
Monday, June 8, 2015
እሙሀይ ብርሐን - ዲማ ቅዱስ ጊዮርጊስ ገዳም

Wednesday, June 3, 2015
የቅዱስ ገብርኤል ጽላት በአንድ አባት ራእይ ተገኘ



በኦሮሚያ ክልል ሰሜን ሸዋ ዞን በአለልቱ ወረዳ ልዩ ስሙ ቁምጤ በተባለ አካባቢ የአብሳሪው ቅዱስ ገብርኤል ጽላት፣ ልዩ የፀበል ቦታና ሌሎች የብራና መፃሕፍት በአንድ ቅዱስ አባት ራእይ( ህልም) አማካኝነት ተገኝቷልና መጥታችሁ ጎብኙ። አካባቢው ከመዲናችን አ.አ 55 km ወጣ ብሎ የሚገኝ ቅርብ ቦታ ስለሆነ መጥታችሁ የበረከቱ ተካፋይ ትሆኑ ዘንድ ጥሪያችንን በእግዚአብሔር ስም እናቀርባለን።
እባካችሁ ይህን መልዕክት ለሌሎች በማካፈል ለሁሉ እንዲደርስ የበኩላችንን አስተዋፅኦ እናድርግ

በአለልቱ ከተማ በአባታችን በአባ ገብረ ሕይወት ራዕይ ከተገኘው የቅዱስ ገብርኤል ፅላት
ጋር አብሮ የተገኘው 600 አመታትን ያስቆጠረው የብራና መጽሐፍ ይህ ነው። የመለዓኩ ቅዱስ ገብርኤል በረከት
በሁላችን ይደር። ቅዱስ ገብርኤል ይጠብቃችሁ።
ታላቅ ተዓምራት- የፈለገ ሕይወት መጥምቀ መለኮት ቅዱስ ዮሐንስ፣ወቅድስት ሃና ወቅዱስ ዑራኤል ቤተክርስቲያን
በቦሌ ክፍለ ከተማ ወረዳ ፲ የሚገኘው የፈለገ ሕይወት መጥምቀ መለኮት ቅዱስ ዮሐንስ፣ወቅድስት ሃና ወቅዱስ ዑራኤል ቤተክርስቲያን ሰሞኑን ታላቅ ተዓምራትን እያሳየ ነው። ሰዎች
ይዘባበታሉ እግዚአብሔር ግን ሥራውን እየሰራ ነው፣ ሰዎች ልብ እንበል "በዚያን ጊዜ ብዙዎች መንገዶቻቸውን
ይስታሉ" እንደተባለው ዘወትር በአጠገባችን ከከበበን ጠላት ዲያብሎስ ርቀን የቃሉን ድምጽ ሰምተን ወደ እርሱ ብንጠጋ
እንባረካለን። ረደኤተ እግዚአብሔር አይለየን አሜን
ደብረ እያሪኮ ቅዱስ ሚካኤል
ምን ዓይነት ጸሎት በየትኛው ሰዓት ልጸልይ?
ኢትዮጵያውያንና የያዕቆብ የመጨረሻ ልጅ የቢኒዖን (ብንያም)ነገድ
የፈለገ ሕይወት መጥምቁ ዮሐንስ ወቅድስት ሃና ወቅዱስ ዑራኤል ገቢረ ተዓምራት -save waldiba
Tuesday, June 2, 2015
ድንቅ ታምር ጃማ ማርያም
ዳግማዊት ጎለጎታ ድንጋይ ገጠም ጃማ ማርያም ቤተ ክርስቲያኗ የተመሰረተችው በ17ተኛው
ክ/ዘ በልጅ እያሱ ዘመነ መንግስት እንደተሰራች የሚነገርላት ጃማ ማርያም ዳግማዊት ጎለጎታ እንድትባል ያስቻላት
ከዕየሩሳለም ጎለጎታ ቀጥላ ሁለተኛዋ በመሆኗ እና ድንቅና
ታምራዊዋ ጸበል ከፈለቀበት ከ1965 ዓ/ም ጀምሮ ደንቅ ታምር እየሰራ የገኛል ለምሳሌ :-\አይነ ስውራንን ፥መንፈስ
የተጠናወታቸውን ፥አካላቸው ሽባ የሆነውን ፥አፋቸው የማይናገረውን፥የዘመኑ በሽታ(HIv)ን ጨምሮ እና ሌሎችንም
በርካታ በሽታወችን የምፈውሰው ከድንጋይንና ከተራራ ላይ የሚፈልቀው ጸበል ድንቅ ታምር እየሰራ ስለመሆኑ ታምሩ
ይመሰክራል በመሆኑም ግንቦት 21/2007ዓ/ም የንግስናዋ እለት ከ2000 በላይ ምዕመናን ለበዓሏ ታድሟል ውድ
ጓደኞቸ ሼርና ላይክ በማድረግ ከዚህ ታምር ተካፋይ ትሆኑ ዘንድ በእግዚዓብሄር ስም አሳሰብኋችሁ የእግዚዓብሄር እና
የቅድስት ድንግል ማርያም በረከት ከሁላችን ጋር ይሁን አሜን፡፡
Subscribe to:
Posts (Atom)