ነው›› አልኩት፡፡ እሱም ‹‹ ተወኝ ባክህ ልቤ ደንድኖ አልሰማ ብዬ ነው እንዲ የሆንኩት አለኝ››፡፡ አልገባኝም አልኩት ‹‹ሰው ንስሀ ገብቶ ወደ በፊቱ ምግባሩ ከተመለሰ የባሰውን ነው የሚሸከመው አለኝ›› ይባስ ግራ አጋባኝ፡፡ ቀስ ብለህ ልታስረዳኝ ትችላለህ አልኩት፡፡ እርሱም፡-
‹‹ ትውልዴ አዲስ አበባ ነው የ22 አካባቢ ልጅ ነኝ ፡፡ይህውልህ የዛሬ 2 ዓመት በፊት እጠጣለሁ ፤አጨሳለሁ ፤ እጨፍራለሁ ብቻ ምንም ከሀጢያት የቀረኝ ነገር የለም ሁሉን አደርጋለሁ ፡፡ በዚህ ሁኔታ ላይ ሳለሁ የዚያን ጊዜ ጉልበቴ ላይ ከዚህ በፊት ሆኖ በማያውቅ በልክ ትልቅ እጢ ወጣብኝ ፤ ብዙ ቦታ ብሄድ ኦፕራሲዮን መሆንን ነበር እንደ መፍትሄ ያስቀመጡልኝ ፤ እሱን ደግሞ እኔ አልፈልገውም ፡፡ እናቴ እስኪ ፃድቃኔ ሂድ አለችኝ ፤ ‹‹ምን ማለትሽ ነው ዶክተሮች ኦፕራሲዮን እያሉ እዛ ምን ልሰራ ነው የምሄደው›› ብዬ ከእሷ ጋር ተጣላን ፤ ውዬ አድሬ ሳስበው መሄድ እንዳለብኝ ውስጤ ነገረኝ ፡፡ ከአዲስ አበባ ተነስቼ በሶ እና ቆሎ ብቻ በመያዘ ቀጥታ እዚህ ቦታ መጣሁ ፤ አንድን አባት አግኝቼ ችግሬን ስነግራቸው በደንብ አደመጡኝና ‹‹በል አሁን ጸበል እንዳትጀምር ፤ ንስሀ ግባ፤ ቀኖናህን ስትጨርስ መጠመቅ ትችላለህ›› አሉኝ፡፡ እሺ ብዬ ንስሀዬን ከራሴ ላይ አወረድኩኝ ፤ ቀኖናዬን ጨረስኩ ፤ከዚያ ጸበል መጠመቅ ስጀምር ሰዎች እምነት ሲቀቡ ተመለከትኩኝ ፤ ለምን እኔስ አልቀባም ብዬ ጸበሉን ከእምነት ጋር እየደባለኩ ቁስሉን መቀባት በጀመርኩኝ በሶስተኛው ቀን ተሸክሜ የመጣሁትን እጢ በመግል መልክ ከሰውነቴ ወጥቶ አለቀ ፤ ተሸሎኝ ወደቤቴ ስመለስ እማዬ ስታየኝ ማመን አልቻለችም ነበር ፤ አለቀሰች ፤ እመቤቴን ወላዲተ አምላክን ማመስገኛ ቃላት አጣች ፤ እኔም ለአንድ ዓመት ያህል ከቤተክርስትያን አልራኩም ነበር ፡፡ የሆነ ጊዜ ላይ ግን ከቤቱ ጠፋሁ ፤ ወደ ቀደመ ምግባሬ ቀስ እያልኩ ገባሁበት ፤ የተደረገልኝን ነገር ዘነጋሁ ፤ ይህው አሁን ደግሜ የዛሬ ሁለት ዓመት ይዥው የመጣሁትን እጢ አሁን ተመልሶ መጣብኝ ›› ብሎ ሲነግረኝ ሰውነቴን አንዳች ነገር አራደኝ፡፡

ስንቶቻችን ነን ገብተን የወጣን ፤ ውለታውን የዘነጋን ፤ የተደረገልንን ነገር የረሳን ፤ ከሞት አፋፍ ከጠላት ወጥመድ ጠብቆ አሳልፎን ዛሬ ላይ ከቤቱ ሸርተት ያልን? ቤት ይቁጠረው ፡፡ እኔ አይኔ የልጁ እጢ ላይ ነው ፤ ልጁ ደግሞ አይኑ እኔ ላይ ነው ፡፡ ‹‹ አሁን አኮ ቀንሶ ነው ያየህው›› አለኝ ፡፡ ‹‹ሳይቀንስ ባየው የቱን ያህል ነበር?›› ብዬ ራሴን ጠየኩኝ፡፡እንዲህ ሲል ቀጠለልኝ ‹‹ ትላንት ምልክት አይቻለሁ በጥቂት ቀናት ውስጥ አፍስሳ ትጨርስልኛለች ፤ በአውራ ጣቴ በኩል በቢጫ ፈሳሽ መልክ ትንሽ ትንሽ ሲወጣ ተመልክቻለሁ ፤ ከአሁን በኋላ ግን ወደ በፊቱ ማንነቴ እንዳልመለስ እግዚአብሔር ይጠብቀኝ ፤ እርግጠኛ ነኝ አሁን እድናለሁ አለኝ፡፡›› የልጁ እምነት ገረመኝ፡፡ ስንቶቻችን ነን አፋችንን ሞልተን በእምነት ‹‹እድናለሁ›› ማለት የምንችል ፤ እንዲህ ለማለትም ፍጹም እምነት ያስፈልጋል፡፡ የመጣሁበትን ጉዳዬ እረስቼ ቁጭ ብለን ስለራሱ ፤ አዛው ቦታ ላይ ስላየው ተዓምር ሲነግረኝ ሰዓቱ መዝለቁን አላስተዋልኩም ነበር፡፡ መጨረሻ ላይ ‹‹በል እመብርሀን ወላዲተ አምላክ ትርዳህ ፤እግዚአብሔር በምህረቱ ይጎብኝህ›› ብዬው ወደ ማረፊያየ ለመሄድ ብድግ አልኩ ፡፡መሬት መሬት አቀርቅሬ ፤ የነገረኝን ታሪክ ከራሴ ጋር እያቆራኝውት እንደ ውሻ የተፋሁትን ነገር ደግሜ የላስኩበትን ሁኔታዎች ሳወጣ ሳወርድ ምንም ሳላውቀው ማረፊያዬ ጋር ደረስኩኝ፡፡

የ ኪዳነ ምሕረት ተአምር

የወላዲተ አምላክ ድንቅ ተአምር