Wednesday, June 10, 2015

የወሊሶ ቤተ ሳይዳ ደብረ ምጥማቅ ቅድስት ማርያም ገዳም

በሚሊዮኖች የሚቆጠሩ ምእመናን የተፈወሱባት የወሊሶ ቤተ ሳይዳ ደብረ ምጥማቅ ቅድስት ማርያም ገዳም ቅዳሴ ቤት ይከበራል አትም ኢሜይል
ግንቦት 8 ቀን 2007 ዓ.ም.
በእንዳለ ደምስስ
01w
በደቡብ ምዕራብ ሸዋ ሀገረ ስብከት በወሊሶ ከተማ የምትገኘው የቤተ ሳይዳ ደብረ ምጥማቅ ቅድስት ማርያም ገዳም ሕንፃ ግንባታ ተጠናቅቆ ቅዳሴ ቤቱ ግንቦት 20 እና 21 ቀን 2007 ዓ.ም. ቅዱስ ፓትርያርኩ፤ ብፁዓን አበው ሊቃነ ጳጳሳት፤ ሊቃውንተ ቤተ ክርስቲያንና ምእመናን በተገኙበት በድምቀት እንደሚከበር የገዳሙ አስተዳደር ገለጸ፡፡
የወሊሶ ቤተ ሳይዳ ደብረ ምጥማቅ ቅድስት ማርያም ገዳም በ1971 ዓ.ም. በብፁዕ አቡነ ዲዮስቆሮስ የተመሠረተች ሲሆን፤ በ1996 ዓ.ም. በብፁዕ ወቅዱስ አቡነ ጳውሎስ ፓትርያርክ የመሠረት ድንጋይ ተቀምጦ የሕንፃ አሰሪ ኮሚቴ በማዋቀር ግንባታው ቢጀመርም በተለያዩ ምክንያቶች ግንባታው ዘግይቶ በዐሥር ዓመቱ ሊጠናቀቅ እንደቻለ አስተዳሩና የሕንፃ አሰሪ ኮሚቴው ገልጸዋል፡፡

የቤተ ክርስቲያኑን ዲዛይን በማኅበረ ቅዱሳን ባለሙያዎች ተሰርቶ ቀድሞ የነበረውን ዲዛይን በድጋሚ ማስተካከያ በማድረግ የወረዳ ማእከሉ ባለሙያዎች በቅርበት እየተከታተሉት ለሁለተኛ ጊዜ በተዋቀረው ሕንፃ አስሪ ኮሚቴ አማካይነት ሊጠናቀቅ ችሏል፡፡

01ww01wy
የገዳሙ መሥራች የሆኑት ብፁዕ አቡነ ዲዮስቆሮስ /መምህር ወልደ ትንሣኤ ግዛው/ የሕይወት ታሪካቸው እንደሚያስረዳው መጋቢት 21 ቀን 1911 ዓ.ም. በቀድሞው በተጉለትና ቡልጋ አውራጃ ኢቲሳ ደብረ ጽላልሽ የተወለዱ ሲሆን፤ በ1921 ዓ.ም. ከግብፃዊው ሊቀ ጳጳስ ብፁዕ አቡነ ቄርሎስ ዲቁና፤ ነሐሴ 24 ቀን 1933 ዓ.ም. በደብረ ሊባኖስ አቡነ ተክለ ሃይማኖት ገዳም ምንኩስናን፤ በ1940 ዓ.ም. በታዕካ ነገሥት በዓታ ለማርያም ገዳም ከኢትዮጵያዊው ሊቀ ጳጳስ ብፁዕ አቡነ ይስሐቅ ቁምስና፤ ግንቦት 30 ቀን 1979 ዓ.ም. በብፁዕ አቡነ ተክለ ሃይማኖት ኤጲስ ቆጶስ ሆነው ተሹመዋል፡፡
በአዲስ አበባ በቀጨኔ መድኃኔዓለም፤ በመንበረ ፓትርያርክ ቅድስተ ቅዱሳን ማርያም፤ በመናገሻ ቅዱስ ጊዮርጊስ፤ በመንበረ ጸባዖት ቅድስት ሥላሴ፤ በድሬደዋ ቅዱስ ሚካኤል፤ በሐረርጌ ሀገረ ስብከት ጅጅጋ፤ ኦጋዴን እና አሰበ ተፈሪ ካገለገሉባቸው አድባራትና ገዳማት ውስጥ ይጠቀሳሉ፡፡ በ1946 ዓ.ም. ወደ ቀድሞው ጨቦና ጉራጌ አውራጃ፤ በአሁኑ ደቡብ ምዕራብ ሸዋ ሀገረ ስብከት ወሊሶ /ግዮን/ ከተማ በመምጣት አሁን ገዳሙ በሚገኝበት ቦታ ላይ መሬት በመግዛት አዳራሽ ሠርተው ከእግዚአብሔር በተሰጣቸው ጸጋ በአጋንንትን የተያዙ ሕሙማን እየፈወሱ ቆይተዋል፡፡ አገልግሎታቸው ወደ ቀድሞው ንጉሥ ዐፄ ኃይለ ሥላሴ በመድረሱ የያዙትን ቦታ አስፍተው እንዲያገለግሉ መሬት እንዲሰጣቸው አድርገዋል፡፡

በ1971 ዓ.ም. የሚያገለግሉበት አዳራሽና ሰፊውን ቦታ በደርግ እንደሚነጠቁ የተረዱት ብፁዕነታቸው በሚያገለግሉበት አዳራሽ ጽላት በማስገባት ቤተ ክርስቲያኗ ተመሠረተች፡፡

01www01wwww
ብፁዕ አቡነ ዲዮስቆሮስ ከ10 ሚሊዮን በላይ ከኢትዮጵያ እና ከመላው ዓለም በአጋንንት የተያዙ ሕሙማንን ከእግዚአብሔር በተሰጣቸው ሀብተ ፈውስ እንደፈወሱ መረጃዎች ያመለክታሉ፡፡

ብፁዕነታቸው ጥር 18 ቀን 1989 ዓ.ም. ዐርፈዋል፡፡
ሕንፃ ቤተ ክርስቲያኑ ግንቦት 20 እና 21 ቀን 2007 ዓ.ም. በቅዱስ ፓትርያርኩ ተባርኮ ጽላቱ የሚገባ ሲሆን፤ ዓመታዊ የእመቤታችን የንግስ በዓል በድምቀት እንደሚከበር ኮሚቴው አስታውቋል፡፡
ምእመናን በዚህ ታሪካዊና የእግዚአብሔር ድንቅ ሥራ ሲከናወንበት በነበረው ገዳም ተገኝተው የበረከቱ ተሳታፊ እንዲሆኑ የገዳሙ አስተዳደርና ሕንፃ አስሪ ኮሚቴ ጥሪያቸውን አቅርበዋል፡፡

Monday, June 8, 2015

እሙሀይ ብርሐን - ዲማ ቅዱስ ጊዮርጊስ ገዳም

በዲማ ቅዱስ ጊዮርጊስ ገዳም 【በቤተክርስታን ቅፅር ግቢ ውስጥ የሚኖሩት 】እሙሀይ ብርሐን እናታችን የተሰጣቸው ፀጋ በጣም ለሰሚው ጆሮ በጣም ሊከብድ ይቻላል እናታች በቤተክርስታን ቅፅር ጊቢ መኖር ከጀመሩ ከ30 ዘመናት በላይ ሆኗቸዋል በነዚህ ዘመናት ባዶ ሜዳ ላይ ተቀምጠው ☞ ዝናብ ሲዘንብ እሳቸው የተቀመጡበት ቦታ ደረቅ ሆኖ እሳቸውንም ሆነ የተቀመጡባትን አካባቢ ዝናብ አያገኘውም እሙሀይ በዚህ ሲኖሩ የሚመገቡት ቱልት የተባለውን ቅጠል ሲሆን እናታችን ብዙ ተማዕራትን በተለያየ ግዜ ሲያደርጉ በአካባበው ምዕመናን ታይተዋል ከዚህ አልፎ በዋልድባ ገዳም የሚኖሩ አባቶች ከሰማይ በቀስተደመና አምሳል ከሰማይ ብርሐን ሲወርድላቸው አይተው መጥተው የእሙሀይን በረከት በረከትዎ ይድረስብን እናታችን ብለው እጅ ነስተዋል የእናታችን በረከት በጣም አስገራሚ እና አስደናቂ ነው እሰኪ ሁላችንም የእሙሀይ ብርሐን በረከት በየአለንበት ይድረሰን እሙሀይንም በቦታው ተገኝተን የበረከቷ ተካፍይ ያድርገን።



Wednesday, June 3, 2015

የቅዱስ ገብርኤል ጽላት በአንድ አባት ራእይ ተገኘ



ታላቅ የምስራች!!
በኦሮሚያ ክልል ሰሜን ሸዋ ዞን በአለልቱ ወረዳ ልዩ ስሙ ቁምጤ በተባለ አካባቢ የአብሳሪው ቅዱስ ገብርኤል ጽላት፣ ልዩ የፀበል ቦታና ሌሎች የብራና መፃሕፍት በአንድ ቅዱስ አባት ራእይ( ህልም) አማካኝነት ተገኝቷልና መጥታችሁ ጎብኙ። አካባቢው ከመዲናችን አ.አ 55 km ወጣ ብሎ የሚገኝ ቅርብ ቦታ ስለሆነ መጥታችሁ የበረከቱ ተካፋይ ትሆኑ ዘንድ ጥሪያችንን በእግዚአብሔር ስም እናቀርባለን።
እባካችሁ ይህን መልዕክት ለሌሎች በማካፈል ለሁሉ እንዲደርስ የበኩላችንን አስተዋፅኦ እናድርግ


 በአለልቱ አካባቢ ስለተገኝ የቅዱስ ገብርኤል ጽላት አጭር መረጃ (ለማታውቁት)፦ ዕለቱ ስኞ ግንቦት 24 /2007 ዓም የተክልዬ የበአል ቀን ነበር። በነገራችን ላይ አለልቱ ማለት የአባታችን ተክለኃይማኖት የትውልድ ቦታ እና የበርካታ አብያተ ቤተ ክርስትያናትና ገዳማት መገኛ ወረዳ ናት። እናም እኝህ በፎቶው ላይ የምታዩዋቸው ባህታዊ አባት የመጡት ከሌላ አካባቢ ሲሆን በእግዚአብሔር መልካም ፈቃድ በህልም (በራእይ) ተገልፃላቸው ወደዚህ አካባቢ በመምጣት ፅላቱ የተገኘበት ቦታ ላይ ሄደው ቁፋሮ እንዲጀመር ያዛሉ። ሆኖም ግን ያው እንደምናውቀው አንዳንድ የኃይማኖት መሪዎችና መናፍቃንን ጨምሮ ጥቂት ሰዎች " አባ ምን ነካቸው ይቃዣሉ እንዴ " እያሉ በጥርጣሬ ሲያሟቸውና ሲሳለቁባቸው ነበር። ነገር ግን ከጥቂት ሰአታት በኋላ እግዚአብሔር ለሁሉም ያስደመመና ያስደነገጠ ልዩ ተአምራቱን አሳየ። እጅግ ግዙፍ ከሆነ ድንጋይ ሥር በጥንታዊ ቆዳ የተጠቀለለና ልዩ መአዛ ያለው ጽላትና የብራና መፅሐፍ ተገኘ። የፀበል ቦታውንም ጭምር። በዚህ ሰአት ቦታው የመንገድ ዳርቻ (አስፋልት) ስለሆነ መንገደኛ ሁሉ ከመኪናው እየወረደ ሁኔታውን ለማየት ይጎርፍ ጀመር። ከመቅፅበትም ሌላ ጉድ ታዬ።

በአለልቱ ከተማ በአባታችን በአባ ገብረ ሕይወት ራዕይ ከተገኘው የቅዱስ ገብርኤል ፅላት ጋር አብሮ የተገኘው 600 አመታትን ያስቆጠረው የብራና መጽሐፍ ይህ ነው። የመለዓኩ ቅዱስ ገብርኤል በረከት በሁላችን ይደር። ቅዱስ ገብርኤል ይጠብቃችሁ።

ታላቅ ተዓምራት- የፈለገ ሕይወት መጥምቀ መለኮት ቅዱስ ዮሐንስ፣ወቅድስት ሃና ወቅዱስ ዑራኤል ቤተክርስቲያን

በቦሌ ክፍለ ከተማ ወረዳ ፲ የሚገኘው የፈለገ ሕይወት መጥምቀ መለኮት ቅዱስ ዮሐንስ፣ወቅድስት ሃና ወቅዱስ ዑራኤል ቤተክርስቲያን ሰሞኑን ታላቅ ተዓምራትን እያሳየ ነው። ሰዎች ይዘባበታሉ እግዚአብሔር ግን ሥራውን እየሰራ ነው፣ ሰዎች ልብ እንበል "በዚያን ጊዜ ብዙዎች መንገዶቻቸውን ይስታሉ" እንደተባለው ዘወትር በአጠገባችን ከከበበን ጠላት ዲያብሎስ ርቀን የቃሉን ድምጽ ሰምተን ወደ እርሱ ብንጠጋ እንባረካለን። ረደኤተ እግዚአብሔር አይለየን አሜን

ደብረ እያሪኮ ቅዱስ ሚካኤል

ምን ዓይነት ጸሎት በየትኛው ሰዓት ልጸልይ? 

ኢትዮጵያውያንና የያዕቆብ የመጨረሻ ልጅ የቢኒዖን (ብንያም)ነገድ

የፈለገ ሕይወት መጥምቁ ዮሐንስ ወቅድስት ሃና ወቅዱስ ዑራኤል ገቢረ ተዓምራት -save waldiba