Friday, June 17, 2016

የሽንቁሩ ቅዱስ ሚካኤል ጠበል ድንቅ ተአምር


እባክሆን ይህን ያላመነ የሚያምንበት ያመነ የሚፅናበትን ተአምር ለወዳጅ ዘመድዋ ያድርሱል...!!!
በስመአብ በወልድ በመንፈስ ቅዱስ አሃዱ አምላክ አሜን
ደዌ ለፈተናም በ ሀጢያት ምክንያትም በብዙ ብዙ ምክንያት ይመጣል እግዚአብሄር አምላክ ፈቅዶ በቸርነቱ ይህን አደረገልኝ እንጂ እንደኔስ ሀጢያት ሌላም በተገባኝ ነበረ ለበሽታዬ ምክንያት ሀጢያት እንደሆነ ስለገባኝ እግዚአብሄርን እየተመላለስኩ በ እንባ ይቅርታ መጠየቅ ጀመርኩ።
ያልሄድኩበት ፀበል ያልያዝኩት ሱባኤ አልነበረም ነገር ግን (የ እግዚአብሔር ምህረት በጊዜዋ ነው ብሎ ነብዩ ቅዱስ ዳዊት እንደተናገረ ሁሉ በመጨረሻ የ ሽንቁሩ ቅዱስ ሚካኤልን ታምር እና ዝና ሰምቼ ወደ ሽንቁሩ መጣሁ እንደቦታው ስርአት ንስሀ ገብቼ ፀበሉን ተጠምቄ መጠጣት ስጀምር ፀበሉን ከጠጣሁ ቡሀላ ባሉ 5 ደቂቃዎች ውስጥ ከሆዴ ውስጥ በስርአት የተከተፈ ስጋ
የሚመስል ነገር ይወጣ ነበር።



በሁኔታው ስደናገጥ በቦታው የቆዩ ፀበልተኞች አይዞህ ይሄ የሚወጣው መርዙ ነው በርታ ይሉኛል ቆይቶ አረንጉዋዴ ፈሳሽ ከሆዴ ወጣ ከዛቡሀላ ከበሽታዬ ሙሉ ለሙሉ ተፈውሻለሁ እኔን የረዳ እናንተንም ይርዳ አሜን።

ይህ የምትመለከቱ ምስል ወንድማችን ባለፈው የሽንቁሩን ደብረ መድሀኒያአለም ቅዱስ ሚካኤል ቦታ ጠይቆኝ በሙሉ እምነት በመሄድ ዕፀበሉ ቦታ በመሄድ ንሰሃ ገብቶ ካንተ በቀር ማንም የለኝ ብሎ በበሽታው ሲጨነቅ ሲጠበብ ይሄው እንደምታዩት ለዘመናት ሲያሰቃየው የነበረውን በሽታ በቅዱስ ሚካኤል ሀይል ፀበሉን በመጠጣት ይሄን ከሆዱ ውስጥ አውቶለታል።

እውነት እንደ ዛሬ የተደሰትኩባት ቀን የለችኝ የሰው ልጅ ስቃይ ሲፈታ ከማየት የበለጠ ምን ደስታ አለ።እንግዲህ እኛ የምናመልከው የምናምነው ፀበል ይሄ ነው ታምሩ ኦርቶዶክስ በማንኛውም በምታደርገው ነገር አትሳሳትም።
ወንድሜ ከዚህ በላይ ታምሩን ለመናገር ያብቃ ለእርሱ የደረሰ አምላክ ስንት በየቤታችን የሚሰቃዩ ያልጋ ቁራኛ ሆነው የሚሰቃዩ እህት ወንድሞች አሉን በምህረቱ አይን ይጎብኝልን።
ታምሩን ሼር በማድረግ ይተባበሩን ሁላችንም ለደጁ አብቅቶ ታምሩን ለመስከር ያብቃን ይችን ቀን በጉጉት እጠብቃት ነበር በእውነት ለእግዚአብሄር የሚሳነው ነገር ምን አለ።

የቅድስት አርሴማ ተአምር

እግዚአብሔር ክብር ምስጋና ይድረሰው የሰማእቷ የቅድስት አርሴማ ተአምር ለኔም አርጋልኛለች ላገኘሁት ሉ ተአምራቷን መሰክራለሁ ፍሬሕይወት ለማ እባላለሁ ምኖረው ለንደን ነው ቤተሰቦቼ ይርጋለም ነው ሚኖሩት በየጊዜ እነሱን ለማየት ስሄድ ፀበሏን እየተጠመኩ ነው ምመጣው ብዙ ነገሮችን አርጋልኛለች የአህኑ ተአምር ግን እናቴ ታመመችብን ስራ ፍቃድ ብጠይቅ አልተሰጠኝም ጠዋት ማታ በፀሎት አምላኬን እየለመንኩ እናቱን እመቤቴን አማልጅኝ እያልኩ ሰማእቷን እየለመንኩ ልክ ፋሲካ እሁድ ሊሆ ሁለት ቀን ሲቀረው ፍቃድ ተሰጠኝ እናቴም አዲስአባ ቤቴል ሆፒታል ለሁለትሳምንት ከትቆየች በሗላ ወደይርጋለም ተመልሳ ቤት ተኝታለች ቅኝ እጇና እግሯ እይቀሳቀስም ቤት ሆኗ ፀበሉን ህክምናውንም እየተከታተለች ነው እኔም ለ20 ቀን ፍቃድ ተሰጥቶኝ ልክ የፋሲካ እለት ማታ ተሳፍሬ ሰኞ ጠዋት አዲሳባ እንደገባህ ቀጥታ ወደይርጋለም ሄድኩ አርሴማ ፀበል እናቴን ይዠ የተወሰነ ቀን ተጠመቅን መሄጃዪ ደረሰና ልክ አውሮፕላን እንደተሳፈርኩ በቀኝ በኩል ጎኔ ላይ ጠዘጠዘኝ ስነካው ብጉር ይመስላል አበጥ ብሎአል በማግስቱ በጣም አበጠ ህመሙ ህይለኛ ስለነበር ፋርማሲ ቅርቤ ስለነበረ ሄጄ ሳሳያቸው ሆስፒታል ሂጂ አለኝ እኔም ስራ መግባት ስላለብኝ ወደቤቴ ተመልሼ ከይርጋለም አርሴማ ያመጣሁት ማር ነበረኝ ቅብት አድርጌው ፕላስተር ለጥፌበት ስራዪ ሄድኩ ህመሙ የት ደረሰ ሳልል ጠፋ ቀኑን ሙሉ ምንም ህመም ሳይሰማኝ ዋለ ስነካው ግን እብጠቱ እንዳለ ነው ህመሙ ስለተወኝ አርሴምዬን በልቤ እያወደስኩ ስራ ጨርሼ ማታ ቤቴ ገብቼ ፀሎቴን አድርሼ ፕላስተሩ አነሳሁትን ያበጠውን ነካ ሳረገው ነፍስ ያለው የሚንቀሳቀስ ነጭ ትል ተፈትልኮ ወጣ

የወጣበት ቁስል





አርሴምዪ በፀበሏ ቀጥቅጣ በማሯ ፈንቅላ በሽታዬን አወጣችልኝ ለእናቴ ሄጄ እኔ ተፈውሼ መጣሁ የቅድስት እርሴምዬ ገድሏ ታምራቷ ብዙ ነው የወጣውን ትል ቪድዮና ፎቶ ለብቻው ልኬአለሁ የሰማእቷ በረከት ይደርብን

Thursday, June 16, 2016

የቅድስት አርሴማ ተአምር

የ ሰማዕቷን የቅድስት አርሴማ ተአምር ልንገራችወ ፎቶዉ ላይ የ ሚታይዋት ታላቅ እህቴ ፋቅረ ማርያም ትባላለች በዝህ አመት በ ቡዳ መንፈስ ስትሰቃይ ነበር ነገር ግን በ አለም ላይ የተወከለችዉ ሰማዕቷ እኛም ቤት መጣች በ ሚያዝያ ወር በ ቀን 9ከ ምሽቱ 4 ሰዓት አከባብ እህቴ ታመመች ቤት ዉስጥ ከ ታናሽ ወንድሜ አብሮን ልያድር ከመጣዉ ከ አጎቴ ልጂ እና ከ እኔ በቀር ሌላ ማንም አልነበረም ግራ ገባን ጎሬበት ተጠራ ሰዉ ተሰበሰበ ( ጠናዳም ግዛዋ...) አጠኗት መንፈሷ ወድያዉ መለፋለፋ ጀመረች የመጀመርያ ቃሏ ግን "አርሴማ ምታቃጥለኝ አንሶነዉ እናንቴ ምታቃጥሉኝ"የምል ነበር ካህን ተጠራ ተፀበለች የት እንዳየቻት በ ጥርሷ እንደገባች እና ማንነቷን ተናገረች የን ዕለት በማግስቱ ከ ረፋዱ10 ሰዓት ላይ እለካታለዉ ብላ ተገዝታ ወጣች በዝህ ሁኔታ እስከ ማክሴኞ ቀጠልን ዕረቡ ዕለት ልክ ከ እረፋዱ 10 ሰዓት ላይ ጀመራት ያለን አማራች ቦንጋ ሄዳ እንድትፀበል ማድረግ ነበር ለ እናታችን ተደዉል ተነገራት እና ለመጨረሻ ጊዜ ቤት ተፀብላ እናታችን ይዛት ወደ ቦንጋ ሄዱ ከዛም
አባታችንም እዛዉ ቦንጋ ክዳነምህረት ፀበል እየተፀበለ ስለነበር ከሱጋር እዛዉ እንድትፀበል ታስቦ በማግስቱ ወደዛዉ ሄዱ ከተፀበለች በዋላ ግን ክዳነምህረት ወደ ቅድስት አርሴማ ላከቻት ምክኛቱም ሁሉም ሰማዕታት የወከሏት እሷን ስለሆነ ነዉ ከዛንቀን ጀምሮ እዛዉ ሰማዕቷ ገዳም ገብታ መፀበል ጀመረች በየቀኑ ስንደዉል የ ምንሰማዉን ነገር ማመን ከበደን ለካ በ እህቴ ላይ አድራ ቤታችንን ልታፀዳልን ነበር በቅናት መንፈስ ተነሳስተዉ እህቴ እንድታብድ በተሰቦቻችን እንዳይስማሙ በ እያንዳዳችን ላይ ታስቦ የተሰራ ተንኮል ነበር ድመት ገለዉ በ 7 ምስማር ወጥረዉ በ ቤታችን ጓሮ እንደተቀበረ እና እሷ እንደምታወጣልን ሰማዕቷ በ እህቴ ተመስላ ነገረችን በዝህ ሁኔታ መፀበሏን ቀጠለች ከ ጥርሷ1ጠጠር ወጣ ከዛም እዛዉ እያለች ሰሞነ ህማማት ደረሰ ሰማዕቷ መንፈሷን ገዝታ በቀጠሮ ማለትም እሰከ ሰኔ ስድስት እንዳትመለስ አዘዘቻት ነገር ግን "ህማማቱን እስከ ስቅለት ልጄ ከነጋር ደጄ ትስገድ " አለች ሌላም ትዛዝ " ልጄ መነፅር ትጠቀም በዛ መነፅር ላይም ሀይሌ ያርፍበታል ሰኔ 6 ምዛን ዉሰዷት ቀርዉ 6 ጠጠር እዛ ይወጣል " የምል ነበር እኛም በቃሏ መሠረት ይደረግ የተባለዉን ሁሉ አደረግን ፀሎተ ሐሙስ ከ ሰአት በዋላ ወደበት ተመለሰች በ አሉን በሰላም አሳለፍን የ ቀጠሮዉን ቀን መጠባበቅ ጀመርን በ መሀል ግን ሰማዕቷ ብዙ ታምሯን በ እኛቤት አደረገች ቁልፍ ጠፍቶብን ስንጨነቅ ለ እህቴ በ ህልሟ መታ ቁልፉ የት እንደ ወደቀ ነገረቻት ቁልፉን ከተባለዉ ቦታ አገኝነዉ ብቻ ብዙ ታምሯን እያየን ግኔቦት 8 ደረሰ አሁንም ቤት ዉስጥ ማንም አልነበረም እንደልማ ዳችን ተሰብስበን ተለቪዥን እያየን የ አጎቴ ልጂ እግሩን ተንተርሳ የ ሰማዕቷን ፎቶ እያየች ማልቀስ ጀመረች ምን እደሆነች ስንጠይቃት ፍቅርተ እንዳል ሆነች እና መንፈሷ እተገረፈች እደሆነ ገረችን ደነገጥን ካህን ልንጠራ ስናስብ " ማንንም እንዳጠሩ ፀበልም ካህንም አታምጡ ሴማዕቷ በ ዘንባባዋ እየገረፈችኝ ነዉ" አለች ተረጋጋን ልክ 3 ሰዐት ስሆን ፀሎት አደረገች በ መጨረሻም ሰማዕቷ ተመስላመታ እንዳንፈራ ና ሁሌም ከቤታችን እንደሆነች ነገረችን በሚግስቲም ቀጠለ 12 ስሆን ምካኤል ገረፋት በ 13 ሰማዕቷ በ14 አቡነ 16 ክድዬ እያለ እስከ ቀን 4 ቆየ ልክ ከ ለልቱ 9 ሰዓት ላይ ተቀብሮ የ ነበረው የጠላት ስራ በ ሰማዕቷ ትዛዝ መሠረት እንደምታዩት ከነ ምስማሩ ወጣ በቀን 5ወደ ምዛን ሄዱ ስሄዱ ፀበሉ መዘጋቱ ያዉቁ ነበር ግን በዛ ምትክ ወደ እመቤታች በቴክርስትያን እንድሄዱ ታዘዙ ከዛም ሰማዕቷ ተመስላ ስለ ፀበሏ መዘጋት አለቀሰች ምዕመኑም አብሯት አለቀሰ እንሆ ዛሬ የመጨረሻዋ ቀን 7 በማያልቀዉ ፈዉሷ የ ቀረት 6 ጠጠሮች ወተዉ እርኩስ መንፈስ ተቃጥሎ ኤህቴ ተፈወሰች ቤታችን ሰላም ገባ ክብር ለ መድአንአለም የኛን ሰላም የ መለሰችልን ሳሰለች የፈወሰችን ቅድስት አርሴማ በ ሁላችዉም ቤት ትግባ ወስበአት ለ እግዝአብሔር!!! 


አንዲት እህት ከሆዷ ውስጥ ጥቁር ወፍ ወጣላት


Monday, June 13, 2016

ተነግሮ የማያልቀው የሸንኮራ ዮሐንስ ድንቅ ተአምር

ስለ ሸንኮራ ቅዱስ ዮሐንስ ጸበል ምን ያህል ያዉቃሉ? የሸንኮራ ዮሐንስ ፀበል በአማራ ክልል በሰሜን ሸዋ ዞን በምንጃር ሸንኮራ ወረዳ ንዑስ ከተማ በሆነችዉ በባልጪ ከተማ አጠገብ በርካታ ተገልጋዮች ከተለያዩ ቦታዎች በመምጣት ፈውስ የሚያገኙበት ፀበል ነው፡፡ ፀበሉ በፈዋሽነቱ በይፋ መታወቅ የጀመረዉ:- አባ ካሳ የሚባሉ መናኝ ባህታዊ በሸንኮራ ቅ/ዮሐንስ ቤ/ክ መቃብር ቤት ዉስጥ ዘግተዉ ይኖሩ ነበር፡፡ ከእለታት አንድ ቀን በህልማቸዉ ከቤተ ክርስቲያኑ በስተምስራቅ ከወንዙ ዉስጥ ጸበል ፈልቋልና ወርደህ አይተህ ለህዝቡ ንገር እዉራን የሚያበራ፣ ለምፅ የሚያነፃ፣ ጎባጣ የሚያቀና ጸበል ፈልቋል በልና ንገር ብሎ በህልማቸዉ ነገራቸዉ፡፡

ሲነጋ ጠዋት በተነገራቸዉ መሰረት ወደ ወንዝ ወርደዉ ጸበሉን ሲፈልጉ አላገኝ አሉት፡፡ አባ ካሳ የዕድሜ ባለፀጋ ሲሆኑ ሲፈልጉ ዉለዉ በድካም ወደ ቤታቸዉ ተመለሱ፡፡ እንደገና ሌሊት በህልማቸዉ "ጠዋት ተነሣና ወደ ጸበሉ ዉረድ ጸበሉ ከጫካ ዉስጥ ፈልቆ ታገኘዋለህ ከፊ ከፊትህ የምትመራህ ርግብ ታሳይሃለች"አላቸዉ፡፡ በታዘዙት መሰረት ከጠዋት ተነስተዉ ወደ ወንዝ ሲሄዱ ርግብ ከፊት ከፊት እየመራቻቸዉ ከወንዙ ዉስጥ ሲደርሱ ጸበሉ ከፈለቀበት ገደል ላይ ክንፏን ዘርግታ አረፈች፡፡ከዚያም አባ ካሣም እግዚአብሔርን አመስግነዉ የፈለቀዉን ጸበል ጠጥተዉ እግራቸዉን ክፉኛ በሽታ ያማቸዉ ስለነበር ጸበሉን ሲያስነኩት ከያዛቸዉ በሽታ ወዲያዉኑ ተፈዉሰዋል፡፡ ከዚህ በኋላ አባ ካሳ የፈለቀዉን ጸበል ለህዝቡ ነግረዉ ሚያዝያ 30 ቀን ታቦተ ህጉ ወደ ጸበሉ ወርዶ በደማቅ ሁኔታ ተክብሯል፡፡ ይህንን ራዕይ ያዩት ሚያዝያ 15ቀን 1654 ዓ.ም ገደማ ሲሆን 354 ዓመት ያስቆተረ ጸበል ነዉ ተብለዉ ይገመታል፡፡ የቅዱስ ዮሐንስ በረከት ከሁላቸን ጋር ይሁን አሜን ።


ቤቱ ከአፋፍ ላይ ጸበሉ ከጅረት የድውያን ዳባሽ መጥምቀ መለኮት የስሙ ትርጉዋሜ ፍስሐ ወሐሴት በልደቱ የፈታ የአባቱን አንደበት እማሆይ ሂሩተ ገብርኤል ይባላሉ ተወልደው ያደጉት እዚሁ አዲስ አበባ ነው ትምህርታቸውን ጨርሰው ዮንቨርስቲም የሁለተኛ አመት ተማሪ ሳሉ በደረሳቸው መለኮታዊ ጥሪ በምናኔ ወደ ገዳም በመግባት ለ5 አመታት አገልግለው ደጅ ጠንተው በገዳሙ ማህበር ፈቃድ ምንኩስናቸውን ተቀብለው አገልግሎታቸውን በሰፊው በመስጠት ላይ ሳሉ ድንገት ባላሰቡት ሁኔታ በጡት ካንሰር በሽታ ይለከፋሉ አዲስ አበባ ለህክምና በመምጣት በጥቁር አንበሳ ሆስፒታልና በሌሎችም የግል ህክምና መስጫ ምርመራ ቢያደርጉም የታመመው አካል በአስቸኩዋይ ካልተቆረጠ ካንሰሩ ይሰራጫል ይባላሉ ህመሙ ከባድና ጽኑ ነበር በተለይ የጨረር ህክምና ተብለው የባሰ ተሰቃዮ እማሆይ ምርር ብለው ያለቅሳሉ ገና በማለዳ ነፍሴን ለገነት ስጋዬን ለአራዊት ብዬ መንኜ እንዴት ገላዬ ተገልጦ ክብሬ ይቃለላል ይህስ እንዲሆን አምላኬ ለምን ፈቀድክ ብለው ያዝናሉ የታመመ አካላቸውን ለማስቆረጥ ቀጠሮ ይይዛሉ እማሆይ እንደተናገሩት ፒያሳ አካባቢ ነዳይ መስለው ተሰውረው የሚኖሩ ባህታዊ ከጊዮርጊስ ቤተክርስቲያን ስወጣ "ሸንኮራ ዮሐንስ ሂጂ አንቺ ፈላሲ "ይሉኛል የምን እብድ ነው ብዬ አለፍኩት ክንክን አደረገኝና ተመልሼ ባይ ጠፉብኝ ልቤ ተነሳሳ ስቃዮ ደግሞ ረፍት ነሳኝ ደምና መግል ከታመመው አካሌ ይወርዳል እንደምንም ሸንኮራ መሪ ሰው ይዜ ገባው እምነቱን ጸበሉን ስቀባው ከረምኩኝ ይፈስ የነበረው የደም ጎርፍ ጠፋ ህመሜም ቀነሰ እንቅልፍም በደንብ እተኛ ጀመር ሰላሜ ተመለሰ የቀጠሮውም ቀን አለፈ ፍጹም ጤነኛ ሆንኩኝ የአይነ ከርሙ ባህታዊ ነብየ ልኡል ሰማእቱ መጥምቁ የጌታዬ የአምላኬ ወዳጅ በአድያመ ዮርዳኖስ በሸንኮራ ምድር በስሙ በፈለቀው ጸበል ጡቴን ከመቆረጥ አዳነኝ ዳግም ተመርምሬ ፍጹም ጤነኛ ነሽ ተብያለው ወደምወደው ገዳሜ በደስታ ተመልሻለው ብለዋል እናታችንይህን ያደረገ የዮሐንስ አምላክ ክብር ይግባው ይግባው ከኛም የማይበጀንን ነገር ቆርጦ ይጣልልን አሜን