የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተክርስቲያን "መልአከ መንክራት ግርማ ወንድሙ" በሚል ስያሜ የተበተነው ደብዳቤ ሕገ ወጥ በመሆኑ የሚመለከተው ሁሉ ይህን ግንዛቤ እንዲወስድ አሳሰበች፡፡
በሚል ከዚህ ጋር ተያይዞ የወጣውን እና የተሰራጨውን ደብዳቤ አስነብበናል:: አሁን ከ ከ ቅዱስ ፓትሪያሪኩ http://www.eotc-patriarch.org/#
ድኅረ ገጽ በወጣው መግለጫ ደብዳቤው ጥንቃቄ እንዲደረግበት ማሳሰቢያ ተሰጥቷል:: ደብዳቤው ከታች እንደምትመለከቱት ነው::
የቀድሞውን ደብዳቤ በተመለከተ መምህር ግርማ በሬድዮ አቢሲኒያም ሆነ ተከታታይ በወጡት VCD 26 እና 27 ላይ የተናገሩት ነገር የለም:: ደብዳቤውም ወጣ የተባለበት ከአመት በላይ ያለፈው ግዜ 05/19/2005 በዚህ ጉዳይ ላይ መምህር ግርማ ያረጋገጡልን ነገር የለም:: ስለዚህ ይህን አይነት ድርጊት እየሰራ የመልአከ መንክራት ግርማ ወንድሙን ስም ለማበላሸት የሚጥሩ ስላሉ እርሳቸውን ተጠያቂ ከማድረግ እንድንቆጠብ እናሳስባለን:: ሰሞኑን የርሳቸው ቭኢዲዮ ከነድረገጹ ሁሉ በማጥፋት የ እግዚያብሔር ስራ እንዳይተላለፍ እንቅፋት የሆኑ እንዳሉ የምናውቀው ነው:: ከ ሁለት ደርዘን በላይ ምስሎች አሁን በ ንቁ ተአምረ ጽዩን ማየት የሚቻለው የተወሰኑንት ብቻ ነው::
ይህ ድረ ገጽ የተሳሳተ መረጃ በማቅረብ አላስፈላጊ መደነጋገር ውስጥ ስለከተትን ይቅርታ እንጠይቃልን:: የመምህር ግርማ አገልግሎት መስፋፋት እና የሕዝቡን መዳን ስለምንወድ አገልግሎታችንን ከበፊቱ ይልቅ የተጠናከረ እንዲሆን እንተጋለን::
መዝ 119: 121 "ፍርድንና ጽድቅን ሠራሁ፤ ለሚያስጨንቁኝ አሳልፈህ አትስጠኝ።"
No comments:
Post a Comment