እመቤታችን በግብፅ ውስጥ በነበረችበት ወቅት ልጅዋን ኢየሱስ ክርስቶስን ሦስት አመት ከስድስት ወር ከ10 ቀን ሲሆን እመቤታችን በወቅቱ ትገለገልበት የነበረው ሙቀጫዋ ፣ድስቷ እንዲሁም: ጌታችንን ገላዉን ልብሱን ታጣጥብበት የነበረዉ
ከዲንጋይ የተሰራ መገልገያ ዕቃዎችዋ ሲሆን ይህን ቅዱስ ስፍራ ለማየት የታደሉት ምዕመናን ጭምር
ደስታቸውን በእልልታ ና በዝማሬ በድምቀት እያከበሩት ይገኛል።
Tuesday, November 15, 2016
Wednesday, September 21, 2016
የቅድስት አርሴማ አዲስ ፀበል
አዲስ የፈለቀ ታላቅ የፀበል ፈውስ ስፍራ ኑ እና የእግዚአብሔር ድንቅ ስራውን መስክሩ::
ቸው ቅዱሳን ስም የሰጠንን ታላቁን የፀበል ፈውስ ነው፡፡ ቅዱስ ፀበል አፍልቆ ህዝቡን እየባረከና እየፈወሰ ይገኛል፡፡ አንከሶች መርገጥ (ቆመው መሄድ) ችለዋል እጃቸው የተቆለፈ ሽባዎች እጃቸው ተፈቶላቸዋል በአልጋ የመጡ ተፈውሰው በእግራቸው ሄደዋል በውስጥ ደዌ የሚሰቃዩ ፈውስ አግኝተዋል እባብ፣ አባጨጓሬ እና ወስፋት ከሆዳቸው ፀበሉን በመጠጣት ወጥቷል፡፡ ከኤች አይ ቪ ኤድስ ከትቪ በሽታ የተፈወሱ ሰዎች አሉ ከአኪንታሮት በሽታ የተፈወሱ ሰዎች አሉ
ፀጋ እ/ር በባዛላቸው በመላው ኢትዮጲያ ባገለገሉ አባት ታግዞ በመቶ የሚቆጠሩ ሰዎች በቅድስት አርሴማ ፀበል ከቁስል ነገር ድነዋል፡፡
አድራሻ ከ ከዊንጌት አደባባይ ተሻግራቸው ወደ ሙለጌታ አባት መናፈሻ በሚወሰደወ መንገደ ከደረሱ ሰዉቸነ መጠየቅ ይቻላል ለበለጠ መረጃ
0910792943(አባ ዜና)
0913986208 ወይም
0920146348.
የሰማእቷ እናታችን ረድኤል በረከት ይደርብን አሜን::
Sunday, August 14, 2016
ተዕምረኛ ድንጋዪች በዳጋ እሥጢፋኖስ
አቡነ ኂሩተ አምላክ ሁለት ድንጋዮችን በተረአምራት እንደ ታንኳ አድርገው በመጠቀም ጣና ባሕርን በበትረ መስቀላቸው እየቀዘፉ ዳጋ ወደተባለው ደሴት ገብተዋል፡፡ ጻድቁ የጣናን ባሕር እንደ ታንኳ ተጠቅመው የተሻገሩባቸው እነዚያ ሁለት ትላልቅ ድንጋዮችም ዛሬ በገዳሙ ውስጥ የጻድቃን ማረፊያ (ምዕራፈ ጻድቃን) ተብሎ በሚጠራው ቦታ ላይ በክብር ተቀምጠው ይገኛሉ፡፡ እሳቸው ያን ጊዜ ያረፉበት ቦታ ዛሬም ድረስ ‹‹ዓቃቤ ሰዓት›› እየተባለ በመዓርግ ስማቸው ይጠራል፡፡ አቡነ ኂሩተ አምላክ በቦታው ላይ በጽኑ ተጋድሎ ኖረው ሥርዓቱን አጽንተው ተጋድሎአቸውን ጨርሰው በዛሬዋ ዕለት ነሐሴ 8 ቀን በክብር ዐርፈዋል፡፡ በረከታቸው ይደርብን፡፡
Subscribe to:
Posts (Atom)