Tuesday, July 7, 2020

ለእግዚአብሔር ያልንተንበረከከ፣ በአጋንንት የተማረከ ትውልድ

በቀሲስ ሄኖክ ወልደ-ማርያም
አጋንንት በሕይወታችን የሚያደርስብንን ችግር እስክናውቅ እንቸገራለን፣ ውጊያው እስኪገባን ግራ እንጋባለን፣ እውነቱ እስኪገለጥልን እውነቱ ሐሰት ይመስለናል፡፡
ሼር በማድረግ ለወዳጆ አዳርሱ!
ተወዳጆች ሆይ በክፍል ሠላሳ ሦስት የጠንካራ መንፈሳውያን ሰዎችን የአጋንንት ፈተና ተመልክተናል፡፡ በዚህ ክፍል ደግሞ ከላይ የጠቀስኩትን እናያለን፡፡ የቅዱሳን አምላክ ምስጢሩን ይግለጽን፡፡ አሁን ያለነው ትውልድ በአጋንንት ስውር ደባ ስለተማረክን ለእግዚአብሔር ተገዝተን መንበርከክ አልቻልንም፡፡ የእኛ ትውልድ ከፍተኛ የማንነት ቀውስ ውስጥ እና የአጋንንት የተንኮል ውርስ ውስጥ ገብቷል፡፡ ከእግዚብሔር መንገድ ርቀን በራሳችን መንገድ ታንቀን ስለምንሄድ የአጋንንት ሰለባ እየሆንን ነው፡፡
በተለይ ወጣቱ የአጋንንትን የፈተና ስልት ስላላወቀ በሥጋ ፍላጎቱ እንደታነቀ ይኖራል፡፡ የእኛ ትውልድ አዋቂ ነኝ ይላል ግን ማወቁ ከፈተናው ለመላቀቁ ፍንጭ አልሰጠውም፡፡ ዛሬ መቶ መስገድ የዳገት መንገድ የሆነብን ለምንድን ነው? አንድ ሰዓት ቆመን ስናወራ የማይታክተን ለሃያ ደቂና ውዳሴ ማርያም መጸለይ ያቃተን ለምንድን ነው? ጽኑ እምነት አጥተን ሃይማኖትን በእምነት ሳይሆን በሥጋዊ እውቀት የምንመዝነው ለምንድን ነው? ጆሮአችን ቃለ እግዚአብሔር ሳይሆን ሐሜት ለመስማት ለምን ይዳክራል?
ጓደኛችን ለፍቶ ሠርቶ ከሚለወጥ አፈር ከደቼ በልቶ ቢፈጠፈጥ ደስ የሚለን ምቀኝነት ናላችንን ያዞረን ለምንድን ነው? እለት እለት ከአንደበታችን እውነት ሳይሆን ውሸት የሚወጣው፣ ከውሸት አልፈን ቅጥፈት የለመድነው ለምንድን ነው? ወዘተ …
ለእግዚአብሔር መንበርከክ ትተን ለአጋንንት ስንማለር መገለጫችን መንፈሳዊ በረከቶችን መጠራጠር፣ በእምነት መነጽር አለማየት፣ አለማመን፣ መንፈሳዊ ጸጋን በሥጋ እውቀት ማየት፣ ቸልተኛ፣ ግዴለሽነት፣ በሥጋም በነፍስም ተስፋ መቁረጥ፣ በዶግማና በቀኖና መናወጥ፣ በመንፈሳዊ ሕይወት አለማደግ አለመለወጥ ወዘተ ነው፡፡ ይህን ገዳፋ የምናተርፈው በቤሰተባችን የእምነት ደካማነት እና በአጋንንት ተጽዕኖ ነው፡፡ ወዳጆቼ መንፈሳዊ ጸጋ የራቀን የሥጋዊ ዝቅጠት የተጫነን ለእግዚአብሔር ከመንበርከክ ይልቅ እኛን እስከጠቀመን ድረስ ለአጋንንት ስንማረክ ትርፋችን ይህ ነው፡፡
ሱስና መጠጥ ያሠረው ወጣት ለአጋንንት መጫወቻና የአጋንንት ፍላጎት ማስፈጸሚያ ቢሆን አይገርምም፡፡ ይህ ትውልድ አይወቀስም አወቅን ዘመናዊ ሆንን ያሉ በእግዚአብሔር መባረክን ያልወደዱት ወላጆች የዘሩት ውጤት ነው፡፡ ቤተሰብ ልጆችን በሕፃንነታቸው በዕለተ ሰንበተ ቅዱስ ቁርባን ማቁረብ ትተው ወደ መጫወቻ ቦታ ይዘው በመሄዳቸው የእግዚአብሔርን ጸጋ ሳይሆን የዓለምን ዋጋ እንዲያዩ ነው ያደረጉት፡፡ በዕለተ እሑድ ማስቀደስ ሳይሆን መደነስ የለመደ ወጣት የአጋንንት ቁራኛ ቢሆን አይደንቅም፡፡
ትላንት በልጅነቱ እናት ‹‹ቅዳሴ ሂድ›› ስትለው ልጅ የዓይነ ጥላውና የአፍዝዝና የቤተሰብ ዛር ልጁ ላይ እያለቀሰ ‹‹አልሄድም›› ሲል አባት ‹‹ተይው ካልፈለገ አታስገድጅው፣ እንዲ ሆኖ ቢሄድም ምንም አይጠቅመውም›› በማለት ከቅድስናው ደጅ እያራቀ ሲከላከል የነበረው ቤተሰብ በሕፃኑ ላይ የዘራውን የቸልተኝነት፣ የእንቢተኝነት፣ የመብቱ ነው ጥያቄ ሲያድግ በልጁ መከራ ያጭደዋል፡፡
ትላንት ልጆችን የአጋንንት አረም ሲበቅልባቸው አረሙን ከመንቀል፣ መንፈሳዊ ሕይወታቸውን ከመከታተል ይልቅ ለሥጋዊ ደስታቸው እያደላን ሰማያዊ ደስታቸውን እናጨልማለን፡፡ ልጆቻችን በአጋንንት ምትሐታዊ ፍላጎት እየተነዱ በሕፃንነታቸው የአዋቂን ጸያፍ ሥራ ሲሠሩ ‹‹እሷ ፈጣን ናት፣ እሱ ብልጥ ነው፣ የሕፃን አዋቂ ናቸው›› እያልን በሃይማኖት ሳንገራቸው አሳድገን የሕፃንነት የኃጢአት ሕልማቸውን ከመሬት ብቅ እንዳሉ ያሳዩናል፡፡ ያኔ ቤተ እግዚአብሔር ሄደን ብንጮህ አጉልና የማይሰማ ጩኸት ነው፡፡ብቻ በልጅነታቸው ያሳየናቸውን የጥፋት መንገድ፣ አድገው መከራና ፈተና ሲያሳጭዱን እንኖራለን፡፡ እኛ ተባርከን ልጆቻችንን እንዳናስባርክ፣ እኛው ተሰላችተን አጋንንቱ መንገድ ዘግቶብን ለልጆቻችን የእርግማን መናፍስትን እናወርሳቸዋለን፡፡
በቅዳሴው በቁርባኑ፣በቃሉ ስላላስባረክናቸው አጋንንት እንደ ፈጣን ፈረስ እየሰገራቸው ወደ ጥፋት እና ወደ ኃጢአት ሜዳ ይጋልባቸዋል፡፡ ለልጆቻችን ንብረት እንጂ ሃይማኖታችንን ስለ ማውረስ ስላልተጨነቅን ልጆቻችን ንብረት አጥፊ፣ እግዚአብሔር ላይ አሿፊ ትውልድ ይሆናሉ፡፡ ሠርተን ያወረስናቸው እንጂ ተባርከን የሰጠናቸው መንፈሳዊ ስጦታ ስለሌለ አመንዝራና ሱሰኛ ይሆናሉ፡፡ ይህ የእኛ ድክመት ልጆቻችንን የአጋንንት መሥዋዕት እንዲሆኑ በሩን መክፈት ብቻ ሳይሆን የጥፋትንም መንገድ አሳይተናቸዋል፡፡ ዛሬ በየቤታችን የተሸከምናቸው የልጆቻችን ችግሮች መሠረቱ እኛው ነን፡፡ ስለዚህ ስንዴ ካልዘራንበት እርሻ አረማችንን አጭደን በቤታችን ከምረን መኖራችን ግድ ነው፡፡
በኖኅ ዘመን የነበረው አመንዝራ ትውልድ፣ በሎጥ ዘመን የነበረው ግብረ ሰዶማዊው ትውልድ ቤተሰባቸው አረም ሆነው የዘሩት የጥፋት እና የመቅሠፍት ትውልድ በእኛም ዘመን እያየነው ነው፡፡ ስለዚህ ለእግዚአብሔር ያልተንበረከከ ትውልድ፣ ለሰይጣን የጥፋት እንጨት ሆኖ ሲማገድ፣ በኃጢአት ሲነድ ማየት ግድ ብሎናል፡፡
ወላጆች እስኪ ልጆቻችሁ የሚያዩትን የሕፃናት ፊልሞች ተመለከቱ፡ ምዕራባውያን በሕፃናት ፊልም ሰይጣንን እያለማመዷቸው ነው፡፡ በሕፃናት ፊልም ላይ የሚታዩትን ገጸ ባህሪያት ብናያቸው ወጣ ያሉ፣ የሚያስፈሩ፣ የሉሲፈር ገጽታ ያላቸው ወዘተ ናቸው፡፡ የሚጫወቱት ጌሞች ለንቃተ ሕሊና የሚረዱ ሳይሆን አጋንንትን የሚያለማምዱ ናቸው። እነዚህን ምዕራባውያን የራሳቸውን ትውልድ በሚፈልጉት መንገድ አበላሽተዋቸው ሱሰኛ፣ ሺሻ የሚያጨስ፣ በወጣትነቱ የሚገድል የሚደበድብ እናት አባቱም የማያከብር እንዲሆም አድርገዋል፡፡ አሁን የእኛ ነው የቀራቸው እኛንም ልጆቻችንን በፊልማቸው በአሻንጉሊት ትዕይንታቸው እያደነዘዙን እያፈዘዙን ነው፡፡
እባካችሁ ጨቅላ ሕፃናቶቻችንን በልጅነታቸው የአምልኮ፣የጾም፣የጸሎት፣የስግደት ሥርዓት እያስተማርን አሳድገን ከአጋንንት ምርኮ እንታደጋቸው፡፡
‹‹ሕዝቤ እውቀት ከማጣቱ የተነሳ ጠፍቶአል›› ት.ሆሴ 4÷6
‹‹ከትውልዱ ማን አስተዋለ?›› ት.ኢሳ 53÷8
ክፍል ሠላሳ አምስት
በጸሎት የራቀን ዲያብስ፣ ወደ እኛ መመለስ
https://www.facebook.com/memehirhenok

Tuesday, September 19, 2017

ሙስሊሟዋ ድንቅ ተዓምር በሸንኮራ ዮሐንስ ተደረገላት

" ደስታና ተድላም ይሆንልሃል፥ በመወለዱም ብዙዎች ደስ ይላቸዋል። በጌታ ፊት ታላቅ ይሆናልና፥ የወይን ጠጅና የሚያሰክር መጠጥ አይጠጣም፤ ገናም በእናቱ ማኅፀን ሳለ መንፈስ ቅዱስ ይሞላበታል።ከእስራኤልም ልጆች ብዙዎችን ወደ ጌታ ወደ አምላካቸው ይመልሳል " ሉቃ.1፡14
ሸንኮራው ቅዱስ ዮሐንስ ድንቅ ተአምር
ሃይማኖቴ "ወልድ ፍጡር፣ ቤተክርስቲያን ድንጋይ ናት" ሎቱ ስበሐት ። ከሚሉ አሕዛብ ወገን ነበርኩ የምትለዋ እህታችን መኖሪያዋ በመዲናችን አዲስ አበባ ነው ። ክርስቲያን የሚባል አልወድም፣ ፍጹም ጥላቻንም የተሞላው ነበርኩ። አምላኬን ያስደሰትኩ መስሎኝ አንድ አብሮ አደግ ክርስቲያን ጓደኛ አለችኝ። ብሰድባት ብተፋባትም ጉዳይዋ አይደለም ኣትቀየመኝም። ቅዱስ ዮሐንስን በጣም ትወደዋለች።
እኔ በስኳር በሽታ ምክንያት አንድ እግሬ በጋንግሪን (የተወሰነ አካል መሞት) እንዲቆረጥ ሐኪም ወሰነ። ያች ጓደኛዬ ግን የዮሐንስ ጸበልን ቤቴ አመጥታ ሰጠችኝ። ተቀብያት ከፊቷ ይህ እኮ "ውሐ" ነው ተረት አታውሪ ብዬ ስደፋው የጸበል ዕቃውን የያዘ እጄ ሰለለ ሽባ ሆነ፤ ደነገጥኩኝ። የጥፋተኝነት ስሜት ተሰማኝ። አይዞሽ ምልክት ነው መጥምቁ ያማልድሻል አለችኝ። "ኦፕራሲዮኑን ተይው አንቺ ካልዳንሽ እኔ ሃይማኖቴን እቀይራለው" ስትል ቤተሰቤ በሃሳብ ለሁለት ተከፈለ። እግሬ በአስቸኳይ ይቆረጥ ተብሏል። እግሬም ቁስሉ ሽታ አመጣ። በዚያ ላይ በሃይማኖቴ፣ ቤተሰቤ ሁሉ በአይነ ርግብ ተሸፍኖ የሚሄድ ነው። መገላለጥ የለም፤ "እዛ ብትሔጂ እንረግምሻለን" አሉኝ። በመጨረሻ ውሳኔ የኔ ሆነና ከሶስት ቤተሰብና፣ ከዚህችው ወዳጄ ጋራ ሸንኮራ ሄድን። ወደ ጸበሉ መውረድ አልቻልኩም አምጥተው አጠመቁኝ። ቁስሉ እንደቅርፊት ወደቀ። እንደውም ጸበሉን የደፋሁበት እጄ ዳነ። የምን መቆረጥ የምን ጋንግሪን።
የሕመሜም ምክንያት የነበረው 23 አመት ያሰቃየኝ ስኳሩም ዳነ። አብራኝ የሄደች አንድዋም ቤተሰቤ በፍንጢጣ ኪንታሮት ትሰቃይ ነበር የባህል መድሐኒት ወስዳ ጽኑ ህመም ላይ ነበረች እርስምዋ ዳነች።በሰማዕትነት ለአምላኩ ምስክር የሆነው መጥምቁ ዮሐንስ ከአምላክ አማልደህ ካዳንከኝ ጥላ በሬ ላምጣ አልልም አንተ ምስክር ለሆንክለት “በክርስቲያን አምላክ በኢየሱስ ክርስቶስ አምናለው” ብዬ ነበር።
ይህም ድኜ ለስዕለቴ በቃው ከስምንት ቤተሰቤ ጋር ሃብተ ወልድና ስመ ክርስትና ተቀበልኩኝ። ትለናለች።
እህተ ዮሐንስ፤ፍቅርተ ዮሐንስ፤ወለተ ብርሐን፤ተጠምቀ መድህን፤ክፍለ ዮሐንስ፤ገብረ ዮሐንስ፤ወልደ ዮሐንስ፤አርከ ዮሐንስ ተብለን የቀራኒዮ ቤዛ ወደ አብ ወልደ ማርያም ኢየሱስ ክርስቶስ ነቢይ ሳይሆን አምላክ እንደሆነ አምነን በአብ በወልድ በመንፈስ ቅዱስ ስም ተጠምቀናል።
ቅዱስ ዮሐንስም ተአምር ግን ድሮ ነው የጀመረው ጎረቤቴ ዝክሩን ስታደርግ አትጥሪኝ እላት ነበር። ዝክሩንም አልበላም ጣኦት አምላኪ አድርጌ ነው የምቆጥራት። የክርስቲያኖች አምላክም ብዙ ነበር የሚመስለኝ። አወይ አለማወቅ በድብቅ ግን ዝክሩን በልጆች ስም አስመጥቼ እበላ ነበር።ይጣፍጠኛል ለካ በስተመጨረሻው የሕይወት እንጀራን ስጋ ወደሙ ሊያበላኝ ኖሯል እንዲያ የጣፈጠኝ፤ ትላለች እህታችን በጥምቀቱ ስነ ስርአት በዓይኔ በአካል ተገኝቼ በከተማችን በሚገኝ አንድ አጥቢያ ተከታትያለው ይለናል አንተነህ ሐይሌ።
እኛ የእምነት አቃቂር ስናወጣ ጥቅስ ስናገላብጥ የዛሬ 2000 አመት አንገቱ የተቆረጠው መጥምቁ ዮሐንስ ስንት የጠፋውን መንጋ ጥቅስ ሳይጠቅስ ቃላት ሳያዥጎደጉድ በፍቅሩ አስሮ በምልጃው ጠብቆ ለጌታው ምርኮን አስገባ። ይህን ያደረገ የመጥምቁ አምላክ ክብር ይግባው ዮሐንስ ነቢይ ሰማዕት እኛንም ያማልደን አሜን።
ከአንተነህ ኃይሌ ገጽ ተገኝቶ ጥቂት እርማት የተደረገበት የእውነት ምስክርነት። ወደፊት ግለሰቦቹ አነጋግረን የበለጠ መረጃ ለማድረስ እሞክራለሁ። “ እላችኋለሁ፥ እንዲሁ ንስሐ ከማያስፈልጋቸው ከዘጠና ዘጠኝ ጻድቃን ይልቅ ንስሐ በሚገባ በአንድ ኃጢአተኛ በሰማይ ደስታ ይሆናል።”ሉቃ 15:7

Wednesday, August 30, 2017

የሰማዕቱ ቅዱስ መርቆሬዎስ ድንቅ ተአምር

በደቡብ አፍሪካ ደርባን ያደረገው
ጥ ብልው ቁጭ እንዳሉ ቡኒ የፓሊስ ልብስ የለበሰ ቀይ ወጣት እናቴ አትፍሪ ምን ሆነሽ ነው አትፍሪ ፓሊስ ነኝ ይላቸዋል ወዲያው አንድ እብድ ድንጋይ ወርውሮ የሱፐር ማርኬቱን መስታወት ይሰብራል ያ ድንጋይ ናድያ ቀሚስ ላይ ቁጭ ይላል ወደውስጥም ዘልቆ አትፍሪ አዕምሮውን የሳተ ሰው ነው ብሎ ያረጋጋቸዋል ዘጠኙ የስራ ባልደረቦቻቸው ሲመጡ በሆነው ነገር ይደነቃሉ ፓሊስም ስላዮ ደስታቸው እጽፍ ሆነ ሆቴላቸው በር ደርሰው አስፓልት ሊሻገሩ ሲሉ ናዲያ ብሎ በስማቸው ጠርቶ ይጨብጣቸውና የት ይግባ የት አያስተውሉም ዘጠኙ ሰዎች የራሳቸውን ጨዋታ ይዘዋልና አላስተዋሉም ያው ነጭ ፓሊስ አግኝታ ወሬ ይዛለች ብለው ትተዋቸዋል ሆቴሉ በር ላይ ላሉት ሴኩሪቲዎች ሲነግሩዋቸው ቡኒ ልብስ እኛ ሐገር የሚለብስ ወታደር የለም ጉዳዮን ለደህንነት ክፍሉ ያመለክታሉ እንዲህ አይነት ሰው አናውቅም ይህ ኢኒፎርምም የለንም ስለተፈጠረው የጥበቃ ክፍተት ይቅርታ ይጠይቃሉ መጀመሪያ አልፈዋቸው የሄዱት ወንበዴዎች 5 ሰው እዛው መንገድ ገድለዋል በዛው ቅጽበት ከዘጠኙ 8 ኢ አማኒ ናቸውና አልተገረሙም መኝታ ክላቸው ገብተው እጃቸውን ሲያዮት በቅባ ቅዱስ እርሶዋል ለካ ናዲያ ብሎ በስሜ የጠራኝ በእግሊዘኛ ሳይሆን በአረብኛ ነበር ያወራኝ ታዳጊው ሰማዕት ነው ይህ እንዴት ይሆናል ብለው ያነባሉ ምስጋናም ያቀርባሉ እዛው ደቡብ አፍሪካ በተመሳሳይ በሌላ አመት ቅዱስ መርቆሬዎስ በገሐድ በመገለጥ ከአደጋ ታድጎዋቸዋል ይህ ታምር ሲሰራ ወላጅ እናቴም ነበረች ይህች ሴት ይህን ነጭ የት አውቃ ነው የሲአይ ኤ ሰላይ ሳትሆን አትቀርም እዛ ኮንፍረንስ ሞል ስንፈራ ስንቸር ለምን አልጠራችውም አሁን ከየት መጣ ደግሞ ሱፐር ማርኬቱ ውስጥ ሳየው አይኑ እሳት ይመስላል ኩዋሱ አይታይም እያልኩኝ አምቻለው ብላኛለች በወቅቱ ስለ እምነት ብዙ ዕውቀቱ ባይኖረኝም የሴኩሪቲዎቹ አናውቀውም ማለትና ሳይሰናበትን መሄድ ገርሞኛል ብላለች ይህ ምስክርነት በአሮጌው ካይሮ በሚገኘው የሰማዕቱ አቡ ሰይፌን ገዳም በተአምራቱ መዝገብ ላይ አጽፈውታል ድንቅ አድራጊው ሰማዕት ከነፍስና ስጋ አጥማጅ ክፉ መናፍስት ምልጃው ይታደገን አሜን ለአምላከ መርቆርዬስ ክብር ይግባው እልልልልልልልልልልልልልልልልልል

በወረብ አብሮ የሚሳተፈው የቅዱስ መርቆርዮስ ስዕል