Tuesday, December 31, 2013

ተአምር በ አቡነ ገብረ መንፈስ ቅዱስ ቤተ ከርስቲያን /ሽሬ/

በሰሜን ትግራይ ክልል ከሽሬ ከተማ ወጣ ብሎ ማይ ወይኒ አቡነ ገብረ መንፈስ ቅዱስ ቤተ ከርስቲያን ለረጅም አመታት በዓታቸውን አጽንተው የኖሩ እድሜ ጠገብና ፍጹም ጸሎተኛ የሆኑ ታላቅ አባት ነበሩ:: ባለፈው ዓመት ማለትም ኅዳር 2005 ሊቀ ትጉኃን ደረጀ ነጋሽ (ዘ ወይንዬ) በሚያዘጋጀው መንፈሳዊ ጉዞ አክሱም ጽዮን ደርሰን ስንመለስ፡ ወደዚህ ታላቅ ገዳም ለመሳለምና የእኚህን ቅዱስ አባት በረከት ለመቀበል የጉዞ ማኅበሩ በየዓመቱ እንደሚያደርገው ገብተን ነበር:: ገመና ሸፋኙ ይቅር ባይ ጌታ እኔን ደካማውን ልጁን ሳይገባኝ የዚህ በረከት ተካፋይ አደረገኝ:: ይህንን ፎቶ አሁን የለቀኩበት ዛሬ እኚህ ቅዱስ አባት በዚህ ዓመት በማረፋቸው ምክንያት ነው::
 
 
 
 
 
 
 
መምሕር ጻውሎስ መልከ ስላሴ ከተጠቀሱት አባት ጋር
ዘንድሮ የሄደው የአክሱም ተጓዥ ሁሉ እንደተለመደው ወደ ቦታው ቢሄድም እኚህን አባት በአካለ ሥጋ አላገኛቸውም ሕይወታቸውን ሙሉ ታምነውለት የኖሩለት እግዚአብሔር ዘንድ : በይባቤ መላእከት እና ዝማሬ ካህናት ታጅበው ሄደዋል:: የኖሩበት ዘመን ከሁለት መቶ ዓመታት በላይ እነደሆነ ይነገራል:: ዘንድሮ ኅዳር አቦ ለቁስቋም ዋዜማ ካህናቱ በአገልግሎት ላይ ሳሉ ያልተለመደ እንግዳ ድምጽ ሰሙ: ይኸውም ከካህናቱ ድምጽ በላይ የነምር (ነብር) ድምጽ ቤተ ክርስቲያኑ ውስጥ ይሰማ ነበር ይላሉ ካህናቱ:: ውዲያውም ድንገት እንግዳ የሆኑ አባቶች መነኮሳት በኚህ ታላቅ አባት በአት (ቤት) ተገኙ:: እነርሱም በመንፈስ ቅዱስ ራእይ እኚህን ታላቅ አባት በክብር ገንዘው እናዲያሳርፉ ከዋልድባ የተላኩ አባቶች ነበሩ:: እነሆ ሳይገባን እኛም ልናገለግልባት የቆምንባት ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ማለት ይህቺ ናት የማትመክን ዛሬም ቅዱሳንን የምትወልድ ሁሌም ተአምር የምትሰራ እነዚህን የመሳሰሉ አባቶችን ያፈራችና ወደፊትም የምታፈራ: በተቀደሱ ጸበሎችዋ የምትፈውስ፡ ተፈትና የምታሸንፍ ሁሌም በድንቅ ነገሮች የተመላችና በዙ ምስክሮች ያሏት ናት:: ተዋሕዶን ይጠብቅልን የአባታችን በረከታቸው ይደርብን በቦታው ተገኝተን ምስክርነቱን አድምጠን ለመባረክም ያብቃን:: "እንግዲህ እነዚህን የሚያህሉ ምስክሮች እንደ ደመና በዙሪያችን ካሉልን፥ እኛ ደግሞ ሸክምን ሁሉ ቶሎም የሚከበንን ኃጢአት አስወግደን፥ የእምነታችንንም ራስና ፈጻሚውን ኢየሱስን ተመልክተን፥ በፊታችን ያለውን ሩጫ በትዕግሥት እንሩጥ፤ እርሱ ነውርን ንቆ በፊቱም ስላለው ደስታ በመስቀል ታግሦ በእግዚአብሔር ዙፋን ቀኝ ተቀምጦአልና። "( ዕብ ፲፪፥፩ )
 ምንጭ
 የመምሕር ጻውሎስ መልከ ስላሴ ምስለ ገጽ (ፌስ ቡክ) የተወሰደ

ተአምራት በባሕታዊ ሳሙኤል ሶሙናዊ 

Miracles of Legedadi Saint Mary Church

 


Tuesday, December 10, 2013

የዝሙት መንፈስ ምንድነው? አይነጥላ ምንድነው?


ዝሙት  
" የእግዚአብሔር ልጆችና የዲያብሎስ ልጆች በዚህ የተገለጡ ናቸው " 1 ዮሐ, 3 : 10

ለብዙ ዘመን ያህል የካበተ የማሣሣቻ ልምድ ያለውና የሰዎችን መልካም ጠባይ የሚያበላሽው አንዱ የዝሙት መንፈስ ሲሆን ዘወትር እንደ አዲስ ነገር አመልካች በመሆንና ግፈትን በማጠናከር በልብ ውስጥ የሩካቤ ቅስቀሳ በማድረግና ሰዎች ዝሙትን እንደ ተለመደ ኖርማል ነገር አድርገው እንዲወስዲና ድርጊቱን በግልጽ ነውረኝነትና በድፍረት እንዲፈጽሙ ያነሣሣል : : የዝሙት መንፈስ እግዚአብሑር ለሰው ልጆች ከሰጠው የተፈጥሮ ጠባይ በማዛነፍና በማዛባት ቀደም ሲል እንደተጠቀሰው ሰዎችን በማስነወር ለተፈጥሮ ግብር ተቃራኒ በማድረግና በማርከስ ፍጹም የአመንዝራነትና የሴሰኝነትን ሰይጣናዊ ጠባይ ያወርሳል ዛሬ በዓለማችን ላይ ያለው የተራቀቀ ቴክኒዎሎጂ በተለይም የኢንተርኔት አግልግሎት ከሰጠው አዎንታዎ ጥቅም በተጨማሪ በአሉታዊ መልኩ ሰዎች በዝሙት : በኮክብ ቆጠራ : በሥነ ልቦናና : በፍልስፍና ወዘተ . . . መንፈሶች እንዲ ልክፍት ከፍተኛ አስተዋጽፆ አበርክቷል : : " እንግዲህ በምድር ያሉትን ብልቶቻችሁን ግደሉ እነዝህም ዝሙትና ርኩሰት ፍትወትም ክፋ ምኞትም ጣዖትንም ማምለክ የሆነ መጐ ምጀት ነው በእነዚህም ጠንቅ የእግዚአብሔር ቁጣ በማይታዘዙ ልጆች ላይ ይመጣል : : "ቄላስይስ. 3 : 5 - 6  

የዝሙት መንፈስ የመግቢያ አቅጣጫዎች -

 አብሮ በሚወለድ አጋንንት ዛር በውርስ መንፈስ በኩል ከሴትዋጋር አብሮ በሚወለድ ወንድ የአጋንንት ዛር በተቃራኒው ደግሞ ከወንዱ ጋር አብራ በምትወለድ ሴት የአጋንት ዛር አማካኝነት - በመተት ለዲያብሎስ ያደሩ ሰዋች ወደ ሌሎች አስመትተው በመላክ - ከዓይን ላይ በሚነሣ መንፈስ (ብዳ) አማካኝነት ከውስጥ ወደ ውጭ በሚያይ የዝሙት መንፈስ ዓይን አማካኝነት የመንፈሱ ስሜት ይገባል : : - በማየት : በማዳመጥ : በማንበብ በኩል የሚገባ የወሲብ ፊልሞችንና ስዕሎችን በማየት ተመሣሣይ ወሲብ ነክ ንግግሮችን በሙሉ ሰሜት በማዳመጥና ጽሁፎችን በማንብ በፊልሙ በንግግሩና በጽሁፉ ላይ በሚናር ሙሉ ተመስጣ ወይም ከፍተኛ ትኩረት የተነሣ የዝሙት መንፈስ ወደ ሰዎች ይገባል : : ከዝህ በተጨማሪ መንፈሱ ከሰፈነበትና የሚውጠውን ለመፈለግ በሚንቀሣቀስበት አየርና መንገድ ላይ ያገኛቸውን ሁሉ ይጠልፋል : : ለዚህ በተለይ ምሳሌ የሚሆኑን በአገራችነ በኑሮና በባህል ተጽዕኖ አስገዳጅት ቺግር የገጠማቸውን አንዳንድ እህቶቻችንን እያሳደደና መጥፏ አማራጭ እያሳያቸው የሴትኛ አድሪነት ሕይወትን እንዲመሩ የመገፋፋቱ ጉዳይ ነው : : የእነዚህ የዝሙት መንፈሶች ተጋቦት ፈጣን በመሆኑ ዱያቢሎስ ስዎቹን ቅብጥብጥ : እፍረተ-ቢስ : ነውረኛ ርካታ-ቢስ ወዘተ. . . በማድረግ በመጨረሻ ሥነ-ምግባራቸውና ግብራቺው ለክርስቲያናዊ ሕይወት የሃይማኖት ቅድስና አደገኛ ይሆናል : : የሩካቤ ክፉ መንፈሶች ከሌሎቹ የጥፋተ መንፈሶች ለየት ባለ መንገድ ብዙ ጠባይ አላቸው : : ከነዚህም ውስጥ ለምሳሌ ሴት አጋንንት ዛር ከውንዱ ጋር አብራ ከተወለደች በእድገቱና በዕድሉ ስለምትቀና ሩካቤውን ለራስዋ በምትፈለልገው መልክ ትቆጣጠራለች : : በዚህ የተነሳ ሰውየውን ዓይነ-አፋር : ፈሪ እና : ድንጉጥ ልታደርገው ትችላለች በሴቷ ውስጥም ያለው ወንድ አጋንንት እንደዚሁ ዓይነት ተመሣሣይ ጠባይ ያሳያል ብዙ ጊዜ ይህ የዝሙት መንፈስ በዛር በኩል ውርስ ሆኖ ሊመጣ ወንዱንም ሆነ ሴቷን ፍጹም ዓይን ወደ አወጣ ሴሰኝነት በታቃራኒው ወደ ዓይነ-አፋርነት በመለወጥ ከፍተኛ አለመግባባት በባልና በሚስት መካከል በመፍጠር የወንዱ ሕይወት በሴቷ የሴቷ ሕይወት ደግሞ ሁለቱንም ጻታዎች ልባቸውን የሩካቤ ስሚታቸወን የሞተ አድርጎ በማሳቀቅ የሚያዝኑና የሚያለቅሱ ብቸኛ ሰው ሆነው የሌሎችን ትዳርና ልጆች ሲያዩ እንዲማረሩ አድርጎ ሕይወታቸውን በራሳቸው እጅ እንዲያሳልፉ ይህ የዛር መንፈስ ግፊት ያደርጋል : : የመንፈሱ ተጽዕኖ እጅግ ከባድና የሰዎች ጠባይ አውሬነት ሁሉ እስከ መለወጥ ያደርሳል ምክንያቱ ደግሞ ተደጋግሞ እንደተገለጸው አብሮ የተወለደው አጋንንት ዛር ሙሉ በሙሉ ከሰዎች ጋር ስለተዋሃደና ቤቱን በላያቸው ላይ ሠርቶ ዘሬናቸው እያለ ስለሚፍክር ነው : : 
 
" ይህን እወቁ አመንዝራም ቢሆን ወይም ርኩስ ወይም የሚመኝ እርሱም ጣዖት የሚያመልክ በክርስቶስና በእግዚአብሔር መግስት ርስት የለውም " ኤፌ 5 : 5 

የሳጥናኤል ሠራዊት  * ባጀት አይፈልጉም የሚንቀሳቀሱት በአንተ በጀት ነው : : * ቢሯቸው አይዘጋም ምን ጊዜ ምክፍት ነው : : * አያንቀላፉም መዘናጋት በእነርሱ ዘንድ የለም : : * አያረጁም ጡረታ አይወጡም * በፓሊስ አይያዙም በፍርድቤት አይዳኙም * አይቀበሩም ወደ ሲኦል ተሸኝተው ካልታሰሩ በስተቀር አይሞቱም : : 

" የድንግል ማርያም ልጅ ኢየሱስ ክርስቶስ ከርኩሳን መናፍስትና ከሴሰኝነት ያውጣንና ይጠብቀን " አሜን !

አይነ ጥላ

በማለዳ መያዝ መጽሐፍ ገጽ.57 
አይነ ጥላ በምናየው በምንረዳው በምንገነዘበው ወዘተ..መንገዳችን ላይ አሸምቆና ተደብቆ ጉዳት የሚያደርስብን የሚያርፍብ የክፉውን መንፈስ ጥላ ዋንኛው የዲያብሎስ የጥቃት ክንድ ነው::
የዓይነ ጥላ መንፈስን ልዩ የሚያደርገው በመጀመርያ ደረጃ በውስጣችን ሲገባ ከጠባያችን ጋር መመሳሰል መቻሉ አንዱ ሲሆን ሁለተኛው ደግሞ ተምረን ጥረን ግረን የት እንደምንደርስ እንዴት እንደምናድግና ዕድላችን እንዴት እንደሚቃና አስቀድሞ በማወቅና አርቆ የማየት ከፍተኛ ችሎታ ያለው መንፈስ መሆኑ ነው:: .....
ለምሳሌ እንመልከት
ቢሮ ከሆነ አንተ ውስጥ ያለው አይነጥላ  ከአንተው ላይ ተነስቶ አለቃህ ውስጥ ቀድሞ ገብቶ ይጠብቅሃል:: ቢሮ እንደደረስክ ራስህን እስክትጠላ በከባድ ቁጣና ሞራል በሚነካ ዘለፋ ያስተናግድሃል::የሥራህ ሕልውናም ሊያከትም እንደሚችል በመግለጽ ያስፈራራሃል ያስጠነቅቅሃል:: አንተም ያዙኝ ልቀቁኝ ማለት ትጀምራለህ:: ወደ አካል ግጭት ሁሉ ልታመራ ትችላለህ::
ተጨማሪ ያንብቡ...
በማለዳ መያዝ ቅጽ አንድ ከገጽ 57 ጀምሮ..