ታላቅ የምስራች!!
በኦሮሚያ ክልል ሰሜን ሸዋ ዞን በአለልቱ ወረዳ ልዩ ስሙ ቁምጤ በተባለ አካባቢ የአብሳሪው ቅዱስ ገብርኤል ጽላት፣ ልዩ የፀበል ቦታና ሌሎች የብራና መፃሕፍት በአንድ ቅዱስ አባት ራእይ( ህልም) አማካኝነት ተገኝቷልና መጥታችሁ ጎብኙ። አካባቢው ከመዲናችን አ.አ 55 km ወጣ ብሎ የሚገኝ ቅርብ ቦታ ስለሆነ መጥታችሁ የበረከቱ ተካፋይ ትሆኑ ዘንድ ጥሪያችንን በእግዚአብሔር ስም እናቀርባለን።
እባካችሁ ይህን መልዕክት ለሌሎች በማካፈል ለሁሉ እንዲደርስ የበኩላችንን አስተዋፅኦ እናድርግ
በአለልቱ አካባቢ ስለተገኝ የቅዱስ ገብርኤል ጽላት አጭር መረጃ (ለማታውቁት)፦ ዕለቱ ስኞ ግንቦት 24 /2007 ዓም የተክልዬ የበአል ቀን ነበር። በነገራችን ላይ አለልቱ ማለት የአባታችን ተክለኃይማኖት የትውልድ ቦታ እና የበርካታ አብያተ ቤተ ክርስትያናትና ገዳማት መገኛ ወረዳ ናት። እናም እኝህ በፎቶው ላይ የምታዩዋቸው ባህታዊ አባት የመጡት ከሌላ አካባቢ ሲሆን በእግዚአብሔር መልካም ፈቃድ በህልም (በራእይ) ተገልፃላቸው ወደዚህ አካባቢ በመምጣት ፅላቱ የተገኘበት ቦታ ላይ ሄደው ቁፋሮ እንዲጀመር ያዛሉ። ሆኖም ግን ያው እንደምናውቀው አንዳንድ የኃይማኖት መሪዎችና መናፍቃንን ጨምሮ ጥቂት ሰዎች " አባ ምን ነካቸው ይቃዣሉ እንዴ " እያሉ በጥርጣሬ ሲያሟቸውና ሲሳለቁባቸው ነበር። ነገር ግን ከጥቂት ሰአታት በኋላ እግዚአብሔር ለሁሉም ያስደመመና ያስደነገጠ ልዩ ተአምራቱን አሳየ። እጅግ ግዙፍ ከሆነ ድንጋይ ሥር በጥንታዊ ቆዳ የተጠቀለለና ልዩ መአዛ ያለው ጽላትና የብራና መፅሐፍ ተገኘ። የፀበል ቦታውንም ጭምር። በዚህ ሰአት ቦታው የመንገድ ዳርቻ (አስፋልት) ስለሆነ መንገደኛ ሁሉ ከመኪናው እየወረደ ሁኔታውን ለማየት ይጎርፍ ጀመር። ከመቅፅበትም ሌላ ጉድ ታዬ።
በአለልቱ ከተማ በአባታችን በአባ ገብረ ሕይወት ራዕይ ከተገኘው የቅዱስ ገብርኤል ፅላት
ጋር አብሮ የተገኘው 600 አመታትን ያስቆጠረው የብራና መጽሐፍ ይህ ነው። የመለዓኩ ቅዱስ ገብርኤል በረከት
በሁላችን ይደር። ቅዱስ ገብርኤል ይጠብቃችሁ።
No comments:
Post a Comment